በድካም የዛለ ሰው አውቶብሱ ውስጥ ተኝቶ

ከ 5 ሰአት በፊት

ኤሚ በዓለም ግዙፍ የሆነ የጤና እንክብካቤ ኩባንያ ውስጥ የግብይት ሥራ ኃላፊ ሆና በምትሰራበት ወቅት ተደራራቢ የሥራ ጫና ነበረባት።

አንድ ዕለት በሥራ ላይ በነበረችበት ወቅት በድንገት የማዞር ስሜት ተሰማት።

“በቂ ምግብ አልበላሁም ወይንም ውሃ አልጠጣሁም ብዬ አስቤ ነበር፤ ነገር ግን ሊሻለኝ አልቻለም። ከዚያን በጣም ብዥ እንዳለብኝ ቀጠለ” ትላለች።

የማያቋርጥ “ጭው” የሚል ድምጽ መስማቷን ታስታውሳለች። ለባለቤቷም “ባህር ላይ ሆኖ መጠጥ መቀማመስ እና መስከር የሚፈጥረው ስሜት” ወይም “በቀለም በተሞላ ውሃ ውስጥ እንዳለሁ ዓይነት ስሜት ነበር” የተሰማኝ ስትል ነግራዋለች።

“በድንገት የአካል ጉዳተኛ የሆንኩ ያህል ተሰማኝ” ስትል መንቀሳቀስ እንዳቃታት ትገልጻለች።

ኤሚ ለወራት የሕመም እረፍት ወስዳ ማረፍ ነበረባት።

“የአእምሮ ጤንነቴ እያሽቆለቆለ መጣ። ገላዬን ልታጠብ በገባሁበት ራሴን መሳት ጀመርኩ፤ ልጆቼን መንከባከብ አልቻልኩም። አካሌ ‘አይ በቃ! አቁሚ!’ እያለኝ ነበር።”

በአንድ እጇ ላፕቶፗ ላይ እየሰራች በሌላ እጇ ልጇን ያቀፈች እናት

Skip podcast promotion and continue reading

የቢቢሲ አማርኛ ዋትስአፕ ቻናል

የቢቢሲ አማርኛ ዋትስአፕ ቻናል

ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በቀጥታ በዋትስአፕ ለማግኘት

ይህን በመጫን የቻናላችን አባል ይሁኑ!

End of podcast promotion

የአንጎል ክብድ ማለት፣ ድካም፣ ለሥራ ጉጉት ማጣት የመሳሰሉት ከሥራ ጫና ጋር ተያይዘው የሚመጡ ስሜቶች በቀላሉ ሊታለፉ ይችላሉ።

ነገር ግን እነሱን ችላ ማለት በጤና ላይ ከባድ መዘዝ ሊያስከትል ይችላል።

ኤሚ በቅርቡ ከሥራ ጫና መብዛት የተነሳ ጤናዋን ማቃወሷን እስክትረዳ ድረስ ችላ ያለቻቸው ምልክቶች በመኖራቸው አቅሟ ተሟጥጦ ባዶዋን ቀርታ ነበር።

የኪንግ ግሎባል የሴቶች አመራር ተቋም ዳይሬክተር የሆኑት ፕሮፌሰር ሄጁንግ ቹንግ “ከተገቢው በላይ፣ በጣም እየሠራን ነው” ሲሉ ያስጠነቅቃሉ።

አክለውም “በዚህ የዲጂታል ዘመን ተደጋግሞ የሚስተዋለው ‘ሁልጊዜ በሥራ ላይ የመገኘት’ ባሕል ሲሆን፣ ይህም በሥራ ጫና ምክንያት መዛል እና መውደቅ እየጨመረ እንዲመጣ አድርጓል። ሠራተኞች ከሥራ ርቀው በቂ አካላዊ እና ሥነ ልቡናዊ እረፍት አያደርጉም” ብለዋል።

ፕ/ር ቹንግ ይህ በሥራ ጫና ምክንያት ሕመም ላይ መውደቅ ዓለም አቀፋዊ ጉዳይ መሆኑን በመጥቀስ፣ አንዳንድ አገራት ከ70 በመቶ በላይ ሠራተኞቻቸው በዚህ እንደሚጠቁ ገልጸዋል።

በ2024 በዩኬ የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው በሥራ ጫና መብዛት ምክንያት በተፈጠረ ሕመም የተነሳ የአገሪቱን ኢኮኖሚ በዓመት ከ102 ቢሊዮን ፓውንድ በላይ ያስወጣል።

እአአ በ2020፣ በ20,000 የጀርመን ሠራተኞች ላይ የተደረገ ጥናት እንደሚያመለክተው 60 በመቶ ያህሉ በርካታ ተግባራትን ማከናወን እጠበቅባቸው እንደነበር ተናግረዋል።

48 በመቶው የጊዜ እና የአፈፃፀም ጫና የነበረባቸው ሲሆን፣ 46 በመቶ ሥራቸውን የማጣት፣ 34 በመቶዎቹ ደግሞ በፍጥነት ሰርተው ማስረከብ ይጠበቅባቸው እንደነበር ተናግረዋል ።

ተመራማሪዎች አሁን በመደበኛነት በተማሪዎች፣ በወላጆች እና በተንከባካቢዎች ላይ በሥራ ጫና ምክንያት የሚመጣ መዛል ሪፖርት መደረጉን ይጠቅሳሉ።

ሳይኮቴራፒስት የሆኑት ዶ/ር ክሌር ፕሉምሊ ይህ በሴቶች ላይ ተመጣጣኝ ያልሆነ ተጽዕኖ እንዳለው ጠቁመዋል።

“የዚህ ሸክም የአንበሳው ድርሻ በእርግጠኝነት በሴቶች ላይ ይወድቃል” ሲሉ አክለዋል።

ምልክቶቹን መለየት

በሥራ ጫና ምክንያት የሚመጣው ድካም ብቻ ሳይሆን፣ ድካምን የሚያመለክቱ ሁለት ቁልፍ ምልክቶችን መኖራቸውን ባለሙያዎች ለይተዋል።

እነዚህም ለሚሰሩት ሥራ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የሚሄድ ጠርጣራ ምላሽ እና ለራስ ያለ አሉታዊ አመለካከት ናቸው።

ይህ በሥራዎ ላይ እየታየ መሆኑን ላያስተውሉ እንደሚችሉ ዶ/ር ፕሉምብሊ ያስረዳሉ።

ብዙ ሰዎች ከዚህ የሚወጡበትን መንገድ ያልማሉ።

“የማምለጫ ሀሳብ ሊኖርዎት ይችላል። አንድ ሰው ሁሉንም ነገር ከሥራ ገበታዎ ላይ ቢወስድልዎት እና ቢገላገሉ ይመኛሉ፤ አንደ ደንበኛ ነበረኝ ‘ኮቪድን ቢይዘኝ ስል እመኛለሁ’ የሚል” ብለዋል።

በሥራ ጫና ምክንያት የሚመጡ ሕመሞች አምስት ምልክቶች

በድካም የተነሳ በመጓጓዣ ውስጥ የተኛ ወጣት

ተጋላጭነትዎን የሚጨምሩ ስድስት ነገሮች

ከሥራ ጫና ድካም ማገገም

ፕሮፌሰር ሳቢኔ ሶኔንታግ “ከፍተኛ የሥራ ውጥረት ውስጥ ካሳለፉ በኋላ በአእምሮ ከሥራ ገበታቸው የሚርቁ” ግለሰቦች በስሜት መዛል እና ለመታመም የመጋለጥ እድላቸው አነስተኛ መሆኑን ይናገራሉ።

ዶ/ር ፕሉምሊ በበኩላቸው ጥሩው መፍትሄ የሚቀርብዎትን ሰው መፈለግ መሆኑን ይመክራሉ።

ይህም በሥራ ጫና ከሚፈጠር የስሜት መዛል፣ እና የአካል መጣመን የሚረዳ እንደሆነ ያሰምሩበታል።ይህ ግለሰብ ግን የምክክር ባለሙያ ሳይሆን ጓደኛ ወይም የሥራ ባልደረባ መሆን አንዳለበት ይመክራሉ።

“ከድካም ስሜት በተሳካ ሁኔታ ለማገገም በሕይወትዎ ላይ ከባድ ለውጦችን ማድረግ አያስፈልግም፣ ለምሳሌ ስራዎን መልቀቅ አይጠበቅብዎትም” የሚሉት ደግሞ ዶ/ር ክሌር አሽሊ ናቸው።

ሥራዎን፣ ጤንነትዎን መቆጣጣር እና፣ በዙርያዎ ሊረድዎት እና ሊደግፉዎት የሚችሉ ሰዎችን ማሰባሰብ ወሳኝ ናቸው ሲሉ መፍትሄ ያሉትን ጠቁመዋል።

በእርስዎ ቁጥጥር ውስጥ ያለውን ነገር መረዳት አስፈላጊ መሆኑን ዶ/ር አሽሊ ይመክራሉ።

አክለውም ሥራን መልቀቅ ወይንም ባሉበት መቆየት ካልሆነም እሴቶቻችሁን ጠብቃችሁ መኖር ጫና ውስጥ የሚፈጠር ሕመምን ለመቀነስ ይረዳል ይላሉ።

“እሴቶቻችሁን መለየት በሥራ ጫና ከሚፈጠር ሕመም ማገገሚያ ሂደት ውስጥ አራተኛው ደረጃ ነው እና ከዚያ በኋላ የምትወስዷቸው ውሳኔዎች ከእነዚህ እሴቶች ጋር በተጣጣመ መልኩ መደረግ አለባቸው” ብለዋል።