
ከ 2 ሰአት በፊት
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አዲስ ታሪፍ መጣላቸውን ተከትሎ ዓለም አቀፍ የአክሲዮን ገበያ ወርዷል።
በእስያ-ፓስፊክ ቀጣና አክሲዮን ገበያ ለሁለኛ ቀን የወረደ ሲሆን፤ በ2020 በኮቪድ ወረርሽኝ ወቅት ከወደቀ በኋላ ግዙፍ የአሜሪካ ኩባንያዎች ገበያ አስጨናቂ ቀናት ገጥሟቸዋል።
ናይክ፣ አፕል እና ታርጌት ከትላልቅ ኩባንያዎች መካከል ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆኑ፤ ሁሉም ኩባንያዎች ከዘጠኝ በመቶ በላይ ሽያጫቸው መውረዱ ተነግሯል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ በዓለም አቀፍ ምርቶች ላይ በጣሉት ዝቅተኛ 10 በመቶ ታሪፍ የፌደራል ገቢን በማሳደግ እና የአሜሪካን አምራቾች ወደ አገራቸው በመሳብ የአገሪቱ ኢኮኖሚ እንደሚያሳድግ በዋይት ሀውስ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
ሐሙስ ዕለት የአክሲዮን ገበያ ያሽቆለቆለ ሲሆን፤ በእንደዚህ አይነት አለመረጋጋት ወቅት ደኅንነቱ የተጠበቀ ጥሪት ተደርጎ የሚታየው ወርቅ ደግሞ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት የዋሽንግተን የንግድ አጋር የሆኑትን ቻይና እና የአውሮፓ ህብረትን ጨምሮ በበርካታ አገራት ምርቶች ላይ የሚፈፀም ከፍተኛ ታሪፍ ጥለዋል።
በጥቅሉ 54 በመቶ ታሪፍ የተጣለባት ቻይና እና 20 በመቶ የተጣለበት የአውሮፓ ህብረት አጸፋዊ እርምጃ እንደሚወስዱ ዝተዋል።
- የዓለማችን አምስት ግዙፍ ምጣኔ ኃብቶች የትራምፕን ታሪፍ እንዴት ተመለከቱት?ከ 5 ሰአት በፊት
- ዛምቢያዊያን በአሰቃቂ የህፃናት መደፈር ሪፖርቶች አደባባይ ወጡከ 4 ሰአት በፊት
- እስራኤል በጋዛ በትምህርት ቤት ላይ በፈጸመችው ጥቃት 27 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸከ 4 ሰአት በፊት
Skip podcast promotion and continue reading

ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በቀጥታ በዋትስአፕ ለማግኘት
ይህን በመጫን የቻናላችን አባል ይሁኑ!
End of podcast promotion
የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የአውሮፓ ድርጅቶች በአሜሪካ ያቀዱትን ኢንቨስትመንት እንዲሰርዙ ጥሪ አቅርበዋል።
ታሪፍ ከሌሎች አገራት የሚገቡ ምርቶች ላይ የሚጣል ታክስ ሲሆን፤ ረቡዕ እለት ትራምፕ ያሳወቁት ታሪፍም ከ100 ዓመታት በኋላ የምርቶች ዋጋ እንዲያሻቅብ ያደርጋል እየተባለ ነው።
የዓለም የንግድ ድርጅት እርምጃው በእጅጉ እንዳሳሰበው የገለፀ ሲሆን፤ ድርጅቱ በዚህ ዓመት የንግድ መጠን በአንድ በመቶ ሊቀንስ እንደሚችልም ግመታውን አስቀምጧል።
ነጋዴዎችም ታሪፉ የዋጋ ግሽበት እንደሚጨምር እና እድገትን ሊያስተጓጉል ይችላል የሚል ስጋት አላቸው።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ እርምጃቸው የዓለምን የንግድ ስርዓት የቀረፀው አሜሪካ መር ነፃ ንግድ ላይ ከፍተኛ ዋጋ ያለው ቁማር መሆኑን አጣጥለዋል።
“በጣም በጥሩ መንገድ እየሄደ ይመስለኛል” ብለዋል።
“አንድ ታካሚ ቀዶ ሕክምና እንደሚደረግለት አይነት ነው። እናም ትልቅ ነገር ነው። ይህ በትክክል በዚህ መንገድ ይሆናል” ሲሉ ገልፀዋል።
“ገበያው እያደገ ይሄዳል። ስቶክ ገበያው ያድጋል። አገሪቱ ታድጋለች” ሲሉም አክለዋል።
የዋይት ሀውስ ባለስልጣናት አዲሱ ታሪፍ የድርድር ስልት አይደለም ቢሉም፤ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ግን ከንግድ አጋሮች ጋር ለመነጋገር በራቸው ክፍት መሆኑን ጠቁመዋል።
ሐሙስ ዕለት አዲሱ የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ካርኒ አገራቸው ከአሜሪካ በሚገቡ ተሽከርካሪዎች ላይ 25 በመቶ ታሪፍ በመጣል አፃፋ ትወስዳለች ብለዋል።
ኩባንያዎች የታሪፉን ጫና ብቻቸውን መቋቋም፣ ከአጋሮቻቸው ጋር መጋራት አሊያም ለደንበኞቻቸው በማስተላለፍ ሽያጫቸን አደጋ ላይ መጣል በሚሉ ምርጫዎች ተከበዋል።
እርምጃው ከዓለም ኢኮኖሚ ከ10 እስከ 15 በመቶ ድርሻ ባላቸውን የአሜሪካ ሸማቾች ላይ ግዙፍ ተፅዕኖ እንደሚኖረው ይጠበቃል።