
ከ 6 ሰአት በፊት
እስራኤል ሁለት የብሪታንያ የሕዝብ እንደራሴዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ወደ አገሯ እንዳይገቡ መከልከሏን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዴቪድ ላሚ ቅዳሜ ዕለት ባወጡት መግለጫ አስታወቁ።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱ አባላት ወደ እስራኤል ያቀኑት ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ነበር ተብሏል።
የእስራኤል ባለስልጣናት ሁለት የሌበር ፓርቲ የፓርላማ አባላት ወደ አገሯ እንዳይገቡ መከልከሏን እና ማሰሯን የዩናይትድ ኪንግደም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴቪድ ላሚ ተችተዋል።
“እርምጃው ተቀባይነት የሌለው፣ ፍሬያማ ያልሆነ እና የሚያሳስብ ነው” ከማለት ባለፈ፤ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ከሁለቱም የፓርላማ አባላት ጋር በመገናኘት ድጋፍ እንዲያገኙ አድርጓል ብለዋል።
የእስራኤል ሕዝብ እና የኢሚግሬሽን ባለስልጣን ለእስራኤል መገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ አብቲሳም መሐመድ እና ዩዋን ያንግ በእስራኤል ላይ “የጥላቻ ንግግር” በማሰራጨት እንዳይገቡ መከልከላቸውን አስታውቀዋል።
“በዚህ መልኩ የብሪታንያ ፓርላማ አባላትን ማስተናገድ እንደማይቻል ለእስራኤል መንግሥት ባልደረቦቼ ግልፅ አድርጌያለው” ብለዋል ላሚ።
- “እጃችሁን አንሱ” በሚል በዩናይትድ ስቴትስ ዋና ዋና ከተሞች የፀረ-ትራምፕ ተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደከ 7 ሰአት በፊት
- አሜሪካ ለደቡብ ሱዳናውያን የሰጠችውን ቪዛ በሙሉ ሰረዘችከ 8 ሰአት በፊት
- እስራኤል በጋዛ በሕክምና ባለሙያዎቹ ላይ በተፈፀመው ግድያ ስህተት መስራቷን አመነችከ 8 ሰአት በፊት
የኤርሊ እና ዉድሊ የፓርላማ አባል የሆኑት ያንግ እና የሼፊልድ ሴንትራል የፓርላማ አባል የሆኑት አብቲሳም ቅዳሜ ዕለት ከሁለት ረዳቶቻቸው ጋር ከሉተን አየር ማረፊያ ወደ እስራኤል በርረዋል።
ምርመራ ከተደረገ በኋላ ወደ አራቱም ግለሰቦች እንዳይገቡ በአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሞሼ አርቤል መከልከላቸውን ባለስልጣኑ መግለጹን ታይምስ ኦፍ እስራኤል ዘግቧል።
እስራኤል ይፋዊ የሥራ ጉብኝት መደረጉን አላረጋገጠችም ሲል ጋዜጣው ቢዘግብም፣ የዩናይትድ ኪንግደም የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አራቱም የፓርላማ ልዑካን ቡድን አባላት መሆናቸውን አረጋግጧል።
“የእንግሊዝ መንግሥት ትኩረቱ ተኩስ አቁም እንዲመለስ እና ደም መፋሰሱን ለማስቆም፣ ታጋቾቹን ለማስለቀቅ እና በጋዛ ያለውን ግጭት ለማስቆም ድርድር ስለማድረግ ነው” ሲሉ ላሚ በመግለጫቸው ተናግሯል።
ቢቢሲ አስተያየት እንዲሰጠው የእስራኤል ሕዝብ እና የኢሚግሬሽን ባለስልጣን ቢያነጋግርም ምላሽ አላገኘም።