
ከ 7 ሰአት በፊት
ናይጄሪያዊው ሜክአፕ አርቲስት ባለፈው ታህሳስ በሰርጉ ላይ በነበረ ጭፈራ ገንዘብ በመበተኑ የስድስት ወራት እስር ተበየነበት።
ግለሰቡ ይህ ቅጣት የተላለፈበት የአገሪቱ መገበያያ ገንዘብ የሆነውን ናይራን “አቃልሏል” በሚል ነው።
በማህበራዊ ሚዲያ ላይ አሙስካፕ በተሰኘ ቅጽል ስሙ የሚታወቀው አብዱላሂ ሙሳ ሁሴይኒ ጥፋተኝነቱን ማመኑን ተከትሎ፤ በካኖ ግዛት የሚገኝ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የእስሩን ቅጣት በይኖበታል።
ገንዘብ መበተን ወይም መርጨት በናይጄሪያ በአብዛኛውን ጊዜ በሰርጎች እንዲሁም በሌሎች ክብረ በዓላት ላይ የሚከናወን ሲሆን፤ ይህም ሰዎች ያላቸውን ሃብት ለማሳየት እንዲሁም ደስታቸውን ለመግለጽ የሚጠቀሙበት ነው።
ነገር ግን የአገሪቱ የኢኮኖሚ እና የፋይናንስ ወንጀሎች ኮሚሽን በአገሪቱ ውስጥ ካሉ ጠቃሚ ምልክቶች አንዱ የሆነው ናይራን ክብሩን የሚያዋርድ ነው የሚል ዘመቻን ከፍቷል።
አሙስካፕ ‘2007 ሴንትራል ባንክ ኦፍ ናይጄሪያ አክት’ የተሰኘውን ህግ በመተላለፍ በቅርቡ ለእስር ከተዳረጉት መካከል ነው።
- ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ “ከሀገር ሉዐላዊነት ያፈነገጡ ግንኙነቶች እንዲቆሙ የማድረግ” ኃላፊነት ተጣለባቸው8 ሚያዚያ 2025
- ጋዛ ‘የግድያ ሜዳ ሆናለች’ ሲሉ የተመድ ዋና ጸሐፊ አሳሰቡከ 7 ሰአት በፊት
- ዩክሬን ለሩሲያ ሲዋጉ ነበር ያለቻቸውን ቻይናዊያን በቁጥጥር ሥር ማዋሏን አስታወቀችከ 7 ሰአት በፊት
ህጉ በግልጽ እንደሚያትተው “ናይራን መርጨት፣ በናይራ ላይ መደነስ ወይም ገንዘቡን መርገጥ” ወንጀል ሲሆን ይህም ቅጣቱ ከስድስት ወር የማያንስ እስራት፣ ወይም 50 ሺህ ናይራ ወይም ሁለቱም ተፈጻሚ ይሆናል ይላል።
እንደ ኮሚሽኑ ከሆነ አሙስካፕ በሰርጉ ላይ 100 ሺህ ናይራ በመበተን “ጉዳት አድርሷል” ሲል ገልጿል።
ከዚህ ቀደም ኦሉዋዳራሲሚ ኦሞሴይን የተባለች ተዋናይት በተመሳሳይ ወንጀል ተከሳ ባለፈው ዓመት ስድስት ወራትን በእስር አሳልፋለች።
አንዳንድ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች በሜካአፕ አርቲስቱ ላይ የተላለፈው የቅጣት ውሳኔ እንዳስቆጣቸው የገለጹ ሲሆን፤ ቅጣቱ ከባድ ነው ሲሉም ትችታቸውን እያቀረቡ ነው።
የአገርን ሃብት መዝብረዋል የተባሉ ሰዎች ሳይቀጡ፣ አንድ ሰው የገዛ ገንዘቡን በትኗል ብሎ ማሰር ግብዝነት ነው ሲሉ አንድ ግለሰብ በማህበራዊ ሚዲያ ወቅሰዋል።