Mengistu Musie

የዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ታሪካዊ መጣትፍ

(ሰቆቃው አብን)

================

ከታሪክ ማህደር ብዙ ምስሎች ይገኛል እነዚያም ማስተማርያ ይሆናሉ፡፡ አስገራሚው ነገር ግን አንባ ገነን መንግስታት እና አድርባይ ግለሰቦች የታሪክ ድግግሞችን እያዩ ይሁንብኝ በሚል ሐገር አጥፍተው ሕዝብ በድለው፤ የራሳቸው ታሪክ ወደቆሻሻ ወርውረው ያልፋሉ፡፡

በሁለተኛው የአለም ጦርነት ሂትለር ፈረንሳይን በስድስት ሳምንት ፓሪስን በ 27 ቀን ውጊያ ተቆጣጠራት፡፡ ለነገሩ ለሂትለር እና የጀርመን ሕዝብ ከሂትለር ጎን እንዲሰለፍ ካደረጉት ዋና ምክኛቶች አንዱ በአንደኛው የአለም ጦርነት ተሸናፊ የነበረችው ጀርመን አቸናፊ የተባበሩት ሐገራት ፈረንሳይ እና እንግሊዝ በማዋረዳቸው ፈረንሳይ የጀርመንን ግዛት (ቨርሳይን) ነጥቃ ወደሷ መጠቅለሏ ነበር፡፡

ሂትለር ፈረንሳይን አይቀጡ ቅጣት ቀጥቶ በቀጥታ በግዛቱ አስገብቷት ነበር፡፡ በዚህ ግዜ ጄኔራ፤ ቻርለስ ዲጎል አርበኛ ሆኖ ዘምቶ የናዚን ወታደራዊ ሐይል ሲዋጋ፡፡ ፈንረንሳይን በተለያየ ግዜ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆኖ ያገለገለው ፔር ላቫል ለሂትለር እጅ ሰጥቶ የሂትለር አድሮ 1942᎐1945 ለናዚው ፓርቲ የፈረንሳይ ጠቅላይ ሚኒስቴር በመሆን አገልግሎአል፡፡ በኋላ የአውሮፓ ናዚዝም እና ፋሽዝም በተባበሩት ሐይሎች ሲቸነፍ ጄኔራል ዴጎል ወደ ፓሪስ ፔር ላቫል የጠላት አገልጋይ በሚል ለፍርድ ቀርቦ 1945 ተረሽኗል፡፡

ዴጎል የስደት መንግስት አቋቁሞ እና ጠላትን ተፋልሞ በድል አድራጊነት ወደፓሪስ ሲገባ ከተለያዩ ክፍለሀገሮች የተሰበሰበ የፈረንሳይ ሕዝብ ድል አድራጊው መሪያችን በሚል ተቀብሎታል፡፡ ፔር ላቫል ሲረሸን ግን የፈረንሳይ ሕዝብ ፌሽታ አድርጎ ሞቱን በደስታ አጅቦታል፡፡

ዛሬ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ በማህበራዊ ሚዲያ የለቀቃት መልእክት ከላይ ያሰፈርሁትን የጄኔራል ዴጎልን እና የፔር ላቫልን ታሪክ አስታወሰኝ፡፡ መኖር ጥሩ ነው፡፡ አያሌ ጓዶቸን በግዜ አጥቻለሁ፡፡ ተርብ ተርብ ታጋዮች ፍጹም ነው እምነቴ በማለት ለሐገራቸው እና ለሕዝባቸው ህይወታቸውን አሳልፈው ሰጥተው አልፈዋል፡፡ ትቂቶች ደግሞ አስገዳይ እና ገዳይ ሆነው ብኩን ሞት ሞተዋል፡፡ ክህደት ሽህ ግዜ ስትደጋገም አይቻለሁ ለማለት ነው፡፡ ክህደት ቆሻሻ ነው ሆኖም ከሀድያን ወይ ለንዋይ፤ ወይንም አሞት የለሽ በመሆን እና ህይወታቸውን ለማትረፍ ቃላቸውን አጥፈው እና ሰርዘው ያወገዙትን የተጠየፉትን መልሰው ሲያቅፉ ተደጋግሞ አይተን ታዝበናል፡፡ የተተፋ አይላስም ቆሻሻ ነው!! ነገር ግን ከሀድያን የተፉትን ይመልሱታል፡፡ ካወገዙት ይተቃቀፋሉ በእኩልነት እና በአቻ ሳይሆን በዝቅተኛነት እና በአገልጋይነት ነው፡፡ ዶ/ር ደሳለኝ ምርር ያለ መልእክቱ የሚነሳም ከዚህ ክህደትን ከመጠየፍ ባንድ ወቅት ያመናቸውን በመታዘብ የተነሳ ሀሳብ ነው፡፡

እውነታውም እሱ የቆመበት ለአማራ ሕዝብ እታገላለሁ ብሎ ቃል መሀላ ይዞ የተነሳ በምን ሎጅክ አማራን እያረደ ላለ አገልጋይ ሆኖ ለወገኑ ሊቆምለት እና ሊከራከርለት ይቻለዋል? ከላይ ያሳየሁት ብኩኑ ከሀዲ ሦሥት ግዜ የፈረንሳይ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆኖ ያገለገለው ሁለት ግዜ በፈረንሳይ ሕዝብ በመመረጥ ሦስተኛው ለሂትለር እጅ በመስጠት እና በማገልገል ሲሆን የሐገር ነጻነት ሲመለስ ዴጎል ወደስልጣን ላቫል በፍርድ እንደውሻ ተጎትቶ ወደመቃብር ተሸኝቷል፡፡

ጄኔራል ቻርለስ ዴጎል 1970 ሲሞት አለም አልቅሶለት ፈረንሳዮች ጀግናቸውን ተሰልፈው በክብር ሸኝተው ፈራሽ ስጋውን ቀብረው ስሙን እና ዝናውን ለዘላለም ታቅፈው ተመልሰዋል፡፡

ዛሬ በሐገራችን ተቃዋሚ ነን፤ የሚሉ በገዳዩ ስልጣን የተቸራቸው የአብን መሪወች ነን ይበሉ እንጅ ስራቸው ለጠላት ማገልገል በመሆኑ የአማራ ሕዝብ በገዳዩ ሊወከል አይችልም የልቁንም ዛሬ በመቶ ሽሆች የሚቆጠሩ አርበኛ ትውልድ አባላት መሳርያ ያነሱበት እና ገዳያቸውን እያርገበገቡት ያለበት ታሪካዊ ወቅት ላይ ነው፡፡ አርበኞቹ እንደዴጎል በክብር አድርባዮቹ እንደስራቸው የፔር ላቫልን ታሪክ ይወርሳሉ፡፡ Adios!!!