
ከ 3 ሰአት በፊት
ዶናልድ ትራምፕ በመታጠቢያ ቤት የሚለቀቀው የውሃ መጠን ከፍ እንዲል በማድረግ “በአሜሪካ ሻወር በድጋሚ ታላቅ እንዲሆን” እንደሚያደርጉ ዋይት ሐውስ አስታወቀ።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ለኢነርጂ ሚኒስቴር በላኩት ትዕዛዝ ለገላ መታጠቢያ የሚሆን ውሃ በርከት ብሎ እንዲለቀቅ ገልፀዋል።
የቀድሞው ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ በአንድ ደቂቃ ከ2.5 ጋሎን አሊያም 9.5 ሊትር ገደማ በላይ ውሀ እንዳይለቀቅ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸው ይታወሳል።
ዋይት ሐውስ እንዳለው “ይህ አክራሪ የአረንጓዴ ልማት አጀንዳ የአሜሪካዊያንን ሕይወት አዘቅት ውስጥ ከቶት ቆይቷል።”
ዶናልድ ትራምፕ ሰውነት መታጠቢያ ክፍል ገብተው ፀጉራቸውን ለማራስ የሚውስድባቸውን ጊዜ “በጣም የሚያናድድ ነው” ሲሉ ገልፀውታል።
የተጠቃሚዎች እና የአካባቢ ጥበቃ ቡድኖች ይህን ሕግ መቀየር ውሀ ማባከን ከመሆኑም ባለፈ አስፈላጊነቱ ያን ያህል ነው ሲሉ ይከራከራሉ።
ኦፕላያንስ ስታንዳርድስ አዌርነስ ፕሮጀክት የተባለው ድርጅት ትራምፕ የቀለበሱትና ከዚህ በፊት ተግባራዊ ይሆን የነበረው ሕግ “የውሃ ብክነትን ለመቀነስ፣ ተጠቃሚዎች ለውሃ የሚከፍሉት ገንዘብ ከፍ ያለ እንዳይሆን ለማድረግ እና ለአካባቢ ጥበቃ አስፈላጊ የሆነ ነው” ሲል ይሞግታል።
- የፀጉር መመለጥን እና መነቃቀልን ማስቆም ይቻላል? ንቅለ ተከላ ማድረግስ መፍትሔ ነው?ከ 5 ሰአት በፊት
- በእስራኤል ጥቃት ከተገደሉ ሐኪሞች አንዱ ከህልፈቱ በፊት በስልኩ ለእናቱ የቀረጸው መልዕክትከ 5 ሰአት በፊት
- የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ትራምፕ በስህተት ወደ ኤል ሳልቫዶር የላኩትን ግለሰብ እንዲመልሱ አዘዘከ 4 ሰአት በፊት
በአውሮፓውያኑ በ1992 በአሜሪካ የወጣው ሕግ የገላ መታጠቢያ ውሃ የሚያፈሱ ‘ሻወሮች’ በደቂቃ ከ9.5 ሊትር በላይ ውሀ እንዳይለቁ ያግዳል።
ባራክ ኦባማ በፕሬዝዳንትነት ዘመናቸው ይህን ሕግ በተወሰነ መልኩ ቢያሻሽሉትም ከሞላ ጎደል እንዳለ ቆይቷል።
ትራምፕ በመጀመሪያው የሥልጣን ዘመናቸው ማብቂያ ገደማ በ2020 ሕጉን አሻሽለው ገላ መታጠቢያ አናቶች ከእያንዳንዱ ቀዳዳ የሚወጣው ውሃ በደቂቃ 2.5 ጋሎን እንዲሆን ትዕዛዝ ማስተላለፋቸው ይታወሳል።
ጆ ባይደን ሥልጣን ሲይዙ ደግሞ ይህን ሕግ ሽረው ወደ ቀደመው እንዲመለስ ማድረጋቸው አይዘነጋም።
የትራምፕ አስተዳደር “አሜሪካዊያን ለውሃ የሚከፍሉት ራሳቸው ናቸው። የፈለጉትን ዓይነት ሻወር የመውሰድ መብት የገዛ ፈቃዳቸው እንጂ የፌዴራል መንግሥቱ አይደለም” ብሏል።
ረቡዕ ዕለት በኦቫል ኦፊስ ትዕዛዙ ላይ ፊርማቸውን ያኖሩት ዶናልድ ትራምፕ “ዞማ” የሆነው ፀጉራቸውን ለማራስ መታጠቢያ ክፍል 15 ደቂቃ እንደሚቆሙ ተናግረዋል።