
ከ 1 ሰአት በፊት
በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ታሪፍ ምክንያት በአሜሪካ የቡና ዋጋ እየናረ ነው።
ከሌሎች አገራት ወደ አሜሪካ የሚገባ ቡና መጠን ስለቀነሰ የቡና ዋጋ ተወዷል። ቡና የሚገዙ ሰዎች ቁጥርም እየቀነሰ ነው።
አሜሪካውያን በዓመት 100 ቢሊዮን ዶላር ለቡና ያወጣሉ። አሁን ባለው የዋጋ መወደድ ምክንያት ግን ይህ ቁጥር መለወጡ አይቀርም።
በዋሽንግተን ዲሲ ብሬድ ባይት ቤከሪ የተባለ ካፌ የሚያስተዳድረው ጆርጅ ፕሩዲንኮ እንዳለው ከኮሎምቢያ የሚያስገቡት ቡና መጠን ስለቀነሰ የቡና ዋጋው ተወዷል።
አሜሪካ በዋናነት ከብራዚል እና ከኮሎምቢያ ነው ቡና የምታስገባው። ቡና ወደ አገር ውስጥ በማስገባት ከዓለም ሁለተኛዋ አገር ናት።
ትራምፕ 10 በመቶ ታሪፍ መጣላቸውን ተከትሎ የቡና ገበያው ተቀዛቅዟል።
ጆርጅ እንደሚለው የቡና ዋጋ እየናረ መሄዱ አይቀርም።
የካፌ ኃላፊው ከማል ሞርታዳ እንዳለው የቡና ዋጋ በቀናት ውስጥ ተለውጧል። አሜሪካ በ40 ዓመታት ያልታየ የዋጋ ንረት የገጠማት በጆ ባይደን አስተዳደር ሥር ነበር።
ታሪፍ ከመጣሉ በፊት በየካቲት ወር ላይ ቡና በአንድ ዶላር ጨምሮ ነበር። በ2020 ከነበረው 3 ዶላር ጭማሪ አሳይቷል።
ከማል የካፌ ደንበኞች ቁጥር መቀነሱን ይናገራል።
“ወተት በቡና ከመጠጣት ይልቅ ቡና ብቻ የሚጠጡ ደንበኞቻችን ቁጥር ጨምሯል” ይላል።
የዋጋ ዝርዝር ላይ የሚታየው የ25 በመቶ ጭማሪ ደንበኞች ውስን ቡና ብቻ እንዲሸምቱ ግድ ብሏል።
- የአሜሪካው ጤና ሚኒስትር የኦቲዝም መንስኤ መስከረም ወር ላይ ይፋ እንደሚደረግ ተናገሩከ 2 ሰአት በፊት
- አሜሪካዊው ፓስተር ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ስብከት ላይ ሳሉ በታጣቂዎች ታፍነው ተወሰዱከ 3 ሰአት በፊት
- የዓለም ገበያ በተቃወሰበት በአሁኑ ወቅት ገንዘብን በወርቅ ላይ ማዋል የሚያዋጣ አማራጭ ነው?ከ 4 ሰአት በፊት

ቡና ቤት ማፍላት የጀመሩም አሉ። ከዚህም በላይ የቡና ዋጋ ይወደዳል ብለው የካፌ አስተዳዳሪዎች ሰግተዋል።
በሳን ፍራንሲስኮ ካፌ ያላት ጄኒ ንጎ የኢትዮጵያ እና የጓታማላ ቡና ነው የምትሸጠው።
ሁለቱም አገራት 10 በመቶ ታሪፍ ተጥሎባቸዋል።
ከቻይና በረዷማ ክፍል ቡና የምታስገባው ጄኒ እንደምትለው የቡና ዋጋ ንሯል።
“ንግዳችን እንዳይሞት እኛም ዋጋ መጨመር አለብን” ትላለች።
ጆርጅ እንደሚለው ቡና ለመግዛት ወደ ካፌ የሚሄዱ ሰዎች በአጠቃላይ ሊቀሩ አይችሉም። ዋጋው ጫና ማሳደሩ ግን አይቀርም።
የኑሮ ውድነት የእንቁላል ዋጋ ላይ ጫና በማሳደሩ ኬክ እና ዳቦ ጋጋሪዎችም ተችግረዋል።
ጆርጅ ከአምስት ወራት በፊት 42 ዶላር ይገዛው የነበረውን የኬክ ግብዓት በ100 ዶላር መግዛት ጀምሯል።
“ዋጋውን እየከፈልን ያለነው ሁላችንም ነን” ይላል።
ትራምፕ የእንቁላል ዋጋ የጨመረው በባይደን አስተዳደር ምክንያት ነው ብለው፣ በእሳቸው አስተዳደር ግን ዋጋው እንደሚቀንስ ቃል ገብተው ነበር።
በባይደን አስተዳደር ወቅት በወፍ ጉንፋን ምክንያት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዶሮዎች ተጎድተዋል።
በትራምፕ አስተዳደር እንቁላል ዋጋው ከዚህ በፊት ባልታየ ሁኔታ እስከ 6.22 ዶላር ደርሷል።

ኮሊያ ኮፊ ሮስተርስ የተባለ ቡና መሸጫ በዲሲ የከፈተው ጆኤል ፊንክሊን እንደሚለው በታሪፍ ምክንያት የዋጋ ንረት ተከስቷል።
ትራምፕ ሥልጣን ከያዙ ጀምሮ የቡና ዋጋ እየጨመረ መምጣቱን ይናገራል።
በተለይም ከዩኤስኤይድ የሚደግለት ድጋፍ መቋረጡ በደቡብ አሜሪካ ድጎማ የሚደረግላቸው አርሶ አደሮች ላይ ጫና ስለሳደረ የቡና ዋጋ ጨምሯል።
“የምንሸጠው የቡና መጠን ማሽቆልቆሉ አይቀርም” ይላል ነጋዴው።
ይህ የቡና ዋጋ በአሜሪካ መናር የተጠቃሚዎችን ቁጥር የሚቀንስ ከሆነ አገራት ወደ አሜሪካ የሚልኩት ቡና መጠንም ይቀንሳል ይህም በአምራች እና በላኪ አገራት ላይ የገቢ ቅናሽን ያስከትላል።