
ከ 3 ሰአት በፊት
በኬንያ ከፍተኛ ተፈላጊነት ያላቸው እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ጉንዳኖችን የሰረቁ አራት ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀረቡ።
ከፍተኛ ተፈላጊነት ያላቸውን እነዚህን ጉንዳኖች ሰርቀው ለማጓጓዝ ሲሞክሩ የተያዙት አራት ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀርበው ጥፋተኛ መሆናቸውን አምነዋል።
የኬንያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ተቋም እንደ አንበሳ እና ዝሆን ያሉ እንስሳት ለመጠበቅ ቢቋቋምም፤ ለጉንዳኖችም ከለላ መስጠቱን በመጥቀስ የፍርድ ቤቱን ጉዳይ “ትልቅ ነው” ሲል አሞካሽቷል።
በአፍሪካ የሚገኙትን እነዚህ African harvester ants ተብለው የሚጠሩት ጉንዳኖች እያንዳንዳቸው በዩናይትድ ኪንግደም እስከ 170 ፓውንድ ይሸጣሉ።
የኬንያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ተቋም በሕገ ወጥ መንገድ የሚዘዋወሩ እንስሳት እምብዛም የማይታወቁ እየሆኑ እንደመጡ እና ይህም አደገኛ መሆኑን ገልጿል።
ተጠርጣሪዎቹ ለጉንዳኖቹ በተዘጋጀ የፕላስቲክ ቱቦ ውስጥ አስቀምጠዋቸው ነው የተያዙት። ጉንዳኖቹ እስከ ሁለት ወር ድረስ በዚህ ቱቦ ውስጥ መኖር ይችላሉ።
ቱቦውን በመደበቅ ከፀጥታ ኃይሎች ሰውረው ከአገር ለማስወጣትም አቅደው ነበር።
- የኤል ሳልቫዶር መሪ በስህተት ወደ አደገኛው እስር ቤት የተላከውን ግለሰብ እንደማይመልሱ ተናገሩከ 6 ሰአት በፊት
- ፍልስጤማዊው የመብት ተሟጋች ተማሪ ለአሜሪካ ዜግነት ቃለ ምልልስ ላይ ሳለ ታሰረከ 6 ሰአት በፊት
- የሀንጋሪ ፓርላማ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያንን እና የጥምር ዜጋ ባለቤቶችን መብት የሚገድብ ሕግ አፀደቀከ 6 ሰአት በፊት

በመቶዎች የሚቆጠሩ ጉንዳኖች ትቦ ውስጥ ገብተው በጨርቅ ተጠቅለለው ተገኝተዋል።
የኬንያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ተቋም ቃል አቀባይ ፖል ኡዶቶ ትክክለኛው የጉንዳኖቹ ቁጥር ገና አልታወቅም ብለዋል።
ከአራቱ ተጠርጣሪዎች ሁለቱ የቤልጂየም፣ አንደኛው የቬትናም እና ሌላኛው የኬንያ ዜግነት አላቸው።
ጉንዳኖቹ ወደ አውሮፓ ወይም እስያ ነበር ለመውሰድ ተዘጋጅተው ነበር ተብሏል ።
የጉንዳኖቹ ተፈላጊነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል። ጉንዳኖቹ መኖሪያቸውን ሲያዘጋጁ ለማየት በሚል የሚገዟቸው ሰዎች እየተበራቱ ነው። ይህ ጉንዳኖቹን የማከማቸት ሂደትም formicariums ይባላል።
በጣም ትልቅ መጠን ያላቸው ጉንዳኖች የበለጠ ተፈላጊነት እንዳላቸውም ተገልጿል።
በኬንያ እነዚህ ጉንዳኖች በዓለም አቀፍ የብዝኃ ሕይወት ጥበቃ ሕግ ከለላ ይሰጣቸዋል። ከፍተኛ ቁጥጥርም ይደረግባዋል።
የኬንያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ተቋም ባወጣው መግለጫ “የፍርድ ቤቱ ሒደት ኬንያ ሕገ ወጥ የዱር እንስሳት ዝውውር ወንጀል ላይ ያላትን ጠንካራ አቋም ያሳያል” ብሏል።