* ከበሮ

* ጸናጽልና

* መቋሚያ የቤተክርስቲያን ንብረቶች ተብለው

በኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን ተመዘገቡ።

ከበሮ፣ጸናጽል፣መቋሚያና ከ10 በላይ ቅዱሳት መጻሕፍትን የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን በቅጂና ተዛማች መብቶች ሥራ ተመዝግቦ ከሚያዚያ 3 ቀን 2017 ዓ/ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አእምሯዊ ንብረት መሆኑ ተረጋግጧል።

ከዚህ ቀደምም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቅርስ ጥበቃ ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር መምሪያ በአእምሯዊ ንብረት ዐቢይ ኮሚቴ አማካኝነት በርካታ የቤተክርስቲያን ንብረቶች ተመዝግበው እውቅና ማግኘታቸውን የመምሪያው ኃላፊ መልአከ ሰላም ዳዊት ያሬድ ገልጸዋል።

Via የ/ኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ/Department of Public Relation,EOTC