የሕክምና ምርመራ እያደረገች ያለች ሴት

ከ 9 ሰአት በፊት

ባለንበት ዘመን እየተስፋፋ ካሉት ተላላፊ ካልሆኑ የጤና ችግሮች መካከል ከፍተኛ የደም ግፊት አንዱ ነው። ይህ የጤና እክል በጊዜው ካልታወቀ እና አስፈላጊው እርምጃ ካልተወሰደ የሚያስከትለው ጉዳት ከባድ እና ውስብስብ ነው።

ስለዚህም የደም ግፊትን በየጊዜው መለካት እና መቆጣጠር አንድ ሰው ከፍተኛ የደም ግፊት እንዳለበት ለማወቅ ወሳኙ መንገድ ነው፤ ምክንያቱም ብዙ ሰዎች ላይ ምልክቱ በይፋ ሳይታይ ቆይቶ ጉዳትን ስለሚያስከትል ነው።

በዓለማችን ከፍተኛ የደም ግፊት ካለባቸው 1.3 ቢሊዮን ሰዎች መካከል ግማሽ ያህሉ የጤና ችግሩ እንዳለባቸው አያውቁም።

በዓለም ላይ በርካታ ከፍተኛ የደም ግፊት ያላባቸው ሰዎች የሚገኙት በአፍሪካ ውስጥ ሲሆን ከአጠቃላዩ 27 በመቶው የሚገኙት በአህጉሪቱ ውስጥ ነው።

ዝቅተኛ ቁጥር ያላቸው ከፍተኛ የደም ግፊት ያለባቸው ሰዎች የሚገኙት ደግሞ በአሜሪካ ሲሆን፣ ሥርጭቱም 18 በመቶ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ያለመለክታል።

ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ባላቸው አገራት የከፍተኛ የደም ግፊት ተጋላጭነት ምክንያቶች እየጨመሩ በመሆኑ ምክንያት ከፍተኛ የደም ግፊት ያለባቸው በርካታ ጎልማሶች ተመዝግበዋል።

የሕክምና ክትትል ያልተደረገበት ከፍተኛ የደም ግፊት መጨመር እንደ የልብ ህመም፣ ስትሮክ እና የኩላሊት ሥራ ማቆምን ለመሳሰሉ ከባድ የጤና ችግሮች የመጋለጥ ዕድልን በእጅጉ ይጨምራል፤ ብዙዎቹም ያለጊዜው ለሞት ሊዳርጉ ይችላሉ ሲል የዓለም ጤና ድርጅት ገልጿል።

የደም ግፊት መጠንን አስቀድሞ ለማወቅ እና ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመቆጣጠር መደበኛ ክትትል አስፈላጊ ነው።

የሚከተለው ዘዴ በዓለም ጤና ድርጅት ደረጃ መሠረት የአንድን ሰው ለከፍተኛ የደም ግፊት ያለውን ተጋላጭነት ለማወቅ፣ የደም ግፊት ልኬት ንባብ ምን ማለት እንደሆነ ለመረዳት እና ጤናን ለመጠበቅ መወሰድ ስላለባቸው እርምጃዎች ምክር ለመስጠት ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

እርስዎም ይሞክሩት፤ ለቤትሰብዎ፣ ለጓደኞችዎ፣ ለሚያውቋቸው እና ጤና ለሚመኙላቸው በሙሉ ያጋሩ።

ለከፍተኛ የደም ግፊት ተጋላጭ መሆንዎን ያጣሩ

የደም ግፊትዎ ጤናማ ነው?

የደም ግፊት መጠንዎ ምንነትን ለማወቅ ይህንን አገልግሎት ይጠቀሙ፤ ምን ማድረግ እንዳለብዎም መረጃ ያግኙ።

ይህንን ዘዴ እንዴት ነው መጠቀም ያለብዎት

አማካይ የደም ግፊትዎ ልኬትን ይከታተሉ

የደም ግፊት ልኬት በሁለት ቁጥሮችን የሚያካትት ነው። የሲስቶሊክ ቁጥር ልባችን ሲመታ በደም ስሮቻችን ውስጥ ያለውን ግፊት የሚያመለክት ነው። የዳያስቶሊክ ቁጥር ደግሞ በልብ ምቶቻችን መካከል ባለው ጊዜ ልባችን ሲያርፍ ያለውን ግፊት የሚያመለክት ነው።

በሁለት የተለያዩ ጊዜያት የተመዘገቡትን የደም ግፊትዎን ልኬት ቁጥሮች ከታች ያስገቡ

የመጀመሪያው ልኬትሲስቶሊክ (የላይኛው ቁጥር)ዲያስቶሊክ (የታችኛው ቁጥር)

ሁለተኛው ልኬትሲስቶሊክ (የላይኛው ቁጥር)ዲያስቶሊክ (የታችኛው ቁጥር)ውጤት