Mengistu Musie

መታዘባችን አልቀረም

120 ንጹሐን ሲጨፈጨፉ ዝምታ አያሳፍርም?

=====================

ያማራ ልጆች እጃቸው አመድ አፋሽ ነው፡፡ ሐገርን በጀግንነት ሞተው ስለጠበቁ ነፍጠኛ ትምክህተኛ ተብለው የእስከዚህ ዘመን ፍጅት ዋጋቸው ሆኗል፡፡

ከሰባት አመት በፊት ሰው መስሏቸው በቀለ ገርባ ይፈታ የሚል መፈክር ይዘው ባሕርዳር ላይ የተሰው ወጣቶችም ነበሩ፡፡ በቀለው ገርባ ከእስር ቤት ወጥቶ ምስጋና አላቀረበም፡፡ ወይንም የተሰውበትን ዝክረ ሰማ’እታት ለመጎብኘት ባሕርዳር ወይንም ጎንደር አልሄደም፡፡ ሳይውል ሳያድር አዲስ መፈክር ይዞ ብቅ አለ፡፡ ምርትህን ለአማራ አትሽጥ ብሎ አወጀ፡፡ አማርኛ የጠላት ቋንቋ ነው በአማርኛ መልስ አትስጥ አለ፡፡ ይህ ሰው የቋንቋ መምህርም ነው ይባላል ግን አማራኛ ጠላቱ ሲሆን እና ቋንቋ የሰው ልጆች መግባቢያነቱን ሳይሆን ከአለም ቋንቋአወች ሁሉ አማርኛ ለበቀለ ወለጋወች ጠላት ነው አትናገሩት ብለው ሰብከዋል፡፡

የአማራ እጅ አመድ አፋሽ ይሏል ይህ ነው፡፡ ለአለፉት ሁለት አመታት የተጨፈጨፈ ንጹሐን ቁጥር ቀን ሲያልፍ ይቆጠራል፡፡ የአማራ እጅ አመድ አፋሽ ስንል ያየነው ያስተዋልነው ጎንደር፤ ባሕርዳት፤ ደብረማርቆስ፤ ደሴ፤ ደብረብረ ብርሐን የዛሬ 8 እና 9 አመት የኦሮሞ ደም ደሜ ነው ብለው የተሰለፉ መፈክር ያነገቡ ወጣቶች በዚያን ዘመኗ ገዥ ቡድን በህወሓት ተገድለዋል እድለኞች ታስረው ተደብድበው ተርፈዋል፡፡

አብይ አህመድ እና የባንዳው የብርሐኑ ነጋ ቡድን የጎጃም አማራ ላይ የተለየ ጥላቻ ጨምሮ ስብከታቸው ሁሉ ማፈሪያ ነው፡፡ አረመኔው አብይ በፓርላማ ለዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ መልስ በሚል የጅብ ቆዳ ለብሰው እየተዋጉን ነው አለ!! ውሎ ሳያድር የአረመኔው መንፈስ ያለው የቶማስ ጃጃው አይነት ፋኖ ነኝ ባይ ጎጠኛ የቡዶች ሰፈር አለ፡፡ በጎጥ ክፍፍል እና የግለሰብ ማን አህሎኝነት (Egocentrism) የአማራ ሕዝብን ትግል አጓትቷል ከዚህ የጅምላ ጭፍጨፋ ነጻ እንዲሆን ግለሰብ ሳይሆን ሕዝብን ማየት ተገቢ ነው ይህም ፅብት ነው፡፡

አንድን የኦሮሞ ወጣት የአረመኔው ቡድን አርዶ የኦሮሞ ወጣት ነን የሚሉ የዩኒቨርስቲ ተማሪወች ከአምቦ እስከ አዲስ አበባ እና ሐረማያ ተሰለፉ ድጋፋቸውን ለአራጁ ወንጀል ፈጻሚ ብልጽግና ሆኖ በጅምላ አማራን ያረዱት ያሳረዱት ያሰደዱት አንሶ ዳግም ሕዝብን ሲረግሙም አይተን ታዝበናል፡፡

በቅድመ የካቲት እና ድህረ የካቲት አብዮት የምናውቀው ተርቡ የአዲስ አበባ ወጣት ዛሬ ነፍዞ እንኳን ለሐገሪቱ ነጻነት ለቆመ ነጻነት ታጋይ ቀርቶ ለጎረቤቱ እና ለራሱ መብት መከራከር ሳይችል አረመኔው እና ቡድኑ በመቶ ሽሆችን የከተማዋ ነዋሪወች የጎዳና ተዳዳሪ አርጓቸዋል፡፡ ይህስ ቢሆን አያስተዛዝብም ትላላችሁ፡፡

ሌላውስ ኢትዮጵያዊ ምን ነካው አማራን የጨረሰ ስርአት ለእሱ የሚመለስ ይመስለዋል? ይህም ትዝብት ነው፡፡ ግን አንድ ነገር እርግጠኛ ነኝ የፈሰሰው የንጹሐን ደም በፍርድ ፊት ቆሞ ደም አፍሳሾችን ይፋረዳል ይህ አይቀሬ ነው፡፡

ከዘመን በፊት የሆነውም ይህ ነበር እነለገሰ አስፋው፤ መንግስቱ ሐይለማርያም የነሱ አሽከር የነበሩት መላኩ ተፈራ እና ካሳየ አራጋው የቀይ ሽብሩ ፊታውራሪው ለገሰ አስፋው ቀን ሲለወጥ በአዲሲ አበባ ጎዳና አህያ ሲነዳ ነበር የተያዘው ሌሎችም በየአልባሌው ቦታ ተሸጉጠው እጅ ሰጥተዋል፡፡ ያን ዘመንም ብዙሀን የቀይ ሽብር ሰለባወች ያው የፈረደበት ለኢትዮጵያ መለወጥ የሁሌ ሰማእቱ አማራው ነበር ሌሎቹ አንዱ ኢጬት ሌላው ህወሐት በሚል ሲልከሰከሱ እና በየዘር ጎራው ተሰልፈው ነፍጠኛን ሲያወግዙ ነበር ያሳለፉት ዛሬም አሁን በአማራ ሕዝብ ላይ እየወረደ ያለው ፍጅት በትውልዱ አመጽ መለውጡ አይቀሬ ነው፡፡ ማን አህያ ሲጎትት እንደሚያዝ ደግሞ የምናየው ይሆናል፡፡

በእናርጅ እናውጋ ምስራቅ ጎጃም 120 ንጹሐን ተቸፍጭፈዋል፡፡ ሁለት ሳምንት በፊት ብራቃት ሰሜን ሜጫ ክ50 በላይ ንጹሐንን ጨፍጭፈው ነበር፡፡ የዚህ ሁሉ መንገድ መሪ የግድያው አስፈጻሚ ባንዳው እና ምስለኔው የአረጋ ከበደ ቡድን መሆኑ ይመዝገብ፡፡

በጸሎተ ሐሙስ የተደረገ ፍጅት!!!

All reactions:

4Estibel Wassie and 3 others