
ከ 4 ሰአት በፊት
የዩክሬን መንግሥት ከአሜሪካ ጋር የማዕድን መግባቢያ ስምምነት መፈራረሙን አስታወቀ።
የኢኮኖሚ ሚኒስትሯ ዩሊያ ስቪሪደንኮ የፍላጎት ማሳያ ስምምነት ላይ በመደረሱ ለኢኮኖሚ ሽርክና ስምምነት መንገድ ጠርጓል ብለዋል።
የመጨረሻው ስምምነት ለዩክሬን መልሶ ግንባታ የኢንቨስትመንት ፈንድን እንደሚያካትትም ገልጸዋል።
የአሜሪካ ባለስልጣናት ስምምነቱ በሚቀጥለው ሳምንት መገባደጃ ላይ ሊጠናቀቅ እንደሚችል ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።
ዶናልድ ትራምፕ በየካቲት ወር በዋይት ሐውስ ከዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ ጋር በጋዜጠኞች ፊት የገቡት ውዝግብ ድርድሩን ለጊዜው ገትቶት ቆይቷል።
ስቪሪደንኮ የመግባቢያ ስምምነት መደረሱን በኤክስ ገጻቸው ላይ ቢያሳውቁም፣ ተጨማሪ ዝርዝር ጉዳዮችን ይፋ አላደረጉም።
የእሳቸው እና የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስትር ስኮት ቤሴንት በተናጠል የተፈራረሙባቸውን ፎቶዎች አካትተው ለጥፈዋል።
“ለኢኮኖሚዊ አጋርነት ስምምነት እና ለዩክሬን መልሶ ግንባታ የኢንቨስትመንት ፈንድ ማቋቋሚያ መንገድ የሚከፍተውን የማዕድን መግባቢያ ስምምነት ከአጋራችን አሜሪካ ጋር መፈራረማችንን ስናበስር በደስታ ነው” ሲሉ ስቪሪደንኮ ጽፈዋል።
የፊርማ ስነስርዓት የተካሄደው ከቤሴንት ጋር በተደረገ የበይነ መረብ ግንኙነት ሲሆን የስምምነቱ ዝርዝሮች ጉዳዮች ላይ እየተሠራ ነው ብለዋል።
“ቀደም ሲል የተስማማንበት ነገር ነው።ፕሬዝዳንቱ [ቮሎዲሚር ዘለንስኪ] እዚህ በነበሩበት ጊዜ የመግባቢያ ስምምነቱ ነበረን። በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ነው ያመራነው። የ 80 ገጽ ስምምነት ይመስለኛል እሱን ነው የምንፈርመው” ብለዋል።
- የኢየሱስ ስቅለት እና ሞት በሕክምና ባለሙያዎች ዓይን እንዴት ይተነተናል?ከ 5 ሰአት በፊት
- ለምክክር ኮሚሽኑ አጀንዳ ያቀረበው ከፋኖ ውጪ ያለ ታጣቂ ቡድን መሆኑ ተገለጸከ 5 ሰአት በፊት
- ሃማስ እስራኤል ያቀረበችውን የተኩስ አቁም ጥያቄ በይፋ ውድቅ አደረገከ 4 ሰአት በፊት
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕም ከጣሊያኗ ጠቅላይ ሚንስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ጋር በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ስለስምምነቱን ፍንጭ ሰጥተዋል።
“በመጪው ሐሙስ ይፈረማል ብዬ የምገምተው የማዕድናት ስምምነት አለን። እናም ስምምነቱን አክበረው ይሠራሉ ብዬ እገምታለሁ። ስለዚህ የምናየው ይሆናል። በዚህ ዙሪያ ግን ስምምነት አለን” ብለዋል።
ዋይት ሐውስ የስምምነቱን ጊዜ እና ይዘት በተመለከተ ተጨማሪ ዝርዝር ጥያቄ ቢቀርብለትም ምላሽ አልሰጠም ሲል ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።
ስምምነቱ አሜሪካ የዩክሬን ወሳኝ ማዕድናት፣እንዲሁም ነዳጅና ጋዝ ማግኘት የሚያስችላት አንድ እርምጃ ነው ተብሏል።
ለዩክሬን መልሶ ግንባታ “የኢንቨስትመንት ፈንድ” እንደሚቋቋም እና በኪዬቭ እና በዋሽንግተን “በእኩል ሁኔታ” እንደሚተዳደር ቀደም ሲል የወጡ ዘገባዎች አመልክተዋል።
ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ ከሩሲያ ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት ሲደረስ አገራቸው ከአሜሪካን የደህንነት ዋስትና እንድታገኝ ስምምነቱን ለመጠቀም ተስፋ አድርገው ነበር።
ሆኖም በየካቲት ወር በዜሌንስኪ እና ትራምፕ መካከል በዋይት ሐውስ በይፋ በገቡበት ውዝግብ ምክንያት ዕቅዱ ውድቅ ተደርጓል።