
ከ 2 ሰአት በፊት
የቴስላ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኤለን መስክ ዶጅ ተብሎ ከሚጠራው የትራምፕ አስተዳደር ወጭ ቆጣቢ ቡድን ጋር ያለውን ኃላፊነት እንደሚያቋርጥ ተናግሯል።
ዶጅ የትራምፕ አስተዳደር የፌደራል መንግሥቱን ወጪ ለመቀነስ እና ሥራዎችን ለማሳለጥ በሚል ያቋቋመው ሲሆን መስክ በኃላፊነት ሲመራው ቆይቷል።
ፕሬዚዳንቱን ጨምሮ የዋይት ሐውስ ሰዎች መስክ በቅርቡ ከኃላፊነቱ እንደሚለቅ የታቀደው ከረጅም ጊዜ በፊት እንደነበር ገልጸዋል።
መረጃው ይፋ የተደረገው የቢሊየነሩ የኤልትሪክ መኪና ንግድ ገቢ እያሽቆለቆለ መምጣቱ ከተነገረ በኋላ ነው።
መስክ ውሳኔውን እፋ ቢያደርግም በትክክል መቼ እንደሚለቅ እና ሲመራ የነበረው ተቋም መጨረሻ ምን ይሆናል የሚሉ ብዙ ያልተመለሱ ጥያቄዎችን ፈጥሯል።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ረቡዕ ዕለት ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄ አስተዳደሩ መስክን ለማሰናበት እየተዘጋጀ ነው የሚለውን መልዕክት አጠናክረዋል።
ትራምፕ በዋይት ሐውስ እንደተናገሩት “እሱን ማሰናበት አለብን። ስለ ጉዳዩ ከኤለን ጋር እነጋገራለሁ” ብለዋል።
ፕሬዚዳንቱ አክለውም መስክ ከተሰናበተ በኋላ ቴስላ ድጋፍ እንደሚደረግለት ገልጸው “በአንዳንድ ሰዎች በጣም ኢፍትሃዊ በሆነ መልኩ እየተገመተ ነው” ሲል ወቅሰዋል።
“እሱ ታላቅ አገር ወዳድ ሰው ነው። ይህ በእርሱ ላይ ፈጽሞ ሊደርስበት አይገባም ነበር” ብለዋል ትራምፕ።
በአሜሪካ መንግሥት ሕግ መሰረት ጥቂት ቀናትን በዶጅ ማሳለፉ ብቻ መስክን በመንግሥት ኃላፊነት ውስጥ ያለውን ጊዜ ሊያራዝመው ይችላል።
በአሜሪካ ህግ መሰረት መስክ “ልዩ የመንግሥት ሠራተኛ” ተብሎ በመሰየሙ በየዓመቱ ለ130 ቀናት ተከፍሎትም ሆነ ሳይከፈለው የመንግሥት ሥራ ላይ እንዲሠራ ያስችለዋል።
በዚህ መመርያ መሰረት መስክ የመንግሥት ሙሉ ቅጥር ሳይሆን፣ የመንግሥትን የስነምግባር ሕግ እና ፍላጎት አክብሮ እነደ አመቺነቱ የሚሰራ ባለሙያ ተደርጎ ነው የሚቆጠረው።
እአአ በ2007 የፍትህ ቢሮ ያወጣው ይህ መመሪያ ማንኛውም “ልዩ ሠራተኛ” የመንግሥት ሥራን በሚያከናውንበት ወቅት እንደ አንድ ሙሉ ቀን ይቆጠራለታል።
ይህንን ከግምት በማስገባት ከትራምፕ በዓለ ሲመት ጀምሮ፣ መስክ ቅዳሜና እሑድን እንደሚሠራ ይገልጻል፣ በሳምንት ለአምስት ቀናት ያህል በዶጅ ሠርቷል ተብሎ ቢታሰብ ኃላፊነቱ ግንቦት ወር መጨረሻ ላይ ያበቃል።
መስክ ስለ ዕቅዱ ዝርዝር መረጃ ባይሰጥም፣ ቴስላ የ71 በመቶ የትርፍ መቀነስን ጨምሮ የገንዘብ ችግሮች እንደገጠሙት ከተዘገበ በኋላ ነው በመንግሥት ኃላፊነት ላይ የሚያሳልፈውን ጊዜ እንደሚቀንስ የገለፀው።
- ቻይና የዶናልድ ትራምፕን ታሪፍ ለመቋቋም ምን ዓይነት እርምጃዎችን ልትወስድ ትችላለች?ከ 5 ሰአት በፊት
- ትራምፕ በንግድ ዙርያ ንግግር ለማድረግ ከፈለጉ የጣሉትን ታሪፍ እንዲያነሱ ቻይና አሳሰበችከ 4 ሰአት በፊት
- የእስራኤል መከላከያ ወታደሮቹ የመንግሥታቱ ድርጅት ሠራተኛን መግደላቸውን አመነከ 4 ሰአት በፊት
Skip podcast promotion and continue reading

ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በቀጥታ በዋትስአፕ ለማግኘት
ይህን በመጫን የቻናላችን አባል ይሁኑ!
End of podcast promotion
የቴስላ ገቢ መቀነስ የመጣው በዓለም ዙሪያ ተደጋጋሚ “ቴስላን አትጠቀሙ” የሚል ተቃውሞ እና በመስክ የመንግሥት ሚና ምክንያት በመኪና አምራቹ ላይ አድማ እንዲደረግ ጥሪ ከቀረበ በኋላ ነው።
አብዛኞቹ የተቃውሞ ሰልፎች ሰላማዊ ናቸው ቢሉም አንዳንዶቹ በቴስላ መሸጫዎች እና ቻርጅ ማድረጊያዎች ላይ እሳት ለኩሰዋል።
ኩባንያው “የፖለቲካዊ ስሜትን መለወጥ” የተሽከርካሪዎችን ፍላጎት ትርጉም ባለው መልኩ ሊጎዳ ይችላል ከማለት ባለፈ ችግሩ ሊቀጥል እንደሚችል ባለሃብቶችን አስጠንቅቋል።
መስክ ለባለሀብቶች ባስተላለፈው መልዕክት ለዶጅ የሚመድበው ጊዜ “በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀንስ እና ብዙ ጊዜውን ለቴስላ እንደሚሰጥ” ተናግሯል።
ከአስተያየቶቹ በኋላ እያሽቆለቆለ የነበረው የቴስላ የአክሲዮን ዋጋ መጨመር አሳይቷል።
የትራምፕ አስተዳደር ለመስክ ከዚህ ቀደም ያልነበረ ቢሮ ለመፍጠር የመንግሥትን ሕጎች ተላልፎ ሊሆን ይችላል በሚል ይወቀሳል።
በዚህ ምክንያትም በመመርያው ላእ የተቀመጠውን የ130 ቀነ ገደብ ሳይጠብቅ ሊለቅ ይችላል የሚል ግምት አለ።
በመንግሥት ልዩ ሠራተኛ ደንቦች መሰረት መስክ የስነምግባር ስልጠና መውሰድ፣ ሚስጥራዊ የፋይናንስ መግለጫ መስጠት እና የጥቅም ግጭቶችን ማስወገድ አለበት።
የእሱ ኩባንያዎች ከአሜሪካ መንግሥት እና ከውጭ መንግሥታት ጋር የንግድ ስራዎችን ይሠራሉ።
ከእነዚህም መካከል ስፔስኤክስን ጨምሮ 22 ቢሊዮን ዶላር የአሜሪካ መንግሥት ኮንትራት ውል እንዳለው የኩባንያው ዋና ስራ አስፈጻሚ ተናግረዋል።
በሕጎቹ መሠረት በመንግሥት መስሪያ ቤቶች ውስጥ ወይም ይፋዊ ተግባራት በሚያከናውኑበት ጊዜ ልዩ የመንግሥት ሠራተኞች የፖለቲካ አቋም የሚያንጸባርቅ ልብስ መልበስን ጨምሮ የፓርቲ እንቅስቃሴዎች ተሳትፎን ይከለክላል።
መስክ በኦቫል ኦፊስ ውስጥ “አሜሪካን እንደገና ታላቅ አድርግ” የሚል ኮፍያ አጥልቆ ታይቷል።

በየካቲት ወር ላይ ማንነታቸው ያልተገለጸ የዋይት ሐውስ ባለስልጣን ለቢቢሲ የአሜሪካ አጋር ለሆነው ለሲቢኤስ ኒውስ መስክ ገንዘቡን በተመለከተ ሚስጥራዊ መግለጫ እንደሚያቀርብ እና የስነምግባር መግለጫ እንደሚሰጠው ገልጸዋል።
የዋይት ሐውስ የፕሬስ ሴክሬታሪ ካሮሊን ሌቪት ለቢቢሲ እንደተናገሩት ደግሞ “ኤለን መስክ ከራስ ወዳድነት ነፃ በሆነ መልኩ የፕሬዚዳንት ትራምፕን አስተዳደር እንደ ልዩ መንግሥት ሠራተኛ እያገለገለ ነው። ሁሉንም የሚመለከታቸው የፌዴራል ሕጎችን አክብሯል” ብለዋል።
በአሁኑ ጊዜ መስክ በፕሬዝዳንቱ ትዕዛዝ ምንም ግልጽ ቁጥጥር ሳይደረግበት እየሰራ ያለ ይመስላል።
ባለፈው ሳምንት ፐብሊክ ሲቲዝን በለቀቀው ዘገባ የትራምፕ አስተዳደርን በመንቀፍ፤ ዋይት ሐውስ የልዩ መንግሥት ሠራተኛ መመርያዎችን “ከሕግ ውጭ እየተጠቀመበት ነው” ብሏል።
ቢቢሲ መስክን እና የግል አስተዳደሩን ስለጉዳዩ ጠይቋል።
ዎል ስትሪት ጆርናል ሐሙስ ዕለት እንደዘገበው ከሆነ 100 የሚጠጉ የዶጅ ሰራተኞች መስክ በዚህ ዓመት ከለቀቀ በኋላ በተለያዩ የመንግሥት ክፍሎች ውስጥ እንደሚቆዩ ዘግቧል።
መስክ እና ትራምፕ ዶጅ ሥራውን እንዲያጠናቅቅ ቀነ ገደብ አስቀምጠዋል። ይህም የአሜሪካ የነጻነት ከተፈረመበት 250ኛ ዓመት ላይ ይውላል ተብሏል።
በትራምፕ የተፈረመው ሰነድ እንደሚያሳያው መስክ የሚመራው ተቋም እአአ ሐምሌ 4 ቀን 2026 ስራውን እንደሚያጠናቅቅ ይገልጻል።
መስክ ቀደም ብሎ በታህሳስ ወር በትዊተር ገጹ በሰጠው ምላሽ፣ ዶጅ በዚያው ቀን ሙሉ በሙሉ እንደሚጠናቀቅ ተናግሯል።
“የዶጅ የመጨረሻ እርምጃ ራሱን ማጥፋት ነው” ሲል ጽፎ ነበር።