#ቤዛ ምንድን ነው?
የቃሉ ትርጉም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እና በሌላ ቦታ ሲጠቀስ ተመሳሳይ የማይሆንበት እድል ሰፊ ነው።
የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማህበር በ፮ኛ እትም መዝገበ ቃላቱ ላይ “ቤዛ” የሚለውን ቃል የተረጎመው “የተያዘን ወይም የተወሰደን ነገር ለማስመለስ የሚከፈል ዋጋ፣ ካሣ፣ ለውጥ” በማለት ነው።
√ ገንዘብ የህይወት ቤዛ ነው፤ ምሳ ፲፫፣፰
√ የእስራኤል ህዝብ መሬታቸውን ወይም
ቤታቸውን ከሸጡ በኋላ ለመቤዠት ይችሉ ነበር፤
ዘሌ ፳፭፣፳፬-፴፬
√ ኢየሱስ ለሚያምኑበት ሁሉ በሞቱ ቤዛ
ሆነላቸው፤ ማር ፲፣፵፭፤ ኤፌ ፩፣፯፤ ፩ጢሞ
፪፣፭-፮
√ ለሰው የተደረገለት ቤዛነት የሚፈጸመው
ከሙታን ትንሣኤ በኋላ ነው፤ ሮም ፰፣፳፫ ኤፌ
፬፣፴
የሚሉትን ነው።
ስለዚህ ይህ ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥም አንድ ዓይነት ትርጉም ብቻ እንዳለው ማሰብ ከባድ ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ በዚህ ቃል ከተነገሩ ምሳሌዎች ውስጥ የሚከተሉት ጭምር ይገኙበታል፦
እኔ የእስራኤል ቅዱስ አምላክኽ እግዚአብሔር መድኀኒትኽ ነኝ። ግብጽን ለአንተ #ቤዛ አድርጌ፥ ኢትዮጵያንና ሳባንም ለአንተ ፋንታ ሰጥቻለኹ። ኢሳ ፵፫፣፫
በኀይላቸው የሚታመኑ፥ በባለጠግነታቸውም ብዛት የሚመኩ፤ ወንድም ወንድሙን አያድንም፥ ሰውም አያድንም፤#ቤዛውን ለእግዚአብሔር አይሰጥም። (መዝ ፵፰ ፮-፯)
#ቤዛ የላቸውምና፥ እግዚአብሔርንም አልፈሩትምና (መዝ ፶፬፣፲፱)
ለሰው ነፍስ #ቤዛው ሀብቱ ነው። ምሳ ፲፫፣፰
ኃጥእየጻድቅ #ቤዛ ነው፤ በደለኛም የቅን ሰው #ቤዛ ነው። ምሳ ፳፩፣፲፰
ከእነርሱ ሰው ዅሉ እንደ ቍጥራቸው መጠንየነፍሱን #ቤዛ ለእግዚአብሔር ይስጥ። ዘጸአት ፴፣፲፪
የዘለዓለምን #ቤዛነት አግኝቶ አንድ ጊዜ ፈጽሞ ወደ ቅድስት በገዛ ደሙ ገባ እንጂ በፍየሎችና በጥጃዎች ደም አይደለም። ዕብ ፱፣፲፪
ራሱንም ለዅሉ #ቤዛ ሰጠ ይህም በገዛ ዘመኑ ምስክርነቱ ነበረ። ፩ኛ ወደ ጢሞቴዎስ ፪፣፮
እርሱ ከጨለማ ሥልጣንአዳነን #ቤዛነቱንም እርሱንም የኀጢአትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደፍቅሩ ልጅ መንግሥት አፈለሰን። ፩ኛ ቆላስይስ ፩ ፲፫-፲፬
እግዚአብሔር የሰጠን የምንድንበት በእርሱ ተስፋ የምንኖርበት የልጁ #ቤዛ ይሁን አለችው። ጦቢት ፭፣፭
ስለ ሁለት መቶ ሰባ ሶስት #ቤዛ በየራሱ አምስት ሰቅል ውሰድ። ኦሪት ዘ ትልቅ ፫
ሰው ስለነፍሱ #ቤዛ ምን ይሰጣል? ማቴ ፲፮፣፳፮
እንዲሁም የሰው ልጅ ሊያገለግል ነፍሱንም ለብዙዎች #ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም። ማቴ ፳፣፳፰
ሊያገለግልና ነፍሱን ለብዙዎች #ቤዛ ሊሰጥ እንጅ እንዲያገለግሉት አልመጣም። ማር፲
ጎብኝቶ ለህዝቡ #ቤዛ አድርጓልና ሉቃ ፩፣፴፰
ሰውስ ስለነፍሱ #ቤዛ ምን ይሰጣል? ማር፰፣፴፯
የኢሩሳሌምንም #ቤዛ ለሚጠባበቁ ሁሉ ስለእርሱ ይናገር ነበር። ሉቃ ፪፣፴፰
ክፉ ቃል ከአፋችኹ ከቶ አይውጣ።
#ለቤዛም ቀን የታተማችኹበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ። ፩ኛ ኤፌ ፬፣፳፱-፴
በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ በኃይልና በብዙ ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል። ይህም ሊሆን ሲጀምር #ቤዛችሁ ቀርቦአልና አሻቅባችሁ ራሳችሁን አንሡ። ሉቃ ፳፩፣፳፯-፳፰
ነገር ግን የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ ተብሎ እንደተጻፈው ይኾን ዘንድ ከእግዚአብሔር ዘንድጥበብና ጽድቅ፣ ቅድስናም፣ #ቤዛነትም በተደረገልን በክርስቶስ ኢየሱስ የኾናችኹ ከእርሱ ነው። ፩ኛ ቆሮ፩፣፴-፴፩
በደሙ የተገኘ #ቤዛችንን አገኘን። ኤፌሶን ሰዎች ፩
የመንፈስ በኵራት ያለን ራሳችን ደግሞ የሰውነታችን #ቤዛ የኾነውን ልጅነት እየተጠባበቅን…ሮሜ ፰
ሙሴንበመልአኩ እጅ እግዚአብሔር ሹምና #ቤዛ አድርጎ ላከው። የሐዋርያት ስራ ፯
በኢየሱስ ክርስቶስም በኾነው #ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ። ሮሜ ፫

