
ከ 7 ሰአት በፊት
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሁለተኛ የሥራ ዘመን 100 ቀን የሥልጣን ቆይታቸውን የምርጫ ዘመቻ በመሰለ ንግግር ስኬቶቻቸውን ሲያወድሱ ጠላቶቻቸውን ደግሞ ወርፈዋል።
“አብዮታዊ የጋራ አስተሳሰብ” ሲሉ በሚቺገን ግዛት ለተሰበሰቡ ደጋፊዎቻቸው ስኬታቸውን ያወደሱት ትራምፕ፤ ሥልጣናቸውን “ለጥልቅ ለውጥ” እየተጠቀሙበት እንደሆነ ተናግረዋል።
“ገና መጀመራችን ነው። ገና ምን አይታችሁ” ሲሉ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ማክሰኞ ዕለት ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ የአሜሪካን ድንበር በሕገ ወጥ መንገድ ጥሰው የሚገቡ ስደተኞችን ቁጥር በእጅጉ ቢቀንሱም፤ ከመላው ዓለም ጋር የገቡበት የንግድ ጦርነት ምጣኔ ሀብት እና ፖለቲካዊ ክፍተት እንደሚፈጥርባቸው ተገምቷል።
ፕሬዝዳንቱ የኢሚግሬሽን አፈፃፀማቸውን ሲያወድሱ የተሰሙ ሲሆን፤ በአገሪቱ ደቡብ ድንበር በሕገ ወጥ መንገድ የገቡ ሰዎች ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር ከነበረው 140 ሺህ ወደ ሰባት ሺህ ዝቅ ማድረጋቸው ተነግሯል።
ዋይት ሐውስ ባለፉት ወራት 65 ሺህ 700 ስደተኞችን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ መደረጉን ያሳወቀ ሲሆን፤ ይህም በባይደን አስተዳደር ባለፈው በጀት ዓመት ከነበረው አፈፃፀሙ ዝቅ ያለ ነው።
በዲሞክራቱ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የተሳለቁት ትራምፕ፤ ተወዳጅነታቸው እየቀነሰ መምጣቱን የሚያሳዩ የሕዝብ አስተያየቶችን አጣጥለዋል።
ጋላፕ የተበለው የሕዝብ አስተያት መሰብሰቢያ በ100 ቀናት የሥልጣን ቆይታቸው ትራምፕ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ከግማሽ በታች የሆነው ሕዝብ የሚደግፋቸው ብቸኛ መሪ ናቸው ብሏል።
የሕዝብ ድጋፋቸው 44 በመቶ እንደሆነም ገልጿል።
- ካናዳ ከትራምፕ ጋር የምትደራደረው “በራሷ ፍላጎቶች መሰረት” እንደሚሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ካርኔይ ለቢቢሲ ተናገሩከ 7 ሰአት በፊት
- በአቶ ጌታቸው የሚመራው ህወሓት ‘ትግራይ ሊብራል ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ’ የሚባል አዲስ ፓርቲ ሊያቋቁም ነው29 ሚያዚያ 2025
- አልኮል መጠጥ በጤናችን እና በዕድሜያችን ላይ የሚያስከትለው ጉድለትከ 8 ሰአት በፊት
ይሁን እንጅ አብዛኞቹ የሪፐብሊካን መራጮች አሁንም ከፕሬዝዳንቱ ጋር ሲሆኑ፤ ዲሞክራቲክ ፓርቲውም ድጋፉ መቀነሱ ታውቋል።
የትራምፕ ተቀናቃኝ ዲሞክራቲክ ፓርቲ የ100 ቀናት አፈፃፀማቸውን “ግዙፍ ውድቀት” በማለት ገልፆታል።
“ትራምፕ ኑሮ የበለጠ እንዲወደድ በማድረግ ተጠያቂ ናቸው። ጡረታ ለመውጣት አሁን ከባድ ነው። የትራምፕ የምጣኔ ሀብት ውድቀት በራችን ላይ ነው” ብሏል።
ዶናልድ ትራምፕ የእንቁላል ዋጋ በ87 በመቶ ቀንሷል በማለት በመንግሥት እየወጡ ያሉ የዋጋ መረጃዎች በመቃረን ተናግረዋል።
ትራምፕ ጆ ባይደን በቅልጥፍናቸውን እና በሰውነት ቅርፃቸው በመወረፍ፤ ባይደን ያሸነፉትን የ2020 ምርጫ እውነተኛው አሸናፊ እኔ ነኝ ሲሉ ተደምጠዋል።
ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው መሀል ስደተኞች ወደ ኤል ሳቫዶር ወይኒ ቤት ሲወሰዱ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል አሳይተዋል።
ትራምፕ ሥልጣን ከያዙ በኋላ የዋጋ ግሽበት፣ የኃይል ዋጋ እና የቤት ባንክ (ሞርጌጅ) ዋጋ መውረዱ ታውቋል።
የሥራ አጥነት ቁጥር በመጠኑ መቀነስ ቢያሳይም፤ የሸማቾች የመግዛት አዝማሚያ ግን ቀንሷል። ለዚህም ትልቁ ማሳያ የአክሲዮን ገበያው ፐሬዝዳንቱ ታሪፍ ከጣሉ ወዲህ በእጅጉ ማሽቆልቆሉ ነው።