የዝክረ ኒቅያ የሊቃውንት ምክክር ጉባኤ ሙሉ የአቋም መግለጫ
እኛ ሊቃውንት እንደምንረዳው ጉባኤ ኒቅያ በምንልበት ጊዜ በቤተ ክርስቲያን አነጋገር ጉባኤ ተደረገ ሲባል ሰዎች ተሰብስበው ይህን ማመን አለብን ያንን መተው አለብን ብለው በድምጽ ብልጫ ተስማምተው የጋራ መግለጫ አወጡ ማለት ሳይሆን ሰፊ እርሻ /ሁዳድ/ ያለው ገበሬ በአዝመራው መሐል እህሉን መስሎ አዝመራውን የሚጎዳ የሚያበላሽ አረም ሲበቅልበት ከእህሉ መካከል አረሙን በጥንቃቄ ነቅሎ እንደሚጥል ሁሉ ቤተ ክርስቲያንም ክርስቶስን በዓይኗ ዓይታ ትምህርቱን በጆሮዋ ሰምታ በአጠቃላይ ቤተ ክርስቲያን በአባቶቻችን በሐዋርያት አማካይነት የቃሉን ትምህርት የእጁን ተአምራት ዓይታ በምታውቀውና በምታምነው እውነተኛ ሃይማኖት መሐል የራሷን እምነት ሳይሆን ተመሳስሎ የሚጎዳትን የመናፍቃን የአስተሳሰብ አረም ነቅላ ለመጣል አረሙን ነቅላ ትምህርት አዝመራዋን ትከላከላለች፡፡በኒቅያ ጉባኤም የተደረገው ይኸው ነው አረም አርዮስ ተነቀሎ የክርስቶስ አምላክነት በምላት በስፋት ተነገረ የሃይማኖት መግለጫ የሆነው ጸሎተ ሃይማኖት ጸደቀ ፡፡ እኛም የሠለስቱ ምዕት የልጅ ልጆች የኢትዮጵያ ሊቃውንት በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የበቀለውንና እየበቀለ ያለውን አረም በትምህርት የአረም ማጥፊያ መድኀኒትነት ለመንቀል ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ለመጠበቅ ምእመናንን ለማጽናት በዚህ በመንበረ ፓትርያርክ ቅጽረ ግቢ ተሰብስበን መክረን ተወያይተን-
1. ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በጉባኤው መክፈቻ የሰጡትን ቃለ ምእዳን አባታዊ መመሪያና ቡራኬን በመቀበል የሰጡትን አባታዊ መመሪያ በየመጣንበት ጉባኤ ቤት ሥራ ላይ ለማዋል ቃል እንገባለን፡፡
2. ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤የባሕር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በጉባኤው መክፈቻና በየመርሐ ግብሩ መካከል ያስተላለፉትን የሥራ መመሪያ ወቅቱ በሚጠይቀው ቤተ ክርስቲያን በምትፈልገው ምእመናን ለሚጠይቁት ጥያቄ ሁሉ ምላሽ ለመስጠት በየጉባኤ ቤታችን ከማስተማር ከማገልገል ባሻገር እንደአባቶቻችን ለሃይማኖታችን አለኝታና ጠበቃ ሆነን ለመሥራት ቃል እንገባለን፡፡
3. ጥንታዊት ሐዋርያዊት የሆነችውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በረጅም ታሪኳ ውስጥ ባሳለፈቻቸው አጋጣሚዎች ሁሉ ያካበተችውን የእቅበተ እምነት (ሃይማኖት) ልምድ ከመጀመሪያው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ያሉትን የዐቃብያነ ሃይማኖት ተጋድሎዎች በመረዳት ቅብብሎሹን ለማስቀጠል ቃል እንገባለን፡፡
4. አሁን ባለንበት ክፍለ ዘመን ከሚከሠቱት አሉታዊ ግድፈቶችና ሥርዋጾች መካከል በቅዱሳት መጻሕፍት፣ በገድላት፣በድርሳናትና በታአምራት የቤተ ክርስቲያን አዋልድ መጻሕፍት በመከለስ በመሸቀጥና በመበረዝ መንፈሳዊነታቸውን ለቀው የተዛባ ሐሳብ እንዲኖራቸው ከእግዚአብሔር ፈቃድና ሐሳብ እንዲወጡ የሚደረገው ሴራ እጅግ አደገኛ ነው፡፡ስለሆነም ጥንታውያን በቀኖና መጻሕፍት የተሠፈሩና የተመዘኑ መጻሕፍቶቻችን ባሉበት ሁኔታ ተጠብቀው ይቀጥሉ ዘንድ እኛ የጉባኤ መምህራን የመጻሕፍቱ ጠበቃ በመሆን በሊቃውንት ጉባኤ በኩል ያላለፉ በትንሣኤ ማሳተሚያ ድርጅት አሳታሚነት ያልታተሙ መጻሕፍት ባለመጠቀም ደቀ መዛሙርትና ምእመናን እንዳይገለገሉባቸው ለማስተማር ቃል እንገባለን፡፡
5. የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሥዕላት፣መስቀል፣ሥነ ሕንፃና ኪነ ጥበብ ይዘትና ቅርጽ በቀኖና ቤተ ክርስቲያን የተለካ ሃይማኖታዊ ምሳሌነታቸው እንደ መጻሕፍት የሚነበብ እንደሰው የሚናገሩ እንደ መምህራን የሚያስተምሩ ንዋያት ናቸው፤ስለሆነም እነዚህን ንዋያተ ቅድሳት በየዘመኑ የሚነሱ የውስጥና የውጭ አጽራረ ቤተ ክርስቲያን የተለያየ ስሜት እንዲፈጥሩ የሚሰጡት ትርጉም እንዲዛባ ለማድረግ የሚያደርጉት ሙከራ እጅግ ብዙ ነው አባቶቻችን በብዙ ውጣ ውረድ ያቆዩልንን የስገኙልንን እነዚህን ንዋያተ ሃይማኖት ጠብቀን በማስጠበቅ ጥቅማቸውን በማስተማር ባሉበት ሁኔታ ለትውልድ ለማስተላለፍ ምትክ የሌለውን ድርሻችንን ለመወጣት ቃል እንገባለን፡፡
6. አጽራረ ቤተ ክርስቲያን የሀገሪቱን የውስጥ ሁኔታ በማጤን ራሳቸው በሚሰጡን አጀንዳ በሚፈጠር የተዛባ የፖለቲካ አመለካከት የመሪዎችን አቋምና ትከሻ በመለካት በሚገኝ አጋጣሚ ሁሉ በመጠቀም ሠርጎ በመግባት ኑፋቄን በመዝራት በቀኖና፣በታሪክና በትውፊት በምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን በዜማ በቅዳሴ በትርጓሜ በበዓላት አከባበር ላይ ሁሉ ኦርቶዶክሳዊ ያልሆኑ እንግዳ ነገሮችን ሊያሸክሙን እንደሞከሩና አንዳንዶቹም አዳዲስ ትርክት እንደጫኑብን ታሪክ እንደቀየሩብን በማኅበረሰቡ ውስጥ ቅራኔ እንደፈጠሩብን ከቀረቡት ጥንታዊ ጽሑፎች ተረድተናል፡፡ስለሆነም የደረሱብን ችግር የቀኖና የትውፊት የታሪክ ተፋልሶ ስህተቶችን በማኅብረሰቡ ውስጥ ሠርጎ የገባ የትርክት አረሙን ከስንዴው በጥንቃቄ በመለየት ወደ ጥንታዊ ማንነታችን ለመመለስ የሚጠበቅብንን ሁሉ ረድኤተ እግዚአብሔርን አጋዥ በማድረግ ለመሥራት ቃል እንገባለን፡፡
7. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከተመሠረተች ጀምሮ መከፋፈል ያልገጠማት የተማከለ የአስተዳደር መርሕ ስለምትከተልና ወጥ በሆነ የአሰራር መዋቅር ስለምትመራ መሆኑ የታወቀ ነው፤ስለሆነም ከቤተ ክርስቲያናችን ኣንጻር የተማከለ ኣሰራር የተሻለ ውጤት እንዳለው ለቤተ ክርስቲያናችን ሃይማኖትና ሥርዐት መጠበቅ ጠቃሚ መሆኑን ስለተገነዘብን ማእከላዊ መዋቅራችንን ለመጠበቅና ለማስጠበቅ የበኩላችንን ድርሻ ለመወጣት ተስማምተናል፡፡
8. በአምስት ሊቃውንት ቅዱሳን ስም በቡድን ተከፋፍሎ በየርእሱ የተደረገው ውይይትና የመፍትሔ ሐሳብ ቀርቧል፡፡ቡድኑ የተወያየበት ሠነድ የዚህ ቃለ ጉባኤ አካል በማድረግ ጥቅል ሠነዱ ለቅዱስ ሲኖዶስ እንዲቀርብ የሚድረግ ሆኖ ለማሳያ ያህል በክብዙ በጥቂቱ በአቋም መግለጫ እንዲወጣበት አድርገናል፡፡በዚህም መሠረት
ሀ. በነገረ ማርያምንና በነገረ ክርስቶስን ዙሪያ በጉባኤው ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን በዚህ ዙሪያ ውይይት ያደረገው ቡድን ለሚነሱ ጥያቄዎች ሰፊ ምላሽ የሚሰጡ ከቅዱሳት ማጻሕፍት በማጣቀስ የውይይቱን ውጤት አቅርቧል በዚህም መሠረት፡- እመቤታችን በተመለከተ ጊዜውን ተደራሽ ያደረጉ ጥያቄዎች ጥንተ አብሶን፣ ቤዛዊተ ዓለም፣ አማላጅነት፣የጌታችን ወንድሞችና የእመቤታችን ትንሣኤና ተያያዝ ጥያቄዎች በቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ መሠረት ሰፊ ውይይትና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል ስለሆነም ቅዱሳት መጻሕፍትን መሠረት በማድረግ አባቶቻችን ነቢያት፣ አባቶቻችን ሐዋርያት ቀደምት ሊቃውንት ያቆዩልንን የነገረ ማርያም ትምህርት ዛይበረዝ ተጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ጠንክረን እናስተምራለን፡፡
ለ. በነገረ ክርስቶስ ዙሪያ በውስጥና በውጭ በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን ከእነዚህ መካከል የክርስቶስ የባህርይ አምላክነት ወልድ ፍጥር በሥጋው ይባላል ወይ? ሊቀ ካህናት ቤዛ አስተራቂነት ነገረ ድኅነት ነገረ ቅብዓት በቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ መሠረት ሰፊ ውይይትና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል ስለሆነም ቅዱሳት መጻሕፍትን መሠረት በማድረግ ቀደምት ሊቃውንት ያቆዩልንን የነገረ ክርስቶስ ትምህርት ዛይበረዝ ተጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ጠንክረን እናስተምራለን፡፡
ሐ. አንድምታ ትርጋሜን በተመለከተ ጉባኤው በስፋትና በምልዓት ውይይት አድርጓል በመሆኑም ትርጋሜው ዘሩን ሳይለቅ መሻሻል እንዳለበት በመጀመሪያ በመምህር ኤስድሮስ ከዚያም በአዓጼ አድያም ሰገድ ኢያሱ ዘመነ መንግሥት ማስፋፍያ እንደተደረገበት ታሪክ ያስረዳል። በሀገሪቱ ያሉ የመጻሕፍት ትርጋሜ ሊቃውንት የሚስተካከሉ አካባቢያዊ ቃላትን ለማስተካከልና ለማዘመን የትርጋሜውን የማሻሻል ሥራ የሚሠሩ ሰዎች በእውቀት ፥ በእምነትና በሥነ ምግባር የጎለበቱ ፥ ከእኔነት ሥሜት ወጥተው የቤተ ክርስቲያን ሐሳብ ብቻ የሚከተሉ ርቱዓን መምህራን መሆን እንዳለባቸው ጉባኤው በአጽንዖት ያሳስባል።
11. በሢመተ ክህነት እና በሥርዐተ ምንኩስና ላይ የሚታዩ ጉልህ ጉድለቶችን በሚመለከት በርካታ ችግር መኖሩ በቡድን ውይይቱ በስፋት ተገልጧል ይህን ችግር ለመቅረፍ ይቻል ዘንድ ለክህነት አገልግሎት የሚያበቃ የትምህረት ዝግጅትና ሥነ ምግባር የእድሜ ወሰን ታይቶ እንደ ቀኖና ቤ/ክ/ መሠረት ከሚኖርበት አጥቢያ ቤ/ክ በቂ ማረጋገጫ ተሰጥቶ በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብቻ እንዲሰጥ እንዲደረግ እንጠይቃለን። በተጨማሪም ሥርአተ ምንኩስና ላይ ያለውን ችግር ለመቅረፍ ሥርዐተ አበውን ጠብቆ መሥፈርቱን አሟልቶ በየቦታው የሚሠጠው ምንኩስና ቀርቶ በታወቁና በጥንታውያን የምንኩስና ገዳማት ብቻ እንዲሆን አበክረን እንጠይቃለን፡፡
በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት የሊቃውንት ጉባኤን በየአህጉረ ስብከቱ ማደራጀት እና በማዕከል ካለው የሊቃውንት ጉባኤ ጋር ተናቦ መሥራት እንዲቻል ምን ቢደረግ ይሻላል? ለሚለው የሊቃውንት ጉባኤው በየ አህጉረ ስብከቱና በየወረዳው ቢደራጅ እጅግ መልካም በመሆኑ በቡድን ውይይቱ በስፋት ስለተገለጠ ሁለገብ ሙያ ባላቸው ሊቃውንት ተደራጅቶ የሚመሰገንበትና የሚወቀስበት የተሰፈረ የተቆጠረ የሥራ መዘርዝር ተዘጋጅቶለት እንዲሠራና በዚህ ዘርፍ የሊቃውንት ጉባኤ ሐላፊነቱን እንዲወጣ አበክረን እንጠይቃለን፡፡
12. ሀ. አዋልድ ቅዱሳት መጻሕፍትን በተመለከተ አንዳንድ ጥያቄዎች ይነሣሉ፡፡ መፍትሔው ምን መሆን አለበት) እንዴት ይታረም) አርትዖትስ እንዴት ይፈጸም) የሚለው የውይይት ሐሳብን በተመለከተ ፡-አዋልድ መጻሕፍት በተለይም ገድላትና ድርሳናት ብዛት ያላቸው የተለያዩ ቅጂዎች ስላሉአቸው ቅጂዎቹ ተሰብስበው በሊቃውት ሊመረመሩና እውነተኛው ሊለይ እንደሚገባ፤በመጻሕፍቱ ውስጥ ከሌሎች ቤተ እምነቶች ጋር ሊያጋጩ የሚችሉ፣ በተለይም ክርስቲያኖች በቁጥር አንሰው በሚታዩባቸው አካባቢዎች አገልጋዮች ካህናትንና ምእመናንን ለጉዳት የሚዳርጉ ሐሳቦችን የያዙ መጻሕፍት መኖራቸው የሚሉ በርካታ ነጥቦችን በማንሳት ቡድኑ በስፋት ተወያይቷል ከዚህ በመነሳት በመፍትሔ ሐሳብ ደረጃ የተቀመጡትንና ጉባኤው የተስማማባቸውን የመፍትሔ ሐሳቦች፣ምእመናን ባለመረዳት እንዳይደነጋገሩ አስፈላጊው ጥናት ተደርጎ ቤተ ክርስቲያን የምትቀበላቸው መጻሕፍትን ለይቶ ለማሳወቅ አስቀድሞ በተጻፉ የብራና ቅጂዎች ውስጥ ሳይኖሩ በኋላ በስርዋጽ የገቡ ጤናማ ያልሆኑ ሐሳቦች ከጥንት ቅጂዎቻቸው ጋር በማመሳከር እና እውነተኛውን በመለየት ለማረም፣ከገድላት ከድርሳናት ከዜማ መጻሕፍትም ሆነ ከሌሎች አዋልድ መጻሕፍት ማብራሪያ የሚያስፈልጋቸውን ለይቶ ማብራራት፣ ማስማማት፣ ማስታረቅ የሚስፈልጋቸውንም ማስታረቅ፣ በስርዋጽ የገባውን በበቂ ጥናት ተለይተው እንዲታረሙ አስፈላጎውን ጥረት እናደርጋለን፣
ለ. የቤተ ክርስቲያን የሆኑ ቅዱሳት መጻሕፍትና ሌላ ማንኛውም ነገር ከቤተ ክርስቲያን ውጪ ያሉ አካላት እንዳያሳትሟቸውና እንዳይጠቀሙባቸው እንዴት እንከላከል) የሚለውን ሐሳብ በተመለከተ የተነሱ ጭብጦች፡-
የቤተ ክርስቲያን ንብረቶች የሆኑት ቅዱሳት መጻሕፍት ግለሰቦች በስማቸው እያሳተሙ ቤተ ክርስቲያን ባለ ቤትነቷን እያሳጧት መሆኑን፣
የትርጓሜና የዜማ መጻሕፍት የየቤታቸው ባህል ስላላቸው ወጥ ለማድረግ አስቸጋሪ መሆኑ ፣
አሳታሚዎችም ያለቤተ ክርስቲያን ፈቃድ የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍትን እያሳተሙ ለግል ጥቅማቸው እያዋሉ መሆኑ፣በትንሣኤ የማተሚያ ድርጅት ብቻ ይታተምልን በማለት ቡድኑ በስፋት ተወያይቷል ።
ከዚህ በመነሳት የቤተ ክርስቲያን ንብረቶች የሆኑት ቅዱሳት መጻሕፍት ግለሰቦች በስማቸው ሊያሳተሙ ስለማይገባ የመጻሕፍቱ ባለቤት ቤተ ክርስቲያን ሆና ለግለሰቦች ሳይሆን ለምስክር ጉባኤ ቤቶቹ፣ ለመንፈሳዊ ኮሌጆቹና ዩንቨርስቲዎች እውቅና እየተሰጠና በሊቃውንት ጉባኤ ሰሰእየታረመ የየቤቱ ባህል ተጠብቆ እንዲታተም የበኩላችንን ጥረት እናደርጋለን፣አሳታሚ ድርጅቶችም የቤተ ክርስቲያን ሀብቶች የሆኑ ቅዱሳት መጻሕፍት ያለቤተ ክርስቲያን ፈቃድ እያሳተሙ ለግል ጥቅማቸው እንዳያውሉ፣ ቢያትሙም ተጠያቂዎች የሚሆኑበትን አሠራር መፍጠር ፣የቤተ ክርስቲያን ሀብቶች የሆኑ ቅዱሳት መጻሕፍትን ያለቤተክርስቲያን ፈቃድ እያሳተሙ ለግል ጥቅማቸው የሚያውሉ ግለሰቦችም እንዲታረሙ ጥብቅ መመሪያ ከማስተላለፍም በተጨማሪ ምእመናን በማዕከል ያልታተሙ መጻሕፍትን እንዳይገዙ መመሪያ ቢተላለፍ፣የበኩላችንን ጥረት እናደርጋለን።
13. ዕቅበተ እምነትን በተመለከተ የሚታዩ ጉድለቶች ምን ምን ናቸው? የመፍትሔ ሐሳቦችስ?ምንም ሳይማሩ ሥልጣነ ክህነት የሚቀበሉና በአስተዳደር ሥልጣን የሚሾሙ አሉ፤ በቂ የቤተ ክርስቲያን ዕውቀት ሳይኖራቸው ክህነት የተቀበሉ በሥልጠና ቢያስታካክሉ፤ ወደፊት የሚቀበሉ ዐውቀው እንዲቀበሉ ቢደረግ የሚሉና ሌሎች በርካታ ጉዳዮች ተነስተው ቡድኑ ተወያይቶባቸዋል። ስለሆነም ይህም ችግር እንዲስተካከል የበኩላችንን ጥረት እናደርጋለን፡፡
14. ሀ. በማኅበራዊ ሚድያ የሚሠራጩ የሃይማኖት ትምህርቶችን እንዴት እንከታተል? የሚፈጠሩ ችግሮችንስ እንዴት እንፍታ? እንዳያሻው የሚስተምርን እንዴት እንከላከል ስለሚለውም የቤተ ክርስቲያኒቱን ሚዲያ በማጠናከር ለሁሉም ተደራሽ መሆን የሚቻልበት አሠራር በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ተጠንቶ ተግባራዊ እንዲሆን እየጠየቅን ምእመናንም ከእውነተኛይቱ ቤተ ክርስቲያን ማኅበራዊ ሚዲያዎች የሚተላለፉ ትምህርቶችን እንዲከታተሉ እናስተምራለን፡፡
ለ. የቤተ ክርስቲያን አንድነትንና የቅዱስ ሲኖዶስን ልዕልና መጠበቅ የሚቻለው በምን ዘዴ ነው? ማእከላዊነት መጠበቅ፣ ጠንካራ የሕግ አስተዳደር እንዲኖረን ማድረግ፣ በሀገር ውስጥም በውጭ ሀገርም ሕግ የሚከበርበትን ሁኔታ ማጠናከር፣ ልጆቻችን በመላው ዓለም ስለሚገኙ ለቤተ ክርስቲያን አንድነት፣ ሕልውና፣ ልዕልና እንደ ሌሎች አብያት ክርስቲያናት ዓለም አቀፍ ሥራ መሥራት፡ ቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ እንዲሰጥበት እንጠይቃለን፡፡
ሐ. በአብነት ት/ቤቶች፣ መምህራን፣ እና ተማሪዎችን እንዴት እንከባከብ? ተጨማሪ መንፈሳዊና ማኅበራዊ ሥልጠናዎች እንዴት ይካተቱ? የአብነት ትምህርትን ቤቶች የሊቃውንት መገኛ፣ የቤተ ክርስቲያን የጀርባ አጥንት የአገልጋዮቿ ሁሉ ምንጭ በመሆናቸው ለአብነት ትምህርት ቤት ልዩ የሆነ ትኩረት መስጠት ስለሚያስፈልግ፤ በየአጥቢያው የሚደራጁበት ሁኔታ እንዲመቻች፣ ለአብያተ ጉባኤ በየደረጃው ልዩ መተዳደሪያ/ሥርዐት እንዲዘጋጅ፣ እንደሚገኙበት ቦታ በገጠር፣ በከተማ፣ በገዳምና በአድባራት ተሳቢ ያደረገ ድጋፍ፣ ክትትል፣ እንክብካቤ፣ ዋስትና፣ ዘላቂ የሕልውና ድጋፍ እንዲደረግ ጠንካራ መመሪያ እንዲወርድ እየጠየቅን እኛም የበኩላችንን ድርሻ ለመወጣት ቃል እንገባለን፡፡
በመጨረሻም፡-
ይህ በሀገር ደረጃ እንዲህ ባማረ ሁኔታ ሊቃውንት ተሰባስበን እንድንመካከር እንድንወያይ በታሪካችን የዚህ እድል ተቋዳሽ እንሆን ዘንድ ለፈቀዱልን ጉባኤያችንን ተገኝተው የባረኩልልን የተቀደሰ ቡራኬያቸውን ለሰጡን ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ከፍ ያለ ምስጋናችንን ከአክብሮት ጋር እናቀርባለን።
በጉባኤው ሙሉ ጊዜያቸውን ሰጥተው ለተከታተሉን ጉባኤያችንን ለመሩልን መመሪያና ትምህርት ለሰጡን ለብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤የባሕርዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከፍ ያለ ምስጋና ከአክብሮት ጋር ስናቀርብልዎ በታላቅ አክብሮት ነው፡፡
የጠቅላይ ቤተ ክህነት አስተዳደር ጉባኤ ይህ ዝክረ ኒቅያ የተሰኘው ሀገር አቀፍ ጉባኤ እንዲካሔድ ከመጀሪያው ጀምሮ ሐሳብ በመስጠት ጉባኤው የተሳካ እንዲሆን በቅርበት ላደረገው አስተዋጽኦና ሁለንተናዊ ድጋፍ ከፍተኛ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡
ሃይማኖት የጸናበትን ርእሰ መናፍቅ የተባለ አርዮስ የተወገዘበትን በኒቅያ ጉባኤ ስያሜ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲህ ዓይነት ድንቅ ጉባኤ እንዲዘጋጅ እኛ የጉባኤ ቤት መምህራን በማዕከል እንድነገናኝ እንድንመካከር እርስ በእርሳችን እንድንተዋወቅ እድሉን ያመቻቸልንን የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሊቃውንት ጉባኤ መምሪያ ዋና ኃላፊ ክቡር መጋቤ ብሉይ ዕዝራ ለገሠ እና የሥራ አጋሮቻቸው ከልብ በመነጨ ምስጋናና አድናቆታችንን ስንገልጽ በታላቅ አክብሮትና በፍጹም ትህትና ነው፡፡ ለወደፊቱም እንደ አመቺነቱ ዛሬ በዚህ ዐቢይ ጉባኤ የተረከብነውን የቤት ሥራ ለመገምገም ለተጨማሪ ሥራና ኃላፊነት ለመዘጋጀት ይህ ጉባኤ በየዓመቱ ከግንቦት የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በፊት እንዲዘጋጅ በአክብሮት እንጠይቃለን ።
ዝክረ ኒቅያ በሚል የተዘጋጀው ይህ ጉባኤ ሊቃውንት የተሳካ ይሆን ዘንድ በገንዘብ በሐሳብ ለተባበሩን ሁሉ በቤተ ክርስቲያን ስም ምስጋናችንን እያቀርብን ይህ ባለ 14 ነጥብ የጋራ የአቋም መግለጫ ከዝርዝር የውይይት ሰነዱ ጋር ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ቀርቦ ውሳኔ እንዲሰጥበት በአክብሮት እንጠይቃለን ፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ የቅዱስነትዎ ቡራኬ ይድረሰን!!!
ሚያዚያ 22 ቀን 2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ
ምንጭ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

All reactions:
108108
ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል – Tewahedo Media Center – TMC · Follow

pnrodeoSstcc5f327152ia6gmt6925fttmt8g4143aah68u9hmc3ft0m0fc4 ·