የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ,

ከ 1 ሰአት በፊት

ትራምፕ ወደ ፕሬዝዳንትነት ከተመለሱ በኋላ የተበላሸውን የሁለቱን አገራት ግንኙነት በተመለከተ ለመነጋገር ወደ አሜሪካ ያመሩት የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ዋይት ሐውስ ውስጥ በተሰበሰቡ ጋዜጠኞች ፊት ከዶናልድ ትራምፕ ወቀሳ ቀርቦባቸዋል።

ከዚህ ቀደም ከዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ጋር ዶናልድ ትራምፕ የገቡት እሰጣ አገባ የዓለም መነጋገሪያ ሆኖ እንደነበር ይታወሳል። ትራምፕ ፕሬዝዳንት ዜሌንስኪ ምላሽ እንዲሰጡ ዕድል ሳይሰጡ በቁጣ የወቀሱበት መንገድ ትችትን አስከትሎባቸው ነበር።

አሁን ከፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ጋር በነበራቸው ንግግር ትራምፕ በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ነጮች የዘር ማጥፋት አደጋ ተጋርጦባቸዋል በሚል ምሥሎች እና ቪዲዮ በማሳየ ቢከሱም፤ ራማፎሳ በተረጋጋ ሁኔታ ምላሽ ሲሰጡ ታይተዋል።

ይህ የሁለቱ ፐሬዝዳንቶች ምልልስ በዓለም ዙሪያ በተለይም በደቡብ አፍሪካ ውስጥ መነጋገሪያ ሆኗል።