የቱርክ መንገድ አውሮፕላነ

ከ 4 ሰአት በፊት

ወደ ቱርክ የሚጓዙ መንገደኞች የአውሮፕላኑ የመቀመጫ ቀበቶ ምልክት ከመጥፋቱ በፊት ከተነሱ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው ተቆጣጣሪዎች ገለጹ።

የቱርክ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ትዕዛዙን ያስተላለፈው ከተሳፋሪዎች ቅሬታ ከደረሰው በኋላ መሆኑን አስታውቋል።

ህጎቹ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ተግባራዊ ሆነዋል።

ባለስልጣኑ ህጎቹን የተላለፉ ቅጣቱ ምን እንደሆነ በመመሪያው ውስጥ ባይጠቅስም፣ 70 ዶላር ገደማ እንደሆነ የቱርክ ሚዲያዎች ዘግበዋል።

እንዲህ አይነት ክስተቶች “በከፍተኛ ሁኔታ” መጨመራቸውን ያስጠነቀቀው ባለስልጣኑ አውሮፕላኑ ከማረፉ በፊት ከመቀመጫዎች በላይ ያለውን የሻንጣ ማስቀመጫ በርካታ መንገደኞች እየከፈቱ ነው የሚል በርካታ ቅሬታዎች ደርሶኛል ብሏል።

ቱርክ በአመት በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ቱሪስቶችን ታስተናግዳለች።

አየር መንገዶች በበራዎች የውስጥ ማስታወቂያዎች ትዕዛዙን ማስተላለፍ እንደሚገባቸውና ይህንን ተላልፈው የሚገኙትን ማሳወቅ እንደሚገባቸው የአቪዬሸን ባለስልጣኑ ተናግሯል።

ተሳፋሪዎች የመቀመጫ ቀበቷቸውን ምልክቱ እስኪጠፋ ድረስ እንዳይፈቱ እንዲነገራቸው እና በመቀመጫቸው በላይ ያለውን የሻንጣዎች ማስቀመጫ ከመክፈት ይታቀቡ ተብለዋል።

እነዚህን ህጎች የማይከተሉ መንገደኞች ለባለስልጣኑ ሪፖርት ሊደረጉ ይገባል ብሏል።

ብሔራዊው የቱርክ አየር መንገድ የበረራዎች ማስታወቂያውን እንዳሻሻለ ዩሮ ኒውስ ዘግቧል።

“በህጎቹ የማይመሩ መንገደኞች ረብሻ በመፍጠር ለሲቪል አቪዬሽን ዳይሬክቶሬት ሪፖርት ይደረጋሉ በህጉ መሰረትም አስተዳደራዊ ቅጣት ይጠብቃቸዋል” የሚል ማስጠንቀቂያ በበራራ አስተናጋጆች መነገሩን ሚዲያው ዘግቧል።

ቢቢሲ አየር መንገዱን አስተያየት ቢጠይቅም እስካሁን ምላሽ አላገኘም።