Batero Belete

ብልጽግ ና የህክምና ባለሙያዎችን ጥያቄ ለመመለስ ገ ንዘብ የለኝም ታገሱ ካለ 6 አመት ሆነው፡፡ የሚገርመው ደግሞ ከዛ ወዲህ የህዝብን ገቢ ማሻሻል ሳይሆን

ትኩረቱ የቅንጦት ቤተመንግስት ቢሊዮኖችን በማውጣት ማሰራት ጀምሯል

ቢሊዮኖች በማውጣት አብለጭላጭ የመንገድ ላይ መብራት በየቦታው ይተክላል

ቢሊዮኖ ዶላር ባማጥፋት የኮሪዶር ልማት በሚል ሰፈር ሲቆፍር ይውላል

ቢሊዮኖችን አውጥቶ በየመንገዱ የቅንጦት ፏፏቴ ውሀ ቀኑን ሁሉ እንዲፈስ ያደርጋል

ይህ ሁሉ ሲሆን የህክምናውን ባለሙያ ይህ ነው በሚባል ደረጃ ማሻሻል አልቻለም እንዳውም ወደ ርሀብ እንዲገቡ አድርጓል፡፡

ጥያቄው ይህ መንግስት ቅድሚያ የሚሰጠው ምን እንደሆነ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡ የብልጥኛ ቅድሚያው የገዝዎቹ የቅንጦት ፐሮጀክቶች ፣ ራሱን ማዝናናት ሊጠቅማቸው የሚፈልገውን ያርሱን ቱጃሮች መፍጠርና ወዳጆቹ የሆኑትን የኤምሬጽ ቱጃሮች ማስደሰት ነው፡፡

ይህ የብልጽግኛ ፍላጎት ነው፣ ሀኪሞችም ይሁኑ ተራው ህዝብ የሚለው ደግሞ ተራብን፣ መኖሪያ ቤት አጣን፣ ቤታችን በመብራት እጦት ጭለማ ውጦታል ነው፡፡

ብልጽግኛ የሚገዛውን ህዝብ ፍላጎት አያውቅም፣ ረስቶታል ብቻ ሳይሆን ለህዝብ ግድ የለውም፡፡

የሚያደርገው ተርበናል የሚሉትን በስድብ ማንጠልጠል፣ ማዋረድ ማሰር ማስፈራራት ሆኗል፡፡

የብልጽግኛ መንግስት በርግጥም ህዝቡን የረሳ ብቻ ሳይሆን የናቀም ሰለራሱና ራሱ እንዲሁም የኤምሬጽ ወዳጆቹ ብቻ የሚያስብ ነው፡፡ ይህን ራስ ወደድ አገዛዝ ተው ማለት እምቢ ማለት ግድ ነው፡፡ 7 አመት ሙሉ እድል ተስጥቶት ሊታረም እንዳልቻለ ግልጥ ነው፡፡

ይህን ሁሉ በማየት ነው የህክምና ባለሙያዎችን ስራ ማቆም የምደግፈው

ሀኪም ማስረብ ይብቃ፡፡