June 5, 2025

በቤርሳቤህ ገብረ

በኤርትራ በኩል “ትንኮሳ” ቢኖርም፤ የኢትዮጵያ መንግስት ከሀገሪቱ ጋር “የቃላት ጦርነት ውስጥ አልገባም” ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ተናገሩ። ኢትዮጵያ ስትራቴጂክ የሆኑ የሀገራዊ ጥቅም ጉዳዮች ስታነሳ “ትኩሳታቸው የሚጨምሩ ሀገራት አሉ” ያሉት ሚኒስትሩ፤ መንግስት በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ያለው አቋም “አይዛነፍም” ሲሉ ለፓርላማ አባላት ገልጸዋል።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት፤ ከፓርላማ አባላት በቃል ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ዛሬ ሐሙስ ግንቦት 28፤ 2017 በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ምላሽ በሰጡበት ወቅት ነው። በዛሬው መደበኛ ስብሰባ ጥያቄ ካቀረቡት አንዱ የሆኑት የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የፓርላማ ተወካይ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ፤ የኢትዮጵያ እና ኤርትራን ወቅታዊ ሁኔታ አንስተዋል።

ኤርትራ እና ኢትዮጵያን “ወደ ጦርነት ጅማሮ” እየወሰዳቸው ያለ “የቃል ጦርነቱ የተጀመረ ይመስለኛል” ያሉት የፓርላማ አባሉ፤ ሁለቱ ሀገራት በአሁኑ ወቅት ያላቸው “ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት” በምን መልኩ እንደሚገልጽ ጠይቀዋል። ዶ/ር ደሳለኝ ከኤርትራ ጋር “ወደ ጦርነት መግባት እድል አለ ወይ?” ሲሉም ተጨማሪ ጥያቄ አክለዋል።   

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ለዚህ ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፤ “ ከኤርትራ መንግስት ጋር የኢትዮጵያ መንግስት የቃላት ጦርነት ውስጥ አልገባም” ሲሉ አስተባብለዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን በመወከል “ንግግር” የሚያድርጉ ተቋማት እንዳሉ ያመለከቱት ዶ/ር ጌዲዮን፤ “እስከማውቀው ድረስ የቃላት ጦርነት ውስጥ፤ እንዲህ እና እንዲያ ወደማለት አልገባንም” ሲሉ ለጥያቄው ምላሽ ሰጥተዋል።

ጉዳዩ የሚያሳስባቸው፣ የሚመለከታቸው ዜጎች፣ የህዝብ ተወካዮች እና የቀድሞ የመንግስት ኃላፊዎች “የራሳቸውን ምልከታ” እንደሚያጋሩ ግን ሚኒስትሩ አልሸሸጉም። እነዚህ አካላት “ጆሮ ሊሰጣቸው ይገባል” ሲሉም አሳስበዋል። “በቅርቡ የእነርሱ ንግግሮችን በተመለከተ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአሁኑ ቃል አቀባይ በተቋሙ መድረክ ላይ የተናገሩት ንግግር አለ። ያ የቃላት ጦርነት የሚባል አይደለም” ሲሉም ሚኒስትሩ ገልጸዋል። 

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቃባይ አቶ ነብያት ጌታቸው ባለፈው ሳምንት በነበራቸው ሳምንታዊ መግለጫ ላይ፤ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በቅርቡ ኢትዮጵያ በተመለከተ ስላቀረቧቸው ውንጀላዎች ተጠይቀው ነበር። “ከዚህ ቀደምም ከተወሰኑ ጎረቤት ሀገራት፣ በመሪዎች ደረጃ የተለያዩ inflammatory የሆኑ ንግግሮች፣ ውንጀላዎች፣ ክሶች፣ ዘለፋዎች የመጡበት አጋጣሚዎች ነበሩ” ሲሉ ቃል አቃባዩ በዚሁ መግለጫዎች ላይ አስታውሰዋል። 

ፎቶ፦ የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር

ሆኖም ኢትዮጵያ እነዚህ በመሰሉ “እንካ ሰላንታ ሳትጠመድ”፤ “የሰከነ ዲፕሎማሲ” አካሄድን ስትከተል መቆየቷን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ “ረጅሙን ርቀት የሚያስኬደውን አማራጭ በማየት፤ አሁንም ቢሆንም ከጎረቤቶቿ ጋር ተባብሮ መስራት ላይ ያተኮረ የውጭ ግንኙነት መርህ ነው የምትከተለው። ስለዚህ በየጊዜው የሚነሱ ጉዳዮች በዚያ አግባብ ነው የሚስተናገዱት” ሲሉ አቶ ነብያት በባለፈው ሳምንት መግለጫቸው አብራርተው ነበር። 

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በዛሬው የፓርላማ ጥያቄ እና መልስ ቆይታቸው የቃል አቃባዩን ምላሽ አስተጋብተዋል። “መንግስት ፎርማሊ የሚላቸውን ነገሮች ብሏል። በፍጹም የቃላት ጦርነት የሚባል ነገር ውስጥ አልገባንም። እዚያ ውስጥ የማንገባው፤ እኛ ቀጠናዊ መረጋጋት እና ቀጠናዊ ሰላም እንዲኖር በኃላፊነት ስሜት የምንቀሳቀስ ሀገር ስለሆንን ነው። ዓለም አቀፍ መርሆዎችን፣ ህጎችን እና አሰራሮችን አክብረን የምንቀሳቀስ ሀገር ስለሆንን ነው” ብለዋል ሚኒስትሩ። 

ከኢትዮጵያ አመራሮች የሚወጣ ቃል “ትልቅ ትርጉም” እና “ክብደት” እንዳለው የጠቆሙት ዶ/ር ጌዲዮን፤ በእንደዚህ አይነት ጉዳዮች ላይ በመንግስት በኩል “በዘፈቀደ” እና “በመሰለኝ” ንግግሮች እንደማይደረጉ አመልክተዋል። “እንነጋገር ብንል ብዙ የሚያነጋግር ነገር አለ” ሲሉ የተደመጡት ሚኒስትሩ፤ ጉዳዩ መመራት ያለበት “በሚዛኑ”፣ “በጊዜው” እና “በጥንቃቄ” እንደሆነም አስረድተዋል። 

በኤርትራ በኩል “ትንኮሳ ቢኖርም፤ አንዳንዴ በሆደሰፊነት፣ አንዳንዴ ሰምቶ አንዳልሰማ፣ አንዳንዱን ደግሞ በራሱ በዲፕሎማቲክ ቻናል የሚመለሰውን ለመመለስ ጥረት እናደርጋለን” ሲሉ ዶ/ር ጌዲዮን ጉዳዩ አጽንኦት ሰጥተዋል። በኢትዮጵያ በኩል ወደፊትም ወደ ቃላት ጦርነት “የምንገባ አይመስለኝም” ሲሉ በድጋሚ ማረጋገጫ የሰጡት ሚኒስትሩ፤ “ነገር ግን ብሔራዊ ጥቅማችን፣ ሀገራዊ ጥቅማችንን አስመልክቶ ያለን አቋም አይዛነፍም” ሲሉ የኢትዮጵያ መንግስት በዚህ ረገድ ያለው አመለካከት ያልተለወጠ መሆኑን አስረድተዋል።  

“የጋራ ተጠቃሚነት እንዳለው ባለመረዳት ወይ በተለያየ ምክንያት፤ ኢትዮጵያ ስትራቴጂክ የሆኑ ሀገራዊ ጥቅም ጉዳዮች [ስታነሳ] ትኩሳታቸው የሚጨምሩ ሀገራት አሉ” ሲሉ የተደመጡት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፤ ሆኖም ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሞቿን በተመለከተ ያላትን አቋም “አጠናክራ” እንደምትቀጥል ገልጸዋል። 

“ግድብ ስንገነባ ‘እንዴት ይገነባል’ ብለው፤ ‘እንዴት ሲደረግ፣ እኛ ሳንፈቅድ፣ እኛ እሺ ሳንል ወይም ያለ እኛ ቡራኬ’ የሚሉ ነበሩ። ያ ሳያስቆመን ግድቡን እንዳጠናቀቅነው ሁሉ፤ ሌሎች መሰል ስትራቴጂ ፋይዳ ያላቸው የሀገራዊ ጥቅም ፕሮጀክቶቻችንም፤ ቅር ቢላቸውም፣ ደስ ባይላቸውም እውን ማድረጋችን አይቀርም” ሲሉ ዶ/ር ጌዲዮን ለፓርላማ አባላቱ ተናግረዋል። 

“የጋራ ተጠቃሚነት እንዳለው ባለመረዳት ወይ በተለያየ ምክንያት፤ ኢትዮጵያ ስትራቴጂክ የሆኑ ሀገራዊ ጥቅም ጉዳዮች [ስታነሳ] ትኩሳታቸው የሚጨምሩ ሀገራት አሉ”– ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

ኢትዮጵያ ጥቅሟን የምታስከብረው “የጋራ ተጠቃሚነት መርህን ታሳቢ ባደረገ መልኩ” እና “የዓለም አቀፍ ህግ አሰራር መርሆዎችን ከግንዛቤ ባስገባ መንገድ” እንደሆነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል። የኢትዮጵያ መንግስት “ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤት መሆን አለባት” የሚል አቋም በጽኑ እያራመደ ይገኛል። (

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከኤርትራ ጋር “የቃላት ጦርነት ውስጥ አልገባንም” አሉ 

ኢትዮጵያ ጥቅሟን የምታስከብረው “የጋራ ተጠቃሚነት መርህን ታሳቢ ባደረገ መልኩ” እና “የዓለም አቀፍ ህግ አሰራር መርሆዎችን ከግንዛቤ ባስገባ መንገድ” እንደሆነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል። የኢትዮጵያ መንግስት “ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤት መሆን አለባት” የሚል አቋም በጽኑ እያራመደ ይገኛል። 

(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)