
ከ 2 ሰአት በፊት
ዩክሬን እና ሩስያ ባደረጉት የወታደሮች አስከሬንን የመለዋወጥ ስምምነት ኪየቭ 1 ሺህ 212፣ ሞስኮ ደግሞ 27 አስከሬኖችን ተቀያየሩ።
አስከሬኖቹ ከሩስያ ወደ ዩክሬን መድረሳቸውን የኪየቭ ባለስልጣናት ተናግረዋል።
ሩስያም 27 አስከሬኖችን መቀበሏን የሞስኮ ዋነኛ ተደራዳሪ ቭላድሚር ሜደኒስክ አረጋግጠዋል።
የእስረኞች እና የአስከሬን ልውውጥ ዩክሬን እና ሩስያ ባለፈው ሳምንት በቱርክ ባደረጉት የሰላም ንግግር የተሳካ ብቸኛው ተጨባጭ ውጤት ነው።
በዚህ ንግግር ሁለቱ አገራት እስከ 6 ሺህ የሚደረሱ አስከሬኖችን እና ከፍተኛ የአካል ጉዳት የደረሰባቸውና ከ25 ዓመት በታች ያሉ ወታደሮችን ለመቀያየር ተስማምተዋል።
ሜንዲንስኪ ከፍተኛ የአካል ጉዳት የደረሰባቸውን ወታደሮች የመቀያየሩ ተግባር ሩስያ ከዛሬ ጀምሮ ልትጀምር እንደምትችል ጠቁመዋል።
የዩክሬን ወታደሮች አስከሬን ከተለያዩ አውደ ውጊያዎች የተሰበሰቡ ሲሆን ይህም ዶኔስቴክ፣ ካርኪቭ፣ ኬርሶን እና ዛፓሪዚያን ይጨራምል ሲል የዩክሬን የጦር እስረኞች እንክብካቤ ማዕከል በቴሌግራም ገጹ አሳውቋል።
ማዕከሉ ጨምሮም ከሩስያ የተረከባቸውን አስከሬኖች ማንነት በተቻለው ፍጥነት ለመለየት እንደሚሞከር አስውቋል።
ሩስያ እና ዩክሬን አስከሬኖችን ሲቀያየሩ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ አይደለም። ከዚህ ቀደም በሺዎች የሚቆጠሩ አስከሬኖችን በ70 የተለያዩ ቦታዎች ተለዋውጠዋል።
አገራቱ ይህንን ልውውጥ ያደረጉት ሩስያ ዩክሬን አስከሬኖችን መቀበል አልቻለችም የሚል ወቀሳ ካቀረበች በኋላ ነው።
ሜዴኒስኪ አሁን ዩክሬን የተረከበቻቸው አስከሬኖችን የያዘ ማቀዝቀዣ ያለው ተሽከርካሪ የመቀበያ ቦታው ላይ የደረሰው ባለፈው ቅዳሜ እንደነበር ተናግረዋል።
ሜድንስኪ ባለፈው ቅዳሜ በሰጡት አስተያየት “ባልተጠበቀ ሁኔታ ዩክሬን አስከሬን የመረከቢያ ጊዜውን አራዝማዋለች” ብለዋል።
ዩክሬን በበኩሏ ሩስያ እውነታዎችን በማዛባት “የቆሸሸ ፖለቲካን” እያራመደች ነው ስትል ምላሽ ሰጥታለች።
የአስከሬን ልውውጡ የመጀመሪያ ዙር ባለፈው ሰኞ ነበር የተጀመረው።
በሩስያ እና ቤላሩስ ድንበር የቤተሰብ አባላቶቻቸው የጠፉባቸው ቤተሰቦች ተሰባስበው የነበሩ ሲሆን በስሜት ተሞልተው ታይተዋል።
በዚያ ዕለት ሁለቱም ሀገራት አስከሬኖችን የተለዋወጡ ቢሆንም ሁለቱም አገራት ትክክለኛውን ቁጥር ከማናገር ተቆጥበዋል።