እስራኤል የኢራን የኒውክሌር ፕሮግራም ማዕከል ላይ ያነጣጠረ ነው ያለችውን ከፍተኛ ጥቃት ሐሙስ ለአርብ አጥቢያ በመላው ኢራን ፈጽማለች።በዚህ ጥቃት የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ዋና አዛዥ፣ የአገሪቱ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም እንዲሁም ስድስት የኒውክሌር ሳይንቲስቶች መገደላቸውን የኢራን መንግሥታዊ ሚዲያ ዘግቧል። አጸፋዊ ምላሽ እንደምትሰጥ ያስጠነቀቀችው ኢራን በበኩሏ ወደ ቴልአቪቭ ሚሳኤሎችን አስወንጭፋለች።

ጭምቅ ሃሳብ

የቀጥታ ሽፋን

  1. ከ 3 ደቂቃዎች በፊትበኢራን እና በእስራኤል ግጭቱ ቢገፋ ምን ሊከሰት ይችላል?እስራኤል በኢራን ላይ የፈጸመችው ጥቃትየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesበእስራኤል እና በኢራን መካከል ያለው ግጭት አሁን ላይ በሁለቱ አገራት መካከል የተገደበ ይመስላል፤ ነገር ግን ሁለቱ አገራት ግጭት እንዲያቆሙ የሚቀርበውን ጥሪ አንሰማም ቢሉስ? ግጭቱ ቢባባስ እና ቢስፋፋስ ምን አስከፊ ሁኔታ ሊከሰት ይችላል?የሚከተሉት ግፋ ቢል ሊፈጠሩ የሚችሉ አስከፊ ሁኔታዎች ናቸው።አሜሪካ በግጭቱ ውስጥ ትገባለችምንምእንኳን አሜሪካ ብታስተባብልም ኢራን የአሜሪካ ኃይሎች ግጭቱን መደገፋቸውንና ቢያንስ ለእስራኤል ጥቃት ስልታዊ ድጋፍ እንደሚያደርጉ በግልጽ ታምናለች።በመሆኑምኢራን በመካከለኛው ምሥራቅ ባሉ የአሜሪካ ኢላማዎች ላይ ጥቃት ልትሰነዝር ትችላለች። አሜሪካ ኢራቅ ውስጥ የልዩ ኃይል ካምፖች፣ በባህረ ሰላጤው አገራት ደግሞ ወታደራዊ ሰፈሮች እና በቀጠናው የዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮዎች አሏት።በኢራን የሚደገፉት ሐማስ እና ሄዝቦላህ ብዙ የተዳከሙ ቢሆንም በኢራቅ የሚገኙት ደጋፊ ሚሊሻዎቻቸው ግን አሁንም ታጥቀውና አቅማቸውን አጠናክረው ቆይተዋል።የባህረ ሰላጤው አገራት ወደ ግጭቱ ሊሳቡ ይችላሉኢራን አስተማማኝ መከላከያ ባለው የእስራኤል ጦር እና ሌሎች ኢላማዎች ላይ ጉዳት ማድረስ ካልቻለች፣በተለይ ጠላቶቿን ለዓመታት ይደግፋሉ በምትላቸው የባህረ ሰላጤው አገራት ላይ የሚሳኤል ጥቃት ልትሰነዝር ትችላለች።እነዚህ አገራት የአሜሪካ አየር ኃይል ሰፈር የሚገኝባቸው ናቸው።በመሆኑም የባህረ ሰላጤው አገራት ጥቃት ከደረሰባቸው ራሳቸውን ለመከላከል የአሜሪካ እና የእስራኤል የጦር አውሮፕላኖችን ድጋፍ ሊጠይቁ ይችላሉ።የኢራን አገዛዝ ሊወድቅ ይችላል፤ ይህም ክፍተት ይፈጥራልእስራኤልየኢራንን እስላማዊ አብዮት ጥበቃ አገዛዝ የማፍረስ የረዥም ጊዜ ህልሟን ብታሳካስ ?ትናንት የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ በሰጡት መግለጫ ዋና አላማቸው አገዛዙን ማፍረስ እንደሆነ በግልጽ ተናግረዋል። የኢራንን መንግሥት መፍረስ በተለይ በአንዳንድ የእስራኤል ወዳጆች ሊደገፍ ይችላል። ግን ይህ ምን ክፍተት ሊፈጥር ይችላል?ያጋሩ, በኢራን እና በእስራኤል ግጭቱ ቢገፋ ምን ሊከሰት ይችላል?
  2. ከ 1 ሰአት በፊትኢራን የእስራኤል ጥቃቶች ‘አረመኔያዊ’ ናቸው ስትል ለተመድ ገለጸችየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢራን ተወካይ ሰኢድ ራቫኒየፎቶው ባለመብት,Reutersእስራኤል በፈጸመችው ጥቃት 78 ሰዎች መገደላቸውን እንዲሁም 320 ኢራናውያን መቁሰላቸውን ያስታወቀችው ኢራን አብዛኞቹ ሰላማውያን ዜጎች ናቸው ብላለች።እስራኤል የፈጸመችውን ጥቃቶች “አረመኔያዊ” እንዲሁም “ወንጀል” ነው ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢራን ተወካይ ሰኢድ ራቫኒ ተናግረዋል።የእስራኤል ጥቃትን ተከትሎ ኢራን ባቀረበችው ጥያቄ በኒውዮርክ ለተሰበሰበው የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ድርጅት ነው ተወካዩ ይህንን የተናገሩት።ሰኢድ ራቫኒ የእስራኤል ጥቃት በኒውክሌር ተቋማት፣ በሲቪል መሰረተ ልማቶች እና የመኖሪያ አካባቢዎች ያነጣጠሩ ናቸው ብለዋል።ተወካዪ አክለውም “ሆን ተብሎ የተፈጸመ ስልታዊ” ግድያ ሲሉ ጥቃቱን ጠርተው “አስደንጋጭ የተሰላ የጠብ አጫሪነት ማሳያ” ነው ብለውታል።”አሜሪካ ለነዚህ ወንጀሎች እርዳታ እና እገዛ በማድረጓ ተባባሪ ናት” ሲሉ ወቅሰዋል።“እስራኤል የአሜሪካን መሳሪያ በመጠቀም በፈጸመችው ጥቃት ህዝባችን ህይወታቸውን ማጣታቸውን አንዘነጋም” ብለዋል።የጸጥታው ምክር ቤት የእስራኤል ን ድርጊት እንዲያወግዝ እና ተጠያቂ እንዲያደረጋትም ጠይቀዋል።ያጋሩ, ኢራን የእስራኤል ጥቃቶች ‘አረመኔያዊ’ ናቸው ስትል ለተመድ ገለጸች
  3. ከ 1 ሰአት በፊትእስራኤል የአየር ክልሏን እና ዋነኛ አየር ማረፊያዋን ዘጋችየአገሪቱ ዋነኛ አየር ማረፊያ ቤን ጉሪዮንየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየእስራኤል የትራንስፖርት ሚኒስቴር የአገሪቱ የአየር ክልል መዘጋቱን አስታወቀ።በተጨማሪም የአገሪቱ ዋነኛ አየር ማረፊያ ቤን ጉሪዮን ለየትኛውም በረራ ዝግ መሆኑን አክሏል።የአየር ክልሉም ሆነ የአየር ማረፊያው ከሚኒስቴሩ ትዕዛዝ እስካልመጣ ድረስ ዝግ ሆነው ይቆያሉ ተብሏል።የቤን ጉሪዮን የአየር ማረፊያ ድረ-ገጽ ዛሬ ጥዋት እየሰራ አልነበረም።ሚኒስቴሩ አርብ፣ ሰኔ 6/ 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ለመጓዝ ያቀዱ መንገደኞች “የአገሪቱ አየር ክልል እንደገና ከመከፈቱ ቢያንስ ከስድስት ሰዓታት በፊት” መረጃው በመገናኛ ብዙኃን ይደርሳቸዋል ብሏል።እስራኤል በኢራን እየፈጸመችው ያለውን ጥቃት ተከትሎ የአየር ክልሏን ዘግታ የነበረችው ዮርዳኖስ ከአንድ ቀን በኋላ መክፈቷን አስታውቃለች።በአገሪቱ በረራዎች ተቋርጠው የነበረ ሲሆን ዛሬ በአገሬው ሰዓት አቆጣጠር 1፡30 የአየር ክልሏን መክፈቷን የዮርዳኖስ ሲቪል አቪዬሽን ኮሚሽን አስታውቋል።ያጋሩ, እስራኤል የአየር ክልሏን እና ዋነኛ አየር ማረፊያዋን ዘጋች
  4. ከ 2 ሰአት በፊትኢራን በቴልአቪቭ አቅራቢያ ያስወነጨፈቻቸው ሚሳኤሎች ያደረሱት ጉዳት በምስልየእስራኤልን ጥቃት ተከትሎ ኢራን አጸፋዊ ነው ባለችው ምላሽ ሚሳኤሎችን ወደ እስራኤል አስወንጭፋለች።ኢራን ባስወነጨፈቻቸው ሚሳኤሎች ቢያንስ ሁለት ሰዎች መገደላቸው ተዘግቧል።የእስራኤል የአደጋ ጊዜ አገልግሎት እንዳስታወቀው 21 ሰዎች ቆስለዋል ብሏል።ከቴልቪቭ በስተደቡብ በምትገኘው ሪሾን ለዛየን በተሰኘችው ከተማ ከኢራን የተወነጨፉ ሚሳኤሎች ያደረሱት ጉዳት ምስሎች ቀጣዮቹ ናቸው።በቴልአቪቭ የደረሰው ጥቃትየፎቶው ባለመብት,ABIR SULTAN/EPA-EFE/Shutterstockበቴልአቪቭ የደረሰው ጥቃትየፎቶው ባለመብት,REUTERS/Ronen Zvulunበቴልአቪቭ የደረሰው ጥቃትየፎቶው ባለመብት,Reutersበቴልአቪቭ የደረሰው ጥቃትየፎቶው ባለመብት,ABIR SULTAN/EPA-EFE/Shutterstockያጋሩ, ኢራን በቴልአቪቭ አቅራቢያ ያስወነጨፈቻቸው ሚሳኤሎች ያደረሱት ጉዳት በምስል
  5. ከ 2 ሰአት በፊትቻይና እስራኤል በኢራን ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት አወገዘችፉ ኮንግየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesእስራኤል “በኢራን ሉዓላዊነት፣ ደህንነት እና የግዛት አንድነት ላይ ጥሰት እየፈጸመች ነው” ስትል ቻይና ጥቃቱን አወገዘች።ቻይና የእስራኤልን ጥቃት ያወገዘችው በተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት በተጠራው የቅዳሜ፣ ሰኔ 7/ 2017 ዓ.ም አስቸኳይ ስብሰባ ላይ በተወካይዋ ፉ ኮንግ በኩል ነው።ቻይና የአሁኑ ጥቃት በኢራን የኒውክሌር ድርድር ላይ የሚያሳድረው አሉታዊ ተጽእኖ “ከፍተኛ ስጋት አሳድሮብኛል” ስትል ነገሮች ከዚህ በበለጠ እንዳይከፉ እስራኤል ሁሉንም ወታደራዊ እርምጃዎችን በአስቸኳይ እንድታቆም አሳስባለች።የቻይና የተመድ ተወካይ በተጨማሪ ኢራን “የኑክሌር ጦር መሳሪያን ያለመስፋፋት ስምምነት ፈራሚ በመሆኗ የኒውክሌር ኃይልን በሰላማዊ መንገድ የመጠቀም መብቷ ሙሉ በሙሉ ሊከበርላት ይገባል” ብለዋል።ቻይና በኃይል እና መሰረተ ልማቶች የኢራን ቁልፍ አጋር ናት።ከጥቂት ወራት በፊትም የኢራን እና የሩሲያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የተሳተፉበት በኢራን የኒውክሌር ጉዳይ ላይ የመከረ ውይይትን አዘጋጅታ ነበር።አገራቱ በኢራን ላይ የተጣለው ማዕቀብ እንዲነሳ አሳስበዋል።ያጋሩ, ቻይና እስራኤል በኢራን ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት አወገዘች
  6. ከ 3 ሰአት በፊትእስራኤል በኢራን ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት መቀጠሏን ጦሯ አስታወቀእስራኤል በኢራን ላይ የቀጠለችው ጥቃትየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየእስራኤል መከላከያ ኃይል በኢራን ኢላማዎች ባላቸው ላይ የአየር ጥቃቱን መቀጠሉን አስታወቀ።መከላከያው በቴሌግራም ባወጣው አጭር መግለጫ “የእስራኤል ኃይል በኢራን ውስጥ ያሉ ስጋቶችን ለማስወገድ ኢላማ ባደረጋቸው ይዞታዎች ላይ ጥቃቱን ቀጥሏል” ብሏል።መግለጫው የተለጠፈው የአየር ጥቃቶችን ከሚያሳይ ቪዲዮ ጋር ነው።እስራኤል በኢራን የኒውክሌር ይዞታዎችን እንዲሁም የጦር አዛዦች ላይ ጥቃት ፈጽማ ሶስት የኢራን ወታደራዊ አዛዦችን ከገደለች በኋላም በጥቃቷ ቀጥላለች።ኢራን ቅዳሜ ማለዳ በእስራኤል ላይ ሚሳኤሎችን አስወንጭፋለች።ያጋሩ, እስራኤል በኢራን ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት መቀጠሏን ጦሯ አስታወቀ
  7. ከ 3 ሰአት በፊትየቀጠለው የእስራኤል ጥቃት እና የኢራን አጸፋከቴል አቪቭ አቅራቢያ በኢራን ጥቃት የደረሰ ጉዳትየፎቶው ባለመብት,REUTERS/Ronen Zvulunየምስሉ መግለጫ,ከቴል አቪቭ አቅራቢያ በኢራን ጥቃት የደረሰ ጉዳትእስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት በመክፈት የጀመረችው ፍጥጫ አርብ ለቅዳሜ አጥቢያ ሌሊትም ቀጥሏል።በሁለቱም አገራት ውስጥ የአየር ጥቃቶች እና ፍንታዳታዎች መከሰታቸው ተዘግቧል።ኢራን የአጸፋ ሚሳዔሎችን ወደ እስራኤል በመተኮሷ በቴል አቪቭ እና ኢሩሳሌም ውስጥ የአየር ጥቃት ማስጠንቀቂያ ደወሎች እና ሲሰሙ ቴህራን ውስጥ ፍንዳታዎች ተሰምተዋል።የኢራን የበላይ መሪ አያቶላህ ኻሜኒ እስራኤል በአገራቸው ላይ ለፈጸመችው ጥቃት “ከባድ አጻፋ” እንሚጠብቃት ዝተዋል።ኢራን ወደ እስራኤል በተኮሰቻቸው ሚሳዔሎች ተጎድተዋል የተባሉ 40 ያህል ሰዎች ወደ ሆስፒታል መግባታቸው እና ከመካከላቸውም ሁለቱ በጽኑ መጎዳታቸው ተዘግቧል።የኢራን አብዮታዊ ዘብ እንዳለው በእስራኤል ላይ ባለስቲክ ሚሳዔሎችን ሲተኩስ፣ የእስራኤል ጦር ሠራዊት ደግሞ ሚሳዔሎቹን ማክሸፉን አስታውቋል።በተባበሩት መንግሥታት የኢራን መልዕክተኛ በእስራኤል ጥቃት ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦችን ጨምሮ 78 ሰዎች መገደላቸውን እና ከ320 በላይ የሚሆኑ ደግሞ መቁሰላቸውን አስታውቀዋል።አሜሪካ እስራኤልን በመደገፍ ስትቆም፣ ቻይና እና ቱርክ የእስራኤልን ድርጊት በማውገዝ አቋማቸውን ገልጸዋል።የተባበሩት መንግሥታት እና ሌሎች አገራት ደግሞ ኢራን እና እስራኤል ግጭቱን ከሚያባብሱ እርምጃዎች እንዲቆጠቡ ጥሪ አቅርበዋል።ያጋሩ, የቀጠለው የእስራኤል ጥቃት እና የኢራን አጸፋ