Banteamlak Ayalew Abate ·Follow

ግዕዝ ወይስ ግእዝ

እናውቀው ዘንድ ይገባል!

“ግዕዝ” እና “ግእዝ” የሚሉትን አጻጻፎችን የተለያየ ትርጒም አላቸው። ለቋንቋው ግን ሁለቱንም መጠቀም እንችላለን። በመጀመሪያ ግእዝ በአልፋው “አ” ሲጻፍ የመጀመሪያ፣ ቀዳሚ አንድ አንደኛ ነባር ማለት ነው። በዚህ አጻጻፍ የግእዝ ቋንቋ ስንል ጥንታዊው፣ ቀዳማዊ፣ አንደኛው እንዲሁም የመጀመሪያ የሀገሪቱ ቋንቋ የሚል ፍች ይኖረዋል።

“ግዕዝ” ብሎ በዐይኑ ዐ ሲጻፍ ደግሞ ሥርወ ቃሉ “ግዕዘ” ነፃ፣ ነፃነት ነፃ መውጣት፣ ነፃ አውጪ የሚል ትርጉም ይሰጣል። ይህም ግዕዝ የነፃ ሕዝቦች ቋንቋ በመሆኑ የሚጠራበት ነው። ለዚህ አስረጁ ምንድን ነው ከተባለ አግዓዚያን የሚባሉ ሕዝቦች ናቸው። እነዚህም የኢትዮጵያ ነባር ሕዝቦች ናቸው። በእርግጥ ዐምሓራ የአግዓዚ የአማርኛ ተለዋጭ መሆኑና ዐምሓራ ማለትና አግዓዚም የአንድ ተመሳሳይ ማኅበረሰብ መገለጫዎች መሆናቸውን ጥናቶች ይጠቁማሉ። ይህም በስምም በታሪክም መሆኑንም ያመላክታሉ።

በዚህ መሠረት “ብሔረ አግአዝያን” ተብሎ ሲጻፍ የጥንታዊ፣ የመጀመሪያ፣ የቀዳሚ ሕዝቦች መኖሪያ ማለት ሲሆን “ብሔረ አግዓዝያን” ሲባል ቅኝ ግዛት ተገዝተው የማያውቁ በነጻነት የሚኖሩና ነጻ የሚያወጡ ሕዝቦች ምድር የሚል ትርጒም ይሰጠናል። ሁለቱም ስሞች ታሪካዊ ድጋፍ አላቸው።

ግዕዝ – የነፃ ሕዝቦች ቋንቋ

ግእዝ – የመጀመሪያ ቋንቋ

@followers @highlight

ይኸ መጽሐፌ ያላችሁ ምዕራፍ አራት ላይ ብሔረ አግዓዝያን የሚለውን ተመልከቱ።