

ቤተ ቅዱስ ያሬድ ·Follow
★ የግእዝ /ግዕዝ ቋንቋ ፣ ታሪካዊ አመጣጥ ★
ግዕዝ ፡ከነፊደሉ ፡ከየት፡ እንደተገኘ ፡የማንስ ፡ቋንቋ፡ እንደሆነ፡ ለማወቅ ፡ቀደምት ፡አባቶቻችንና የዓለም ሊቃውንት በጥረታቸው፡ ያስቀመጡት ፡ማስረጃ፡ ለአሁኑ፡ ትውልድ መማረያና የጥናት ፡ መንደርደሪያ ፡ መሰረት ነውና ማጤን ያስፈልጋል።
ግዕዝ ግዕዝ ማለት በቁሙ መጀመሪያ (ቀዳማዊ) ማለት ነው። ግዕዝ ብለን ስለ ቋንቋው ስናነሳ ደግሞ ጥንታዊ ቋንቋ ነው ። የመጀመሪያው ሰው የአዳም ቋንቋ ነው ። የአዳም የስሙን ትርጉም ስንመለከት አደመ፣ አማረ ተዋበ ከሚለው የግዕዝ ግስ የወጣ ሲሆን ያማረ የተዋበ ፍጡር ማለት ነው። ስለዚህ ፡ግዕዝ ፡ቋንቋ ፡ከእነፊደሉ፡ ለመጀመሪያው ፡ሰው ፡አዳም ፡ከፈጣሪው፡ የተሰጠው ፡ሀብተ፡ ፀጋ ፡እንደሆነ ፡የእምነት፡ ሰዎች ፡ያምናሉ።
ግዕዝ ፡አዳማዊ ፡ቋንቋ ፡ሆኖ ፡ሲያያዝ የመጣ ፡መሆኑን ፡ብዙ ሊቃውንት፡ በብዕራቸው ፡አስፍረውታል። ለምሳሌ
የኢትዮጵያ ፡እምነት፡ በ3ቱ ህግጋት፡ ዘአለቃ፡ አያሌው በ1953አ.አ የታተመ፡ እንዲህ፡ ይላል፦ ይህ ፡ቋንቋ ፡ከአዳም፡ አንስቶ ፡እስከ፡ ባቢሎን ፡ግንብ ፡መፍረስ ፡ድረስ:አለም፡ በጠቅላላ ፡የሚነጋገርበት ፡ብቸኛ ፡ቋንቋ፡ እንደነበርም ፡መጻሕፍት ይናገራሉ።ዘፍ:፲፩÷፩(11÷1) “እስመ አሐዱ ነገሩ ለኲሉ ዓለም”እንዲል።ይህንን ቃልም ፡መነሻ ፡በማድረግ ፡ብዙ ፡ሊቃውንት፡ ለግዕዝ ቋንቋ ፡ጥንታዊነትን ይሰጡታል።ይሁን እንጂ፡ በዘመናችን፡ የሚገኙ ፡ሳይንሳውያን፡ ሊቃውንት ፡ይህን ሀሳብ ፡አይቀበሉትም።ምክንያቱም ቋንቋ፡ ከአንድ ፡ህብረተሰብ፡ የእድገት ፡ደረጃ ፡ጋር አብሮ ፡የሚሄድ፡ እንጂ፡ እንደ ፡እምነት ፡ሰዎች አባባል፡ ከመለኮት፡ የመጣ/መለኮታዊ/አይደለም ፡ይላሉ ።ያምሆነ ይህ ግን፡ የግዕዝ ፡ቋንቋን ፡ጥንታዊ፡ መሆን፡ ማንም፡ አይክድም።በነፃ ህዝቦች የሚነገር ቀዳሚ የዓለማችን ቋንቋ መሆኑን ፣ እዲህ ሐረገ ፡ዝርያውንም ፡ሊቃውንት ፡ይመለከቱታል።ዘፍ:(10÷25) ፋሌክ ፡በተባለ ፡አንድ ፡ባለታሪክ፡ ሰው ፡ዘመን የተለያዩ፡ 72 ቋንዎች ፡ተገኝተዋል።በዚህ ጊዜም ፡በክፍፍል፡ ደረጃ 15 ለሴም 25 ለያፌት 32 ለካም ተስጥቷቸዋል።መርሐ-ልቡና ዘሊቀ ጠበብት አክሊለ ብርሃን (1945 አ.አ)።በመሆኑም ፡ግዕዝ ቋንቋ፡ ከነገደ ሴም ፡እንደመጣ ፡ከዚያም፡ ጊዜ፡ በኋላ ለነገደ ፡ዮቅጣን ፡የተሰጠ ፡እንደሆነ ይናገራል ።ነገደ ፡ዮቅጣን፡ እየተባሉ በሚጠሩት በሳባ፣በኦፌር፣በኦባልም፡ግዕዝ ቋንቋ ፡ተገኝቷል፡ይባላል።(ዘፍ፡9፥19)እነዚህም ሰዎች የሴም ዘር የዮቅጣን ነገዶች እንደሆኑ የታሪክ ሰዎች ይናገራሉ። ሌላው ለቋንቋው ቀዳሚነት ማስረጃ የዚህ ብሔር ቋንቋ ነው ተብሎ እስካሁን አለመሰየሙ ነው። ከዚህ በኋላም አይመጣም ። ምክንያቱም ከማንኛውሞ ቋንቋ ጥገኝነት ነጻ የሆነ ለብዙ ቋንቋዎች መነሻ መሠረት በመሆኑ ነው።
አንዳንድም የግዕዝ ሰዋስው በመጻፍና በማቀናበር ወደ ላቲን ቋንቋ በመተርጎም የታወቁት ጀርመናዊ ሊቅ ዲልማን አንዱ ሲሆኑ ሌሎችም እንደ ሲዲ ጳውሎስ ግዕዝ ጥንታዊ ቋንቋ እንደነበረ በጽሑፋቸው ገልጸዋል።
የግዕዝ ትንሣኤ!
ግዕዝ በኢትዮጵያ የሥልጣኔ ታሪክ ውስጥ እስከ 10 ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድረስ የንግግር ቋንቋ ሆኖ አገልግሏል፡፡
ከ 10 ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በኋላ ደግሞ ከንግግር ቋንቋነቱ ይልቅ ጽሁፋዊ ቋንቋነቱ እየበለፀገ መጣ፡፡
ከ 13 ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ አማርኛ በብዛት መነገርና መስፋፋት ሲጀምር ግዕዝ ከመደበኛ የንግግር ቋንቋነት ይልቅ ወደ ቤተክርስቲያን ቋንቋነት እና የጽሁፍ ቋንቋነት እየቀረበ ሄደ፡፡
ይህ ዘመን ለግዕዝ ሥነ ጽሑፍ ዕድገት ወሳኝ ምዕራፍ ነበር፡፡ተአምረ-ማርያም እና ፍትሐ- ነገሥት የመሳሰሉት መጻሕፍት በዚህ ዘመን በግዕዝ ተከትበዋል፡፡
ከዳግማዊ ቴዎድሮስ መነሳት በኋላ መጽሐፍ ቅዱስ ወደ አማርኛ ሲመለስና በብሔራዊ ቋንቋነት ሲለመድ ግዕዝ ስልጣኑን ለአማርኛ እየለቀቀ መጣ፡፡በኢትዮጵያ አብያተክርስቲያን ውስጥ ብቻ ተወሰነ፡፡ በአንዳንዶች ዘንድ ግን እንደጠፋ ቋንቋ ተቆጠረ፡፡
የጀርመን የቋንቋ ጥናት ተቋም፣ግዕዝን እስከ ሦስተኛ ዲግሪ ሲያስተምር በዓለም ላይ መነቃቃትን ፈጠረና ግዕዝ ዓለማአቀፋዊ ትኩረት ሳበ፡፡ በ 2008 ዓም የካናዳው ቶሮንቶ ዩኒቨርሲቲ ግዕዝን ከዕብራይስጥ፣ከግሪክ ፣ ከፅርዕ፣ከአራማይክ፣ከላቲን ፣ ከአረብኛና ሌሎች ጥንታዊ የዓለም ቋንቋዎች ጋር እያስተማረ ነው፡፡
የምስራቅ አፍሪካን ታሪክና ባህል ለማጥናት ግዕዝ ተመራጭ ሆኗል፡፡በሚያዚያ 2009 ዓ ም የአሜሪካው ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲም ግዕዝን ማስተማር መጀመሩን ባሳለፍነው ሳምንት ይፋ ባደረገ በጥቂት ጊዜ ውስጥ ግዕዝን ለመማር ተማሪዎች ሰልፍ ይዘዋል፡፡
በዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ የግዕዝ መምህር የሆኑት ፕሮፊሰር ሀምዛ ዛፊር”ግዕዝ የአፍሪካ ጉዳዮችን ብቻ ሳይሆን የዓለም ሃይማኖቶችን አመጣጥ ለማጥናት ተመራጭ ቋንቋ ነው”ይላሉ፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ግዕዝ፣ለባህላዊ መድሐኒት ቅመማ፣ለዘመን ቆጠራ ፣ለሂሳባዊ ስሌት፣ ለሥነ ፈለክ ምርምር፣ስለ ከበሩ ማዕድናት ጥናትና ምርምር፣ስለ ማይታወቁ ዓለማትና በውስጣቸው ስላሉ ልዩ ልዩ ፍጥረታት ምርምር ወዘተ አጋዥ ቋንቋ ነው፡፡
በሀገር ውስጥ ደግሞ አማርኛን የሚያስተምሩ ዩኒቨርሲቲዎች ግዕዝን እንደ አንድ ኮርስ ይሰጣሉ፡፡ለታሪክ ተማሪዎችም ግዕዝን ማስተማር እየተጀመረ ነው፡፡ የጎንደር እና የባህርዳር ዩኒቨርሲቲዎች በዚህ በኩል ተጠቃሽ ናቸው፡፡
በቤተክርስቲያን ብቻ ተወስኖ ከነበረበት ወጥቶ ለአደባባይ የበቃው ግዕዝ ከአፍሪካ ብቸኛው ባለፊደል ቋንቋ ነው ፡፡ ግዕዝ ዳግም እንዲያንሰራራ ከትምህርት ተቋማት ልዩ ትኩረት ይሻል፡፡
አሁን በየትምህርት ቤቱ የሚሰጠው ሀሰተኛ ትምህርት በፍጥነት ሊገመገም ይገባል። በተለይ ከ፬ኛ ክፍል ጀምሮ ያሉት መፅሐፍቶች ትውልድን ከማነጽ ይልቅ ወደ ባርነት የሚያዘጋጃቸው ሆኖ አስተውለናል እንንቃ። ኢትዮጵያ የራሷን ፊደል የቀረጸች ፣ ብርቱ ሀገር ናት !! በንዝህላልነት አሳነስናት እንጂ!!!
ሀ ብላ ሀልዎተ እግዚአብሔር የምትል ለፊደላቱ ትርጓሜ ሰጥታ በጥልቅ የምትመረምር ምስጢር የሚፈታባት እውቀት የሚፈስባት ሀገር ናት በዓለም ላይ የራሳቸውን ፊደል የቀረጹ ጥቂት ሀገራት ሲሆኑ ኢትዮጵያ ግንባር ቀደም ናት በዚህ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊኮራ ይገባል በኢትዮጵያ ያለ ሀብት ሁሉ የኢትዮጵያውያን ነው ዓለምም የሚያውቀን በኢትዮጵያዊነት እንጂ በመንደር በጎጥ አይደለም። ወገኖቼ ንቁ !
ግዕዝ የአዳምና ሔዋን (የተፈጥሮ ቋንቋ) የመጀመሪያው መነጋገሪያ ልሳን መኾኑ እንዴት ማረጋገጥ ይቻላል?
፩ኛ. የ ”ግዕዝ” የጥሬ ዘሩ ቃል ትርጉም፡ “መጀመሪያ”, “ነፃ” እና “የጥንት ተፈጥሮ ጠባይ ወይም ባህሪይ” ማለት መኾኑ
፪ኛ. የእያንዳንዱ ፊደል የመጀመሪያ ቅርጽ አፍ ሳያስከፍት በድን በኾነው በተፈጥሮ ድምፅ ብቻ የሚነገር መኾኑ
፫ኛ. የፊደሉ መነሻ “አ” “አዳም” በሚል ቃል በወንድና ሴት ጾታ ለተፈጠሩት ለመጀመሪያዎቹ ሰዎች መጠሪያ መኾኑ
፬ኛ. በሰባት ብዛት የሚወሰን ቁጥር፤ የመለኮታዊ ሥራ ምስጢር እንዳለበት ስለሚታመን፤ እያንዳንዱ ፊደል፤ በሰባት ስሞች ድምጾችና መልኮች ተለይቶ የሚታወቅና የሚነገር መኾኑ
፭ኛ. ሌሎቹ የሰዎች ቋንቋዎችና ፊደሎቻቸው በተናጋሪዎቻቸው ሕዝቦች ወይም ጎሣዎች ስም ለምሳሌ፤ ዐማርኛ፤ በዐምሓሮች፤ ዕብራይስጥ በዕብራዊያን፤ ዐረብኛ በዓረቦች ስም ሲጠሩ “ግዕዝ” ግን በራሱ ብቻ የሚጠራ መኾኑ
፮ኛ. በ ”አ” ጀምሮ በ “ኦ” የሚፈጸም ፊደል ያለው እርሱ፤ ግእዝ ብቻ ከመኾኑ ጋር “አልፋና ኦሜጋ፤ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ” ብሎ፡ ኃላ “ኢየሱስ ክርስቶስ” ተብሎ፤ ራሱን በሰውነት የገለጸው “እግዚአብሔር” በዚህ ስሙ የታወቀበትና አምልኮቱ የሚፈጸምበት ቋንቋና ፊደል ኾኖ በሕያውነት እስከዛሬ መቀጠሉ
፯ኛ. በምድር ላይ የሚኖሩ የሰው ልጆች ኹሉ፡ ተወልደው በሕፃንነታቸው መናገር በሚጀምሩበት ጊዜ ቋንቋቸውና ፊዲፈላቸው የተለያዩ ሲኾኑ፤ አፋቸውን መፍታት አባቶቻቸውናና እናቶቻቸውንም ለይተው መጥራት የሚጀምሩበት “አባባ”፤ “እማማ!” የሚባሉት ቃላት “አብ አብ አብ”፤ “እም እም እም” የተባሉት፤ ትርጉማቸው፡ “አባት አባት አባት”፡ “እናት እናት እናት” የኾነውን ቀጥታ የግእዙን ቃላት መኾኑ ናቸው።
ግዕዛውያን ስለምን የራሳችን ፊደል እያለን በማይገባ ጥላቻ የኛነታችንን ሀብት ጥለን በሰው ሀገር ፊደል እንጎለዳደፋልን? በሰለጠነው ዓለም በቋንቋህ አስተርጓሚ ቆሞልህ ታወራለህ ለአስተርጓሚው መንግስት ከፍሎልህ አንተ በነጻ ታወራለህ ቋንቋ መግባቢያ ስለሆነ አትነፈግም ወይም ቋንቋ ስለማትችል አናክምህም አይሉም በትርጉም ያክሙሃል እኛ የተውነውንና የቀበርነውን የኛን ፊደል ጀርመኖች አጥንተው የኛን መጻህፍት ከትራሳችን ስር ወስደው ተርጉመውና ተራቀው ለዓለም በሚያቀርቡት መድኃኒት አንቱ ተብለውበታል በዩንቨርሲቲዎቻቸው በስፋት በማስተማር ተዝቆ የማያልቅ እውቀትን ያፍሱበታል ።
በኛ ሀገር ግን በዚህ ክልል ይህ ቋንቋ እንዳይነገር ይህ ፊደል ልጆች እንዳያውቁት እያሉ ከፍተኛ ጥላቻን በመስበክ እነሱ አቀላጥፈው የሚናገሩትን ቋንቋ ሚድያ ከፍተው የሚነግዱበትን ቋንቋ ልጁን እንዳትማር እንዳታውቅ ብሎ ትውልድን ማደንቆር ምን ይሉት ስልጣኔ ይሆን? እንዲህ ትውልድን ለመግደል ወንድም ከወንድሙ ጋር እንዳይግባባ ማድረግ ህሊናን ከማጣት ውጪ ሌላ ምን ይባላል ፤ቋንቋን እውነት ነው ቋንቋ መግባቢያ ነው። ቋንቋ ታሪክ ነው።
ላወቀበት ከአንድ በላይ ቋንቋ ማወቅ ምንኛ መታደል ነው።
ቋንቋን ማወቅ ማንን ሲጎዳስ አየን? ቋንቋን አለማወቅ ግን ብዙ ጉዳት አለው። እውነትም ሀሰተኛንብቻ ነው ሚጎዳው። ስለዚህ ሁሉን መገር የፖለቲካ ቅርጫት ፣ የሐሰት ቅርጫት ፣ የመከራ ቅርጫት ፣ የጥላቻ ቅርጫት፣ የብሔር ቅርጫት፣ ሕይወት ሁሉ ቅርጫትበቅርጫ ውስጥ እየከተቱ ስንወዘጋገብ አንኑር። ሰከን ብሎ የሚጠቅመውን በቅን ልቦና ማየትና ይዞ መጓዝ ለሀገርም ለትውልድም ይጠቅማል! !
ቋንቋ እውነት እና ታሪክ ነው።
ከደብተራ ወልደ ደብተራ
ተከተበ::
ቤተ ቅዱስ ያሬድ
የቅኔና የግእዝ መንደር ባሕር ዳር![]()
