ዳታን በመቆጠብ ጽሑፍ ብቻ ለማንበብ

አልጋዋ ላይ በነጭ የአልጋ ልብስ ተጠቅልላ ቁጭ ያለችና አረንጓዴ ኩባያ የያዘች ሴት።ሴትዮዋ ጥቁር ፀጉር ያላት ሲሆን ወደ መሬት እየተመለከተች ነው።

ከ 5 ሰአት በፊት

ሳል፣ የድምፅ መሻከር እና የጉሮሮ መከርከር ገጥሟችሁ ያውቃል?

እንዲህ ዓይነት ምልክቶች ያሏቸው በቫይረስ የሚመጡ እንደ ጉንፋን እና ኢንፍሉዌንዛ ያሉ በሽታዎች በየትኛውም ጊዜ ሊያጋጥማችሁ ይችላል።በተለይ ደግሞ በቀዝቃዛ ወቅት በስፋት ይከሰታሉ።

ሆኖም ምልክታቸው ተመሳሳይነት ስላለው አንዳንዴ ለየትኛው በሽታ እንደተዳረግን ግራ እንጋባለን። ለጉንፋን፣ ለኢንፍሉዌንዛ ወይስ ለኮቪድ? እንዴት ልንለያቸው እንችላለን?

የሕክምና ዶክተር እንዲሁም የቢቢሲ ሞርኒንግ ላይቭን ጨምሮ በሌሎች ፕሮግራሞች አቅራቢ የሆነው ዶክተር ኦስካር ዳክ በዚህ ዙርያ የተወሰኑ ምክሮችን ይሰጠናል።

ቀዝቃዛ የአየር ጠባይ ለጉንፋን ያጋልጣል?

ታዳጊ ልጁን ጭኑ ላይ አስቀምጦ አፍንጫዋን የሚያፀዳ አባት።ታዳጊዋ ቢጫ ቀሚስ የለበሰች ሲሆን አባቷ ደግሞ ጥቁር የዓይን መነጽር እና ካኪ ቀለም ያለው ካናቴራ ለብሷል።

ቀዝቃዛ የአየር ጠባይ የበሽታ መከላከል ሥርዓታችን ላይ ተፅዕኖ ያሳድር እንደሆነ የሚያሳዩ ግልጽ ጥናቶች የሉም።

ሆኖም ቀዝቃዛ የአየር ጠባይ እና የበሽታ መከላከል ሥርዓት መዳከም በተዘዋዋሪም ቢሆን ይገናኛሉ።

በጣም ቀዝቃዛ በሆነ የአየር ጠባይ ወቅት ሙቀት ለማግኘት ስንል ተደርድረን የመቀመጥ፣ የመጠጋጋት እና በቤት ውስጥ የማሳለፍ ሁኔታዎች አሉ። እንዲህ ዓይነት አካባቢ ደግሞ ለቫይረስ መዛመት ምቹ ነው።

እንደ ዩናይትድ ኪንግደም ባሉ አንዳንድ አገራት ደግሞ ታዳጊ ሕፃናት ከበጋ እረፍት በኋላ ወደ ትምህርት ቤት የሚመለሱት በቀዝቃዛ ወቅት ነው።

ትምህርት ቤቶችና የሕፃናት ማቆያዎች ደግሞ ቫይረሶች በቀላሉ የሚዛመቱባቸው ሥፍራዎች ሲሆኑ፤ ሕፃናቱም እነዚህን ጀርሞች ተሸክመው ወደ ቤት ይሄዳሉ።

በዚህ ወቅት ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ አዲስ ተማሪዎችም ከሌሎች ጋር በሚቀላቀሉበት ጊዜ በተመሳሳይ መልኩ ጀርሞች ይዛመታሉ። በዚህ ላይ አብዝቶ የአልኮል መጠጥ መጠጣት እና ‘ፓርቲ’ [የመዝናኛ ድግሶች] ሲጨመሩበት የበሽታ መከላከል ሥርዓትን ያዳክማሉ።

ጉንፋን፣ ኢንፍሉዌንዛ ወይስ ኮቪድ?

የጉንፋን ፣የኢንፍሉዌንዛ እንዲሁም ከበድ ባለ ቫይረስ የሚከሰተው ኮቪድ ምልክቶቻቸው ተቀራራቢ ናቸው።

ሆኖም በየትኛው እንደተያዝን ለመለየት የሚረዱን ጥቂት ፍንጮች አሉ።

ጉንፋን ከሆነ የህመም ስሜቱ እየተሰማን የሚሄደው ቀስ በቀስ ነው። መጀመሪያ አፍንጫችንን እና የጉሮሯችንን መጨረሻ ነው የሚያጠቃን።አንዳንዶች በአፋቸው መጨረሻ የማሳከክ ስሜት ይሰማቸዋል።

ሌላኛው ምልክት ደግሞ በጆሯችሁ ላይ የመደፈን ስሜት መሰማት ነው። ቫይረሱ እየተሰራጨ ከሄደ ወደ ሳንባችን ሊደርስ የሚችል ሲሆን ሳንባችን ጋር ከደረሰ ሳል ይፈጥራል። በአብዛኛው እነዚህን ስሜቶች የተለመዱ አድርገን ስለምንቆጥራቸው ከተለመደው እንቅስቃሴያችን አያስተጓጉሉንም።

አልጋ ላይ የተኛ አንድ ግለሰብ በግራ በኩል ፊቱን በእጁ ይዞ ይታያል።ግለሰቡ ጠቆር ያለ አረንጓዴ ቀለም ያለው ካናቴራ ልብሷል።

ኢንፍሉዌንዛም ተመሳሳይ ምልክት ያለው ሲሆን ቁርጥማት ፣ ትኩሳት እና የጡንቻ መዛል ያስከትላል።

አልጋ ላይ ባይጥላችሁም እንደዚያ ዓይነት ስሜት እንዲሰማችሁ ሊያደርግ ይችላል።

የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ ወዲህ ኮቪድ ከኢንፍሉዌንዛ ጋር የሚመሳሳሉ ምልክቶች ስላሉት ነገሮች የባሰ እንዲወሳሰቡ አድርጓል።

ሆኖም ኮቪድ ከሌሎቹ የሚለይበት ቁልፍ ምልክት አለው። ይህም የማሽተት ወይም የመቅመስ ችሎታችንን ማጣት ነው።

በክረምት ወቅት ‘ስትራተስ’ እና ‘ኒምበስ’ የተባሉ አዳዲስ ዝርያዎችም ተከስተው የነበረ ሲሆን፣ ከባድ የጉሮሮ መከርከር ምልክቶች ነበራቸው።ተቅማጥም የተለመደ ነው።ስለዚህ እንዲህ ዓይነት ምልክቶች ካሏችሁ ቤት መሆን፣ማረፍ እና ማገገም ይመከራል።

ነገር ግን ሥር የሰደደ በሽታ ካለባችሁ፣ የትንፋሽ ማጠር ወይም ከሦስት ሳምንት በኋላ ህመሙ እየቀለላችሁ ካልመጣ ወደ ሐኪም ለመሄድ ማመንታት የለባችሁም።

ራሳችንን ማከም እንችላለን?


የተለያየ ቀለም ያላቸው ኪኒኖች

ሰውነታችን በተፈጥሮው ቫይረሶችን እና ኢንፌክሽኖችን ይዋጋል።ሆኖም በትክክለኛው መድሃኒት ልናግዘውም እንችላለን።

ክትባትስ?

ክትባት የምትከተብ ሴት

የዓለም ጤና ድርጅት እንደሚለው ከሆነ በኢንፍሉዌንዛ ቫይረስ የሚከሰቱ ከባድ ህመሞች እና ኢንፌክሽኖችን ለመከላከል ክትባት ውጤታማው መንገድ ነው።

ኢንፍሉዌንዛ በሽታን የሚያስከትለው ኢንፍሉዌንዛ ቫይረስ በየጊዜው ራሱን ይለውጣል።በመሆኑም አዳዲስ ዝርያዎችን ለመዋጋት ክትባቶች በየዓመቱ ይሻሻላሉ። ዶክተር ኦስካር እንደሚለው ክትባቱን ከዚህ ቀደም ካልወሰዳችሁ ዓመታዊውን የጉንፋን ክትባት መውሰድ ጠቃሚ ነው።

ይበልጥ ተጋላጭ ለሆኑት ቅድሚያ ለመስጠት ክትባቱን መውሰድ የሚችሉት ሰዎች እንደየ አገራቱ ይለያያል።

የአውሮፓ የበሽታ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ማዕከል እንደሚለው ሥር የሰደደ የጤና ችግር ላለባቸው፣ ለነፍሰጡር ሴቶች፣ ከ6 ወር እስከ አምስት ዓመት ላሉ ሕፃናት፣ አረጋውያን እንዲሁም የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ ከጉንፋን ጋር በተያያዘ ውስብስብ የጤና እክል ለሚያጋጥማቸው ሰዎች ክትባቱ ወሳኝ ነው።