Teshome Berhanu Kemal ·Follow

አንድ ትልቅ ኢትዮጵያዊ በአሜሪካ

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኢንስትራክተር ሆኖ ያገለገለውና አሁን በአሜሪካ የጥናትና ምርምር የአርትኦት ሥራውን እያከናወነ የሚገኘው ዶክተር ግርማ አውግቸው ደመቀ “ቋንቋ፣ ታሪክ፣ ሀይማኖት፣ እና ነገድ” ኩሽ እና ኩሻዊ በሚል ርዕስ አዲስ መጽሐፍ ለንባብ ያበቃ ሲሆን ይህም መጽሐፍ በሀገር እምነት የሚወክለውን ጥንታዊ ሀገር፣ በዚያ ሀገር ይኖሩ የነበሩ ህዝቦች ማንነትና የነበራቸውን ስልጣኔ፣ በመፅሀፍ ቅዱስ ያለውን የኩሽ አጠቃቀም፣ እንዲሁም ኩሻዊ በመባል የሚታወቁት ቋንቋዎችን እና ተናጋሪዎቻቸውን በጥልቀት ቃኝቷል።

ኩሽ ከመፅሀፍ ቅዱሱ አጠቃቀም እና ከጥንታዊ የኩሽ መንግሥት ጋር አንዳንዴ እየተደባለቀ በኢትዮጵያ ታሪክ መቅረቡንም ዳስሷል። ኩሽ በሚል ይጠቀስ ከነበረው ሀገርና በዚያ ከሚኖሩ ህዝቦች ጋር አሁን ያለው ኩሸቲክ ኩሻዊ የሚለው የቋንቋ ቤተሰብ ስያሜ አጠቃቀም የሚያገናኘው ነገር መኖር አለመኖሩን ሰፋ አድርጎ ዳሷል።

የኢትዮዽያ ሕዝብ ማንነትና ቅድመ ታሪክ ከቋንቋ አንፃር እንዴት ይታያል?

2018 መጋቢት ወር በሀገረ አሜሪካ ለንባብ ካበቁት አካዴሚያዊመጻሕፍት ተጠቃሹ ‹‹ቋንቋና ነገድ በኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ሕዝብማንነትና ቅድመ ታሪክ›› የሚል ርዕስ ያለው የዶ/ር ግርማአውግቸው ደመቀ መጽሐፍ ነው፡፡

D.r Girma A. Demeke የሥነ ልሳንናየኢትዮጵያዊ ቋንቋዎች ባለሙያ ሲሆኑ፣የምርምር ትኩረታቸው በአብዛኛው የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ታሪክና ሥነ መዋቅር ላይ ነው፡፡ በቅርቡ በእንግሊዝኛ ካሳተሟቸው መጽሐፎች መካከልየአማርኛ ጥንተ አመጣጥ፣ ሰዋስዋዊ ለውጥ በሴሜቲክ #የአማርኛ ሰዋሰው በዘመን፣ሒደትና #የአርጎብኛ ንግግር ዓይነቶች/ቋንቋዎች ይገኙባቸዋል፡፡

ስለአዲሱ መጽሐፋቸው በመጽሐፉ የጀርባ ሽፋን እንደተገለጸው፣መጽሐፉ ስለኢትዮጵያ ቋንቃዋችና ቤተሰቦቻቸው የታሪካዊ ሥነልሳን ጥናት መውሰድ እስከሚችለው ጊዜ ገደብ ድረስ በመጓዝመሠረታዊ መረጃ ያቀርባል፡፡ ቋንቋና ተናጋሪው የሚለያይ

አይደለምና፣ከቋንቋዎቹ አንፃር በመነሳት የኢትዮጵያን ሕዝብማንነትና ቅድመ ታሪክ ይዳስሳል፡፡ የኢትዮጵያ ቋንቋዎችከተወሰኑ ብቸኛ ቋንቋዎች በስተቀር አፍሮ ኤሽያቲክናናይሎሰሀራን ከሚባሉ ታላቅ ቤተሰቦች ይመደባሉ፡፡

ከጥቂት የናይሎ ሰሃራን ቋንቋዎች በስተቀር ሌሎቹ ለረዥም ጊዜበኢትዮጵያ የነበሩ ናቸው፡፡ መጽሐፉ የአፍሮ ኤሽያቲክ ቋንቋዎችከኤሽያ በተለያየ ወቅት ወደ ኢትዮጵያ ገቡ የሚለውን መላምትበስፋት መርምሮ ይህ ስለመሆኑ አሁን ያለው መረጃ ማረጋገጫ እንደሌለው ያሳያል፡፡

ከዚህም በላይ በኅብረተሰብ መካከልስላለው ውህደትና ልዩነት በስፋት ይረዝራል፡፡

የመጽሐፉ አዘጋጅ ዶ/ር ግርማ ‹‹መሠረታዊ መነሻ የቅጾች ማስታወቂያ›› በሚለው ምዕራፋቸው እንደገለጹት መጽሐፉአራት ቅጾች ይኖሩታል፡፡ ለኅትመት የበቃው ቅጽ አንድ የኢትዮጵያሕዝብ ማንነትና ቅድመ ታሪክ፤ ቅጽ ሁለት ኦሞቲክ፣

ናይሎሰሀራንና ምድባቸው ያልለየላቸው ቋንቋዎች፤ ቅጽ ሦስትኩሽና ኩሽቲክ፤ ቅጽ አራት ሴማዊ ቋንቋና ሕዝብ ናቸው፡፡

.

ቀዳሚው ቅጽ በስድስት ምዕራፎች በ248 ገጾች የተደራጀሲሆን፣ የኢትዮጵያን ሕዝቦች ማንነትና ታሪካዊ አመጣጥ ከቋንቋአንፃር ተተንትኖ መረጃዎቹም በታሪካዊና ንፅፅራዊ ሥነ ልሳን ዘዴ መቅረቡ ተወስቷል፡፡

ዶ/ር ግርማ በመቅድማቸው ያነሷቸው ዐበይት ጉዳዮች አሉ፡፡አንዱ ‹‹የሴሜቲክ ሕዝብ ከዓረብ ወደኢትዮጵያ ገባ›› የሚለውመላምት፣ ሌላው ስለ ኩሽቲክ ቋንቋ ተናጋሪዎች የሚቀርበውሐሳብና የኩሽ ምንነትን ፈትሸዋል፡፡ እንዲሁም የሀበሻንምንነትንም መርምረውታል፡፡ በቅጽ አንድ መጽሐፋቸው ላይ ያነሷቸውን ነጥቦች እዚህ ላይ እንደወረደ ማቅረብ ወደድን፡፡መቅድማዊው ሐሳብ‹‹በትምህርት ዓለም መፍትሔና ማብራሪያ ያገኙ ጉዳዮች ወደኅብረተሰቡ ሳይወርዱ ይቀሩና መረጃ የሌለው ‹‹አፈ ታሪክ››

ነግሦ የሚታይበት አጋጣሚ ብዙ ነው፡፡ ከእነዚህ ውስጥየሴሜቲክ ሕዝብ ከዓረብ ወደ ኢትዮጵያ የገባ ነው የሚለውመላምት አንዱ ነው፡፡ሌላኛው በሥነ ልሳን ጥናት ኩሽቲክቋንቋዎች የሚባሉትንና የእነዚህ ተናጋሪዎችን የሚመለከት ነው፡፡

የኩሽቲክ ቋንቋ ተናጋሪዎች ላይ የሚቀርበው ታሪካዊ ትንታኔበአንዳንድ ሥራዎች ከጥንታዊ ኩሽ መንግሥት ሕዝብናከመጽሐፍ ቅዱስ ኩሽ አጠቃቀም ጋር እየተምታታ ሲቀርብይስተዋላል፡፡ በተለይ ትንሽ በተማረው ዘንድ አንዱ የወሬመክፈቻ የሴሜቲክ – ኩሽቲክ ጉዳይ እስከመሆን ደርሷል፡፡

‹‹ኩሽቲክና ሴሜቲክ ከቋንቋ ዘር ግንድ አንፃር ምንጫቸው አንድነው፡፡ በኢትዮጵያ የሚገኙትን ኦሞቲክ፣ ከኢትዮጵያ ውጭ ያሉትንእነ ጥንታዊ ግብፅን፣ በርበርን፣ ቻዲክ ቋንቋዎችን ጨምሮ የእነዚህ ወላጅ/ልዕለ ቋንቋ በአሁኑ ጊዜ አፍሮ ኤስያዊ/አፍሮኤሽያቲክ በመባል የሚታወቀው ነው፡፡

ከአፍሮኤሽያቲክቋንቋዎች በተጨማሪ በኢትዮጵያ የናይሎሰሃራን ቋንቋዎችናየተወሰኑ በቋንቋ ዘር ዝምድና ምደባቸው ያልየላቸው ቋንቋዎች አሉ፡፡

‹‹ኩሽ የሚለው ቃል (ወይም የዚህ ዝርያ ቃል) በጥንታዊሥራዎች ነገድን፣ሕዝብንና አገርን ሲያመለክት፣ በአሁኑ ወቅትደግሞ ሕዝብንና የቋንቋ ቤተሰብን ያመለክታል፡፡ በዘመናችንበትምህርታዊ ዐውድ አሁን በዚህ ቃል የሚገለጹትን የቋንቋ ቤተሰቦችም ሆኑ እነዚህን ቋንቋዎች የሚናገሩ ሕዝቦች ጥንትበቅድመ – ክርስቶስ ከሁለት ሺሕ ዓመት በፊት ጀምሮ በነበረውኩሽ በሚባለው አገር ከሚኖሩ ነገዶችም ሆነ በሌላ ከተጠቀሱት ሕዝቦች በቀጥታ የወረዱ ናቸው ማለት አይደለም፡፡

የመጽሐፍ ቅዱሱ ኩሽም አሁን በሥነ ልሳን ጥናት ካለው አጠቃቀም ጋርቀጥተኛ ግንኙነት የለውም፡፡ የምርምር ዕውቀት ሁልጊዜ ወደሕዝብ አይወርድምና በኅብረተሰባችን በተለይም በፖለቲከኞችና ትንሽ ፊደል በቆጠሩት ዘንድ የጥንቱ አጠቃቀምን አሁን ካለውጋር እያገናኙ ለሙገሳም፣ ለወቀሳም ሲጠቀሙበት ይስተዋላል፡፡

‹‹ቀደምት በአገራችን ሊቃውንት በቀረቡ ሥራዎች፣ ለምሳሌበእነ ተክለ ፃዲቅ መኩሪያና ኅሩይ ወልደ ሥላሴ የጥንቱአጠቃቀም ከአሁኑ ጋር እየተጋጨ ብዙም ግልጽ ሳይሆንቀርቷል፡፡ በአብዛኛዎቹ ቀደም ባሉት ጊዜያት በተለይ በስልሳዎቹናበሰባዎቹ ዘመናዊ የታሪክ ጸሐፊዎች ሥራዎችም ቢሆን ያለው የሕዝብ ታሪክ/ቅድመ ታሪክ ትንታኔ ቀደምት የሥነ ልሳን ሥራዎች ላይ የተመሠረተ በመሆኑ አሁን ስለቋንቋዎቹና ስለሕዝቡ ያለንዕውቀት የሚያንፀባርቅ አይደለም፡፡

‹‹በውጭ ጸሐፊዎችም ሆነ በአገራችን በተለይ ቀደምትጸሐፊዎች፣በኩሽ ላይ ብቻ ሳይሆን፣ ስለኢትዮጵያ ሕዝብማንሳት፣ባህና ታሪክ/ቅድመ ታሪክ በስፋት የተሠራጨው ትረካየተስተካከለ ነው ማለት አይቻልም፡፡ ይልቁንም በኢትዮጵያዊያን ጸሐፍት በተደረጉ ሥራዎች በከፊል የሚታየው የእርስ በርስየመጣረስ ችግር ነገሩን በውል ሳያጤኑ ከተዛባና አንዳንዴምበዘረኝነት መርዝ ከተቀባ የውጭ ሥራዎች ከመገልበጥ የመጣነው፡፡

‹‹ከላይ የጠቀስናቸው ሥራዎች ከወጡ በኋላ፣ በሥነ ልሳን ዘርፍበርካታ እመርታዎች ተካሂደዋል፡፡ በሥነ ሰብ፣ ሥነ ማኅበረሰብና በታሪክ ዘርፎችም እንዲሁ፡፡ በእነዚህ ዘርፎች የተደረጉምርምሮች አመርቂ ደረጃ ላይ የደረሱ ናቸው ባይባልም፣ ከበፊቱበተሻለ ስለቋንቋዎቹና ስለሕዝቡ ግንዛቤ አሁን አለን፡፡

.

ይሁንእንጂ፣በአገራችን ከዘመናችን ባሉት አዳዲስ ጥናቶች የታዩግኝቶች ጋር እኩል በመሄድ የማስተማሪያ መጻሕፍቶቻችን ሲታደሱ ብዙም አይስተዋልም፡፡ ይህ የሚከተለውን የኪዳነ ወልድ ክፍሌን ቃል ያስታውሰናል፤‹‹ሀገራችንና ቋንቋችን ያረገዙትን ለመውለድ፣ ወልዶምለማሳደግ፣ ሐኪምና ጊዜ አላገኙም፤ የተወለደውም ትምርታችን ወላጆቹና ሞግዚቶቹ ታርደው፣ ተሰደው ስላለቁ እንደ ሙት ልጅሆኖ ከመጫጨትና ከመመሥጨት በቀር እያደገና እየሰፋ፣እየፋፋ መሄድ አልቻለም፡፡

‹‹አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ከዛሬ ምዕት ዓመት በፊት አካባቢያሉት አሁንም የተለወጠ አይመስልም፡፡ በየሙያው በአገራችንያለን የሰው ኃይል ከቁጥር የማይገባ ብቻም ሳይሆን፣ ያለውየኢኮኖሚክ ሁኔታና የምሁሮቻችን ዝግጅት በሰል ያለ ጥናትለማድረግ የሚያስችል ደረጃ ላይ አይደለም፣ ያሉት ከኢኮኖሚክ ችግሩ በላይ በፖለቲካው እየተገፉ በየሰው አገር ተበትነውለመኖር የተገደዱበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ ይህን ሥራ ያዘጋጀ ነውከላይ ያሉትን ችግሮች በማሰብ ነው፡፡ የታሪካዊ ሥነ ልሳንናየዓይነታዊ ሥነ ልሳን ሥራዎችን፣ እንዲሁም ወቅታዊ የታሪክናየሥነ ሰብ ግንዛቤዎችን ከሥር ከሥሩ እየተከታተሉ የማስተማሪያመጽሐፎቻችን መታደስ እስከሚችሉ ለመነሻ ግንዛቤ እንዲሆን በማሰብ ነው፡፡

.

#ሀበሻ

‹‹ሀበሻ ኢትዮጵያዊ ከሚለው ቃል ይልቅ በአጠቃቀም በኅብረተሰቡ ዘንድ ሥር የሰደደ ነው፡፡ በርካታ አገራዊ (ቁሳዊናሐሳባዊ) ባህሎች በዚህ ቃል ቅፅልነት ሲገልጹ ይስተዋላል፡፡

ለዚህ አስረጅ፣ የሀበሻ ዶሮ፣ የሀበሻ ጎመን፣ የሀበሻ መድኃኒት፣ የሀበሻ ኩራት፣ የሀበሻ ተንኮል፣ የሀበሻ ምቀኝነት፣ ወዘተየሚሉትን አጠቃቀሞች መጥቀስ ይቻላል፡፡ ሀበሻ የሚለው ቃልከህንድ እስከ አውሮፓ መላው ዓለም ኢትዮጵያን ለመግለጽሲጠቀሙበትም ቆይቷል፡፡ በህንድ፣ በፓኪስታንና በአጎራባች አገሮች ሀበሽ የሚባሉ በጀግንነታቸው የተመሰገኑ ከአካባቢያችንየሄዱ ሕዝቦችም አሉ፡፡

‹‹በአሁኑ ወቅት በውጭው አገር ኢትዮጵያዊውና ኤርትራዊውመሰሉን ሲያይ ‹‹ሀበሻ ነህ?›› የሚል ጥያቄ ያቀርባል፡፡ ይህንቃል ኢትዮጵያዊ የመሰለውን ሰው ለመተዋወቅ ከአጎራባችአገሮች በተለይ ከሶማሊያ የመጡም ሲጠቀሙበት ይስተዋላል፡፡ ይሁን እንጂ ሀበሻ የሚለው ቃል የተለየ ፖለቲካዊ ትርጉምሰጥቶትም ይገኛል፡፡

#ሀበሻና_ሴም

‹‹ሀበሻ የሚለውን ቃል ከሴማዊ ቋንቋ ተናጋሪዎች ጋርየማገናኘት ሁኔታ ታሪካዊ መረጃ እንደሌለው ቢገለጽም፣በአሁኑጊዜ በተለይ በአገራችን ተደጋግሞ ሲሰማ ይስተዋላል፡፡

በእግረ መንገድ ይህን ቃል የሚያነሱ ሥራዎችም ይህንኑ ሲደግሙት ይስተዋላል፡፡ ለምሳሌ ሚረን የቀይ ባህር ዜጎች በሚለውመጽሐፉ ሀበሻ የሚለውን ቃል በሙዳየ ቃላት የበየነውበኢትዮጵያና በኤርትራ ደጋማ ቦታዎች የሠፈሩ ሴማዊ ቋንቋተናጋሪ ሕዝቦችን የሚመለከት እንደሆነ ነው፡፡

‹‹ሀበሻና ሴምን የማገናኘት ጉዳይ በኅብረተሰቡ ዘንድ በስፋትእንዲሠራጭ ያስቻለው በየትምህርቱ ቤቱ ሲሰጥ የነበረ ታሪክይመስላል፡፡ ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ሲሰጥ የነበረው በጣምየተለመደው መላምት ሴማዊ ሕዝቦች ከደቡብ ዓረቢያ ወደ ኢትዮጵያ ተሻግረው መጡ የሚል ነው፡፡

‹‹በዚህ ጉዳይ ቀደምት ሥራዎች ውስጥ ኢዮብ ሉዶልፍ ሊጠቀስይችላል፡፡ የመጡበትም ጊዜ በአብዛኛው ከ1,000 እስከ 500 ቅጋአ (ቅድመ የጋራ አቆጣጠር) ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ለዚህመላምት ሥር መስደድ በግንባር ቀደምትነት ከሉዶልፍበማስከተል ከሚጠቀሱት ውስጥ አንደኛው ኮንቲ ሮሲኒ ናቸው፡፡

እነ ተክለ ፃዲቅ መኩሪያ በዚሁ በወቅቱ አሳማኝ መስሎ በታየውመላምት ላይ ተመርኩዘው የማስተማሪያ መጻሕፍት በማዘጋጀት፣ሐሳቡን ወደ ትምህርት ቤት አወረዱት፡፡ ታደሰ ታምራትም ታላቅ ናቸው ብሎ ያሰባቸውን እነ ኮንቲ ሮሲኒን ሐሳብ እንዳለ ተቀብሎአጠቃላይ የኢትዮጵያን ታሪክ የሴማዊ ሕዝቦች መስፋፋትአድርጎ ማቅረቡ ለአመለካከቱ ሥር መስደድ ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል ማለት ይቻላል፡፡

በቀዳሚዎቹ ምዕራፎችእንደገለጽነው፣እንደእነዚህ ጸሐፊዎች እምነት ወደ ኢትዮጵያመጡ ከሚባሉት የሴም ነገዶች ውስጥ ዋና ዋናዎቹ ነገደሐበሽትና ነገደ አግዓዚ የተሰኙ ናቸው፡፡ ነገደ ሐበሸት ስሙን ለሕዝቡ መጠሪያ ሲያሳልፍ ነገደ አግዓዚ ደግሞ ቋንቋውንተወልን፡፡

‹‹በዚህ ሥር በሰደደ መላምት ሀበሻ ከሀበሸት፣ ግዕዝ ደግሞከአግዓዚ ከሚሉት ቃላት የመጡ ናቸው፡፡ ግዕዝም ከሳባበቀጥታ የመጣ ነው የሚለውን የግምት አነጋገር የእኛዎቹእንዳለ ተቀብለውት በትምህርት ቤት ማስተማሪያዎች ውስጥ ይሰጥ ነበር፤ ‹‹ይህ ግዕዝኛ አነጋገር የመጣ ከክርስትና በኋላነው እንጂ የፊተኛው አነጋገርና ጽሑፍ ቀድሞ በደቡብ ዓረብ ሳሉየሚጽፉበትና የሚነጋገሩበት የሳባ ቋንቋ ነው፡፡ ይኼም የሳባ ፊደልና ቋንቋ ለግዕዝ እንደ አባት የሚቆጠር ነው፡፡ የዚህመላምት ቅርሻ እስካሁን ላለው በኅብረተሰቡ ዘንድ ለተስፋፋውየተሳሳተ አስተያየት መሠረት የሆነ ይመስላል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሥነልሳን ፕሮፌሰር ዘለዓለም ልየውስለ መጽሐፉ በሰጡት አስተያየት፣ ዶ/ር ግርማ የኢትዮጵያንሕዝቦች ማንነትና ታሪካዊ አመጣጥ ከቋንቋ አንፃር ተንትኖያቀረቡባቸው መረጃዎች በታሪካዊና ንጽጽራዊ ሥነልሳን ዘዴዎች ተቀነባብረው በመቅረባቸው ስለኢትዮጵያ ቋንቋዎች እና ተናጋሪዎቻቸው ያለንን ዕውቀት ለማሳደግ በእጅጉ ይረዳልብለዋል።

‹‹ከበቂ መረጃ ጋር አብዛኛዎቹ የኢትዮጵያ ሕዝቦችና ቋንቋዎችምንጫቸው አንድ መሆኑን እንረዳለን። የተናጋሪዎች ለብዙዘመናት ተራርቆ መኖር ከአንድ ቤተሰብ የተገኙ ቋንቋዎችንሊያለያይ እንደሚችል ሁሉ፣ ለብዙ ዘመናት አብሮ በመኖር የተነሳከተለያዩ የቋንቋ ቤተሰቦች የተገኙ ቋንቋዎች ደግሞ በቋንቋ ባህርያትና በሌሎችም እሴቶች እየተመሳሰሉ ሊሄዱ እንደሚችሉ በውል ያስገነዝባል፤››በማለትም በመጽሐፉ ላይ አስፍረዋል፡፡

ግርማ አውግቸው ደመቀ በስነልሳን የዶክተሬት እና በመረጃ መረብ ደህንነት የማስተርስ ኦፍ ሳይንስ ዲግሪዎች አሏቸው። በቅርቡ በአማርኛ ካሳተሟቸው ስራዎች መሀከል ቋንቋና ነገድ በኢትዮጵያ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ማንነትና ቅድመታሪክ ከቋንቋ አንፃር፣ ቅፅ አንድ (2018 እአአ)፣ ቋንቋና ነገድ በኢትዮጵያ፣ ቅፅ ሁለት (2018 እአአ)፣ እና የኢትዮጵያ ዘመን አቆጠጠር (2016 እአአ) ይገኙበታል።

Kush/Cush and Cushitic: Language, History, Race, and Religion offers a multifaceted examination of the term “Kush/Cush” and its related concepts, drawing from historical, linguistic, and cultural perspectives. In the realm of historical linguistics, “Cushitic” is employed to describe a hypothetical language family within the Afroasiatic phylum. This term may also be used to refer to the people who speak these languages.

However, there is often confusion between this academic usage and the ancient kingdom of Kush, which is frequently referred to Nubia in historical works. The confusion extends to the usage of the same term in Biblical texts. The book delves into the history of the Kingdom of Kush, the Biblical usage of Kush/Cush, and the so-called Cushitic languages, offering a nuanced discussion of these intertwined topics.

Girma A. Demeke holds a PhD in linguistics. His notable publications

include The Origin of Amharic (2nd Edition, 2013), Grammatical Changes in

Semitic: A Diachronic Grammar of Amharic (2014), Argobba Speech Varieties

(2015), The Ethiopian Calendar (2016), the two-volume work Language and

Identity in Ethiopia (2018), and The Syntax of Nominal Clauses: Amharic

Infinitives (2023).