የጣሊያን እና የኢትዮጵያ መንግስት ስምምነቶች
==========================
በጣሊያን እና በኢትዮጵያ ሶስት ግዜ የድንበር ስምምነት ተፈራርመዋል። በ1900፣ በ1902፣ በ1929 የድንበር ሰነዶች ዝርዝር ከጣሊያን ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ከመዝገብ ክፍል የተገኘ እንመለከት
1) 1900 ዓ.ም. የውሽሌ (Wuchale) ስምምነት ፋይል pcacases.com – chapter iv – 1900 treaty https://pcacases.com/web/sendAttach/899
2) 1902 ዓ.ም አባላት ድንበር ስምምነት ፋይል PCACases.com 1902 Treaty, Western https://pcacases.com/web/sendAttach/899
3) 1929 ዓ.ም. አንግሎ-ኢትዮጵያ-ጣሊያን ስምምነት (Anglo-Ethiopian-Italian Agreement)
ኢትዮጵያ ከጣሊያን መንግስት ጋር ባደረገቺው ሶስት ስምምነቶች ውስጥ በምስራቅ በኩል የኤርትራ ግዛት ጎልፍ ዙላ ላይ ይቆማል (Golf Zula) የኤርትራ የመሸረጫ ግዛት ተደርጎ ስምምነት የተደረገበት golf zula ሲሆን ከቀይ ባህር ጠረፍ ጀመሮ ወደ ውስጥ 60km እንዲገባ ስምምነት ተደርሷል። ማለትም ከጎልፍ ዙላ ቀይ ባህር ተነስቶ ወደ ውስጥ 60 KM እንዲገባ ተደርጓል።
በኢትዮጵያ እና በጣሊያን መንግስት መሃከል አሰብ ግዛት በተመለከተ ምንም አይነት ስምምነት የተፈራረሙት የለም። በጣሊያን ምክር ቤት የጸደቀው የአሰብ ካርታ እንደሚያሳየው ከሆነ በሰረዝ ሰረዝ ቀለም ተቀብቶ የኢኮኖሚ ዞን ብሎ አስፍሮ የኢትዮጵያ ግዛት እንደሆነ ይቀበላል። በተረፈ በአሰብ ግዛት ላይ በሁለቱ መንግስታት መሃከል የተደረገ ስምምነት የለም። ጣሊያን በሁለተኛ አለም ጦርነት ወቅት ዳግም ወደሃገራችን ለወረራ ሲመጣ ያንኑ የኢኮኖሚክ ዞን አስተዳደር ቀጥሏል እንጂ ወደ ኤርትራ አስተዳደር ያጠቃለለው አዲስ ስምምነት እና በጣሊያን ምክር ቤት የጸደቀ ምንም አይነት ሰነድ የለም።
ባጭሩ አሰብ ግዛት በኤርትራ ስር የሚያደርግ ምንም አይነት ህጋዊ በመንግስታት መሃከል የተፈረመ ስምምነት የለም። ከጣሊያን ምክር ቤት ጸድቀው የወጡ ህጎች እና ውሎች የተሰበሰቡ ሰነዶች የሚያሳዩት ሃቅ ይሄኑኑ ነው።
ዋና ዋና ነጥብ ያዙ
===========
1) አሰብ ያለ ምንም ጩህት እና ኳኳታ ለኢትዮጵያ መመለስ ትክክለኛ ውሳኔ ይሆናል። የቅኝ ግዛት ህጎች ብንመለከት በእኛ ጎን ነው። የ1908 ከጣሊያን ጋር ያደረግነው ስምምነት አሰብ የኤርትራ ግዛት ነው አይልም። የኤርትራ ግዛት የሚቆመው ጎልፍ ዙላ ላይ ነው።
2) የአፍሪካ አንድነት ድርጅት Uti Possidetis Juris (OAU 1964 Principle) መሰረት ኤርትራ የጎልፍ ዙላ ግዛት ድረስ ህጋዊ መብቷ ተከብሮ 300 km የአሰብ ግዛት ለኢትዮጵያ መመልስ ህጋዊ ይሆናል።
3) 1950 UN Resolution 390(V) (Eritrean Federation) አሰብን ብቻ ሳይሆን ምጽዋን ጭምር በጋራ ከኢትዮጵያ ጋር ማስተዳደር መብት ይፈቅዳል ሁኖም ግን አሰብ ለኤርትራ ግዛት የሚል ምንም አይነት ቃላት ሆነ ፊደል የለውም። አሰብ የኢትዮጵያ ግዛት እንደሆነ ሙሉ ለሙሉ ተቀብሏል።
4) 1993 ኤርትራ ከኢትዮጵያ ስትለይ በሁለቱ መንግስታት መሃከል ምንም አይነት የጸደቀ ስምምነት የለም። የአሰብ አስተዳደር ብቻ ሳይሆን የኤርትራ ድንበር በምክር ቤት የጸደቀ ውል የለም። በመንግስት ደረጃ የተደረገም ስምምነት የለም።
5) Vienna Convention on the Law of Treaties (1969) መሰረት አሰብ ሆነ የኤርትራ ግዛት ጥያቄ ማቅረብ ኢትዮጵያ ሙሉ መብት አላት።
******************
ከላይ የዘረዘርኳቸው ዋና ዋና ነጥቦች እና ኤርትራ በቅኝ ግዛት ውል እና ሌሎች ህጋዊ የመንግስታ የደብዳቤ ውልልጥ ደምረን አሰብ አውራጃን 300 Km የቀይ ባህር ክልል ከእነ ሙሉ ክብሩ ለኢትዮጵያ መመለስ ህጋዊም፣ ፍትሃዊ ይሆናል። በአለም ላይ የጸደቁ ህጎች እና ስምምነቶች እንዲሁም አለም አቀፍ ህጎች የሚደግፉት ማስረጃ ያለው ፍጥጥ ያለ ሃቅ ነው እናም አሰብ አውራጃ በፍቅር ይመለስልን።

