
ወሎ/ምሁራን/ፔጅ/Kallu Scholars Page/ ·Follow
☞ከሙሃመድ ጀማል የተሰጠ ሂስ “ከቤተ አምሓራ አስከ ወሎ በሚለው መፅሀፍ ውስጥ ያሉት የታሪክ ስህተት![]()
#① “ከቤተ አምሓራ እስከ ወሎ” ከሚለው የመፅሐፉ ስያሜ ስነሳ ቤተ አምሓራ የምትባለው ባንድ ወቅት ደቡብ ወሎ ውስጥ የነበረች የቦታ ስያሜ ሰፊው የወሎ ግዛት ጋር ትይዩ (equate) ተድርጎ መቅረቡ ስተት ነው። ምንም እንኳ ቤተ አምሃራ ማለት ወሰኗ ከአሁኑ ከደቡብ ወሎ ዞን ብዙም የማታልፍ መሖኗን በመፀሐፉ ቢገለፅም መፀሐፉ በአጠቃላይ የተቃኘው ቤተ አምሓራ የወሎ የድሮ ስሙ በሚመስል መልኩ ነው። ነገር ግን ቤተ አምሓምራ በደቡብ ወሎ ውስጥ የነበረች ቦታ ስትሆን ወሎ ደግሞ 12 ክፍለሀገራት የነበሩት ሰፊ ግዛት ነው። በተጨማሪም እንዴ አንጓትና ዶባ የመሳሰሉ ወሳኝ የወሎ ጥንታዊ ስሞች ትኩረት ተነፍጓቸዋል። አማራ ሳይንት፣ ላስታ፣ ዋግ፣ ዋድላደላንታ የመሳሰሉ ቤተ አምሓራ ጋር አብረው የተጠቀሱ በወሎ ውስጥ የነበሩ ጥንታዊ ስሞች ቢሆኑም በመፀሐፉ ትኩረት ተነፍጓቸዋል። በተለይ አምሓራ ሳይንትና ቤተ አምሓራ ባንድ ወቅት የነበሩ ስሞች መሆናቸውን ቢገልፅም የሁለቱ ግዛቶች ግንኙነት በግልፅ መፀሐፉ አላስረዳም። ብዙ ሰው ቤተ አምሓራ እና አምሐራ ሳይንትን እያፈራረቀ ይጠቃማል። ነገር ግን ስተት ነው። ደራሲው የአምሓራ መነሻ ቤተ አምሓራ ነው ወይንስ አምሓራ ሳይንት የሚለውን በግልፅ ማስቀመጥ ነበረበት።
#② ሁለተኛ የማነሳው ጥያቄ ይህ መፀሐፍ በልማድ ከሚፃፉ የታሪክ መፀሐፍ በምን ይለያል የሚለውን ሀሳብ ነው።
ሌሎች የታሪክ ፀሐፊዎች የድሮ መፀሐፎቻቸውን ኢድት እያደረጉ እያስተካከሉ ባሉበት ሰዓት ደራሲው ከአንድ ፕሮፌሽናል ታሪክ ፀሐፊ የማይጠበቁ አገላለፆችን ተጠቅሟል።
ለምሳሌ ገፅ 76 ላይ የአህመድ ግራኝ ወረራ፣ የኦሮሞ ወረራ፣ በገፅ 81 ላይም የአህመድ ግራኝ ወረራ፣ የግራኝ ወረራ የሚሉ አገላለፆችን ተጠቅሟል። ደራሲው በዚሁ መፀሐፍ ገፅ 117 ላይ የኢማም አህመድን ዘመቻ ወረራ ማለት አይቻልም ሲል ከላይ የፃፈውን የራሱን ሀሳብ ተቃውሟል። ከዚህም በተጨማሪ በብዙ ቦታ ሰሚታዊ ሆኖ የፃፋቸው ነገሮች በስፋት ይንፀባረቃሉ። ለምሳሌ 175 ላይ “…የፓለቲካ አላማን ማስፈፀሚያ የራስን ርዕዮት ለማጉላት ብቻ ሲባል በተረኛ ፓለቲከኞች የተሰነዱ ልቦናዊ ሰነዶች…” የሚል አገላለፅ ተጠቅሟል። ይህ ደግሞ ደራሲው እንደ ታሪክ ሙያ ገልተኛ ነው እንደ ፓለቲከኛ ወገንተኛ? የሚለውን ጥያቄ እንድናነሳ ያደርጓል። በተጨማሪው መፀሐፉ በሁሉም ወገን ተዓማኝነትን አግኝቶ እንደ ማጣቀሻ እንዳይውል ያደርገዋል።
በሚቀጥለው ክፍል ስለ የታሪክ ምንጭ አጠቃቀሙ ሳነሳ በሰፊው የማነሳው ሆኖ በአጠቃላይ መፀሐፉን በልምድ ፀሐፍያን ከተፃፉ መፀሐፍቶች የሚለየው ነገር ብዙም አልታየኝም።
#③ ከገፅ 113 እስከ ገፅ 124 የእስልምና በወሎ መስፋፋትን በሰፊው ከኢማም አህመድ አገዛዝ ጋር ለማያያዝ ሞክሯል። ይህ ደግሞ በሚከተሉት ምክናየቶች ስተት ነው።
¹ ኢማም አህመድ ከምጣቱ በፊት እስልምና በወሎ ውስጥ ተስፋፍቷል ብቻ ሳይሆን ገንግኖ የመንግስት ስርዓት ጭምር መስርቶ ነበር። ለምሳሌ በ10ኛው ክፍለ ዘመን የተመሰረተው የሸዋ ሱልጣኔትም ሆኖ በኋላ የሸዋ ሱልጣኔትን የተካው የኢፋት ሱልጣኔት መዓከላቸው ሸዋ ቢሆንም የአሁኗን ደቡብ ወሎን ያካትቱ ነበር። ለዚህም የሾንኬ የኢልም ማዕከል ዛሬም ቆሞ ምስክርነት እየሰጠ ነው። ምንም እንኳ ደራሲው በወሎ የእስልምና መስፋፋትን ከኢማም አህመድ ጋር ቢያይዘውም ከኢማም አህመድ ዘመቻ በፊት ወሎ ላይ እስልምና በሚገባ ተስፋፍቶ መንግስታዊ ቅርፅ ይዞ ነበር።
² ኢማም አህመድ ከወሎ ይልቅ የቆየው በሸዋ ነበር። ማዕከሉም ደምቢያ ነበረች። በመሆኑም የኢማም አህመድ ዘመቻ እስልምናን ለማስፋፋት ቢጠቅም ኖሮ እስልምናን የሚቀበሉት ከወሎ ይልቅ ሸዋ፣ ጎጃምና ጎንደር መሆን ነበረባቸው። በኢማሙ አገዛዝ ለረጅም ግዜ በኢማሙ አገዛዝስር የነበረው ሸዋ ክርስትናውን ይዞ ተቀምጦ፣ የኢማሙ ማዕከል የነበረችው ደንቢያ እስልምናን ሳትቀበል ጠንካራ የክርስትና አስተምሮ በነበረበት ቤተ አምሓራ እንደት በኢማሙ ዘመቻ እስልምናን ተቀበለ የሚለው ነገር ሌላው ደራሲው የዘነጋው ነገር ነው። በኢማም አህመድ እስልምናን የተቀበሉ፣ በአፄ ዩሐንስ ዘመን ክርስትናን እንድቀበሉ የተገደዱ ግለሶቦች ባመዛኙ ወደነባሩ ሀይማኖታቸው ተመልሰዋል።
በአጠቃላይ የወሎን እስልምና ከኢማሙ ዘመቻ ጋር ማያያዝ እስልምና በወሎ ያለውን ሚና ማሳነስ ነው።
ክፍል ሶስት ወሳኙ ነጥብ ይቀጥላል….
