Wollo Addis

#ሸር ”ኢሕአፓ የአማራ የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ ጠየቀ” በማንነታቸው ብቻ በግፍ እስር ላይ የሚገኙ የአማራ ተወላጆች በአስቸኳይ እንደፈቱ ኢሕአፓ ጠይቋል?

የኢሕአፓ ዋና ጸሐፊ ሚስጥረሥላሴ ታምራት እና የኢሕአፓ ሕዝብ ግንኙነት ሓላፊ ይስሀቅ ወልዳይ በዛሬው ዕለት በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የሚገኙ የፖለቲካ እና የማንነት እስረኞችን ጎብኝተዋል።

በዚህም ለአመታት በግፍ እስር ላይ የሚገኙትን ዮሀንስ ቧያለው፣ ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው፣ ክርስቲያን ታደለ፣ ሲሳይ አውግቼው(ረ/ፕ)፣ ቴዎድሮስ ኃይለማርያም (ዶ/ር)፣ ወንድወሰን አሰፋ(ዶ/ር)፣ ጫኔ ከበደ (ዶ/ር)እና ካሳ ተሻገርን (ዶ/ር) ጠይቀዋል።

እነዚህ በስም የተጠቀሱትም ሆነ ስማቸው ያልተገለጹ የፖለቲካ፣ የማንነት እና የህሊና እስረኞች ለሀገር እና ለወገን እየከፈሉ ያለው ዋጋ እጅግ ከባድ ነው።

ኢሕአፓ ለፖለቲካ እና ለማንነት እስረኞቹ ያለውን ጽኑ አጋርነት እየገለጸ መንግስት በአስቸኳይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈታቸውም ያሳስባል።

የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶችና ዓለም ዓቀፉ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብም የግፍ እስር እንዲቆም መስራት ይጠበቅባቸዋል።

ዋጋ እየከፈሉለት ያለው የኢትዮጵያ ሕዝብም ከእነርሱም ሆነ ከቤተሰባቸው ጎን በመቆም ውግንናውን በተግባር ሊያሳያቸው ይገባል ስንል ጥሪ እናቀርባለን።

Via – ኢሕአፓ