ዳታን በመቆጠብ ጽሑፍ ብቻ ለማንበብ

የቬንዚዌላ ፕሬዚዳንት ኒኮላስ ማዱሮ (በስተግራ) እና መከላከያ ሚኒስትር ቭላድሚር ፓድሪኖ ሎፔዝ (በስተቀኝ)
የምስሉ መግለጫ,የቬንዚዌላ ፕሬዚዳንት ኒኮላስ ማዱሮ (በስተግራ) እና መከላከያ ሚኒስትር ቭላድሚር ፓድሪኖ ሎፔዝ (በስተቀኝ)

3 ጥር 2026, 13:56 EAT

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዋሽንግተን “ቬንዙዌላ ላይ ሰፊ ጥቃት” መፈፀሟን እና መሪውን ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮን እና ባለቤታቸውን መያዟን አስታወቁ።

ትራምፕ በትሩዝ ማኅበራዊ የትስስር ገጻቸው “ዩናይትድ ስቴትስ ውጤታማ የሆነ ሰፊ ጥቃት በቬንዙዌላ እና በመሪዋ ላይ ፈፅማለች። ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ ከባለቤታቸው ጋር ተይዘው ከአገሪ ውጭ እንዲወጡ ተደርጓል” ብለዋል።

በአሜሪካ የቢቢሲ አጋር የሆነው ሲቢኤስ የአሜሪካ ፀረ ሽብር ጦር ፕሬዚዳንቱን እና ባለቤታቸወን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ዘግቧል።

ትራምፕ በማኅበራዊ ድረገጻቸው ላይ “ተልዕኮው በአሜሪካ የህግ ማስከበር መሰረት ተካሂዷል። ዝርዝሮች መውጣታቸውን ይቀጥላሉ. . . በማለት በመኖሪያ ቤታቸው መግለጫ እንደሚሰጡ ጠቅመዋል።

የቬንዙዌላ መንግሥት እስካሁን የፕሬዝዳንቱን መያዝ በሚመለከት ማረጋገጫ አልሰጠም።

አሜሪካ ቬንዚዌላ ላይ ጥቃት የፈጸመችው ለሊቱን ሲሆን አገሪቱን ለረዥም ጊዜ ያስተዳደሩትን ኒኮላስ ማዱሮን በቁጥጥር ሥር ማዋሏን ተናግራለች።

አሜሪካ ላለፉት ጥቂት ወራት የቬንዚዌላው ፕሬዚዳንቱ በአደንዛዥ ዕጽ ዝውውር እና ሕገወጥ በሆነ መልኩ ሥልጣንን በመያዝ ስትከስ ነበር።

ዋሺንግተን በላቲን አሜሪካ እአአ በ1989 ወታደራዊውን ፕሬዚዳንት ማኑኤል ኖሪዬጋን ከሥልጣን ለማውረድ በፓናማ ወረራ ከፈጸመች ወዲህ በቀጥታ ጦሯን አሳትፋ አታውቅም።