ዳታን በመቆጠብ ጽሑፍ ብቻ ለማንበብ

የደም ናሙና የያዘ የሕክምና ባለሙያ

9 ጥር 2026, 06:58 EAT

በሕንድ በዘር የሚተላለፍ የነጭ ደም ሕዋስ እክል ታላሴሚያ (thalassemia) ያለባቸው ልጆች ለኤችአይቪ መጋለጣቸው ወላጆችን ልብ በእጅጉ ሰብሯል።

ልጆቹ በሕይወት እንዲቆዩ በሚያስላቸው የደም ልገሳ ምክንያት ነው በኤችአይቪ ኤድስ የተያዙት።

የደም ማነስን ለመግታት እና ሕይወትን ለማስቀጠል ለልጆቹ ደም ሊሰጣቸው ይገባል።

የሕንድ ማዕከላዊ ግዛት ማዳያ ፕራዴሽ ባለሥልጣናት እንዳሉት፤ አምስት ህመሙ ያለባቸው እና ዕድሜያቸው ከሦስት እስከ 15 የሆኑ ልጆች ኤችአይቪ በደማቸው ተገኝቷል።

ስለ ደም ልገሳ ጥያቄ በመነሳቱም መርማሪ ኮሚቴ ተዋቅሯል።

ወላጆቹ የሚኖሩት በሳንታ ግዛት ነው። ልጆቹ በደማቸው ውስጥ ኤችአይቪ እንዳለ የታወቀው ባለፈው ዓመት ከጥር እስከ ግንቦት በተደረገላቸው መደበኛ ምርመራ ነው።

ከዚህ ቀደም በምሥራቃዊ ሕንድ ጃራካንድ ግዛትም ተመሳሳይ ነገር ተከስቷል። ዕድሜያቸው ከስምንት ዓመት በታች የሆነ አምስት ታዳጊዎች በመንግሥት ሆስፒታል ደም ተሰጥቷቸው ለቫይረሱ መጋለጣቸው ተገልጿል።

ኤችአይቪ በግብረ ሥጋ ግንኙነት፣ ከእናት ወደ ልጅ እንዲሁም ጥንቃቄ በጎደለው የሕክምና አሰጣጥ ከሰው ወደ ሰው ይተላለፋል። የደም ልገሳም በዚህ ውስጥ ይካተታል።

ኤችአይቪ የዕድሜ ልክ የጤና ክትትል የሚያስፈልገው ህመም ነው። በሕንድ ከ2.5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን፤ በየዓመቱ 66 ሺህ በላይ ሰዎች በህመሙ ይያዛሉ።

ከ1.6 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የዕድሜ ልክ ሕክምና (antiretroviral therapy ወይም ART) እየተከታተሉ እንደሆነ የመንግሥት መረጃ ያሳያል።

የሳንታ ግዛት አመራር ሳታሽ ኩማር ኤስ እንዳሉት፤ አምስት ልጆች በተለያዩ ቦታዎች እና ከተለያዩ ደም ለጋሾች ደም ተሰጥቷቸዋል።

በዚህ ውስጥ የመንግሥት ሆስፒታሎች እና የግል የሕክምና ተቋማትም ይገኙበታል። ልጆቹ አሁን ሕክምና እየተደረገላቸው ይገኛል።

የሦስት ዓመት ታዳጊ እናት እና አባት ቫይረሱ እንዳለባቸው ሲገለጽ፤ የተቀሩት ወላጆች ግን ኤችአይቪ አልተገኘባቸውም።

ይህም ከእናት ወደ ልጅ ቫይረሱ እንዳልተላለፈ ያሳያል።

የሳንታ የሕክምና ኃላፊ ዶ/ር ማኖጅ ሻኩላ እንዳሉት፤ የተለያየ የደም ልገሳ የተሰጣቸው ልጆች የበለጠ ለኤችአይቪ ተጋላጭ ሆነዋል።

“ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ እንደተገኘ ወደ ሕክምና በአፋጣኝ እንወስዳቸዋለን” ብለዋል።

ዶክተሩ እንዳሉት የሚለገስ ደም ምርመራ ከተደረገለት በኋላ ለህሙማን ይሰጣል።

“ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ሕክምናውን ወዲያውኑ እንዲጀምሩ ተደርገው እንዲቀጥሉ ይደረጋል። በአሁኑ ጊዜ የልጆቹ ጤና በደህና ሁኔታ ላይ ይገኛል።”

ሆኖም ግን ኤችአይቪ ወደ ደማቸው ከገባ ብዙም ያልቆየ ሰዎች ደም ሲመረመር የቫይረሱን መኖር የሚያሳይ ምልክት ላይስተዋል ይችላል።

የሕንድ ሆስፒታል