Shenkut Ayele Page

 ·

የፋኖ-ሀይላት ሁላችሁ እንኳን ደስ አላችሁ:- የመሰረት ድንጋዩ ተጥሏል

==================

ሸንቁጥ አየለ

==========

ለመላው የአማራ ፋኖ-ሃይሎች እንኳን ደስ አላችሁ። ይህ ትልቅ እና የመጀመሪያ ደረጃ እርምጃ ነው:: ምክንያቱም መለያየት እያንዳንዱን ፍትሃዊ ትግል የሚያዳክም ሲሆን ህበረት እና አንድነት ደግሞ የድል ቁልፍ ነዉ::

————-

የፋኖ-ሀይል የተነሳበት አላማ ፍትሃዊ መሆኑን አለም ያውቃል:: ይሄዉም የአማራን የህልውና ስጋት መቅጨት እና በአማራ ላይ እየተከናወነ ያለዉን የዘር ማጥፋት ወንጀል ስርን ነቅሎ በሳት ማቃጠል ::

———

አሁን የፋኖ-ሀይል ባከናወነዉ የአንድነት ሂደት ዉሳኔ ዉስጥ የመድሃኒአለም እጅ አለበት ብዬ አምናለሁ:: ይሄም ለተወሰነ ወገን ለድል ብቻ ሳይሆን በጠቅላላ የኢትዮጵያዉያንን ህይወትን ለመጠበቅ እና ወደ ነጻ ኢትዮጵያ የሚወስደውን መንገድ መሰረት ለመጣ : መላዉ ኢትዮጵያዉያን ነገዶችን በማስተባበር የህግ የበላይነት፣ ፍትህ እና ለሁሉም ኢትዮጵያውያን እኩልነትን የሚፈነጥቅ የተስፋ ጮራ ጥንሥ አሁን ተጠንሧል::

————

ዉህዱ የፋኖ-ሀይል በዚህ ወቅት ምን ምን ጉዳዮች ላይ ያተኩር የሚለዉን ነጥብ በጥልቀት እንደምትሄዱበት እርግጠኛ ነኝ:: በዚህ ወቅት በመላዉ የአማራ ፋኖ-ሀይላት መሀከል የተደረገ አንድነት በከፍተኛ መርህ: በዲሲፕሊን እና በተጠያቂነት እየጎመራ እና እየበሰለ እንዲሄ ሁሉንም ነገር በተቋማዊ ስርዓት እንደምታከናዉኑት ደጋፊዎቻችሁ ሁሉ ከፍተኛ ተስፋ አድርገዉ እየጠበቋችሁ መሆኑን ሁሌም ማስታወስ ይገባል:: ይሄም ማለት ከሞላ ጎደል የሚከተሉን ነጥቦች የሚያካትት ይሆናል:-

1. እርስ በርስ ፍቅርን ወንድማማችነትን እና እምነትን ማጠናከር፣

2. ሰርጎ ገቦችን መንጥሮ ማዉጣት:

3. የፋኖ-ሀይል እራሱ የሚቆጣጠረዉ ሚዲያ ፈጥኖ መመስረት:

4. በየትኛዉም የግለሰብ የሚዲያ ሀይል ላይ አለመታመን:

5. የጠላት ፕሮፖጋንዳን እየተከታተሉ ማክሸፍ እና የፕሮፖጋንዳ ስራዉን በጠላት ሀይል ላይ በማድረግ የጠላትን ወንጀል ማጋለጥ

6. በተለይም የትግሉ አጋር መስለዉ የፋኖ-ሀይላትን ከቀረቡ ብኋላ በፋኖ-ሀይላት መሃከል ጥላቻን እና አሉባልታ የሚዘሩትን የሚዲያ ሰዎች/አክቲቪስቶች/ጋዜጠኞች ያለምንም ርህራሄና ፍርሃት ማጋለጥ

7 ፋኖ ከዲያስፖራ ጋር ያለዉን ግንኙነት በተቋማዊ ስርዓአት ብቻ መምራት::እንዲሁም ዲያስፖራዉ ላይ የገቢን ምንጭ ሙሉ ለሙሉ የማድረግ አካሂያድን መለወጥ

8. እያንዳንዱ የፋኖ-ሀይል መሪ እየተነሳ ከዲያስፖራ ከግለሰቦች ጋር ግንኙነት እንዳያደርግ ጥብቅ ስርዓት መስራት:

9. የኮሚኒኬሽን ስርዓትን መዘርጋት::ይሄም ማለት ቁልፍ አመራሮች በምን አይነት መሳሪያዎች እና በምን ቅድመ ሁኔታ ነዉ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን የሚጠቀሙት የሚለዉን እና መሰል ጉዳዮችን የሚያካትት ግልጽ እና የዘመኑን የተክኖሎጅ ደረጃ የተረዳ የኮሚኒኬሽን ፖሊሲን ጭምር ማዉጣት ብቻ ሳይሆን ተፈጻሚ እንዲሆን ማድረግን ጭምር ያካትታል:

10.የፋኖ-ሀይል በሚያስተዳድራቸዉ አካባቢዎች ህዝብ እንዳይመረር ፍትሃዊ ስርዓት በመዘርጋት የሚያስመሰግን ዲሞክራሲያዊ የጥበብ አሰራርን ተግባራዊ ማድረግ

11.የፋኖ ሀይል የገቢ ምንጩን ከሚያስተዳድራቸዉ አካባቢዎች በሚገኝ ቀረጽ ላይ ብቻ ሳይወስን በመላ ሀገሪቱ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ ልዩ ልዩ የገቢ ዘርፎችን ፈጥኖ መዘርጋት ይገባዋል::

ይሄም በስርዓአት እና በዲሲፕሊን እንዲሁም እኔ አዉቃለሁ ከሚል አንባገነናዊ አካሄያድ በጸዳ የባለሞያዎች ቁልፍ ሚና በተከበረበት ሂደት እንዲከወን ማድረግ

12. በመላ ሀገሪቱ ከሚገኙ እዉነተኛ ነፃነትን እና ፍትህን ከሚሹ ሀይላት ጋር ሁሉ ጥበባዊ አጋርነትን በመገንባት እና ስልታዊ መናበብ በመፍጥር ኢትዮጵያዉያን ነገዶችን ሁሉ በማሳተፍ ትግሉን መላው ህዝብ በባለቤትነት የሚቀላቀለዉ እንዲሆን ብሎም ኢትዮጵያን ነጻ ሀገር ትሆን ዘንድ እርሾ እንዲጥል አድርጎ ስትራቴጂያዊ ንድፈ ሀሳቦችን መቀመር