በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኘውን ኃይሏን እያጠናከረች ካለችው አሜሪካ ጋር የተፋጠጡት የኢራን የጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ፤ ዋሽንግተን ቴህራን ላይ የምትፈጽመው ማንኛውም ጥቃት ቀጣናዊ ጦርነት እንደሚያስነሳ አስጠነቀቁ። የኢራኑ ጠቅላይ መሪ፤ “[ትራምፕ] በየጊዜው መርከቦችን አመጣሁ ይላል… የኢራን ሕዝብ እነዚህን ነገሮች አይፈራም” ብለዋል።

ጭምቅ ሃሳብ

የቀጥታ ሽፋን

  1. ከ 1 ሰአት በፊትኢራን በመጪዎቹ ቀናት ለአውሮፓ ኅብረት የአሸባሪነት ፍረጃ የአጸፋ ምላሽ እንደምትሰጥ ገለጸችየኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ አባላት ወታደራዊ ሰልፍ ላይየፎቶው ባለመብት,EPAየአውሮፓ ኅብረት፤ የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብን በአሸባሪነት መፈረጁን ተከትሎ ቴህራን በአገሯ ውስጥ የሚገኙ ሁሉንም የኅብረቱ አምባሳደሮች ማብራሪያ እንዲሰጡ እንደጠራች እና በመጪዎቹ ቀናት የአጸፋ ምላሽ እንደምትሰጥም ገለጸች።የኢራን መንግሥት በመላ አገሪቱ የተነሳበትን ተቃውሞ ለማፈን በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲገደሉ እና በአስር ሺህዎች እንዲታሰሩ ያደረገ እርምጃ ወስዷል። ይህንን ተከትሎም የአውሮፓ ኅብረት ባለፈው ሳምንት የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብን የአሸባሪዎች ዝርዝር ውስጥ አካትቷል።ከዚህ ቀደም እንደ አሜሪካ እና ካናዳ ያሉ አገራትም ይህንን ወታደራዊ ኃይል በአሸባሪ ድርጅትነት ፈርጀው ነበር። ይህ ዓይነቱ እርምጃ በአዛኛው ትዕምርታዊ ቢሆንም አብዮታዊ ዘቡ በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ያለው ተጽዕኖ ቀላል ባለመሆኑ የኢራን ምጣኔ ሀብትን የበለጠ አጣብቂኝ ውስጥ ይከትተዋል።ይህንን እርምጃ የተቃወመችው ኢራን ከእሑድ ዕለት ጀምሮ አምባሳደሮች መጥራት መጀመሯን የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ኢስማኤል ባግሃይ ለጋዜጠኞች መናገራቸውን አሶሺየትድ ፕሬስ ዜና ወኪል ዘግቧል። ይህ ሂደት ዛሬ ሰኞም ቀጥሎ እንደሚውልም ቃል አቀባዩ አክለዋል።ቃል አቀባዩ፤ ሊወሰዱ የሚችሉ “ተከታታይነት ያላቸው እርምጃዎች ተገምግመዋል። በርካታ አማራጮች እየተዘጋጁ ነው፤ ወደ ውሳኔ ሰጪ አካላት ተልከዋል” ብለዋል።“በመጪዎቹ ቀናት የኢራን ኢስላማዊ ሪፐብሊክ የአውሮፓ ኅብረት ለወሰደው ሕገ ወጥ፣ ኢ-አመክንዮአዊ እና እጅግ የተሳሳተ እርምጃ የሚሆን የአጸፋ ምላሽ ላይ ውሳኔ ታሳልፋለች” ሲሉም ጠቁመዋል።ከዚህም ባሻገር፤ ኢራን በአውሮፓውያኑ 2019 የወጣን ሕግ በመጠቀም ሁሉምን አውሮፓ ኅብረት ሠራዊቶች በአሸባሪነት ለመፈረጅ እያሰበች መሆኑን አገሪቱ ፓርላማ አፈ ጉባኤ ገልጸዋል።ኢራን እነዚህን እርምጃዎች እየወሰደች ያለችው ከአሜሪካ የተቃጣባት የወታደራዊ እርምጃ ስጋት እያየለ ባለበት ወቅት ነው። የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ የኢራን መንግሥት ተቃዋሚዎች በመግደሉ እና የጅምላ የሞት ቅጣት ሊፈጸም እንደሚችል በመግለጽ እርምጃ ለመውሰድ መዛታቸው ይታወቃል።የአሜሪካ ጦር “ዩኤስኤስ አብራሃም ሊንከን” የተባለው ግዙፍ የጦር መርከብ እንዲሁም በርካታ ሚሳኤል አውዳሚ መሣሪያዎችን ወደ መካከለኛው ምሥራቅ አንቀሳቅሷል።እስካሁን ድረስ ግን ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኃይል ለመጠቀም ይወስኑ እንደሆነ ግልጽ አይደለም። በመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት እንዳይነሳ እየጣሩ ያሉ የቀጣናው አገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶችን ለመፍጠር እየሞከሩ ነው።ያጋሩ, ኢራን በመጪዎቹ ቀናት ለአውሮፓ ኅብረት የአሸባሪነት ፍረጃ የአጸፋ ምላሽ እንደምትሰጥ ገለጸች
  2. ከ 4 ሰአት በፊትእስራኤል ኤምኤስኤፍ በጋዛ እንዳይሠራ ልታግድ ነውኤምኤስኤፍ በጋዛ ሰብአዊ እርዳታ ከሚሰጡ ተቋማት አንዱ ነበርየፎቶው ባለመብት,AFP via Getty Imagesእስራኤል፤ የድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን (ኤምኤስኤፍ) በጋዛ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ እንደምታግድ አስታወቀች።የተራድኦ ድርጅቱ በጋዛ ያሉትን ሠራተኞች ዝርዝር ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆኑ ምክንያት እገዳው እንዲጣል መወሰኑ ተገልጿል።የእስራኤል መንግሥት 37 ተቋማት አገር በቀል እና ዓለም አቀፍ ተቋማት በጋዛ ያሉ ሠራተኞቻቸውን የተመለከቱ ሰነዶች እንዲያስረክቡ ጠይቋል።የእስራኤል መንግሥት ከኤምኤስኤፍ ሠራተኞች የተወሰኑት ከሐማስ እና ኢስላሚክ ጂሃድ ጋር ግንኙነት አላቸው ብሎ ቢከስም ድርጅቱ ክሱን አስተባብሏል።ተቋሙ የፍልስጤማውያን እንዲሁም የሌሎች አገራት ሠራተኞቹን ዝርዝር ለእስራኤል መንግሥት እንደማይሰጥ አስታውቋል። የሠራተኞቹ ደኅንነት የተጠበቀ ስለመሆኑ ከእስራኤል ማረጋገጫ እንዳላገኘም ገልጿል።የእስራኤል መንግሥት “ኤምኤስኤፍ ሌሎች በቀጣናው እንደሚሠሩ ተቋማት የአገር ውስጥ ሠራተኞቹን ዝርዝር ለመስጠት አልፈቀደም” ብሏል።ታኅሣሥ ወር መጨረሻ ላይ እስራኤል “አዲሱን የምዝገባ ሒደት አልተከተሉም” ያለቻቸውን የ37 ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅቶችን ፈቃድ እንደምትሰርዝ አስታውቃለች።ተቋማቱ በጋዛ እና በግዳጅ ይዞታ ሥር ባለው ዌስት ባንክ ይሠሩ የነበሩ ናቸው። ከተቋማቱ መካከል ኤምኤስኤፍ፣ አክሽንኤድ እና ሮርዌጅያን ሬፍዩጂ ካውንስል የሚገኙበት ሲሆን፤ ሥራቸውን በ60 ቀናት ውስጥ እንዲያቋርጡ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸዋል።ያጋሩ, እስራኤል ኤምኤስኤፍ በጋዛ እንዳይሠራ ልታግድ ነው
  3. ከ 5 ሰአት በፊትቻይና ምያንማር ውስጥ የሳይበር ማጭበርበሪያ ካምፖችን የሚመሩ ተጨማሪ አራት ሰዎችን በሞት ቀጣችየተፈረደባቸው ሰዎች ፍርድ ቤት ውስጥየፎቶው ባለመብት,CCTVቻይና፤ ምያንማር ውስጥ የሳይበር ማጭበርበሪያ ካምፖችን ከሚያስተዳድሩ ቡድኖች አንዱ የሆነው ‘ባይ’ የተሰኘ የቤተሰብ ማፊያ ቡድን አባላት የሆኑ አራት ሰዎችን በሞት መቅጣቷን የአገሪቱ መንግሥት መገናኛ ብዙኃን ዘገበ።በሞት የተቀጡት ግለሰቦች፤ በማጭበርበር፣ በነፍስ ግድያ፣ በአካል ጉዳት ማድረስ እና በሌሎች ወንጀሎች ከተፈረደባቸው 21 የቤተሰቡ አባላት እና ግብረ አበሮቻቸው መካከል ናቸው።ባለፈው ኅዳር ላይ የቤተሰቡ መሪ የሆነው ባይ ሱኦቼንግን ጨምሮ አምስት ሰዎች በሞት እንዲቀጡ ፍርድ ቤት ወስኖ ነበር። ይሁን እንጂ የማፊያ ቤተሰቡ መሪ ከፍርዱ በኋላ ታምሞ ሕይወቱ እንዳለፈ የመገናኛ ብዙኃኑ ዘገባ ያመለክታል።በደቡብ ምሥራቅ እስያ በሚገኙት የሳይበር ማጭበርበሪያ ማዕከላት ላይ ዘመቻ የከፈተችው ቻይና፤ ‘ሚንግ’ የተባለ ሌላ የማፊያ ቤተሰብ አባል የሆኑ 11 ሰዎችን ባለፈው ሳምንት በሞት ቀጥታለች።የሞት ቅጣት ተፈጻሚ የሆነባቸው የባይ እና ሚንግ እንዲሁም ሌሎች በርካታ ቤተሰቦች የምያንማር የድንበር ከተማ የሆነችው ላውካይንግን ተቆጣጥረው የቁማር፣ የወሲብ ንግድ እና የሳይበር ማጭበርበር ተግባራት ለዓመታት ሲያከናውኑ ቆይተዋል።እነዚህ ተግባራት የሚፈጸሙባቸውን ማዕከላት ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በ100 ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በግዳጅ ሠራተኝነት ተይዘው ስቅይት እና እንግልት ሲፈጸምባቸው ነበር። ታይላንድ ውስጥ ሥራ እንደሚያገኙ ተነግሯቸው ወደ እነዚህ ካምፖች የተወሰዱ በሺህዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ባለፈው ዓመት ወደ አገራቸው መመለሳቸው ይታወሳል።ካምፖቹን ከሚመሩ ቤተሰቦች መካከል “ቁጥር አንድ” ላይ የሚቀመጠው የባይ ቤተሰብ እንደሆነ የባይ ሱኦቼንግ ልጅ በቁጥጥር ሥር ከዋለ በኋላ ለመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ተናግሮ ነበር።የቻይና መንግሥት ባለሥልጣናት እንደሚናገሩት የባይ ቤተሰቦች የራሳቸውን ሚሊሻ የሚያስተዳድሩ ሲሆን ለሳይበር ማጭበርበር እና ለቁማር የሚውሉ 41 ካምፖችን መስርተው ነበር።በእነዚህ ካምፖች ውስጥ በሚገኙ የግዳጅ ሠራተኞች ላይ ድብደባ እና ስቅይት መፈጸም የተለመዱ ተግባራት እንደነበሩም ተገልጿል። የቤተሰቡ የወንጀል ድርጊቶች ስድስት ቻይናውያን እንዲሞቱ፣ አንድ ሰው ራሱን እንዲያጠፋ እንዲሁም በርካታ ሰዎች የአካል ጉዳት እንዲደርስባቸው ምክንያት እንደሆኑ ፍርድ ቤቱ ተናግሯል።ያጋሩ, ቻይና ምያንማር ውስጥ የሳይበር ማጭበርበሪያ ካምፖችን የሚመሩ ተጨማሪ አራት ሰዎችን በሞት ቀጣች
  4. ከ 6 ሰአት በፊትየኢራን ጠቅላይ መሪ ኻሜኒ አሜሪካ ጥቃት የምትፈጽም ከሆነ ቀጣናዊ ጦርነት እንደሚነሳ አስጠነቀቁየኢራን የጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒየፎቶው ባለመብት,Iranian leader press office via Getty Imagesበመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኘውን ኃይሏን እያጠናከረች ካለችው አሜሪካ ጋር የተፋጠጡት የኢራን የጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ፤ ዋሽንግተን ቴህራን ላይ የምትፈጽመው ማንኛውም ጥቃት ቀጣናዊ ጦርነት እንደሚያስነሳ አስጠነቀቁ።ኻሜኒ፤ “አሜሪካውያኖቹ ጦርነት ከጀመሩ በዚህ ጊዜ [የሚነሳው] ቀጣናዊ ጦርነት እንደሚሆን ማወቅ አለባቸው” ሲሉ መናገራቸውን ከአገሪቱ መንግሥት ጋር ግንኙት ያለው ታስኒም የዜና ወኪል ዘግቧል።የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን “ቁም ነገር ያለው ውይይት” ላይ እንደሆነች እና ይህ ውይይት “ተቀባይነት ያለው” ውጤት ላይ እንደሚያደርስ ተስፋ ማድረጋቸውን ገልጸው ነበር።የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ በበኩላቸው፤ በቴህራን የኒውክሌር መርሃ ግብር ላይ “ስምምነት ላይ መድረስ እንደምንችል እርግጠኛ ነኝ” ሲሉ ለሲኤንኤን ተናግረዋል።ፕሬዝዳንት ትራምፕ የኢራንን ኒውክሌር የማበልጸግ ፍላጎት እና ጸረ መንግሥት ተቃዋሚዎች ላይ በወሰደችው በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የገደለ እርምጃ ምክንያት በማድረግ ጣልቃ እንደሚገቡ ዝተዋል።የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አራግቺ፤ “እንደ አለመታደል ሆኖ አሜሪካን እንደ ተደራዳሪ አጋር ለማየት ያለን እምነት አጥተናል” ብለዋል።ሆኖም በቀጣናው ባሉ ወዳጅ አገራት በኩል የሚደረገው የመልዕክት ልውውጥ ከዋሽንግተን ጋር “ፍሬያማ” ንግግር እንዲኖር እያመቻቸ መሆኑን አክለዋል።የኢራን ከፍተኛ የደኅንነት ባለሥልጣን አሊ ላሪጃኒ የድርድር ማዕቀፍ የማዘጋጀት ሂደት ለውጥ እየታየበት እንደሆነ ገልጸው ነበር።በቀጣናው የሚገኘው ኃይሏን እያጠናከረች ያለችው አሜሪካ፤ ‘የዩኤስኤስ አብርሃም ሊንከን’ የተሰኘውን የአውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ ወደ አካባቢው ልካለች። ባለፈው ሳምንት ደግሞ የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ በአረቢያን ባሕር ላይ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አስታውቋል።የኢራኑ ጠቅላይ መሪ ኻሜኒ፤ “[ትራምፕ] በየጊዜው መርከቦችን አመጣሁ ይላል… የኢራን ሕዝብ እነዚህን ነገሮች አይፈራም” ብለዋል።ኢራን ከዓለም ወሳኝ የመርከብ መተላለፊያዎች አንዱ በሆነው ሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ ከእሑድ ዕለት አንስቶ ለሁለት ቀናት የሚቆይ እና ተኩስን የሚያካትት የባሕር ኃይል ልምምድ ማድረግ እንደምትጀምር ሲጠበቅ ነበር።ይሁን እንጂ የዜና ወኪሉ ሮይተርስ ያነጋገራቸው አንድ የኢራን ባለሥልጣን፤ የኢራን አብዮታዊ ዘብ የባሕር ኃይል እንዲህ ዓይነት ልምምድ የማድረግ ዕቅድ እንደሌለው መግለጻቸውን እሑድ ዕለት ዘግቧል።የዓለም ገበያ ላይ ከሚቀርበው ነዳጅ ውስጥ አንድ አምስተኛው የሚሆነው የሚተላለፈው ኢራን በምትቆጣጠረው የሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ነው። ቴህራን ከዚህ ቀደም ጥቃት የሚሰነዘርባት ከሆነ ወሽመጡን እንደምትዘጋ ዝታ ነበር።ያጋሩ, የኢራን ጠቅላይ መሪ ኻሜኒ አሜሪካ ጥቃት የምትፈጽም ከሆነ ቀጣናዊ ጦርነት እንደሚነሳ አስጠነቀቁ