
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ እና የግብፁ ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ ካይሮ ውስጥ ባደረጉት ውይይት ያላቸውን የደኅንነት ትብብር በማጠናከር ላይ መስማማታቸው ተዘገበ።
ጭምቅ ሃሳብ
- የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ እና የግብፁ ፕሬዝዳንት አል ሲሲ በካይሮ
- ሱዳን ዳግም ኢጋድን ተቀላቀለች
- የኢራን የበላይ መሪ አሊ ኻሜኒ ባልተለመደ ሁኔታ በኢራን አብዮት በዓል ላይ ሳይገኙ ቀሩ
- በአሜሪካ እና ኢራን መካከል የተጀመረው ድርድር መቀጠል እንዳለበት ሩሲያ ገለፀች
- ሆንግ ኮንጓዊው የሚዲያ ባለቤት እና የዲሞክራሲ አቀንቃኝ የ20 ዓመት እስር ተፈረደበት
የቀጥታ ሽፋን
- ከ 1 ሰአት በፊትየሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ እና የግብፁ ፕሬዝዳንት አል ሲሲ በካይሮ
የፎቶው ባለመብት,Egyptian Presidencyየሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ እና የግብፁ ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ ካይሮ ውስጥ ባደረጉት ውይይት ያላቸውን የደኅንነት ትብብር በማጠናከር ላይ መስማማታቸው ተዘገበ።ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ ወደ ካይሮ ያቀኑት የሶማሊያው ፕሬዝዳንት፤ ከፕሬዝዳንት አልሲሲ ጋር በሰጡት የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ “የሶማሊያን አንድነት የሚጋፋ የትኛውንም ተግባር በጋራ እንቃወማለን” ብለዋል።ግብፅ በበኩሏ በአፍሪካ ኅብረት የሶማሊያ የድጋፍ እና የማረጋጋት ተልዕኮ ሥር ወታደሮቿን ለመላክ በያዘችው ዕቅድ መሠረት ተግባራዊ እንደምታደርግ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።የግብፁ ፕሬዝዳንት ጨምረውም የሶማሊያ መረጋጋት ለቀጣናው ልማት እና ደኅንነት “ወሳኝ ጉዳይ ነው” በማለት ሶማሊያን ለመደገፍ አገራቸው የሚጠበቅባትን ታደርጋለች ብለዋል።ሶማሊያ የግዛቷ አካል እንደሆነች ለምትመለከታት ሶማሊላንድ እስራኤል የአገርነት ዕውቅና መስጠቷን ተከትሎ ግብፅ እና ሶማሊያ የጋራ አቋም ይዘው ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።ይህ በእንዲህ እንዳለ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ በአልጀዚራ ቴሌቪዥን ላይ በሰጡት ቃለ ምልልስ ላይ ሶማሊላንድ ከጋዛ የሚፈናቀሉ ፍልስጤማውያንን ለማስፈር እና ለእስራኤል ጦር ሰፈር ለመስጠት ተስማምታለች ማለታቸውን ሶማሊላንድ ወቅሳለች።ፕሬዝዳንቱ በቃለ ምልልሱ ላይ እስራኤል በሶማሊላንድ ውስጥ የጦር ሰፈር የምትመሠርት ከሆነ “እራሳችንን ለመከላከል ባለን አቅም ሁሉ እንፋለማለን” ሲሉ ተቃውሟቸውን አሰምተው ነበር።ነገር ግን የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት ቃል አቀባይ ሐሰን አደን በሰጡት ምላሽ ፕሬዝዳንቱ ያሉትን “እውነታ የሌለው ግልጽ ውሸት” በማለት ውድቅ አድርገውታል።ቃል አቀባዩ ጨምረውም የሶማሊያ መሪ አስተያየት “በውስጡ የገጠመውን ውድቀት በሌሎች ላይ ለማንጸባረቅ የሚፈለግ የተለመደው ዓይነት ያልተሳካለት አመራር አካሄድ ነው” በማለት ሶማሊያ የራሷን ደኅንነት እንኳን መጠበቅ ያልቻለች ናት በማለት ተናግረዋል።ያጋሩ, የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ እና የግብፁ ፕሬዝዳንት አል ሲሲ በካይሮ - ከ 1 ሰአት በፊትሱዳን ዳግም ኢጋድን ተቀላቀለች
የፎቶው ባለመብት,@DrWorknehሱዳን ከሁለት ዓመት በኋላ ዳግም የምሥራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታት ድርጅትን መቀላቀሏን አስታወቀች። ወደ ድርጅቱ ዳግም መቀላቀሏን ይፋ ያደረጉት የድርጅቱ የወቅቱ ፕሬዚዳንት የጂቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ ናቸው።የምሥራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) ዋና ጸሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ሱዳን ወደ ቀጣናዊ ድርጅቱ ዳግም በመመለሷ የተሰማቸውን ደስታ ገለፀዋል።የኢጋድ የወቅቱ ሊቀመንበር የሆኑት የጂቡቲው ፕሬዚዳንት፤ ሱዳን ዳግም ቀጠናዊ ድርጅቱን መቀላቀሏን ያስታወቁት እሁድ ዕለት ነበር።ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ሱዳን ወደ ቀጣናዊ ድርጅት መመለሷን “ለቀጣናዊ አንድነት” ያላትን ቁርጠኝነት ያጋገጠ ነው ያሉ ሲሆን፤ እንዲሁም “በቀጣናው ውስጥ ላለው ሰላም፣ መረጋጋት እና ትብብር ያላትን” ፍላጎት የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል።ሱዳን ከኢጋድ አባልነቷ የወጣችው በኡጋንዳ በተዘጋጀው የድርጅቱ ጉባዔ ላይ የፈጥኖ ደራሽ አዛዡ ሞሐመድ ሀምዳን ዳጋሎ መገኘታቸውን በመቃወም ነው።የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል እአአ ከሚያዚያ 2023 ጀምሮ ከሱዳን ጦር ጋር እየተዋጋ ይገኛል።ሱዳን የኢጋድ መስራች አባል አገራት መካከል አንዷ መሆኗን ያስታወሱት የደርጅቱ ዋና ጸሐፊ ዳግም ወደ ድርጅቱ መመለሷ “የኢጋድን አንድነት እንደሚያጠናክር እና በቀጠናው ቅድሚያ የሚሰጣቸውን የጋራ ጉዳዮች የመፍታት አቅሟን እንደሚያሳድግ” ተናግረዋል።የወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበር የጂቢቲው ፕሬዚዳንት ሱዳን ወደ ድርጅቱ እንድትመለስ ላደረጉት ጥረትም አመሰግነዋል።ኢጋድ በምሥራቅ አፍሪካ የሚገኙ ስምንት አገራትን ያቀፈ ቀጣናዊ ድርጅት ሲሆን እነርሱም ኢትዮጵያ ፣ ጂቡቲ፣ ኤርትራ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳን እና ኡጋንዳ ናቸው።ኤርትራ በቅርቡ ከአባልነት ራሷን ማግለሏን ማስታወቋ ይታወሳል።ተቋሙ ቀጣናዊ ትብብር ላይ የተመሠረተ ፖለቲካዊ መረጋጋትና የምጣኔ ኃብት እድገት እንዲገኝ የሚሠራ ነው።ያጋሩ, ሱዳን ዳግም ኢጋድን ተቀላቀለች - ከ 2 ሰአት በፊትበአሜሪካ እና ኢራን መካከል የተጀመረው ድርድር መቀጠል እንዳለበት ሩሲያ ገለፀች
የፎቶው ባለመብት,Reutersየሩሲያ እና የኦማን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በስልክ ከተወያዩ በኋላ በኢራን እና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል የተጀመረው ድርድር መቀጠል አለበት አሉ።የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ እና የኦማኑ ባድር አል አሳዲ በሁለቱ ተደራዳሪ አገራት መካከል ወታደራዊ እሰጥ አገባን ለማስቀረት ንግግራቸው መቀጠል አለበት ብለዋል።የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ላይ ኦማን ሁለቱን አገራት ለማደራደር እያደረገች ያለውን ጥረት አድንቋል።በኢራን እና በአሜሪካ መካከል ድርድር የተጀመረው አርብ ዕለት ነበር።የኢራን ልዑካን ቡድን በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አባስ አራጋቺ የተመራ ሲሆን በስቲቭ ዊትከር ከተመራው የአሜሪካው ተደራዳሪ ቡድን ጋር በኦማን ተገናኝቶ ተነጋግሯል።እንደ ኦማን የውጭ ጉዳይ ሚኒሲቴር መግለጫ ተደራዳሪዎቹ በኢራን ኒውክለር ፕሮግራም ላይ ጠንካራ ውይይት ያካሄዱ ሲሆን ንግግሩንም የመቀጠል ፍላጎት እንዳላቸው ገልጿል።ያጋሩ, በአሜሪካ እና ኢራን መካከል የተጀመረው ድርድር መቀጠል እንዳለበት ሩሲያ ገለፀች - ከ 3 ሰአት በፊትየኢራን የበላይ መሪ አሊ ኻሜኒ ባልተለመደ ሁኔታ በኢራን አብዮት በዓል ላይ ሳይገኙ ቀሩ
የፎቶው ባለመብት,Reutersበየዓመቱ የካቲት ወር መጀመሪያ ላይ የሚከበረው የኢራን አብዮት መታሰቢያ ዝግጅት ላይ ባልተለመደ ሁኔታ የኢራን የበላይ መሪ አሊ ኻሜኒ ሳይገኙ ቀሩ።በእርሳቸው ምትክ የኢራን ጦር የበላይ አዛዥ የሆኑት ሜጀር ጄነራል አብዶልራሂም ሚሳቪ ክብረ በዓሉ ላይ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል።የሚሳቪ ጠቅላይ መሪውን ወክለው በመገኘታቸው የተሰማቸውን ክብር ለታዳሚዎቹ ባደረጉት ንግግር ላይ ገልጸዋል።በኢራኑ የበላይ መሪ ምትክ በበዓሉ ላይ የታደሙትን የተለያዩ ወታደራዊ አዛዦችን ያገኙት ሚሳቪ በንግግራቸው ላይ ከአሜሪካ ጋር ሊኖር ስለሚችል ግጭት በማንሳት “ቀጠናዊ ጦርነት ለመጀመር ምንም ፍላጎቱ የለንም” ብለዋል።ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ተቃዋሚዎች አያቶላህ አሊ ኻሜኒ ከሥልጣን እንዲወርዱ እና በሕዝባዊ አብዮት የመጣውን የእስላማዊውን ሪፐብሊክ አገዛዝ እንዲያበቃ ሲጠይቁ ነበር።በኢራን ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች ለሳምንታት በተካሄዱት የተቃውሞ ሰልፎች ላይ የተሳተፉ በርካቶች ሲታሰሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ደግሞ መገደላቸው ይታወሳል።ያጋሩ, የኢራን የበላይ መሪ አሊ ኻሜኒ ባልተለመደ ሁኔታ በኢራን አብዮት በዓል ላይ ሳይገኙ ቀሩ - ከ 4 ሰአት በፊትታዋቂው ሆንግ ኮንጓዊ የሚዲያ ባለቤት እና የዲሞክራሲ ተሟጋች የ20 ዓመት እስር ተፈረደበት
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየሆንግ ኮንግ ፍርድ ቤት የዲሞክራሲ አቀንቃኝ እና የሚዲያ ባለቤት የሆነው ጂሚ ላይ ከብሔራዊ ደኅንነት ጋር ተያይዞ በቀረበበት ክስ ጥፋተኛ ሆኖ በማግኘቱ የ20 ዓመት እስር ፈረደበት።ቻይና ከከተማዋ መረጋጋት ጋር በተያያዘ አስፈላጊ ነው በምትለው እና አወዛጋቢ በሆነው የብሔራዊ ደኅንነት ሕግ መሠረት የተሰጠው ይህ የፍርድ ውሳኔ በጣም ከባዱ ነው ተብሏል።ላይ የብሪታኒያ ፓስፖርት ያለው ሲሆን የቻይና መንግሥትን ክፉኛ በመተቸት ይታወቃል።አፕል ዴይሊ የተሰኘ በየዕለቱ የሚታተም ጋዜጣ ባለቤት የሆነው ላይ በተደጋጋሚ በአገሪቱ ውስጥ ለተካሄዱ የተቃውሞ ሠልፎች መነሻ ሆኗል።ሰኞ ዕለት ስድስት የጋዜጣው የቀድሞ ኃላፊዎች ከስድስት እስከ 10 ዓመት እስር ተፈርዶባቸው በቁጥጥር ሥር ውለዋል።በዲሞክራሲ አቀንቃኞች ዘንድ እንደ ጀግና የሚቆጠረው ላይ፣ በቤይጂንግ ግን አንደ አገር ከዳተኛ ይወነጀላል።በተደጋጋሚ የቻይና መንግሥት የሚያቀርበብትን ክስ የሚያስተባብለው የሚዲያ ባለቤቱ ላይ የሆንግ ኮንግ እሴቶች የሆኑ የሚላቸው የሕግ የበላይነት እና የመናገር ነጻነትን እንዲሚሰብክ ይናገራል።የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲን በድፍረት በመጋፈጡ ዋጋ እየከፈለ ያለው ቢልየነርያጋሩ, ታዋቂው ሆንግ ኮንጓዊ የሚዲያ ባለቤት እና የዲሞክራሲ ተሟጋች የ20 ዓመት እስር ተፈረደበት
