

ቦርከና ዜና
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ዛሬ የካቲት 1/2018 ዓ.ም ለኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌህ በጻፉት ደብዳቤ የሁለቱን ሀገራት የጋራ ብሔራዊ ጥቅምን ባስከበረ መልኩ በላቀ የመከባበር ስሜት ከኤርትራ ጋር ለመመካከር ዝግጁ መሆኗን አስታውቀዋል።
ኤርትራ የኢትዮጵያን ድንበር በመጣስ ወረራ መፈጸሟን የጠቆሙት ሚኒስትሩ፣ የኤርትራ መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ ታጣቂ ቡድኖች በቀጥታ የቁሳቁስ ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል በማለት ወንጅለዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት ባለፉት ቀናት ያለው ሁኔታ የኤርትራ መንግስት ሌላ ግጭት እንዲቀሰቀስ የሚያመላክቱ ናቸው ያሉት ጌዲዮን፣ የኤርትራ ኃይሎች በእኛ ሰሜን ምስራቅ ድንበሮችን ጥሰው በመግባትና በሰሜን ምዕራብ በኩልም ከአማፂ ሀይሎች ጋር በመቀናጀት የጋራ ወታደራዊ ጥቃት እየፈጸሙ ይገኛሉ በማለት ይህ ፀብ አጫሪነት ብቻ ሳይሆን ወረራ ነው ሲሉ ወቅሰዋል።
ሚኒስትሩ በዚሁ ደብዳቤያቸው እንዲህ አይነቱን ተቀባይነት የሌለውን ድርጊት ለመቋጨት የኤርትራ ጦር በኢትዮጵያ ግዛት የሚገኙ ሀይሎችን በአስቸኳይ እንዲያስወጣ እና ከታጣቂ ቡድኖች ጋር ያለውን ትብብር እንዲያቆም ጠይቀዋል።

ከግማሽ በላይ ለሚሆን ክፍለ ዘመን ግጭት የሁለቱ ሀገራት መለያ ገፅታ ሆኖ ቆይቷል ሲል ያስታወሰው የሚኒስትሩ ደብዳቤ፣ ይህ አይነቱን የጦርነት አዙሪትና አለመተማመን በውይይትና በዲፕሎማሲያዊ ተሳትፎ ማስወገድ ይገባል ብለን እናምናለን በማለት አሳስበዋል።
ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ፍላጎታችን አወንታዊ ምላሽ ካገኘን፣ የኢትዮጵያ መንግስት የባህር በር ጉዳዮችን እና በአሰብ በኩል የቀይ ባህር አቅርቦትን ጨምሮ በጋራ ጥቅሞቻችን ላይ በጥሩ መተማመን ለመነጋገር ፍላጎት አለው በማለት የመንግስትን አቋም ገልፀዋል።
ጌዲዮን ለኤርትራ አቻቸው በፃፉት ደብዳቤ በጋራ መከባበርና ትብብር ግንኙነታችንን በማሳደግ ብዙ የጋራ የሆኑ ጉዳዮች ያሏቸውን የሁለቱን ሀገራት ህዝቦች አዲስ የሰላም እና የብልግና ዘመን ማምጣት እንችላለን ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ቦርከናን ለመደገፍ/ለማገዝ :- ይሄንን ይጫኑ

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ BorkenaEthiopian News–Borkena English
