February 10, 2026

በሰኔ 2013 ዓ.ም በተካሄደው ሀገር አቀፍ ምርጫ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄን ወክለው የፓርላማ አባል የሆኑት ዶ/ር አበባው ደሳለው፤ በመጪው ምርጫ ኢሕአፓን ወክለው ሊወዳደሩ ነው። የአብን የአዲስ አበባ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የነበሩት ዶ/ር ይህዓለም ታምሩም በተመሳሳይ መልኩ የፓርቲ ለውጥ አድርገው በመጪው ምርጫ እንደሚቀርቡ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ዛሬ ማክሰኞ ጥር 3፤ 2018 ማምሻውን በበይነ መረብ በሰጠው መግለጫ ሁለቱ ቀድሞ የአብን አባላት ፓርቲውን መቀላቀላቸውን ይፋ አድርጓል። በበይነ መረብ የተካሄደውን መግለጫ ከሁለቱ የምርጫ ተወዳዳሪዎች ጋር በመሆን የሰጡት፤ የኢሕአፓ ዋና ጸሐፊ ሚስጥረስላሴ ታምራት ናቸው።
ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ:- https://ethioelections.com/የአብን-የፓርላማ-አባሉ-ዶ-ር-አበባው-ደሳለ-2/
