
Achamyeleh Tamiru ·Follow
አስመሮም ለገሠና ኦነጋውያን… ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ…
ኦነጋውያን አስመሮም ለገሠን አመስግነው አይበቃቸውም፤ የክብር ዶክትሬትና አባ ገዳነት ደርበውለታል። አስመሮም በኦነጋውያን ዘንድ ክብር ያገኘው ለዶክትሬት ዲግሪው ማሟያነት በ1965 ዓ.ም. ለሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ባቀረበው GADA Three Approaches to the Study of African Society ጥናቱ ስለ ገዳ ምንነት ግንባር ቀደም አጥኚ ነው ተብሎ ነው። አስመሮም ስለ ገዳ ግንባር ቀደም አጥኚ ተደርጎ የተቆጠረበትን ጥናት ያዘጋጀው ስለ ኦሮሞ ታሪክ ብቸኛ የጽሑፍ ታሪክ ምንጭ ከሆነው ከአባ ባሕርይ ዜናሁ ለጋ*ላ የቻለውን ያህል ዝቆ ወደ እንግሊዝኛ በመተርጎም ነው።
እውነታው ይህ ቢሆንም ቅሉ አስመሮም ለገሠን አመስግነው የማይበቃቸው ኦነጋውያን አስመሮም ለዶክትሬት ዲግሪው ማሟያነት በብቸኛ የተጠቀመውን የጽሑፍ ታሪክነት የከተቡትን አባ ባሕርይን፣ የአባ ባሕርይን ድርሳን አስመሮም ዩኒቨርሲቲ ከመግባቱ በፊት ወደ አማርኛ ቋንቋ ለመጀመሪያ ጊዜ ተርጉመው ያስቀመጡትን ብላታ መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስን፣ ኋላ ላይ ደግሞ ጽሑፉን አርመውና የአርትዖ ስራ ጨምረውበት ያሳተሙትን ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌንና አባ ባሕርይን ጨምሮ እነዚህ ምሁራን ያፈራችውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ግን አውግዘውና ረግመው አይበቃቸውም።
አስመሮም ለገሠ ገዳ ስለሚባለው የወረራ አደረጃጀት ለመጀመሪያ ጊዜ ያቀረበው GADA Three Approaches to the Study of African Society በሚል ርዕስ ለሀርቫርድ ዩኒቨርሲቱ የዶክትሬት ማሟያነት በ1965 ዓ.ም. ባቀረበው ጥናታዊ ጽሑፉ ነው። አስመሮ ለገሠ የአባ ባሕርይን ዜናሁ ለጋ*ላ የቻለውን ያህል ዝቆ ወደ እንግሊዝኛ በመተርጎም ያዘጋጀውን ይህንን ጥናታዊ ጽሑፍ ለሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ከማቅረቡ በፊት የንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት ብላታ መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ ወደ አማርኛ የመለሱትን የአባ ባሕርይን ዜናሁ ለጋ*ላ መጽሐፍ “ሕዝብ ይከፋፍላል” በሚል የዘመኑ እሳቤ እንዳይታተም አግዶ ነበር።
ብላታ መርዔ ኀዘንም የሳንሱር እገዳውን ለማለፍ ዜናሁ ለጋ*ላ በሚል የተረጎሙትን የአባ ባሕርይ ጽሑፍ “ዜናሁ ለአባ ባሕርይ ዘጸሐፎ በልሳነ ግዕዝ” ወደሚል ርዕስ እንዲቀይሩት ተገደው ነበር። መጽሐፉ ዜናሁ ለጋ*ላ በሚል ርዕስ ተተርጉሞ እንዳይታተም ያደረገው አመድ አፋሹ የንጉሠ ነገሥቱ መንግሥትም በአረመኔዎቹ ኦነጋውያን ከመወገዝ፣ ከመረገምና ባልዋለበት ከመዋል አልተረፈም።
የሆነው ሆኖ ኦነጋውያን አስመሮም ለገሠን አብዝተው የሚያመሰግኑት ስለ ገዳ አደረጃጀታቸው ዲሞክራሲያዊነት ጻፈ እያሉ ነው። ሆኖም ግን አስመሮም ለገሠ ግንባር ቀደም አጥኚ በተደረገበቱ በ1965 ዓ.ም. በጻፈው GADA Three Approaches to the Study of African Society መጽሐፍ ውስጥ አንድም ቦታ ስለ ገዳ የወረራ አደረጃጀትነት እንጂ ስለ ዲሞክራሲያዊነት የተነፈሰው አንድም ቃል የለም።
ባጭሩ አስመሮም ለገሠ ኦነጋያን በሚያመሰግኑበት ግንባር ቀደም ጥናቱ አዲስ ነገር አልጻፈም፤ ከብቸኛው የኦሮሞ ታሪክ የጽሑፍ ምንጭ ከአባ ባሕርይ ዜናሁ ለጋ*ላ ጽሑፍ የቻለውን ያህል ዝቆ ወደ እንግሊዝኛ በመተርጎም የዶክትሬት ዲግሪውን አገኘ እንጂ።
አስመሮም በዚህ የኦሮሞ ጥናት ግንባር ቀደም ምሁር በተደረገበት ጽሑፉ፣ አንድም ቦታ ዲሞክራሲ የሚል ቃል ተጠቅሞ ገዳ የሚባለውን የወረራ አደረጃጀት የገጸበት አረፍተ ነገር አይገኙም። አስመሮም ለገሠ ኦነጋውያን በኩር አጥኚ አድርገው በሚያመሰግኑበት ጥናቱ የጻፈው ጋ*ላ ገዳ በሚባለው የወረራ አደረጃጀት እየተደራጀ ግማሽ የሚሆነው የኢትዮጵያ ክፍል እንደወረረና እንደዳመጠ፤ በተለይም ከሸዋ በታች ያለውን የኢትዮጵያ ክፍል ቢዛሞን [ወለጋን] እንደወረረና እንዳወደመ፤ ገዳ የሚባለው የወረራ አደረጃጀትም የጋ*ላ ሳይሆን ጋ*ላ ከባንቱ የተዋሰው ሊሆን እንደሚችል ነው የጻፈው።
አስመሮም አባ ገዳነት በተሾመበት፣ የኦሮሞ ጥናት ግንባር ቀደም አጥኚ በተደረገበቱና የኦነጋውያንን የክብር ዶክትሬት ባገኘበቱ የ1965ቱ GADA Three Approaches to the Study of African Society መጽሐፉ ስለ ገዳ የጻፈው የወረራ አደረጃጀት መሆኑን፣ ጋ*ላ ግማሹ የሚሆነው የኢትዮጵያ ክፍል በዚህ አደረጃጀት እየተሰራ እንደወረራና እንዳወደመ፤ በዚህ አደረጃጀት በየ ስምንት አመቱ ባካሄደው የወረራ ጦርነት የኢትዮጵያ ጥንታዊ ነገዶችን ያጠፋውን አጥፍቶ የተረፈውን እንደሰለቀጠ ቢጽፍም እነሱ ግን አስመሮምን ሲያወሱ ይህንን የአስመሮም “የጥናት ውጤት” ማስታወስ አይፈልጉም። “ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ” ይላል ይህ ነው።
እስቲ በየትኛው የጥናቱ ገጽ ነው አስመሮም ለገሠ የኦሮሞ ጥናት ግንባር ቀደም አጥኚ በተደረገበቱ GADA Three Approaches to the Study of African Society ውስጥ አዲስ ነገር የጻፈው? ስለ ገዳ አደረጃጀት ዲሞክራሲያዊነት የመሰከረው? እስቲ ያያችሁ ወዲህ በሉን!
አስመሮም ለገሠ GADA Three Approaches to the Study of African Society ጥናቱ ውስጥ ግን ጋ*ላ ገዳ በሚባለው የወረራ አደረጃጀት እየተመራ በየ ስምንቱ አመቱ ባካሄደው ወረራ ግማኝ ያህሉን የኢትዮጵያ ክፍል እንደወረረና እንደ ዋርካ ተስፋፍቶ እንደያዘ ፣ ነባር የኢትዮጵያ ነገዶችን እንዳጠፋና እንደሰለቀጠ፤ ገዳ የሚባለው አደረጃጀትም የተወረሰ እንደሆነ የጻፈውን ከታች አያይዘናል።




