
በካናዳ ብሪቲሽ ኮሎምቢያ ትምህርት ቤት ላይ በተከፈተ ተኩስ ቢያንስ ሰባት ሰዎች መገደላቸውን ፖሊስ አስታወቀ። ሁለት ተጨማሪ ሰዎች በሌላ አካባቢ ሞተው መገኘታቸውን ፖሊስ ጨምሮ ገልጿል።
ጭምቅ ሃሳብ
- ጋና በየሳምንቱ ረቡዕ የባህል ልብስ የሚለበስበት ቀን እንዲሆን አወጀች
- 1.3 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ያላቸው የቀድሞው የዛምቢያ ፕሬዚዳንት ልጅ ንብረቶች እንዲወረሱ ታዘዘ
- ዚምባብዌ የፕሬዚዳንቷን የሥልጣን ዘመን ለማራዘም የሚያስችል አዲስ ረቂቅ ሕግ አወጣች
- በካናዳ ትምህርት ቤት ላይ በተከፈተ ተኩስ ሰባት ሰዎች ተገደሉ
- የግብፅ ፕሬዝዳንት ጉብኝት በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ
- ኢራን ሁሉም ማዕቀቦች የሚነሱላት ከሆነ የበለጸገ ዩራኒየሟን የጥራት ደረጃ ልትቀንስ እንደምትችል አስታወቀች
የቀጥታ ሽፋን
- ከ 21 ደቂቃዎች በፊትፕሬዝዳንት ትራምፕ ኢራን “በጣም ከባድ እርምጃ” ይጠብቃታል ሲሉ አስጠነቀቁ
የፎቶው ባለመብት,EPAኢራን ከአሜሪካ ጋር በቶሎ ከስምምነት ላይ ካልደረሰች “በጣም ከባድ እርምጃ” እንደሚጠብቃት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ተናገሩ።ባለፈው ሳምንት ኦማን ውስጥ በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የተጀመረው ድርድር ቀጣይ ዙር ይካሄዳል ተብሎ እየተጠበቀ ባለበት ጊዜ ትራምፕ ኢራንን አስጠንቅቀዋል።አስካሁን ቀጣዩ ዙር ድርድር መቼ እና የት እንደሚካሄድ ያልተገለጸ ሲሆን፣ ትራምፕ “ኢራን ከስምምነት ላይ ለመድረስ በጣሙን ትፈልጋለች” በማለት በዲፕሎማቲክ መንገድ መፍትሔ ይገኛል የሚል ተስፋ እንዳላቸው አመልክተዋል።ፕሬዝዳንቱ ለእስራኤል ቻናል 12 የቴሌቪዥን ጣቢያ እና ለአሜሪካው የዜና ድረ ገጽ አክሲዮስ እንደተናገሩት ተጨማሪ አዲስ የጦር አውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ለመላክ እያሰቡ ነው።የአሜሪካ ባለሥልጣናት ለሮይተርስ እንደተናገሩት ጆርጅ ዋሽንግተን የተባለው የጦር አውሮፕላን ተሸካሚ በእስያ አህጉር እንዲሁም ጆርጅ ደብሊው ቡሽ የተባለው ደግሞ በአሜሪካ ምሥራቃዊ የባሕር ዳርቻ ላይ ይገኛሉ። ነገር ግን ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ለመድረስ ቢያንስ አንድ ሳምንት ያስፈልጋቸዋል።በተጨማሪም የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ቬንዙዌላ ላይ ጥቃት ከመሰንዘሩ በፊት ወደ ካሪቢያን አካባቢ የተላከችውን ጄራርድ ፎርድ የጦር መርከብን ወደ አካባቢው ሊልክ ይችላል ተብሎ እየተነገረ ነው።ያጋሩ, ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኢራን “በጣም ከባድ እርምጃ” ይጠብቃታል ሲሉ አስጠነቀቁ - ከ 44 ደቂቃዎች በፊትጋና በየሳምንቱ ረቡዕ የባህል ልብስ የሚለበስበት ቀን እንዲሆን አወጀች
የፎቶው ባለመብት,Zambia’s Ministry of Information and Media/Xጋና በየሳምንቱ ረቡዕ ‘ፉጉ’ የተሰኘው የአገሪቷ የባህል ልብስ የሚለበስበት ቀን እንዲሆን አወጀች።አገሪቷ ይህን ያወጀችው ከልብሱ ጋር በተያያዘ በዛምቢያውያን እና በጋናውያን መካከል የበይነ መረብ ክርክር ከተነሳ ከቀናት በኋላ ነው።ባለፈው ሳምንት ፕሬዚደንት ጆን ድራማኒ ማሃማ በዛምቢያ ባደረጉት ጉብኝት ወቅት የባህል ልብሱን ለብሰውት ከታዩ በኋላ መነጋገሪያ ሆኗል።ልብሱን አንዳንድ ዛምቢያውያን ” ቀሚስ” ሲሉ የተሳለቁበት ሲሆን ጋናውያን ለዚህ ምላሽ እንዲሰጡ አድርጓል።በበይነ መረብ የተነሳውን ክርክር ተከትሎም ለዛምቢያ የባህል ልብሱን በብዛት እንደሚልኩ ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል።የጋና የቱሪዝም ሚኒስትር አብላ ድዚፋ ጎማሼ ማክሰኞ ዕለት የባህል አልባሳቱን በየሳምንቱ ረቡዕ መልበስ “በዓለም አቀፍ መድረክ የአገሪቷን ማንነት በኩራት ለማስተዋወቅ ይረዳል” ብለዋል።ከዚህም በተጨማሪ በተለይ በአገር ውስጥ ላሉ አምራቾች እና ዲዛይነሮች፣ ጠበብቶች እና ነጋዴዎች ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ይኖረዋል ብለዋል።በመሆኑም የባህል ልብሱ “ በተለያየ ዲዛይን፣ ቅርጽ እና አለባበስ አብረውት ከሚሄዱ ቆንጆ ጌጣ ጌጦች ጋር እንዲለበስ” ሚኒስትሯ አበረታተዋል።ባታካሪ ወይም ፉጉ እየተባለ የሚጠራው የባህል ልብስ በሰሜናዊ ጋናውያን ዘንድ ይዘወተራል።ልብሱ ቀጫጭን መስመሮች እንዲኖረው ተደርጎ ከጥጥ በእጅ የሚሸመን ሲሆን ሰፋ ተደርጎ የሚሰፋ ነው።ያጋሩ, ጋና በየሳምንቱ ረቡዕ የባህል ልብስ የሚለበስበት ቀን እንዲሆን አወጀች - ከ 4 ሰአት በፊት1.3 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ያላቸው የቀድሞው የዛምቢያ ፕሬዚዳንት ልጅ ንብረቶች እንዲወረሱ ታዘዘ
የፎቶው ባለመብት,The National Prosecution Authority of Zambiaየምስሉ መግለጫ,የመንግሥት አቃቤያነ ሕጎች የነዳጅ ማደያን ጨምሮ የተወረሱትን የዳልቲሶ ሉንጉን ንብረቶች የሚያሳዩ በርካታ ምሥሎችን በፌስቡክ አጋርቷል።የዛምቢያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1.3 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ያላቸው የቀድሞው የዛምቢያ ፕሬዚደንት ኤድጋር ሉንጉ ወንድ ልጅ ዳልቲሶ ሉንጉ ንብረቶች እንዲወረሱ አዘዘ።የንብረት ውርሱ 79 ተሽከርካሪዎችን እንዲሁም የገበያ ማዕከል፣ የነዳጅ ማደያ፣ ዘመናዊ የመኖሪያ አፓርትመንቶችን እና መኖሪያ ቤትን ጨምሮ በሉሳካ ከተማ የሚገኙ 23 መሬቶች እና ሪል ስቴቶችን የሚያካትት ነው።ፍርድ ቤቱ ትዕዛዙን ያስተላለፈው የ39 ዓመቱ ዳልቲሶ ሉንጉ እነዚህን ንብረቶቹን እንዴት እንዳፈራቸው የሚያሳዩ ተጨባጭ እና የተረጋገጡ ማስረጃዎችን ማቅረብ ባለመቻሉ እንደሆነ ገልጿል።ዛምቢያን ከአውሮፓውያኑ 2015 ጀምሮ ለስድስት ዓመታት የመሩት ኤድጋር ሉንጉ ባለፈው ዓመት በደቡብ አፍሪካ ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን በቤተሰባቸው እና አሁን ባለው መንግሥት መካከል በተፈጠረ ውዝግብ እስካሁን አልተቀበሩም።በልጃቸው ላይ የተላለፈው ውሳኔ የተሰማውም በሉንጉ እና በ2021 ምርጫ በአብላጫ ድምጽ ባሸነፏቸው ተተኪያቸው ፕሬዚዳንት ሃኬንዴ ሂችሌማ መካከል የተፈጠረ የረዥም ጊዜ ውዝግብን ተከትሎ ነው።የሂችሌማ መንግሥት የሉንጉ አስክሬን ወደ አገራቸው ተመልሶ በመንግሥታዊ ሥርዓት በሙሉ ክብር እንዲቀበሩ ይፈልጋል። የደቡብ አፍሪካ ፍርድ ቤትም ባለፈው ነሐሴ ወር ላይ ሃሳባቸውን የሚደግፍ ውሳኔ አስተላልፏል።ቤተሰባቸው ደግሞ ሉንጉ “በቀብር ሥነ ሥርዓታቸው ላይ ሂቺሌማ እንዲገኙ አይፈልጉም ነበር” በማለት በደቡብ አፍሪካ ቤተሰባቸው እና ወዳጆቻቸው በተገኙበት የግል የቀብር ሥነ ሥርዓት እንዲፈፀምላቸው ይፈልጋሉ።ያጋሩ, 1.3 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ያላቸው የቀድሞው የዛምቢያ ፕሬዚዳንት ልጅ ንብረቶች እንዲወረሱ ታዘዘ - ከ 5 ሰአት በፊትዚምባብዌ የፕሬዚዳንቷን የሥልጣን ዘመን ለማራዘም የሚያስችል አዲስ ረቂቅ ሕግ አወጣች
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,አሁን ባለው ሕገ መንግሥት መሠረት ፕሬዚደንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ ከሁለት ዓመት በኋላ ከሥልጣን ይወርዳሉ።የዚምባብዌ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ83 ዓመቱ ፕሬዚደንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ ቢያንስ ለሚቀጥሉት አራት ዓመታት ሥልጣን ላይ እንዲቆዩ የሚፈቅድ አዲስ ረቂቅ ሕግ አፀደቀ።አዲሱ ረቂቅ ሕግ ፕሬዚደንቶች በምርጫ ሳይሆን በምክር ቤት አባላት እንዲመረጡ እና ሰባት ዓመታት ላሉት ሁለት የሥልጣን ዘመን እንዲያገለግሉ ይፈቅዳል።አሁን ላይ ተግባራዊ እየሆነ ባለው ሕግ አንድ የሥልጣን ዘመን አምስት ዓመታትን የያዘ ነው።የፍትሕ ሚኒስትሩ ዚያምቢ ዚያምቢ ረቂቅ ሕጉ ለምክር ቤት ከመቅረቡ በፊት ከሕዝብ ጋር ውይይት እንደሚደረግበት ገልጸዋል። ሆኖም ሁለቱም ምክር ቤቶች በገዥው ዛኑ ፒኤፍ ፓርቲ በበላይነት የተያዙ ናቸው።ቢሆንም ሕጋዊ ተግዳሮቶች ሊገጥሙት ይችላል።የሕገ መንግሥት ባለሙያዎች የሥልጣን ዘመን የሚቀየር ከሆነ ሕዝበ ውሳኔ ያስፈልጋል ያሉ ሲሆን አዲሱ ረቂቅ ሕግ አሁን ያሉትን ፕሬዚደንት የሚጠቅም አይደለም ሲሉም ተከራክረዋል።ምናንጋግዋ ለመጀመሪያ ጊዜ ሥልጣን ላይ የወጡት ለረጅም ጊዜ የአገሪቷ ፕሬዚደንት የነበሩት ሟቹ ሮበርት ሙጋቤ በወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ከተነሱ በኋላ እአአ በ2017 ነበር።ከዚያም በቀጣይ ዓመት በነበረው ምርጫ ያሸነፉ ሲሆን እአአ በ2023 በተካሄደው አወዛጋቢ ምርጫ ደግሞ ለሁለተኛ የሥልጣን ዘመን ተመርጠዋል።ያጋሩ, ዚምባብዌ የፕሬዚዳንቷን የሥልጣን ዘመን ለማራዘም የሚያስችል አዲስ ረቂቅ ሕግ አወጣች - ከ 5 ሰአት በፊትበካናዳ ትምህርት ቤት ላይ በተከፈተ ተኩስ ሰባት ሰዎች ተገደሉ
የፎቶው ባለመብት,Madi Taylor / Facebookየምስሉ መግለጫ,ጥቃቱ በተፈጸመበት ስፍራ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ደርሰዋልበካናዳ ብሪቲሽ ኮሎምቢያ ትምህርት ቤት ላይ በተከፈተ ተኩስ ቢያንስ ሰባት ሰዎች መገደላቸውን ፖሊስ አስታወቀ።በተምብለር ሪጅ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ስድስት ሰዎች ሞተው መገኘታቸውን እና አንዱ ወደ ሆስፒታል እየተወሰደ ባለበት ወቅት ሕይወቱ ማለፉ ተገልጿል።ተኩሱን በመክፈት የተጠረጠረ ግለሰብ እንዲሁ ራሱ ላይ ባደረሰው ጉዳት ሞቶ መገኘቱን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።ሁለት ሌሎች ግለሰቦች በሌላ አካባቢ ሞተው መገኘታቸውን እና ከትምህርት ቤቱ ጥቃት ጋር ግንኙነት ሊኖረው እንደሚችል ፖሊስ አስታውቋል።የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ካርኔ ጥቃቱን “አሳዛኝ” ሲሉ ወደ ጀርመን ለመጓዝ ይዘውት የነበረውን ዕቅድ ሰርዘዋል።ፖሊስ ጥቃት ስለተፈጸመበት መሳሪያ ወይንም ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮች ተጨማሪ መረጃ ይፋ አላደረገም።ያጋሩ, በካናዳ ትምህርት ቤት ላይ በተከፈተ ተኩስ ሰባት ሰዎች ተገደሉ - 10 የካቲት 2026ኢንዶኔዢያ ወታደሮቿን ጋዛ ውስጥ ለማሰማራት እየተዘጋጀች ነው
የፎቶው ባለመብት,AFP via Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,ፕሬዝዳንት ፕራቦዎ ሱቢያንቶ ኢንዶኔዢያ ጋዛን ለማረጋጋት ድጋፍ ማድረግ አለባት ሲሉ ተናግረዋልኢንዶኔዢያ ስምንት ሺህ ወታደሮችን በጋዛ ለማሰማራት እየተዘጋጀች መሆኗን አስታወቀች።ኢንዶኔዢያ ወታደሮቿን የምታሰማራው ባለፈው ዓመት አሜሪካ ያሸማገለችው የተኩስ አቁም ስምምነት አካል ነው ተብሏል።የጦር አዛዡ ጄኔራል ማሩሊ ሲማንጁንታክ ለወታደሮቹ የሚሰጠው ሥልጠና አስቀድሞ መጀመሩን እና በጋዛ በሚገኙ የሕክምና እና የምህንድስና ሥራዎች ላይ እንደሚያተኩሩ ተናግረዋል።ኢንዶኔዢያ ባለፈው ወር የታወጀውን የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሰላም ቦርድ ተቀላቅላለች።የሰላም ቦርዱ ከተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት የተላከ ዓለም አቀፍ አረጋጊ ኃይል ለማቋቋም ሥልጣን ተሰጥቶታል።ይህም በጋዛ ውስጥ የድንበር አካባቢዎችን ለመጠበቅ እና ግዛቱን ከወታደራዊ እንቅስቃሴ ነጻ ማድረግ፣ ሐማስን ትጥቅ ማስፈታትን ጨምሮ ሌሎችም ኃላፊነት ይኖረዋል።ቦርዱ በሚቀጥለው ሳምንት በዋሽንግተን የመጀመሪያውን ስብሰባ እንደሚያካሂድ የሚጠበቅ ሲሆን፣ በጋዛ አዲስ የፍልስጤም ከምሁራን የሚውጣጣ መንግሥት እና ከጦርነቱ በኋላ የሚካሄደውን የመልሶ ግንባታ ሥራም ይቆጣጠራል።ያጋሩ, ኢንዶኔዢያ ወታደሮቿን ጋዛ ውስጥ ለማሰማራት እየተዘጋጀች ነው - 10 የካቲት 2026ኬንያ ዜጎቿን በዩክሬን ጦርነት ውስጥ እንዲሳተፉ መመልመላቸውን በሚመለከት ከሩሲያ ጋር ልትነጋገር ነው
የፎቶው ባለመብት,Ukraine Defence Intelligenceየምስሉ መግለጫ,ክሊንተን ሞገሳ በዩክሬን ለሩሲያ ሲዋጋ ሕይወቱ ማለፉ ተገልጿልኬንያ ዜጎቿ በዩክሬን ጦርነት ውስጥ እንዲዋጉ እየተመለመሉ እንደሆነ የሚገልጹ ዘገባዎች እየጨመሩ በመምጣታቸው ከሩሲያ ጋር ልትነጋገር ነው።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሙሳሊያ ሙዳቫዲ ለቢቢሲ ድርጊቱ “ተቀባይነት የሌለው እና በድብቅ የሚፈጸም” መሆኑን ተናግረዋል።ሚኒስትሩ ጨምረውም ኬንያ ሕገወጥ የሠራተኛ ቅጥር ያካሂዷሉ ያላቸውን ኤጀንሲዎች ማገዷን ገልጸዋል።ሁለቱ አገራት በሚኖራቸው ውይይት ወቅት ሞስኮ የኬንያ ዜጎችን ለውትድርና እንዳይመለመሉ የሚከለክል ስምምነት እንድትፈርም እንደምታሳስብ ተናግረዋል።የኬንያ መንግሥት እስካሁን ድረስ ወደ 200 የሚጠጉ ዜጎቹ ለሩሲያ እንዲዋጉ መመልመላቸውን ይገምታል።ኬንያውያኑ በመደበኛ መንገድ ወደ ሩሲያ ባለመጓዛቸው የተነሳ ምን ያህል ዜጎቿ በዩክሬን ጦርነት ውስጥ ለመሳተፍ እንደተመለመሉ የሚያሳይ ይፋዊ መረጃ የላትም።“ኬንያ እና ሩሲያ ከነፃነት ጊዜ ጀምሮ መልካም ግንኙነት ነበራቸው። ስለዚህ ይህ በእኔ ዕይታ በሁለቱ አገራት አወንታዊ እና ወዳጃዊ ግንኙነት መካከል የተፈጠረ በጣም አሳዛኝ ክስተት ይሆናል” ብለዋል ሚኒስትሩ።ሙዳቫዲ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ኬንያ ከሩሲያ ጋር የምታደርገው ውይይት ሕገ ወጥ የቅጥር ልምዶችን በመግታት ላይ ያተኩራል።በቪዛ ፖሊሲ እና ወታደራዊ ምልመላን ሳይጨምር በሁለትዮሽ የሠራተኛ ስምምነቶች ላይ ውይይት እንደሚደረግ ገልጸዋል።የኬንያ ባለሥልጣናት ዜጎቻቸውን በውጭ አገር የሥራ ዕድል እንደሚሰጡ ቃል በመግባት አታልለዋል ተብለው የተጠረጠሩ ከ600 በላይ የቅጥር ኤጀንሲዎችን መዘጋታቸውን አስታውቀዋል።እስካሁን ድረስ በዩክሬን የሚዋጉ 27 ኬንያውያን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተደርገዋል።ያጋሩ, ኬንያ ዜጎቿን በዩክሬን ጦርነት ውስጥ እንዲሳተፉ መመልመላቸውን በሚመለከት ከሩሲያ ጋር ልትነጋገር ነው - 10 የካቲት 2026የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት አውሮፓ ራሷን እንደ “ኃያል” አህጉር ማቅረብ እንድትጀምር አሳሰቡ
የፎቶው ባለመብት,AFP via Getty Imagesየፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑዔል ማክሮን አውሮፓ ራሷን በዓለም መድረክ ላይ እንደ “ኃያል” አህጉር ማቅረብ የምትጀምርበት ጊዜ አሁን እንደሆነ በመግለጽ አሳሰቡ።ከቻይና፣ ከሩሲያ እና አሁን ደግሞ ከአሜሪካ እየጨመረ የመጣውን ተገዳዳሪነት በተመለከተ ሲናገሩም ለአህጉሪቱ “የማንቂያ ደወል” እንደሚሆናት ለመገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል።“ኃያል ለመሆን ዝግጁ ነን? ይህ በኢኮኖሚ እና በፋይናንስ፣ በመከላከያ እና በደኅንነት ዘርፍ እንዲሁም በዴሞክራሲያዊ ሥርዓቶቻችን ውስጥ ጥያቄ ነው።”“በሌላ ዘመን ቢሆን ‘አብላጫ መሆናችንን የምናሳይበት ጊዜ ነው’ ብለን ልንናገር እንችል ነበር” ሲሉ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ላይ በብራስልስ ከሚካሄደው የአውሮፓ ኅብረት ጉባኤ አስቀድመው ተናግረዋል።ማክሮን ለኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንት የሚያስፈልገውን መቶ ቢሊዮን ዩሮዎች ለማሰባሰብ የአውሮፓ አገራት የጋራ ብድር እንዲያገኙ ጥሪያቸውን ዳግም አቅርበዋል።”የወደፊት ወጪያችንን ለመደገፍ የጋራ የዕዳ የምንወስድበት ጊዜ ላይ ደርሰናል። ምርጥ ፕሮጀክቶችን ለመደገፍ ትላልቅ የአውሮፓ ፕሮግራሞች ያስፈልጉናል” ብለዋል።ቀደም ባሉት ጊዜያት የተደረጉ ተመሳሳይ ጥሪዎች በጀርመን እና በሌሎች አገራት በጥርጣሬ ታይተዋል።ያጋሩ, የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት አውሮፓ ራሷን እንደ “ኃያል” አህጉር ማቅረብ እንድትጀምር አሳሰቡ - 10 የካቲት 2026የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር በትግራይ ያለው ውጥረት እንዲረግብ ጥሪ አቀረቡ
የተባበሩት መንግሥታት ለሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር የሆኑት ቮልከር ተርክ በቅርቡ በፌደራል መንግሥቱ እና በትግራይ ኃይሎች መካከል የተከሰተውን ግጭት በሚመለከት ሁሉም ወገኖች ግጭትን ከማባባስ እንዲቆጠቡ አሳሰቡ።ተርክ ማክሰኞ የካቲት 3/2018 ዓ.ም. ባወጡት መግለጫ ላይ በቅርቡ በፌደረል መንግሥቱ እና በትግራይ ክልል ኃይሎች መካከል የተከሰተው ግጭት በሰሜን ኢትዮጵያ አሳሳቢ የሆነውን የሰብዓዊ መብቶች እና የሰብዓዊ ሁኔታ ሁኔታ አደጋ ላይ የሚጥል ነው ብለዋል።ተርክ እንዳሉት “ሁኔታው በጣም ተለዋዋጭ ነው፤ የበለጠ እየተባባሰ እንደሚሄድም እንሰጋለን፤ ይህም የክልሉን አደገኛ የሰብአዊ መብቶች እና የሰብዓዊ ሁኔታን ያባብሳል።”አክለውም ሁለቱም ወገኖችበጦር መሣሪያ የታገዘ ግጭት ውስጥ ከመግባት ይልቅ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በመታገዝ ውጥረቱን በፖለቲካዊ ውይይት እና በራስ መተማመንን ለማርገብ “የተቀናጀ እና ቀጣይነት ያለው ጥረት” ማድረግ እንደሚያስፈልጋቸው አሳስበዋል።ከጥቂት ሳምንት በፊት የትግራይ እና የአማራ ክልሎች በይገባኛል በሚወዛገቡበት ጸለምት አካባቢ በህወሓት እና በፌዴራል መንግሥት መካከል ግጭት ተከስቶ የድሮን እና የከባድ መሣሪያ ጥቃት እንደነበር ተዘግቧል።ተርክ በግጭቱ ወቅትም ሆነ ከግጭቱ በኋላ ሰላማዊ ዜጎች በሁለቱም ወገኖች በኩል በቁጥጥር መዋላቸውን መስማታቸው እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል።“ሰላማዊ ዜጎች ዳግም ውጥረቱ እየተባባሰ ባለበት ሁኔታ ውስጥ ዳግም ቅርቃር ገብተዋል” ያሉት ተርክ ለሁለቱም ወገኖች ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል የሚደረገው እስር “መቆም አለበት” ብለዋል።ተርክ በቅርቡ በኢትዮጵያ እና በጎረቤት አገር ኤርትራመካከል የተፈጠረው ውጥረት አሳሳቢመሆኑን በመግለጽ፤ ሁኔታው እየተባባሰ የሚሄድ ከሆነ አገራቱ እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድ ያሉ የሰብአዊ እና የሰብአዊ መብት ተግዳሮቶችን እንደሚያባብስ አስጠንቅቀዋል።ያጋሩ, የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር በትግራይ ያለው ውጥረት እንዲረግብ ጥሪ አቀረቡ - 10 የካቲት 2026የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስቴር ከዶናልድ ትራምፕ ጋር በኢራን ጉዳይ ሊወያዩ ነው
የፎቶው ባለመብት,Reutersየእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የአሜሪካውን ፕሬዚዳንት በዚህ ሳምንት በዋሺንግተን ሲያገኟቸው ከኢራን ጋር ስለነበራቸው ድርድር እንደሚወያዩ ገለፁ።“በርካታነገሮችን እንወያያለን። ስለ ጋዛ፣ ስለቀጠናው፣ ነገር ግን በቅድሚያ ከኢራን ጋር ስለነበራቸው ድርድር እናወራለን። ለፕሬዚዳንቱ በድርድሩ መርሆች ላይ ያለኝን ዕይታ አጋራቸዋለሁ” ብለዋል።ኔታንያሁበዋሺንግተን ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ረቡዕ ዕለት ለመገናኘት ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ያመራሉ።የኔታንያሁእና የዶናልድ ትራምፕ ውይይት የሚካሄደው በኢራን እና በአሜሪካ መካከል በኦማን ድርድር በተደረገ በጥቂት ቀናት ልዩነት ውስጥ ነው።ያጋሩ, የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስቴር ከዶናልድ ትራምፕ ጋር በኢራን ጉዳይ ሊወያዩ ነው - 10 የካቲት 2026የግብፅ ፕሬዝዳንት ጉብኝት በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ
የፎቶው ባለመብት,Egyptian Presidencyየምስሉ መግለጫ,ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ እና ፕሬዝዳንት ሼክ ሞሐሙድ ቢን ዛይድ አል ናህያንየግብፅ ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ በዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ጉብኝት አድርገው ከአገሪቱ ፕሬዝዳንት ሼክ ሞሐሙድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር ተወያዩ።ሁለቱ መሪዎች አቡዳቢ ውስጥ በመካከለኛው ምሥራቅ በተከሰተው ውጥረት እንዲሁም በፍልስጤም እና በእስራኤል ጉዳይ ላይ መወያየታቸው ተነግሯል።የግብፅ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ መሪዎቹ ቀጠናዊ መረጋጋት የመካከለኛው ምሥራቅ አገራትን “የግዛት አንድነት እና ሉዓላዊነት” ማክበር ላይ የሚመሠረት ነው በማለት በአካባቢው ያለው ውጥረት የሚባባስ ከሆነ ሁሉም አገራት ላይ ተጽእኖ ይኖረዋል ሲል አሳስቧል።የግብፁ ፕሬዝዳንት ባለፉት ቀናት ከቱርክ እና ከሶማሊያ አቻዎቻቸው ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው ወደ ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ያቀኑት።ኤምሬትስ በመካከለኛው ምሥራቅ እና በአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተጽእኖ ያላት ሲሆን፣ ግብፅ በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ከምትወዛገባት ኢትዮጵያ ጋር የጠበቀ ግንኙነት አላት።ሲሲ ከኤምሬትስ መሪ ጋር የምጣኔ ሀብታቸውን ትስስር ለማጠናከር ከመወያየታቸው በተጨማሪ የአገሪቱን የሰው ሠራሽ አስተውሎት ዩኒቨርስቲን በጋራ መጎብኘታቸው ተዘግቧል።የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በቢሊዮን ዶላሮች የሚቆጠር ገንዘብ በመመደብ በሜዲትራኒያን የባሕር ዳርቻ ላይ ግዙፍ ግንባታዎችን ለማካሄድ ከግብፅ ጋር ከአንድ ዓመት በፊት ከስምምነት መድረሷ ይታወሳል።
የፎቶው ባለመብት,Egyptian Presidencyያጋሩ, የግብፅ ፕሬዝዳንት ጉብኝት በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ - 10 የካቲት 2026ንጉሥ ቻርለስ ወንድማቸው በኤፕስቲን ሰነድ ላይ መጠቀሱን ተከትሎ “ጥልቅ ስጋት” እንደተሰማቸው ገለጹ
የፎቶው ባለመብት,EPAየእንግሊዝ ንጉሥ ቻርለስ፤ ከወሲብ ወንጀለኛው ጄፍሪ ኤፕስቲን ጋር በተያያዘ ወንድማቸው አንድሪው ማውንትባተን ዊዶሰር ላይ ለሚደረግ ምርመራ ቤተ መንግሥቱ ከፖሊስ ጋር እንደሚተባበር ገለጹ።የቤተ መንግሥቱ ቃል አቀባይ፤ “ንጉሡ ከማውንትባተን ዊዶሰር ባሕሪ ጋር በተያያዘ መውጣት በቀጠሉት ውንጀላዎች የተሰማቸውን ጥልቅ ስጋት በቃላቸው እንዲሁም በተግባራቸው ግልጽ አድርገዋል” ብለዋል።ሪፐብሊክ የተባለ ጸረ ንጉሣዊ ቡድን የቀድሞው ልዑል አንድሪው ማውንትባተን ዊዶሰር በሕዝብ ስልጣን ላይ በተፈጸመ ያለአግባብ የሆነ ተግባር እንዲሁም የመንግሥት ምሥጢሮችን በማውጣት ጉዳዮች እንደሚጠረጠሩ በመግለጽ ለፖሊስ አቤቱታ አቅርቦ ነበር።ፖሊስም በቀረበው አቤቱታ መሠረት ምርመራ ለማካሄድ የሚያስችል ሁኔታ መኖሩን ወይም አለመኖሩ እየገመገመ እንደሆነ አረጋግጧል።ከዚህ ጋር በተያያዘም ንጉሣዊው ቤተ መንግሥት ከፖሊስ ጋር እንደሚተባበር አስታውቋል። የቤተ መንግሥቱ ቃለ አቀባይ፤ “ተለይተው የቀረቡት ጥያቄዎች በማውንትባተን ዊዶሰር የሚመለሱ ቢሆኑም፤ በቴምስ ቫሊ ፖሊስ የምንጠየቅ ከሆነ እናንተም እንደምትጠብቁት ለመተባበር ዝግጁ ነን” ብለዋል።በቅርቡ ይፋ የተደረጉ የኤፕስቲን ሰነዶች የቀድሞው ልዑል ወደ ሲንጋፖር፣ ሆንግ ኮንግ እና ቪየትናም ከሚደረጉ ጉዞዎች ጋር የተያያዙ መረጃዎችን ሲያስተላልፉ እንደነበር ጠቁመዋል። ዝርዝር የምሥጢራዊ ኢንቨስትመንት መረጃዎችም ከተላለፉት የመንግሥት መረጃዎች መካከል እንደሆኑ ሰነዶቹ አመልክተዋል።በመንግሥት መመሪያ መሠረት የንግድ ልዑኮች ከይፋዊ ጉዞ ጋር የተገናኙ ጥበቃ የሚያስፈልጋቸው የንግድ ወይም የፖለቲካ መረጃዎችን በምሥጢራዊነት መያዝ አለባቸው።የንጉሣውያኑ ቤተ መንግሥት ባወጣው መግለጫ፤ ንጉሡ እና ንግሥቷ በወሲብ ወንጀለኛው ኤፒስቲን ተግባራት “ማንኛውም ዓይነት በደል ለደረሰባቸው ተጎጂዎች” ያላቸውን ሐዘን ገልጸዋል።አዲስ የተለቀቁ ሰነዶች ኤፕስቲን ከቀድሞው ልዑል ጋር ወሲባዊ ግንኙነት እንድታደርግ እንዲት ሴትን ወደ ዩናይትድ ኪንግደም መላኩን አሳይተዋል።የቀድሞው ልዑል መሬት ላይ ከተኛች አንዲት ሴት ሥር ተንበርክኮ እና እጆቹን መሬት ላይ አድርጎ የሚያሳይ ፎቶግራፍ መለቀቁም ጫናውን አበርትቶታል።ያጋሩ, ንጉሥ ቻርለስ ወንድማቸው በኤፕስቲን ሰነድ ላይ መጠቀሱን ተከትሎ “ጥልቅ ስጋት” እንደተሰማቸው ገለጹ - 10 የካቲት 2026ኢራን ሁሉም ማዕቀቦች የሚነሱላት ከሆነ የበለጸገ ዩራኒየሟን የጥራት ደረጃ ልትቀንስ እንደምትችል አስታወቀች
የፎቶው ባለመብት,Reutersኢራን የተጣሉባት ማዕቀቦች በሙሉ የሚነሱላት ከሆነ በከፍተኛ መጠን ያበለጸገችውን ዩራኒየም የጥራት ደረጃ ዝቅ ለማድረግ ልትስማማ እንደምትችል የአገሪቱ የአቶሚክ ኃላፊ መናገራቸውን የዜና ወኪሉ ሮይተርስ ዘገበ።ኢራን ያቀረበችው ይህ ሐሳብ ከአሜሪካ ጋር እያደረገችው ባለችው ድርድር በግልጽ አቋሟ የተንጸባረቀበት ተደርጎ ተቆጥሯል።የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የባሕር ኃይላቸውን ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ማሰማራቸውን ተከትሎ በዋሽንግተን እና ቴህራን መካከል ጦርነት ይነሳል የሚል ስጋት በርትቶ ቆይቷል። ይህ ስጋት ማየሉን ተከትሎም የአሜሪካ እና ኢራን ዲፕሎማቶች ካለፈውሳምንት ጀምሮ በኦማን አደራዳሪዎች አማካኝነት ኦማን ውስጥ ንግግር እያደረጉ ነው።የተባበሩት መንግሥታት የኒውክሌር ተቋም ባለፈው ዓመት ይፋ ያደረገው ግምት እንደሚያሳየው ኢራን ከ400 ኪሎ ግራም በላይ የሆነ ዩራኒየም አከማችታለች። የኢራን ዩራኒየም እስከ 60% የሚደርስ የጥራት ደረጃ እንዳለውም ተገልጿል።ዩራኒየም ለጦር መሣሪያነት ደረጃ ደርሷል የሚባለው 90% ጥራት ሲኖረው ሲሆን የኢራን ክምችት እዚህ ላይ ለመድረስ አንድ እርምጃ ብቻ የቀረው እንደሆነም ተቋሙ አስታውቋል።ባለፈው ዓመት የኢራን የኒውክሌር ጣቢያዎች ላይ የአየር ድብደባ የፈጸመችው አሜሪካ፤ ይህን የዩራኒየም ክምችት እንድትተው ትፈልጋለች።የኢራን የአቶሚክ ኢነርጂ ድርጅት ኃላፊ መሐመድ ኢስላሚ፤ “60 በመቶ የበለጸገውን ዩራኒየም የመበረዝ (diluting) አማራጭ… በምላሹ የተጣሉብን ሁሉም ማዕቀቦች ይነሳሉ ወይስ አይነሱም በሚለው ላይ የተመሰረተ ነው” ብለዋል።እስካሁን ድረስ ከአሜሪካ ባለሥልጣናት ጋር በተደረገው ንግግር የኢራንን የበለጸገ ዩራኒየም ወደ ሌላ አገር የመላክ ሐሳብ እንዳልተነሳም ኃላፊው መናገራቸውን የኢራን የዜና ወኪል አይኤስኤንኤ ዘግቧል።ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ የቅርብ አማካሪ እና የብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት ጸሐፊ የሆኑ አሊ ላሪጃኒ፤ ከአሜሪካ ጋር ድርድር እየተደረገባት ወዳለችው ኦማን እንደሚጓዙ ተዘግቧል።”በዚህ ጉዞ [ላሪጃኒ] ከኦማን ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ተገናኝተው ስለ ወቅታዊው ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች እንዲሁም ስለ ሁለትዮሽ ትብብር ይመክራሉ” ሲል ከፊል ይፋዊ የዜና ወኪል የሆነው ታስኒም ዘገባ አመልክቷል።ቀጣዩ ዙር የአሜሪካ እና ኢራን ድርድር የሚካሄድበት ጊዜ እና ቦታ እስካሁን አልታወቀም። የኢራኑ ፕሬዝዳንት መስዑድ ፔዜሽኪያን፤ ቀጣዩ ዙር ንግግር “ለዚህ ጉዳይ ፍትሐዊ እና ሚዛናዊ መፍትሄ ለማግኘት የሚያስችል ተገቢ አጋጣሚ ነው” ብለዋል።አሜሪካ ከፍተኛ ጫናዎችን ከማሳደር ከተቆጠበች እና ቃሏን የምታከብር ከሆነ ተፈላጊው ውጤት ላይ መድረስ እንደሚቻልም ገልጸዋል።ያጋሩ, ኢራን ሁሉም ማዕቀቦች የሚነሱላት ከሆነ የበለጸገ ዩራኒየሟን የጥራት ደረጃ ልትቀንስ እንደምትችል አስታወቀች - 9 የካቲት 2026ሶማሊያ ከሳዑዲ አረቢያ ጋር የመከላከያ እና ወታደራዊ ስምምነት ተፈራረመች
የፎቶው ባለመብት,@MoDSomaliyaየምስሉ መግለጫ,የሶማሊያ እና የሶዑዲ የመከላከያ ሚኒስትሮች ስምምነቱን ሲፈራረሙሶማሊያ እና ሳዑዲ አረቢያ በመካከላቸው ያለውን የመከላከያ እና ወታደራዊ ትብብር የበለጠ ለማጠናከር የሚስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።ስምምነቱ ሁለቱ አገራት ያላቸውን የደኅንነት ትብብር ከማስፋት ባሻገር በቀይ ባሕር ቀጣና መረጋጋትን ለማጠናከር የታለመ መሆኑን የሶማሊያ የመከላከያ ሚኒስቴር ገልጿል።ሳዑዲ አረቢያ ሪያድ ውስጥ በሶማሊያው የመከላከያ ሚኒስትር አህመድ ሞአሊም ፊቂ እና በሳዑዲ አቻቸው ልዑል ኻሊድ ቢን ሳልማን የተፈረመው ይህ ስምምነት፤ የተለያዩ የጋራ ወታደራዊ እና የመከላከያ ጉዳዮችን የሚመለከት ነው።ሶማሊያ ከሌላ አገር ጋር ወታደራዊ እና ምጣኔ ሀብታዊ ስምምነት ስትደርስ ይህ ከሳዑዲ አረቢያ ጋር የፈረመችው የመጀመሪያዋ አይደለም።ከዚህ ቀደም ከቱርክ እና ከግብፅ ጋር ተመሳሳይ ስምምነት መድረሷ የሚታወስ ሲሆን፣ እስራኤል በቅርቡ ለሶማሊላንድ የአገርነት ዕውቅናን ከሰጠች በኋላ በርካታ አገራት ከጎኗ እንዲቆሙ ጥረት እያደረገች ነው።ያጋሩ, ሶማሊያ ከሳዑዲ አረቢያ ጋር የመከላከያ እና ወታደራዊ ስምምነት ተፈራረመች - 9 የካቲት 2026በሊባኖስ የመኖሪያ ሕንፃዎች ተደርምሰው 14 ሰዎች ሞቱ
የፎቶው ባለመብት,Reutersበሰሜናዊ ሊባኖስ ከተማ ትሪፖሊ በሁለት የመኖሪያ ሕንፃዎች መደርመስ አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 14 መድረሱን የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ።የሲቪል ደኅንነት ጥበቃ መሥሪያ ቤት ዳይሬክተር ኢማድ ክሬይስ የስምንት ሰዎችን ሕይወት መታደግ መቻሉን ተናግረዋል።ዳይሬክተሩ እንዳሉት አደጋው በደረሰባቸው ሁለት የተያያዙ ሕንፃዎች ውስጥ 22 ሰዎች ይኖሩ ነበር። ሆኖም አሁንም ያልወጡ ሰዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ የከተማዋ አስተዳደር ባለሥልጣናት አስጠንቅቀዋል።በከተማዋ ከታኅሳስ ወር ጀምሮ ባሉት ወራት ብቻ ሕንፃ ሲደረመስ ይህ አምስተኛው ነው።ይህም በሊባኖሷ ድሃ ከተማ ውስጥ በሚገኙ ያረጁ እና እድሳት ባልተደረገላቸው ሕንፃዎች ላይ ያለው ስጋት እንዲጨምር አድርጓል።የትሪፖሊ ከንቲባ አብደል ሃሚድ ካሪሜህ፣ “በትሪፖሊ የሚኖሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ለዓመታት በቸልተኝነት ምክንያት ስጋት ውስጥ ወድቀዋል” ብለዋል።ሁኔታው ከትሪፖሊ ማዘጋጃ ቤት አቅም በላይ እንደሆነም ገልጸዋል።በኋላ ላይም ለአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ የሥራ መልቀቂያ አስገብተዋል።ፕሬዝዳንትጆሴፍ አውን በበኩላቸው “ያሉትን ክስተቶች እየተከታተልኩ ነው” ሲሉ በመላ አገሪቱ የሚገኙ የነፍስ አድን ሰራተኞችን እንዲንቀሳቀሱ ጥሪ አቅርበዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር ናዋፍ ሳላም የሕንፃዎቹን መፍረስ “ ሰብዓዊ አደጋ “ ሲሉ መንግሥታቸው እርዳታ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።በኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ ያለችው ሊባኖስ ሁለተኛ ትልቅ ከተማ የሆነችው ትሪፖሊ በተደጋጋሚ የሕንፃ መፍረስ አደጋዎች አጋጥመዋታል።ባለፈው ወር የአገሪቷ የአደጋ መከላከያ እና ምላሽ ሰጪ ተቋም በከተማዋ ከ100 በላይ ሕንፃዎች ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ለቀው እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ገልጿል።ያጋሩ, በሊባኖስ የመኖሪያ ሕንፃዎች ተደርምሰው 14 ሰዎች ሞቱ - 9 የካቲት 2026የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ እና የግብፁ ፕሬዝዳንት አል ሲሲ በካይሮ
የፎቶው ባለመብት,Egyptian Presidencyየሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ እና የግብፁ ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ ካይሮ ውስጥ ባደረጉት ውይይት ያላቸውን የደኅንነት ትብብር በማጠናከር ላይ መስማማታቸው ተዘገበ።ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ ወደ ካይሮ ያቀኑት የሶማሊያው ፕሬዝዳንት፤ ከፕሬዝዳንት አልሲሲ ጋር በሰጡት የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ “የሶማሊያን አንድነት የሚጋፋ የትኛውንም ተግባር በጋራ እንቃወማለን” ብለዋል።ግብፅ በበኩሏ በአፍሪካ ኅብረት የሶማሊያ የድጋፍ እና የማረጋጋት ተልዕኮ ሥር ወታደሮቿን ለመላክ በያዘችው ዕቅድ መሠረት ተግባራዊ እንደምታደርግ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።የግብፁ ፕሬዝዳንት ጨምረውም የሶማሊያ መረጋጋት ለቀጣናው ልማት እና ደኅንነት “ወሳኝ ጉዳይ ነው” በማለት ሶማሊያን ለመደገፍ አገራቸው የሚጠበቅባትን ታደርጋለች ብለዋል።ሶማሊያ የግዛቷ አካል እንደሆነች ለምትመለከታት ሶማሊላንድ እስራኤል የአገርነት ዕውቅና መስጠቷን ተከትሎ ግብፅ እና ሶማሊያ የጋራ አቋም ይዘው ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።ይህ በእንዲህ እንዳለ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ በአልጀዚራ ቴሌቪዥን ላይ በሰጡት ቃለ ምልልስ ላይ ሶማሊላንድ ከጋዛ የሚፈናቀሉ ፍልስጤማውያንን ለማስፈር እና ለእስራኤል ጦር ሰፈር ለመስጠት ተስማምታለች ማለታቸውን ሶማሊላንድ ወቅሳለች።ፕሬዝዳንቱ በቃለ ምልልሱ ላይ እስራኤል በሶማሊላንድ ውስጥ የጦር ሰፈር የምትመሠርት ከሆነ “እራሳችንን ለመከላከል ባለን አቅም ሁሉ እንፋለማለን” ሲሉ ተቃውሟቸውን አሰምተው ነበር።ነገር ግን የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት ቃል አቀባይ ሐሰን አደን በሰጡት ምላሽ ፕሬዝዳንቱ ያሉትን “እውነታ የሌለው ግልጽ ውሸት” በማለት ውድቅ አድርገውታል።ቃል አቀባዩ ጨምረውም የሶማሊያ መሪ አስተያየት “በውስጡ የገጠመውን ውድቀት በሌሎች ላይ ለማንጸባረቅ የሚፈለግ የተለመደው ዓይነት ያልተሳካለት አመራር አካሄድ ነው” በማለት ሶማሊያ የራሷን ደኅንነት እንኳን መጠበቅ ያልቻለች ናት በማለት ተናግረዋል።ያጋሩ, የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ እና የግብፁ ፕሬዝዳንት አል ሲሲ በካይሮ - 9 የካቲት 2026ሱዳን ዳግም ኢጋድን ተቀላቀለች
የፎቶው ባለመብት,@DrWorknehሱዳን ከሁለት ዓመት በኋላ ዳግም የምሥራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታት ድርጅትን መቀላቀሏን አስታወቀች። ወደ ድርጅቱ ዳግም መቀላቀሏን ይፋ ያደረጉት የድርጅቱ የወቅቱ ፕሬዚዳንት የጂቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ ናቸው።የምሥራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) ዋና ጸሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ሱዳን ወደ ቀጣናዊ ድርጅቱ ዳግም በመመለሷ የተሰማቸውን ደስታ ገለፀዋል።የኢጋድ የወቅቱ ሊቀመንበር የሆኑት የጂቡቲው ፕሬዚዳንት፤ ሱዳን ዳግም ቀጠናዊ ድርጅቱን መቀላቀሏን ያስታወቁት እሁድ ዕለት ነበር።ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ሱዳን ወደ ቀጣናዊ ድርጅት መመለሷን “ለቀጣናዊ አንድነት” ያላትን ቁርጠኝነት ያጋገጠ ነው ያሉ ሲሆን፤ እንዲሁም “በቀጣናው ውስጥ ላለው ሰላም፣ መረጋጋት እና ትብብር ያላትን” ፍላጎት የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል።ሱዳን ከኢጋድ አባልነቷ የወጣችው በኡጋንዳ በተዘጋጀው የድርጅቱ ጉባዔ ላይ የፈጥኖ ደራሽ አዛዡ ሞሐመድ ሀምዳን ዳጋሎ መገኘታቸውን በመቃወም ነው።የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል እአአ ከሚያዚያ 2023 ጀምሮ ከሱዳን ጦር ጋር እየተዋጋ ይገኛል።ሱዳን የኢጋድ መስራች አባል አገራት መካከል አንዷ መሆኗን ያስታወሱት የደርጅቱ ዋና ጸሐፊ ዳግም ወደ ድርጅቱ መመለሷ “የኢጋድን አንድነት እንደሚያጠናክር እና በቀጠናው ቅድሚያ የሚሰጣቸውን የጋራ ጉዳዮች የመፍታት አቅሟን እንደሚያሳድግ” ተናግረዋል።የወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበር የጂቢቲው ፕሬዚዳንት ሱዳን ወደ ድርጅቱ እንድትመለስ ላደረጉት ጥረትም አመሰግነዋል።ኢጋድ በምሥራቅ አፍሪካ የሚገኙ ስምንት አገራትን ያቀፈ ቀጣናዊ ድርጅት ሲሆን እነርሱም ኢትዮጵያ ፣ ጂቡቲ፣ ኤርትራ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳን እና ኡጋንዳ ናቸው።ኤርትራ በቅርቡ ከአባልነት ራሷን ማግለሏን ማስታወቋ ይታወሳል።ተቋሙ ቀጣናዊ ትብብር ላይ የተመሠረተ ፖለቲካዊ መረጋጋትና የምጣኔ ኃብት እድገት እንዲገኝ የሚሠራ ነው።ያጋሩ, ሱዳን ዳግም ኢጋድን ተቀላቀለች - 9 የካቲት 2026በአሜሪካ እና ኢራን መካከል የተጀመረው ድርድር መቀጠል እንዳለበት ሩሲያ ገለፀች
የፎቶው ባለመብት,Reutersየሩሲያ እና የኦማን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በስልክ ከተወያዩ በኋላ በኢራን እና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል የተጀመረው ድርድር መቀጠል አለበት አሉ።የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ እና የኦማኑ ባድር አል አሳዲ በሁለቱ ተደራዳሪ አገራት መካከል ወታደራዊ እሰጥ አገባን ለማስቀረት ንግግራቸው መቀጠል አለበት ብለዋል።የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ላይ ኦማን ሁለቱን አገራት ለማደራደር እያደረገች ያለውን ጥረት አድንቋል።በኢራን እና በአሜሪካ መካከል ድርድር የተጀመረው አርብ ዕለት ነበር።የኢራን ልዑካን ቡድን በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አባስ አራጋቺ የተመራ ሲሆን በስቲቭ ዊትከር ከተመራው የአሜሪካው ተደራዳሪ ቡድን ጋር በኦማን ተገናኝቶ ተነጋግሯል።እንደ ኦማን የውጭ ጉዳይ ሚኒሲቴር መግለጫ ተደራዳሪዎቹ በኢራን ኒውክለር ፕሮግራም ላይ ጠንካራ ውይይት ያካሄዱ ሲሆን ንግግሩንም የመቀጠል ፍላጎት እንዳላቸው ገልጿል።ያጋሩ, በአሜሪካ እና ኢራን መካከል የተጀመረው ድርድር መቀጠል እንዳለበት ሩሲያ ገለፀች - 9 የካቲት 2026የኢራን የበላይ መሪ አሊ ኻሜኒ ባልተለመደ ሁኔታ በኢራን አብዮት በዓል ላይ ሳይገኙ ቀሩ
የፎቶው ባለመብት,Reutersበየዓመቱ የካቲት ወር መጀመሪያ ላይ የሚከበረው የኢራን አብዮት መታሰቢያ ዝግጅት ላይ ባልተለመደ ሁኔታ የኢራን የበላይ መሪ አሊ ኻሜኒ ሳይገኙ ቀሩ።በእርሳቸው ምትክ የኢራን ጦር የበላይ አዛዥ የሆኑት ሜጀር ጄነራል አብዶልራሂም ሚሳቪ ክብረ በዓሉ ላይ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል።የሚሳቪ ጠቅላይ መሪውን ወክለው በመገኘታቸው የተሰማቸውን ክብር ለታዳሚዎቹ ባደረጉት ንግግር ላይ ገልጸዋል።በኢራኑ የበላይ መሪ ምትክ በበዓሉ ላይ የታደሙትን የተለያዩ ወታደራዊ አዛዦችን ያገኙት ሚሳቪ በንግግራቸው ላይ ከአሜሪካ ጋር ሊኖር ስለሚችል ግጭት በማንሳት “ቀጠናዊ ጦርነት ለመጀመር ምንም ፍላጎቱ የለንም” ብለዋል።ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ተቃዋሚዎች አያቶላህ አሊ ኻሜኒ ከሥልጣን እንዲወርዱ እና በሕዝባዊ አብዮት የመጣውን የእስላማዊውን ሪፐብሊክ አገዛዝ እንዲያበቃ ሲጠይቁ ነበር።በኢራን ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች ለሳምንታት በተካሄዱት የተቃውሞ ሰልፎች ላይ የተሳተፉ በርካቶች ሲታሰሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ደግሞ መገደላቸው ይታወሳል።ያጋሩ, የኢራን የበላይ መሪ አሊ ኻሜኒ ባልተለመደ ሁኔታ በኢራን አብዮት በዓል ላይ ሳይገኙ ቀሩ - 9 የካቲት 2026ታዋቂው ሆንግ ኮንጓዊ የሚዲያ ባለቤት እና የዲሞክራሲ ተሟጋች የ20 ዓመት እስር ተፈረደበት
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየሆንግ ኮንግ ፍርድ ቤት የዲሞክራሲ አቀንቃኝ እና የሚዲያ ባለቤት የሆነው ጂሚ ላይ ከብሔራዊ ደኅንነት ጋር ተያይዞ በቀረበበት ክስ ጥፋተኛ ሆኖ በማግኘቱ የ20 ዓመት እስር ፈረደበት።ቻይና ከከተማዋ መረጋጋት ጋር በተያያዘ አስፈላጊ ነው በምትለው እና አወዛጋቢ በሆነው የብሔራዊ ደኅንነት ሕግ መሠረት የተሰጠው ይህ የፍርድ ውሳኔ በጣም ከባዱ ነው ተብሏል።ላይ የብሪታኒያ ፓስፖርት ያለው ሲሆን የቻይና መንግሥትን ክፉኛ በመተቸት ይታወቃል።አፕል ዴይሊ የተሰኘ በየዕለቱ የሚታተም ጋዜጣ ባለቤት የሆነው ላይ በተደጋጋሚ በአገሪቱ ውስጥ ለተካሄዱ የተቃውሞ ሠልፎች መነሻ ሆኗል።ሰኞ ዕለት ስድስት የጋዜጣው የቀድሞ ኃላፊዎች ከስድስት እስከ 10 ዓመት እስር ተፈርዶባቸው በቁጥጥር ሥር ውለዋል።በዲሞክራሲ አቀንቃኞች ዘንድ እንደ ጀግና የሚቆጠረው ላይ፣ በቤይጂንግ ግን አንደ አገር ከዳተኛ ይወነጀላል።በተደጋጋሚ የቻይና መንግሥት የሚያቀርበብትን ክስ የሚያስተባብለው የሚዲያ ባለቤቱ ላይ የሆንግ ኮንግ እሴቶች የሆኑ የሚላቸው የሕግ የበላይነት እና የመናገር ነጻነትን እንዲሚሰብክ ይናገራል።የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲን በድፍረት በመጋፈጡ ዋጋ እየከፈለ ያለው ቢልየነርያጋሩ, ታዋቂው ሆንግ ኮንጓዊ የሚዲያ ባለቤት እና የዲሞክራሲ ተሟጋች የ20 ዓመት እስር ተፈረደበት
