
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ ስማቸውን ያልጠቀሷቸው ጎረቤት አገራት እስራኤል ለሶማሊላንድ የሰጠችውን የአገርነት ዕውቅና ይደግፋሉ ሲሉ ከሰሱ።
ጭምቅ ሃሳብ
- የሶማሊያው መሪ ጎረቤት አገራት እስራኤል ለሶማሊላንድ የሰጠችውን ዕውቅና ይደግፋሉ ሲሉ ከሰሱ
- የሳዑዲ አረቢያ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከኤርትራው ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ
- አሜሪካ በዓለም ትልቁ የጦር መርከቧን ከቬንዙዌላ የባሕር ዳርቻ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ አንቀሳቀሰች
- የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዳግመኛ ኢራንን አስጠነቀቁ
- የአሜሪካ ጦር በሶሪያ ካለው ቁልፍ ወታደራዊ የጦር ሰፈር ጠቅልሎ ወጣ
- ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኢራን “በጣም ከባድ እርምጃ” ይጠብቃታል ሲሉ አስጠነቀቁ
- ጋና በየሳምንቱ ረቡዕ የባህል ልብስ የሚለበስበት ቀን እንዲሆን አወጀች
- 1.3 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ያላቸው የቀድሞው የዛምቢያ ፕሬዚዳንት ልጅ ንብረቶች እንዲወረሱ ታዘዘ
- ዚምባብዌ የፕሬዚዳንቷን የሥልጣን ዘመን ለማራዘም የሚያስችል አዲስ ረቂቅ ሕግ አወጣች
- በካናዳ ትምህርት ቤት ላይ በተከፈተ ተኩስ ሰባት ሰዎች ተገደሉ
- የግብፅ ፕሬዝዳንት ጉብኝት በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ
- ኢራን ሁሉም ማዕቀቦች የሚነሱላት ከሆነ የበለጸገ ዩራኒየሟን የጥራት ደረጃ ልትቀንስ እንደምትችል አስታወቀች
የቀጥታ ሽፋን
- ከ 7 ሰአት በፊትከቤጂንግ ጋር ውጥረት ውስጥ የገባችው ጃፓን የቻይና መርከብን በቁጥጥር ስር አዋለች
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየጃፓን ባለስልጣናት ለምርመራ እንዲቆም ትዕዛዝ ሲሰጠው ለማምለጥ ሞክሯል ያሉትን የቻይና አሳ አጥማጅ መርከብ በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን አስታወቁ።ይህ የጃፓን እርምጃ ከቻይና ጋር የገባችበትን ውጥረት ሊያባብሰው እንደሚችል ተነግሯል።የአገሪቱ የአሳ ሀብት አስተዳደር ኤጀንሲ እንደገለጸው መርከቡ ሐሙስ ዕለት በቁጥጥር ስር የዋለው በደቡብ ምዕራብ ናጋሳኪ ግዛት አቅራቢያ በሚገኘው የጃፓን ልዩ የኢኮኖሚ ቀጣና ውስጥ ነው።የመርከቡ ካፒቴንም እንደተያዘ ተገልጿል። እንደ ኤጀንሲው መረጃ ከሆነ በመርከቡ ላይ የ47 ዓመቱን ቻይናዊ ካፒቴንን ጨምሮ 11 ሰዎች ነበሩ።የተያዘው መርከብ ከፍተኛ አቅም ያለው “ታይገር ኔት አሳ አጥማጅ ጀልባ” እንደሆነ ባለስልጣናት እና የጃፓን መገናኛ ብዙኃን ገልጸዋል።መስሪያ ቤቱ ባወጣው መግለጫ፤ “የመርከቡ ካፒቴን የአሳ ማጥመድ ተቆጣጣሪዎች ለምርመራ እንዲቆም አዝዘውት የነበረ ቢሆንም መርከቡ ትዕዛዙን ሊያከብር አልቻለም፤ አምልጧልም” ብሏል።ኤጀንሲው፤ የቻይናን አሳ አጥማጅ መርከብን በቁጥጥር ስር ሲያውል ከአውሮፓውያኑ 2022 ወዲህ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ጉዳዩን በተመለከተ እስካሁን ቻይና ምላሽ አልሰጠችም።ጃፓን ይህንን እርምጃ የወሰደችው አገሪቱ ከቻይና ጋር ያላት ግንኙነት በሻከረበት በዚህ ወቅት ነው።የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳናኤ ታካኢቺ ባለፈው ኅዳር ላይ ቻይና ታይዋንን በኃይል ለመያዝ የምትሞክር ከሆነ ጃፓን ጣልቃ እንደምትገባ መጠቆማቸው ቤጂንግን አስቆጥቷል።የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሰጠው ምላሽ፤ የጃፓኑን መሪ ንግግር “በጣም መጥፎ” ሲል ገልጾታል። ቻይና ቶኪዮ ውስጥ የሚገኙትን አምባሳደሯን ጠርታ ያነጋገረች ሲሆን ለትምህርት ወደ ጃፓን የሚሄዱ ዜጎቿን ውሳኔያቸውን እንዲያጤኑ አስጠንቅቃለች።ያጋሩ, ከቤጂንግ ጋር ውጥረት ውስጥ የገባችው ጃፓን የቻይና መርከብን በቁጥጥር ስር አዋለች - ከ 9 ሰአት በፊትየአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አዲስ የጂኦፖለቲካ ዘመን ላይ ነን ሲሉ አውሮፓን አስጠነቀቁ
የፎቶው ባለመብት,Reutersበሙኒክ የጸጥታ ኮንፈረንስ ላይ ተጠባቂ ንግግር ለማድረግ ወደ አውሮፓ የተጓዙት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ፤ ወሳኝ ሲሉ ስለገለጹት ምዕራፍ እንዲሁም “አዲስ ዘመን” ማስጠንቀቂያ አዘል መልዕክት አስተላለፉ።ጀርመን ውስጥ በሚካሄደው በዚህ ወሳኝ ጉባኤ ላይ የሚሳተፈው የአሜሪካ ልዑክ የሚመራው በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ነው።ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ግሪንላንድን ለመጠቅለል ያላቸውን ፍላጎት በአጽንኦት በመግለጽ የዴንማርክ ሉዐላዊነት ላይ አደጋ ከቃጡ በኋላ አሜሪካ በትልቅ ዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ስትሳተፍ ይህ የመጀመሪያው ነው።ሩቢዮ ጉዟቸውን ከመጀመራቸው በፊት ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ በዚህ ጉባኤ ላይ ለአውሮፓውያን የሚያስተላልፉት መልዕክት ባለፈው ዓመት ከተደረገው በተሻለ የሚያስታርቅ ይሆን እንደሆን ተጠይቀዋል።ባለፈው ዓመት በተካሄደው ጉባኤ ላይ የአሜሪካው ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ የአውሮፓ አገራትን ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት እና የስደት ፖሊሲዎች በማንሳት ጠንካራ ትችት ሰንዝረዋል።የጄዲ ቫስ ንግግር ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ለአንድ ዓመት የዘለቀ ውጥረት ፈጥሮ ቆይቷል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሩቢዮ ለጥያቄው ሲመልሱ፤ “ዓለም በፊታችን ላይ በፍጥነት እየተለወጠች ነው” ብለዋል።“የምንኖረው በአዲስ የጂኦፖለቲካ ዘመን ውስጥ ነው። ይህ [ሁኔታ] ሁላችንም አዲሱ ዘመን ምን እንደሚመስል እና የእኛ ሚና ምን መሆን እንዳለበት እንደገና እንድንመረምር የሚያደርገን ነው” ሲሉም ተናግረዋል።ከቀናት በፊት የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት አማኑኤል ማክሮን፤ አውሮፓ ከአሜሪካ ጥገኝነት ለመላቀቅ መዘጋጀት እንዳለባት አሳስበው ነበር። የኔቶ ዋና ጸሐፊ ማርክ ሩተ በበኩላቸው በአትላንቲክ ዙሪያ ያሉ አገራት ግንኙነት እየተጠናከረ መሆኑን እንዲሁም ይህንን ማድረግ ከመቼውምጊዜ በላይ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።በሙኒክ የጸጥታ ኮንፈረንስ ላይ በዩክሬን የሚደረገው ጦርነት፣ ከቻይና ጋር የተፈጠረው ውጥረት፣ እንዲሁም በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ሊደረግ የሚችል የኒውክሌር ስምምነት በአጀንዳነት እንደሚቀርቡ ይጠበቃል።ያጋሩ, የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አዲስ የጂኦፖለቲካ ዘመን ላይ ነን ሲሉ አውሮፓን አስጠነቀቁ - 13 የካቲት 2026ደቡብ አፍሪካ ወንበዴዎችን ለመቆጣጠር ሠራዊቷን ልታሰማራ ነው
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ፤ የወንጀል ቡድኖችን እና ሕገ ወጥ የማዕድን ቁፋሮን ለማስቆም ፖሊስ የሚያደርገውን ጥረት ለማገዝ የአገሪቱን ሠራዊት እንደሚያሰማሩ ተናገሩ።ከፍተኛ ቁጥር ያለው ግድያ ከሚፈጽማባቸው የዓለም አገራት አንዷ በሆነችው ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በወንበዴዎች የሚፈጸም ጥቃት ትልቅ ችግር ነው።ፕሬዝዳንት ራሳፎሳ የአገሪቱን ሁኔታ በተመለከተ ሐሙስ ዕለት ባደረጉት ዓመታዊ ንግግር፤ “በአሁኑ ወቅት የተደራጀ ወንጀል ለዴሞክራሲያችን፣ ለማኅበረሰባችን እና ለኢኮኖሚ እድገታችን ድርስ ስጋት ሆኗል” ብለዋል።”የደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ መከላከያ ሠራዊት ፖሊስን እንዲደግፍ አሰማራለሁ” ሲሉም ዕቅዳቸውን ይፋ አድርገዋል።ባለፈው ወር የፖሊስ ሚኒስትሩ ፊሮዝ ካቻሊያ፤ ፖሊስ የሰዎችን ሕይወት የሚቀጥፉ ወንጀሎችን የሚፈጽሙትን ወንበዴዎች እስካሁን ማሸነፍ እንዳልቻለ አምነዋል። ይህ የሚኒስትሩ ንግግርም በአገሪቱ ያለውን የወንጀል ቀውስ ምን ያህል ስር የሰደደ እንደሆነ የሚያመለክት ሆኗል።ራማፎሳ በፓርላማ ባደረጉት ንግግር፤ የፖሊስ እና የመከላከያ ሠራዊት አዛዦች “በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ የፀጥታ ኃይሎች የት መሰማራት እንዳለባቸው” የሚያሳይ ዕቅድ እንዲያዘጋጁ ትዕዛዝ መስጠታቸውን ገልጸዋል።ሠራዊቱ የወንበዴዎች ጥቃት እና ሕገ ወጥ የማዕድን ቁፋሮ ወደተባባሰባቸው ዌስተርን ኬፕ እና ጋውቴንግ ግዛቶች ሊሰማራ እንደሚችል ጠቁመዋል።“ዌስተርን ኬፕ ውስጥ ያሉ ልጆች በወንበዴዎች ጦርነት የተባራሪ ጥይት ሰለባ እየሆኑ ነው።ፕሬዝዳንቱ “እዚህ ዌስተርን ኬፕ ውስጥ ልጆች በወንጀል ቡድኖች የተኩስ ልውውጥ መካከል እየተቀጠፉ ነው። ጋውቴንግ ደግሞ ሕዝቡ ሰዎች በሕገ ወጥ ማዕድን አውጪዎች ከመኖሪያ ቤታቸው እየተባረሩ ነው” ብለዋል።የደቡብ አፍሪካ ባለሥልጣናት፤ በአገሪቱ ለሚታየው የተደራጀ የወንጀል እንቅስቃሴ ተጠያቂ የሚያደርጉት “ዛማ ዛማስ” ተብለው የሚጠሩትን አካላት ነው። እነዚህ ታጣቂ ቡድኖች ሕጋዊ ሰነድ የሌላቸው የውጭ አገር ዜጎችን በአባልነት ይዘዋል።በአገሪቱ ያለውን ከፍተኛ የወንጀል ምጣኔ ለመግታት ሠራዊት ከማሰማራት በተጨማሪ ሌሎች እርምጃዎችም እንደሚወዱ ፕሬዝዳንት ራማፎሳ ገልጸዋል።5,500 አዳዲስ የፖሊስ መኮንኖች መቅጠርን፣ የመረጃ (አቅምን ማጠናከርን እንዲሁም የተደራጁ ወንጀል ቡድኖችን ዒላማ ማደርግ ከአዲሶች እርምጃዎች መካከል ተጠቅሰዋል።የፖሊስ መረጃ እንደሚያሳየው ባለፈው ዓመት ከሚያዝያ እስከ መስከረም ባለው ጊዜ ውስጥ በአንድ ቀን በአማካይ 63 ሰዎች ይገደሉ ነበር።ያጋሩ, ደቡብ አፍሪካ ወንበዴዎችን ለመቆጣጠር ሠራዊቷን ልታሰማራ ነው - 13 የካቲት 2026የሶማሊያው መሪ ጎረቤት አገራት እስራኤል ለሶማሊላንድ የሰጠችውን ዕውቅና ይደግፋሉ ሲሉ ከሰሱ
የፎቶው ባለመብት,Villa Somaliaየምስሉ መግለጫ,የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድየሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ ስማቸውን ያልጠቀሷቸው ጎረቤት አገራት እስራኤል ለሶማሊላንድ የሰጠችውን የአገርነት ዕውቅና ይደግፋሉ ሲሉ ከሰሱ።ፕሬዝዳንቱ ለንደን ውስጥ ለሚታተመው አሽራቅ አል-አውሳጥ ለተባለው የአረብኛ ጋዜጣ በሰጡት ቃለ ምልልስ ላይ አገራቱ እስራኤል ለሶማሊላንድ የሰጠችውን ዕውቅና ለራሳቸውን ጥቅም ሊያውሉት ይፈልጋሉ ሲሉ ከስሰዋል።ፕሬዝዳንት ሐሰን ለዚህ ክሳቸው የትኛውንም አገር በስም ያልጠቀሱ ሲሆን፣ “አንዳንድ የቀጣናው አገራት ይህንን አጋጣሚ የሶማሊያን አንድነት እና የቀጣናው መረጋጋት ለአደጋ አጋልጠው ጠባብ እና የአጭር ጊዜ ጥቅማቸውን ለማሳካት ይፈልጋሉ” ብለዋል።ለዚህ ክሳቸው “የትኛውንም አገር በስም መጥቀስ አልፈልግም” ያሉት ፕሬዝዳንቱ “ነገር ግን ይህንን ዕውቅና አንዳንዶች ውስን ጥቅም ማግኘት የሚያስችላቸው አድርገው ሊመለከቱት ይችላሉ” በማለት ተናግረዋል።እስራኤል ባለፈው ታኅሣሥ ወር ሶማሊያ የግዛቷ አካል አድርጋ ለምትቆጥራት እና የራሷን ነጻ አገርነት ላወጀችው ሶማሊላንድ ዕውቅና ከሰጠች በኋላ ሶማሊያን በመደገፍ በርካታ አገራት እና ተቋማት ተቃውሟቸውን ገልጸዋል።ነገር ግን የሶማሊያ ጎረቤት ከሆኑት አገራት መካከል አስካሁን በይፋ ተቃውሟቸውን ወይም ድጋፋቸውን ያልገለጹት ኢትዮጵያ እና ኬንያ ናቸው።ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር ከሁለት ዓመት በፊት ከሶማሊላንድ ጋር ስምምነት ላይ በደረሰችበት ጊዜ ከሶማሊያ ጋር ውዝግብ ውጥ ገብተው እንደነበር ይታወሳል።የሶማሊያው ፕሬዝዳንት የአገራቸው የግዛት አንድነት ሊታለፍ የማይገባው “ቀይ መስመር” ነው በማለት አስጠንቅቀው፤ መንግሥታቸው የሶማሊያን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ የተለያዩ ፖሊሲዎችን እየተጠቀመ ነው ብለዋል።ሶማሊላንድ ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ የራሷን መንግሥት መሥርታ በነጻ አገርነት ብትቆይም በቅርቡ የአገርነት ዕውቅና ከሰጠቻት እስራኤል ውጪ ከየትኛውም አገር ዕውቅናን አላገኘችም።ያጋሩ, የሶማሊያው መሪ ጎረቤት አገራት እስራኤል ለሶማሊላንድ የሰጠችውን ዕውቅና ይደግፋሉ ሲሉ ከሰሱ - 13 የካቲት 2026የሳዑዲ አረቢያ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከኤርትራው ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ
የፎቶው ባለመብት,MOIየምስሉ መግለጫ,የሳዑዲ አረቢያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋሊድ አብዱልከሪም አል ካሪጅ ከኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳላህ ጋርየሳዑዲ አረቢያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋሊድ አብዱልከሪም አል ካሪጅ ከኤርራው ፕሬዚዳንት ጋር በአሥመራ ተገናኝተው መወያየታቸው ተገለፀ።የኤርትራው ፕሬዚዳንት ከሳዑዲ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር የተገናኙት ሐሙስ የካቲት 5/2018 ዓ.ም. መሆኑን የአገሪቱ ማስታወቂያ ሚኒስትር በይፋዊ የኤክስ ገጹ ላይ ይፋ አድርጓል።የሳዑዲ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢንጂነር ማሌን ቢን አብዱልካሪም አል ካሬጂ እና ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ሁለቱ አገራት ያላቸውን ወዳጅነት እና ትብብር ለማጠናከር መነጋገራው ተገልጿል።ከዚህም በተጨማሪ የሳዑዲ ልዑካን ከኤርትራው ፕሬዚዳንት ጋር በቀጠናው እና በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ተነጋግረዋል።በዚህ ሳምንት አጋማሽ ላይ የሳዑዲ አረቢያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልዑል ፋይሰል ቢን ፋርሐን ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በአዲስ አበባ በሁለትዮሽ እንዲሁም ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸው ተገልጿል።የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና የሳዑዲው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ውይይት በዝርዝር ባይገለጽም “በቁልፍ ዘርፎች ላይ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ትብብር ማጠናከር” እንዲሁም “የሁለቱም አገራት ፍላጎት በሆኑ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ መተባበር” ላይ ያተኮረ እንደሆነ ተገልጿል።የሳዑዲ አረቢያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለሥልጣናት ወደ ሁለቱ አገራት ጉብኝት ያደረጉት ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ዳግም ወፈደ ግጭት ይገባሉ የሚለው ስጋት ባየለበት ወቅት ነው።የኤርትራው ፕሬዚዳንት እና የሳዑዲ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በበኩላቸው በቀይ ባሕር ዙሪያ የሚገኙ አገራት የቀጠናውን ሰላም እና ደኅንነት ዋስትና በማረጋገጥ ረገድ የሚኖራቸው ሚና ላይ መነጋራቸውን የአገሪቱ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ገልጿል።የሳዑዲ አረቢያ ልዑክ ከኤርትራው ፕሬዚዳንት ጋር “በቀይ ባሕር ዙሪያ የሚገኙ አገራት ተለዋዋጭ በሆነው ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች እና አዝማሚያዎች ባሻገር የአካባቢውን ሰላም እና ደኅንነት በማረጋገጥ ረገድ ስለሚኖራቸው አስተዋጽኦ ተነጋግረዋል።”ሁለቱ አገራት በፖለቲካ፣ በምጣኔ ሀብት፣ በደኅንነት፣ በባህል እና በማኅበራዊ ዘርፎች ከዚህ ቀደም የደረሱባቸውን ሁለትዮሽ ስምምነቶች ተግባራዊ ለማድረግ መነጋገራቸው ተገልጿል።ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አወርቂ በታኅሣሥ ወር መጀመሪያ ላይ ወደ ሳዑዲ አረቢያ በማቅናት ከአልጋ ወራሽ ልዑል መሐመድ ቢን ሳልማን ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል።የኢትዮጵያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌድዮን ጢሞቴዎስ ባለፈው ሳምንት ወደ ሳዑዲ አረቢያ ተጉዘው ከልዑል ፋይሰል ቢን ፋርሐን ጋር መወያየታቸው ይታወሳል።ከሳዑዲው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልዑል ፋይሰል ቢን ፋርሐን ጋር በተደረገው ውይይት “ሁለቱ አገራት የአፍሪካ ቀንድን ሰላም እና መረጋጋትን ለማስጠበቅ” በጋራ ለመሥራት እንደተስማሙ ተገልጿል።ያጋሩ, የሳዑዲ አረቢያ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከኤርትራው ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ - 13 የካቲት 2026አሜሪካ በዓለም ትልቁ የጦር መርከቧን ከቬንዙዌላ የባሕር ዳርቻ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ አንቀሳቀሰች
የፎቶው ባለመብት,Reutersአሜሪካ በዓለም ካሉ ግዙፍ የጦር አውሮፕላን ተሸካሚ መርከቦች ትልቁ የሆነውን እና ወደ ቬንዙዌላ የባሕር ዳርቻ አሰማርታው የነበረውን የጦር መርከብ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ እንዲያቀና አዘዘች።አሶሺየትድ ፕሬስ እንደዘገበው ዩኤስኤስ ጄራርድ ፎርድ የተባለው ግዙፍ የጦር መርከብ “ከካሪቢያን ባሕር ወደ መካከለኛው ምሥራቅ እንዲጓዝ” ትዕዛዝ ተሰጥቶታል።የዜና አገልግሎቱ ከአሜሪካ የመከላከያ መሥሪያ ቤት ምንጭ ጠቅሶ እንዳመለከተው “ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን ላይ ወታደራዊ እርምጃ ሊወሰድ ይችላል ባሉት መሠረት” የጦር አውሮፕላን ተሸካሚው መርከብ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ተንቀሳቅሷል።በአሜሪካ የቢቢሲ አጋር የሆነው ሲቢኤስ ሦስት የአሜሪካ ባለሥልጣናትን ጠቅሶ “ጄራርድ ፎርድ የጦር መርከብ እና አጋዥ መርከቦች ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ይሰማራሉ ተብሎ ይጠበቃል” በማለት ዜናውን አረጋግጧል።እጅግ ዘመናዊ የሆነው ይህ አውሮፕላን ተሸካሚ ግዙፍ የጦር መርከብ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ሲያመራ ከሳምንታት በፊት ወደ አካባቢው የተሰማራውን አብርሃም ሊንከን የተባለውን ሌላ ተመሳሳይ መርከብን በመቀላቀል ከፕሬዝዳንት ትራምፕ የሚሰጣቸውን ትዕዛዝ ይጠብቃሉ።አሶሺየትድ ፕሬስ እንዳለው አሁን ወደ መካከለኛው ምሥራቅ እንዲጓዝ የታዘዘው ጄራርድ ፎርድ የጦር መርከብ ባለፈው ጥምት ወር ነበር ከሜዲትራኒያን ባሕር ተነስቶ ቬንዙዌላ ላይ ጥቃት ከመፈጸሙ በፊት ወደ ካሪቢያን የደረሰው።አሁን ደግሞ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ እንዲያቀና የታዘዘው አሜሪካ እና ኢራን የሚያደርጉት ድርድር ውጤት የማያስገኝ ከሆነ ወታደራዊ እርምጃ በኢራን ላይ እንደሚወስዱ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በተናገሩት መሠረት ጫና ለመፍጠር ሊሆን እንደሚችል ዎል ስትሪት ጆርናል ከሁለት ዘግቦ ነበር።ፕሬዝዳንት ትራምፕ እና ምክትላቸው ጄዲ ቫንስ ባለፉት ቀናት ተጨማሪ የጦር መርከብ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ እንደሚያሰማሩ እና “ፕሬዝዳንቱ ሁሉንም አማራጮች እንደሚጠቀሙ” ገልጸው፤ ነገር ግን ቅድሚያ የሚሰጡት ከኢራን ጋር ስምምነት ላይ መድረስ እንደሆነ አስታውቀዋል።
የፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,ዩኤስኤስ ጄራርድ ፎርድ በዓለም ትልቁ የጦር አውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ ነውያጋሩ, አሜሪካ በዓለም ትልቁ የጦር መርከቧን ከቬንዙዌላ የባሕር ዳርቻ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ አንቀሳቀሰች - 13 የካቲት 2026የአሜሪካ ጦር በሶሪያ ካለው ቁልፍ ወታደራዊ የጦር ሰፈር ጠቅልሎ ወጣ
የፎቶው ባለመብት,Reutersየአሜሪካ ጦር ሐሙስ ዕለት ከሶሪያ ወሳኝ አል ታንፍ ከተባለው ወታደራዊ ካምፕ ጠቅልሎ መውጣቱን አስታወቀ።የአሜሪካ ጦር ለቅቆ የወጣው ወታደራዊ ካምፕን ለሶሪያ ጦር ማስረከቡን አስታውቋል።አሜሪካ እና ሶሪያ በቅርቡ የሁለቱን አገራት ወታደራዊ ትብብር የሚያጠናክር ስምምነት ፈርመው ነበር።አል ታንፍ ወታደራዊ ጦር ሰፈር በሶሪያ፣ በዮርዳኖስ እና በኢራቅ ድንበር አካባቢ የሚገኝ ነበር።ወታደራዊ ጦር ሰፈሩ የተመሠረተው በአውሮፓውያኑ 2014 ሶሪያ የእርስ በርስ ጦርነት ላይ በነበረችበት ወቅት ነበር።አሜሪካ በኢስላሚክ ስቴት ታጣቂዎች ላይ ለምትፈጽመው ጥቃት ይህ የጦር ካምፕ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ነበረው ተብሏል።የእስላሚክ ስቴት በአንድ ወቅት ሰፊ የኢራቅ እና የሶሪያ አካባቢዎችን ይቆጣጠር የነበረ ሲሆን፣ በአውሮፓውያኑ 2019 ተሸንፏል።ከዚያ በኋላ ግን የጦር ሰፈሩ የሚገኘው ደማስቆ እና ቴህራንን በሚያገናኘው መንገድ አቅራቢያ በመሆኑ አሜሪካ ከኢራን ጋር ላላት ፍጥጫ ስትራቴጂክ ስፍራ በመሆን እያገለገለ ነበር።ዋሺንግተን ጦር ሰፈሩን ይዛ መቆየት ፈልጋ የነበረ ቢሆንም፤ የሶሪያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ባሽር አል አሳድ በ2024 መጨረሻ ላይ ከሥልጣን መነሳታቸውን ተከትሎ ውሳኔዋን ዳግም አጢናዋለች።የሶሪያ መከላከያ ሚኒስቴር የጦር ካምፑን መረከቡን ይፋ አድርጓል።ያጋሩ, የአሜሪካ ጦር በሶሪያ ካለው ቁልፍ ወታደራዊ የጦር ሰፈር ጠቅልሎ ወጣ - 13 የካቲት 2026የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዳግመኛ ኢራንን አስጠነቀቁ
የፎቶው ባለመብት,Bloomberg via Gettyየአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቴህራን በኒውክሌር መርሃ ግብሯ ላይ ስምምነት ላይ መድረስ ካልቻለች “በጣም ከባድ የሆነ መዘዝ” ሊገጥማት እንደሚችል በመግለጽ በድጋሚ አስጠነቀቁ።የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን ከሥምምነት ላይ መድረስ አለባቸው ካሉ በኋላ ይህንንም በሚቀጥለው ወር ማድረግ ይቻላል ብለዋል።አክለውም ስምምነት ላይ የማይደረስ ከሆነ ግን ወደ ሁለተኛው ዙር እርምጃ እንደሚገቡ እና ያም ለኢራን “በጣም ከባድ” እንደሚሆን ተናግረዋል።ትራምፕ ለመገናኛ ብዙኃን ሲናገሩ ስምምነት የመድረስ አስፈላጊነት ላይ አፅንዖት ሰጥተዋል።”ከኢራን ጋር ስምምነት ላይ መድረስ አስፈላጊ ነው፤ ይህ ካልሆነ ግን ሁኔታው በጣም የከፋ ሊሆን ይችላል። ምንም ስምምነት ላይ መድረስ ካልተቻለ፣ የኢራን ሁኔታ በጣም ከባድ እና በጣም የከፋ ይሆናል” ብለዋል።“ከስምምነት ላይ መድረስ አለብን፤ አለበለዚያ ሁኔታዎች የበለጠ ይካረራሉ እና አስቸጋሪ ይሆናሉ” ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ድርድሩ እንዲቋረጥ ጠይቀዋቸው እንደሆን ተጠይቀው “እንደዚያ አልተነጋገርንም። የምፈልግ ከሆነ ግን አነጋግራቸዋለሁ” ብለዋል።ፕሬዚዳንቱ ኢራናውያን “መጀመርያ ላይ መስማማት ነበረባቸው ያንን ማድረግ ስላልቻሉ ወደ ዘመቻ ‘ሚድናይት ሀመር’ ገባን። አሁን ከስምምነት ላይ የማይደርሱ ከሆነ ለኢራን እጅግ ከባድ ይሆናል።”ኢራን እና ዩናይትድ ስቴትስ ዳግም ድርድር የጀመሩት ባለፈው ሳምነት አርብ በኦማን ዋና ከተማ መስካት ነበር።ያጋሩ, የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዳግመኛ ኢራንን አስጠነቀቁ - 12 የካቲት 2026በሱዳን በደረሰ የጀልባ አደጋ ቢያንስ 21 ሰዎች ሞቱ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesበሰሜናዊ ሱዳን በናይል ወንዝ ላይ የመንገደኞች ጀልባ ሰጥማ ቢያንስ 21 ሰዎች መሞታቸውን የሱዳን የሐኪሞች ቡድን ለቢቢሲ ገለጸ።ሱዳን ዶክተርስ ኔትዎርክ የተባለው የሐኪሞች ቡድን ጀልባዋ ወደ 30 የሚጠጉ ሰዎችን አሳፍራ በታይባ አል ኻዋድ እና በዴም አል ቃራይ መንደሮች መካከል እየተጓዘች ነበር ብሏል።ከተሳፋሪዎቹ መካከል ሴቶች፣ አረጋውያን እና ሕፃናት ይገኙበታል።የቡድኑ ቃል አቀባይ ዶክተር መሐመድ ፈይሰል ሐሰን “ያልወጡ አስክሬኖች ሊኖሩ ስለሚችሉ የነፍስ አድን ቡድኖች ሥራቸውን ቀጥለዋል” ብለዋል።ኤኤፍፒ የዜና ወኪል ሐሙስ ዕለት 21 አስክሬኖች መውጣታቸውን የሪቨር ናይል ግዛት ባለሥልጣናትን ጠቅሶ ዘግቧል።የሐኪሞች ቡድኑ ቀደም ብሎ ባወጣው መግለጫ ስድስት ሰዎች ከአደጋው መትረፋቸውን ገልጿል።ጀልባዋ የተገለበጠችው ረቡዕ ዕለት ምሽት በሸንዲ አካባቢ በነበረው ኃይለኛ ማዕበል ምክንያት እንደሆነ የዐይን እማኞች ተናግረዋል።በናይል ወንዝ ላይ አገልግሎት የሚሰጡ ጀልባዎች የግል ንብረት ሲሆኑ፣ ባለሥልጣናት በእነዚህ ጀልባዎች ላይ ተገቢ የቁጥጥር ሥርዓቶች እንዲሁም የደኅንነት እርምጃዎች እንደሌሏቸው ዶክተር መሐመድ ተናግረዋል።ባለሥልጣናት በዚህ ላይ የሰጡት ምላሽ የለም።በአገሪቷ በተለይ የገጠር መንደሮችን የሚያገናኙ ድልድዮች ባለመኖራቸው ምክንያት የናይል ወንዝን ለማቋረጥ አገልግሎት ላይ የሚውሉ ባህላዊ ጀልባዎች ብዙውን ጊዜ አደጋዎች ያጋጥማቸዋል።ያጋሩ, በሱዳን በደረሰ የጀልባ አደጋ ቢያንስ 21 ሰዎች ሞቱ - 12 የካቲት 2026ኪም ጆንግ ኡን የ13 ዓመት ልጃቸው ተተኪያቸው እንድትሆን መምረጣቸው ተገለጸ
የፎቶው ባለመብት,KCNA via Reutersየሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆን ኡን 13 ዓመቷ እንደሆነ የሚታመነውን ልጃቸውን ተተኪያቸው አድርገው መምረጣቸውን የደቡብ ኮሪያ የስለላ ድርጅት አስታወቀ።የብሔራዊ የደኅንነት ተቋሙ ሐሙስ ዕለት ለሕግ አውጪዎች እንደገለጸው፤ እዚህ ግምገማ ላይ ለመድረስ በይፋዊ ዝግጅቶች ላይ በአደባባይ መገኘቷን ጨምሮ በርካታ ሁኔታዎችን ከግምት ውስጥ አስገብቷል።ኪም ጁ ኤ መስከረም ወር ላይ የመጀመሪያ የውጭ አገር ጉዞዋ የሆነውን የቤይጂንግ ጉብኝትን ጨምሮ በቅርቡ በትላልቅ ዝግጅቶች ላይ ከአባቷ አጠገብ ሆና ታይታለች። ሆኖም ስለእርሷ ብዙም የሚታወቅ ነገር የለም።ተቋሙ ኪም ጁ ኤ በዚህ ወር መጨረሻ ላይ በሰሜን ኮሪያ የገዥው ኮሚኒስት ፓርቲ ስብሰባ ላይ ትገኝ እንደሆነ እና እንዳልሆነ ለማወቅ በቅርበት እንደሚከታተልም ገልጿል።ስብሰባው በየአምስት ዓመቱ አንድ ጊዜ የሚካሄድ ትልቅ ፖለቲካዊ ሁነት ነው።የሰሜን ኮሪያ የመሪነት ሥልጣን ለኪም ቤተሰብ ሦስት ትውልድ የተላለፈ ሲሆን ኪም ጆንግ ኡንም በትረ ሥልጣናቸውን ለጁ ኤ ያስተላልፋሉ ተብሎ በስፋት ይታመናል።ጁ ኤ የኪም ጆንግ ኡን እና ባለቤታቸው ሪ ሶል ጁ የምትታወቅ ብቸኛ ልጅ ናት።ምንም እንኳን የደኅንነት አገልግሎቱ ኪም ጆንግ ኡን ሌላ ትልቅ ወንድ ልጅ እንዳላቸው ቢያምንም ይህ ልጃቸው ዕውቅና ተሰጥቶትም ሆነ በሰሜን ኮሪያ ሚዲያ ላይ ታይቶ አያውቅም።የ13 ዓመት ታዳጊ እንደሆነች የሚታመነው ጁ ኤ ለመጀመሪያ ጊዜ በመንግሥት ቴሌቪዥን ላይ የታየችው በአውሮፓውያኑ 2022 ነበር።በወቅቱ ጁ ኤ የአባቷን እጅ ይዛ የሰሜን ኮሪያን አዲስ አህጉር አቋራጭ የባልስቲክ ሚሳኤል ስትጎበኝ ነበር።ከዚያ በኋላም በተለያዩ ሁነቶች ላይ ከአባቷ ጋር ታይታለች።ያጋሩ, ኪም ጆንግ ኡን የ13 ዓመት ልጃቸው ተተኪያቸው እንድትሆን መምረጣቸው ተገለጸ - 12 የካቲት 2026በመካከለኛው ምሥራቅ እየተዘጋጀ ያለው የአሜሪካ ሠራዊት
የፎቶው ባለመብት,CENTCOMFarsiበመካከለኛው ምሥራቅ የተሰማራው የአሜሪካ ጦር ኃይል ማዕከላዊ ዕዝ አስፈላጊ ሊሆን ለሚችል ስምሪት እየተዘጋጀ መሆኑን የሚገልጽ ፎቶ እና መልዕክት አሠራጨ።ሴንትኮም በሚል የሚታወቀው የአሜሪካ ጦር ኃይል ማዕከላዊ ዕዝ አዛዥ “አፓቼ ተዋጊ የጦር ሄሊኮፕተሮች በመካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ ዝግጅት ሲያደርጉ” ከሚል ጽሑፍ ጋር ፎቶግራፎችን በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ አጋርተዋል።በምሥሎቹ ላይ የአሜሪካ ወታደራዊ ሄሊኮፕተር አብራሪዎች “ኤኤች-64 አፓቼ ተዋጊ ሄሊኮፕተር ለውጊያ እያዘጋጁ” ከሚል መግለጫ ጋር ተጋርቷል።ሴንትኮም በኤክስ ገጹ ላይ በፋርስ ቋንቋ ለኢራናውያን ባሰፈረው ጽሑፍ “አፓቼ ሄሊኮፕተሮች በቅርቡ ሶሪያ ውስጥ በሽብርተኞች ዒላማ ላይ እና በተለያዩ ተልዕኮዎች ውስጥ አገልግሎት ላይ ውለዋል” ብሏል።የአሜሪካ ጦር ሠራዊት ስለሄሊኮፕተሮቹ “ለእግረኛ ኃይሎች በቅርበት የአየር ላይ ድጋፍ የሚሰጥ እና የረጅም ርቀት ሚሳዔሎችን በመጠቀም ከፍተኛ ጥቃት የመፈጸም አቅም አለው” በማለት ብቃቱን ገልጿል።ይህ በመካከለኛው ምሥራቅ ያለው የአሜሪካ ኃይል ዝግጁ መሆኑ የተገለጸበት መልዕክት የተላለፈው ከኢራን ጋር የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ ሁለተኛው ዙር ድርድር ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቅበት ጊዜ ነው።ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከኢራን ጋር የሚደረገው ድርድር ውጤት ካላስገኘ ሠራዊታቸው እርምጃ እንደሚወስድ በተደጋጋሚ ሲናገሩ ከመቆየታቸው በላይ ተጨማሪ የጦር መርከቦችን ወደ አካባቢው ለማሰማራት ሃሳብ እንዳላቸው ገልጸዋል።
የፎቶው ባለመብት,CENTCOMFarsiያጋሩ, በመካከለኛው ምሥራቅ እየተዘጋጀ ያለው የአሜሪካ ሠራዊት - 12 የካቲት 2026ኢራን ላይ ጥቃት ከተፈጸመ የሆርሙዝ ሰርጥ እንደሚዘጋ አንድ ባለሥልጣን አስጠነቀቁ
የፎቶው ባለመብት,Gallo Imagesየምስሉ መግለጫ,ሆርሙዝ ሰርጥበኢራን ላይ ጥቃት የሚፈጸም ከሆነ ከባሕረ ሰላጤው አገራት የሚመረተው ነዳጅ የሚተላለፍበት የሆርሙዝ ሰርጥ እንደሚዘጋ አንድ የኢራን ከፍተኛ ባለሥልጣን አስጠነቀቁ።የኢራን የውጭ ግንኙነት ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ ጃላል ዴጋኒ ፊሩዛባዲ እንዳሉት “በቀጣናው ጦርነት የሚቀሰቀስ ከሆነ የአገራት የኃይል አቅርቦት አደጋ ላይ ይወድቃል፣ የሆርሙዝ ሰርጥም ይዘጋል።”በዚህም ምክንያት “የመጀመሪያዋ ተጎጂ አገር የምትሆነው ቻይና ናት፤ ስለዚህም ድርድሩ ለቻይና አስፈላጊ ነው። ሩሲያም ብትሆን ጦርነቱን በመቃወም እንዳይከሰት እየሞከረች ይመስለኛል” ብለዋል።ባለፈው ሳምንት በተካሄደው ድርድር ምንም እንኳ ኢራን እና አሜሪካ ገና ወደ ወሳኙ ዝርዝር ጉዳይ ባይገቡም “አሜሪካ ለድርድር ፈቃደኛ በመሆኗ” ለኢራን ድል ነው ብለዋል።ጨምረውም አሜሪካ ለኢራን የኒውክሌር መረሃ ግብር “ወታደራዊ መፍትሄ እንደሌለው” ተረድታ ወደ ድርድር እና ዲፕሎማሲ መምጣቷን አመልክተዋል።የቀደመውን ድርድር በተመለከተም “ሁለቱም ወገኖች አቋማቸውን እና የማይደራደሩባቸውን ጉዳዮች አሳውቀዋል። ከዚያም ወደ ዋና ከተሞቻቸው ተመልሰው ድርድሩ ሊቀጥል ይችል የሚለውን ይወስናሉ” ብለዋል።የኢራን የውጭ ግንኙነት ምክር ቤት ለኢራን የውጭ ግንኙነት ፖሊሲዎችን፣ ስትራቴጂዎችን እና የመፍትሄ ሃሳቦችን እንዲያቀርብ በአገሪቱ ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ ትዕዛዝ ከ20 ዓመታት በፊት የተመሠረተ ነው።
ያጋሩ, ኢራን ላይ ጥቃት ከተፈጸመ የሆርሙዝ ሰርጥ እንደሚዘጋ አንድ ባለሥልጣን አስጠነቀቁ - 12 የካቲት 2026በካናዳ ተማሪዎችን እና ቤተሰቦቹን በመግደል የተጠረጠረው ግለሰብ መሞቱን ፖሊስ አስታወቀ
የፎቶው ባለመብት,Western Standardበምዕራብ ካናዳ ብሪቲሽ ኮሎምቢያ ግዛት ትምህርት ቤት እና መኖሪያ ቤት ውስጥ የጅምላ ተኩስ በመክፈት ስምንት ሰዎችን በመግደል የተጠረጠረውን ሰው ማንነት መለየቱን ፖሊስ አስታወቀ።የካናዳ ፖሊስ እንደገለጸው፤ ድርጊቱን በመፈጸም የተጠረጠረው 18 ዓመቱ ጄሲ ቫን ሩትሴላር፤ ራስ ላይ በተተኮሰ ጥይት ሕይወቱ አልፎ ትምህርት ቤቱ ውስጥ ተገኝቷል።እንድ ግለሰብ ‘ታምብለርሪጅ’ ወደ ተባለው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ገብቶ በከፈተው ተኩስ ስድስት ሰዎች ሲገደሉ ቢያንስ 25 ሌሎች ደግሞ ቆስለዋል።የተጠርጣሪው እናት የሆነች የ39 ዓመት ሴት እና የ11 ዓመት ዕድሜ ያለው የእንጀራ አባቱ ልጅ ከትምህርት ቤቱ አቅራቢያ በሚገኝ ቤት ውስጥ ሞተው ተገኝተዋል።የአካባቢው ፖሊስ በታምብለርሪጅ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተኩስ ስለመከፈቱ መረጃ የደረሳቸው ከቀኑ ሰዓት ሰዓት ተኩል አካባቢ ነበር።የፖሊስ አባላት ጥቆማ በደረሳቸው “በሁለት ደቂቃ ውስጥ” ወደ ትምህርት ቤት መድረሳቸውን የብሪቲሽ ኮሎምቢያ ግዛት ባለሥልጣናት ተናግረዋል።በዚህ ፈጣን ምላሽ የተነሳ “ያለምንም ጥርጥር” የብዙዎችን ሕይወት ማዳኑ መቻሉን የብሪቲሽ ኮሎምቢያ የሕዝብ ደኅንነት ሚኒስትር ኒና ክሪገር ገልጸዋል።ይሁን እንጂ በጥቃቱ ሦስት12 እና 13 ዓመት ዕድሜ ያላቸው አምስት ተማሪዎች እና ዓመት አንዲት የ39 ዓመት መምህርት ተገድለዋል።ጉዳት ከደረሰባቸው 25 ሰዎች ውስጥ አብዛኞቹ በጥይት እንዳልቆሰሉ ፖሊስ ገልጿል።ፖሊስ መኖሪያ ቤት ውስጥ ስለተፈጸመው ግድያ ጥቆማ የደረሰው ከ17 ደቂቃዎች በኋላ ነው። ፖሊሶች እናደሚናገሩት ተጠርጣሪው ወደ ትምህርት ቤቱ ያመራው ቤቱ ውስጥ እናቱን እና የእንጀራ አባቱን ልጅ ከገደለ በኋላ ነው።ተጠርጣሪው ይህንን ጥቃት ለመፈጸም ምን እንዳነሳሳው እስካሁን አልታወቀም። የፖሊስ መረጃ እንደሚያመለክተው የ18 ዓመቱ ተጠርጣሪ ከአራት ዓመት በፊት ትምህርቱን ያቋረጠ የትምህርት ቤቱ ተማሪ ነው።ያጋሩ, በካናዳ ተማሪዎችን እና ቤተሰቦቹን በመግደል የተጠረጠረው ግለሰብ መሞቱን ፖሊስ አስታወቀ - 12 የካቲት 2026ትራምፕ፤ ኒውክሌርን በተመለከተ ከኢራን ጋር የሚደረገው ውይይት እንደሚቀጥል ለኔታንያሁ አስታወቁ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የሚደረገው ኒውክሌርን የተመለከተ ውይይት እንደሚቀጥል ለጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ መግለጻቸውን አስታወቁ።ኢራን ስምምነት ላይ የማትደርስ ከሆነ ግን እርምጃ እንደሚወሰድ ትራምፕ አስጠንቅቀዋል።ትራምፕ እና ኔታንያሁ ትናንት በዋይት ሀውስ ሲገናኙ ውጥረት ስለሰፈነበት መካከለኛው ምሥራቅ ተወያይተዋል። የኢራን የኒውክሌር ጦር መሣሪያ መርሃ ግብርም ከውይይት አጀንዳዎቻቸው አንዱ ነበር።ትራምፕ፤ ኢራን ዩራንየም ማበልጸግ እንድታቆም፣ የባለስቲክ ሚሳዔል ፕሮግራሟን እንድታጥፍ እንዲሁም እንደ ሐማስ እና ሔዝቦላህ ያሉ ታጣቂዎችን እንዳትደግፍ ጫና እንዲያሳድሩ ኔታንያሁ እንደሚፈልጉ ተገልጿል።ኢራን የኒውክሌር መርሃ ግብሯን ለመገደብ ዝግጁ መሆኗን አስታውቃለች። በምላሹም የተጣሉባት ማዕቀቦች እንዲነሱ ጠይቃለች።ኢራን ሌሎች የተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎችን እንደማትቀበል ገልጻለች።ትራምፕ እና ኔታንያሁ ከመገናኘታቸው አስቀድሞ፤ የኢራኑ ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን አገራቸው ከአሜሪካ ጋር በምታደርገው ሁለተኛ ዙር ድርድር “ከልክ ያለፈ ጥያቄ አትቀበልም” ብለዋል።ፕሬዝዳንቱ ከአሜሪካ በኩል የሚቀርቡ ቅድመ ሁኔታዎችንም ተችተዋል።ትራምፕ ሥልጣን ከያዙ በኋላ ኔታንያሁ በዋሽንግተን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሲያደርጉ የአሁኑ ስድስተኛቸው ነው። ይህም የየትኛውም አገር መሪ ወደ አሜሪካ ካደረገው የጉዞ ብዛትይበልጣል።መሪዎቹ ለሦስት ሰዓት ገደማ ከተወያዩ በኋላ ትራምፕ ጋዜጣዊ መግለጫ አልሰጡም። በትሩዝ ሶሻል የማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ውይይቱ “በጣም ጥሩ ነበር” ብለዋል።“ምንም ውሳኔ ላይ አልደረስንም። ከኢራን ጋር ድርድር መቀጠል አለበት የሚለውን አጽንዞት ሰጥቼ ተናግሬያለሁ” ሲሉም አክለዋል።ያጋሩ, ትራምፕ፤ ኒውክሌርን በተመለከተ ከኢራን ጋር የሚደረገው ውይይት እንደሚቀጥል ለኔታንያሁ አስታወቁ - 11 የካቲት 2026ማዳጋስካርን በመታው ከባድ አውሎ ነፋስ ምክንያት ቢያንስ 20 ሰዎች ሞቱ
የፎቶው ባለመብት,AFPየምስሉ መግለጫ,አውሎ ነፋሱ 90 በመቶ የሚሆኑ ቤቶች ጣሪያ አውድሟልደቡብ አፍሪካዊቷ የደሴት አገር ማዳጋስካርን በመታው ከባድ አውሎ ነፋስ ምክንያት ቢያንስ 20 ሰዎች መሞታቸውን የአገሪቱ የአደጋ ጉዳዮች ባለሥልጣን አስታወቀ።የማዳጋስካር የአደጋ መቆጣጠሪያ መሥሪያ ቤት እንዳለው አውሎ ነፋሱ ቤቶችን በማፈራረስ፣ ዛፎችን በመገንደስ እና የኤሌክትሪክ መስመሮችን በመበጣጠስ ከፍተኛ ጉዳት አስከትሏል።በአጎራባቿ የፈረንሳይ ደሴት ሪዩኒየን የሚገኘው የከባድ አውሎ ነፋስ ትንበያ ማዕከል ለፈረንሳይ ዜና ወኪል እንዳስታወቀው አደጋው በደሴቲቱ አስካሁን ካጋጠሙ ተመሳሳይ አደጋዎች የከፋው ነው።ጊዛኒ የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ከባድ አውሎ ነፋስ ቶማሲና የተባለችውን የማዳጋስካር ሁለተኛ ትልቅ ከተማ በመታበት ጊዜ አብዛኞቹ ሰዎች የሞቱት ቤታቸው ላያቸው ላይ በመፍረሱ መሆኑን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።በአደጋው ከሞቱት በተጨማሪ በርካታ ሰዎች ቆስለው ከከተማዋ እንዲወጡ የተደረጉ ሲሆን፣ 400 ሺህ ያህል ሕዝብ ከሚኖርባት ከተማ 90 በመቶ የሚሆኑ ቤቶች ጣሪያቸው በነፋሱ ተወስዷል።የአሁኑ አደጋ በአንድ ወር ውስጥ ሁለተኛው ሲሆን፣ የቀደመው አውሎ ነፋስ 14 ሰዎችን በመግደል ከ31 ሺህ በላይ ሰዎችን ማፈናቀሉን የተባበሩት መንግሥታት አስታወቋል።ያጋሩ, ማዳጋስካርን በመታው ከባድ አውሎ ነፋስ ምክንያት ቢያንስ 20 ሰዎች ሞቱ - 11 የካቲት 2026ኢራን ከአሜሪካ ጋር ስትደራደር ‘ከልክ ያለፈ ጥያቄ’ እንደማትቀበል አስታወቀች
የፎቶው ባለመብት,MEHRየምስሉ መግለጫ,የኢራኑ ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያንየኢራኑ ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን አገራቸው ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር በሚደረገው ሁለተኛ ዙር ድርድር ‘ከልክ ያለፈ ጥያቄ አትቀበልም’ ሲሉ ከአሜሪካ በኩል የሚቀርብን ቅድመ ሁኔታ ተቹ።ፕሬዝዳንቱ በኢራን እስላማዊ አብዮት 47ኛ ዓመት በዓል ላይ ባደረጉት ንግግር ኢራን እያካሄደች ያለው የኒውክሌር መረሃ ግብር ለሰላማዊ አገልግሎት ብቻ እንደሆነ ለማጣራት እንደምትተባበር ገልጸው ነገር ግን “አገራችን ኢራን የትኛውንም ዓይነት ከልክ ያለፈ ጥያቄን አትቀበልም” ብለዋል።የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ አማካሪ የሆኑት አሊ ሻምኻኒም የኢራን የሚሳኤል ግንባታ ተቋማት ለድርድር የማይቀርቡ ቀይ መስመሮች ናቸው በማለት መናገራቸው ተዘግቧል።ይህ የባለሥልጣናቱ ንግግር የተሰማው ከአሜሪካ ጋር ሁለተኛው ዙር ድርድር እየተጠበቀ ባለበት እና የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ለምክክር ዋሽንግተን በገቡበት ጊዜ ነው።ኔታኒያሁ ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር በሚያደርጉት ውይይት በድርድሩ ላይ ኢራን የኒውክሌር ግንባታዋን እንድታቆም እንዲሁም ሐማስን እና ሄዝቦላህን የመሳሰሉ ታጣቂ ቡድኖችን ላለመርዳት ከስምምነት እንድትደርስ እንዲያደርጉ ይጠይቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።ያጋሩ, ኢራን ከአሜሪካ ጋር ስትደራደር ‘ከልክ ያለፈ ጥያቄ’ እንደማትቀበል አስታወቀች - 11 የካቲት 2026ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኢራን “በጣም ከባድ እርምጃ” ይጠብቃታል ሲሉ አስጠነቀቁ
የፎቶው ባለመብት,EPAኢራን ከአሜሪካ ጋር በቶሎ ከስምምነት ላይ ካልደረሰች “በጣም ከባድ እርምጃ” እንደሚጠብቃት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ተናገሩ።ባለፈው ሳምንት ኦማን ውስጥ በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የተጀመረው ድርድር ቀጣይ ዙር ይካሄዳል ተብሎ እየተጠበቀ ባለበት ጊዜ ትራምፕ ኢራንን አስጠንቅቀዋል።አስካሁን ቀጣዩ ዙር ድርድር መቼ እና የት እንደሚካሄድ ያልተገለጸ ሲሆን፣ ትራምፕ “ኢራን ከስምምነት ላይ ለመድረስ በጣሙን ትፈልጋለች” በማለት በዲፕሎማቲክ መንገድ መፍትሔ ይገኛል የሚል ተስፋ እንዳላቸው አመልክተዋል።ፕሬዝዳንቱ ለእስራኤል ቻናል 12 የቴሌቪዥን ጣቢያ እና ለአሜሪካው የዜና ድረ ገጽ አክሲዮስ እንደተናገሩት ተጨማሪ አዲስ የጦር አውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ለመላክ እያሰቡ ነው።የአሜሪካ ባለሥልጣናት ለሮይተርስ እንደተናገሩት ጆርጅ ዋሽንግተን የተባለው የጦር አውሮፕላን ተሸካሚ በእስያ አህጉር እንዲሁም ጆርጅ ደብሊው ቡሽ የተባለው ደግሞ በአሜሪካ ምሥራቃዊ የባሕር ዳርቻ ላይ ይገኛሉ። ነገር ግን ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ለመድረስ ቢያንስ አንድ ሳምንት ያስፈልጋቸዋል።በተጨማሪም የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ቬንዙዌላ ላይ ጥቃት ከመሰንዘሩ በፊት ወደ ካሪቢያን አካባቢ የተላከችውን ጄራርድ ፎርድ የጦር መርከብን ወደ አካባቢው ሊልክ ይችላል ተብሎ እየተነገረ ነው።ያጋሩ, ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኢራን “በጣም ከባድ እርምጃ” ይጠብቃታል ሲሉ አስጠነቀቁ - 11 የካቲት 2026ጋና በየሳምንቱ ረቡዕ የባህል ልብስ የሚለበስበት ቀን እንዲሆን አወጀች
የፎቶው ባለመብት,Zambia’s Ministry of Information and Media/Xጋና ረቡዕ ‘ፉጉ’ የተሰኘው የአገሪቷ የባህል ልብስ የሚለበስበት ቀን እንዲሆን አወጀች።አገሪቷ ይህን ያወጀችው ከልብሱ ጋር በተያያዘ በዛምቢያውያን እና በጋናውያን መካከል የበይነ መረብ ክርክር ከተነሳ ከቀናት በኋላ ነው።ባለፈው ሳምንት ፕሬዚደንት ጆን ድራማኒ ማሃማ በዛምቢያ ባደረጉት ጉብኝት ወቅት የባህል ልብሱን ለብሰውት ከታዩ በኋላ መነጋገሪያ ሆኗል።ልብሱን አንዳንድ ዛምቢያውያን ” ቀሚስ” ሲሉ የተሳለቁበት ሲሆን ጋናውያን ደግሞ ለዚህ መልስ እንዲሰጡ አድርጓል።በበይነ መረብ የተነሳውን ክርክር ተከትሎም ለዛምቢያ የባህል ልብሱን በብዛት እንደሚልኩ ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል።የጋና የቱሪዝም ሚኒስትር አብላ ድዚፋ ጎማሼ በበኩላቸው ማክሰኞ ዕለት የባህል አልባሳቱን በየሳምንቱ ረቡዕ መልበስ “በዓለም አቀፍ መድረክ የአገሪቷን ማንነት በኩራት ለማስተዋወቅ ይረዳል” ብለዋል።ከዚህም በተጨማሪ በተለይ በአገር ውስጥ ላሉ አምራቾች እና ዲዛይነሮች፣ ጠበብቶች እና ነጋዴዎች ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ይኖረዋል ብለዋል።በመሆኑም የባህል ልብሱ “ በተለያየ ዲዛይን፣ ቅርጽ እና አለባበስ አብረውት ከሚሄዱ ቆንጆ ጌጣ ጌጦች ጋር እንዲለበስ” ሚኒስትሯ አበረታተዋል።ባታካሪ ወይም ፉጉ እየተባለ የሚጠራው የባህል ልብስ በሰሜናዊ ጋናውያን ዘንድ ይዘወተራል።ልብሱ ቀጫጭን መስመሮች እንዲኖረው ተደርጎ ከጥጥ በእጅ ተሸምኖ የሚሰራ ሲሆን ሰፋ ተደርጎ የሚሰፋ ነው።ያጋሩ, ጋና በየሳምንቱ ረቡዕ የባህል ልብስ የሚለበስበት ቀን እንዲሆን አወጀች - 11 የካቲት 20261.3 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ያላቸው የቀድሞው የዛምቢያ ፕሬዚዳንት ልጅ ንብረቶች እንዲወረሱ ታዘዘ
የፎቶው ባለመብት,The National Prosecution Authority of Zambiaየምስሉ መግለጫ,የመንግሥት አቃቤያነ ሕጎች የነዳጅ ማደያን ጨምሮ የተወረሱትን የዳልቲሶ ሉንጉን ንብረቶች የሚያሳዩ በርካታ ምሥሎችን በፌስቡክ አጋርቷል።የዛምቢያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1.3 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ያላቸው የቀድሞው የዛምቢያ ፕሬዚደንት ኤድጋር ሉንጉ ወንድ ልጅ ዳልቲሶ ሉንጉ ንብረቶች እንዲወረሱ አዘዘ።የንብረት ውርሱ 79 ተሽከርካሪዎችን እንዲሁም የገበያ ማዕከል፣ የነዳጅ ማደያ፣ ዘመናዊ የመኖሪያ አፓርትመንቶችን እና መኖሪያ ቤትን ጨምሮ በሉሳካ ከተማ የሚገኙ 23 መሬቶች እና ሪል ስቴቶችን የሚያካትት ነው።ፍርድ ቤቱ ትዕዛዙን ያስተላለፈው የ39 ዓመቱ ዳልቲሶ ሉንጉ እነዚህን ንብረቶቹን እንዴት እንዳፈራቸው የሚያሳዩ ተጨባጭ እና የተረጋገጡ ማስረጃዎችን ማቅረብ ባለመቻሉ እንደሆነ ገልጿል።ዛምቢያን ከአውሮፓውያኑ 2015 ጀምሮ ለስድስት ዓመታት የመሩት ኤድጋር ሉንጉ ባለፈው ዓመት በደቡብ አፍሪካ ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን በቤተሰባቸው እና አሁን ባለው መንግሥት መካከል በተፈጠረ ውዝግብ እስካሁን አልተቀበሩም።በልጃቸው ላይ የተላለፈው ውሳኔ የተሰማውም በሉንጉ እና በ2021 ምርጫ በአብላጫ ድምጽ ባሸነፏቸው ተተኪያቸው ፕሬዚዳንት ሃኬንዴ ሂችሌማ መካከል የተፈጠረ የረዥም ጊዜ ውዝግብን ተከትሎ ነው።የሂችሌማ መንግሥት የሉንጉ አስክሬን ወደ አገራቸው ተመልሶ በመንግሥታዊ ሥርዓት በሙሉ ክብር እንዲቀበሩ ይፈልጋል። የደቡብ አፍሪካ ፍርድ ቤትም ባለፈው ነሐሴ ወር ላይ ሃሳባቸውን የሚደግፍ ውሳኔ አስተላልፏል።ቤተሰባቸው ደግሞ ሉንጉ “በቀብር ሥነ ሥርዓታቸው ላይ ሂቺሌማ እንዲገኙ አይፈልጉም ነበር” በማለት በደቡብ አፍሪካ ቤተሰባቸው እና ወዳጆቻቸው በተገኙበት የግል የቀብር ሥነ ሥርዓት እንዲፈፀምላቸው ይፈልጋሉ።ያጋሩ, 1.3 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ያላቸው የቀድሞው የዛምቢያ ፕሬዚዳንት ልጅ ንብረቶች እንዲወረሱ ታዘዘ - 11 የካቲት 2026ዚምባብዌ የፕሬዚዳንቷን የሥልጣን ዘመን ለማራዘም የሚያስችል አዲስ ረቂቅ ሕግ አወጣች
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,አሁን ባለው ሕገ መንግሥት መሠረት ፕሬዚደንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ ከሁለት ዓመት በኋላ ከሥልጣን ይወርዳሉ።የዚምባብዌ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ83 ዓመቱ ፕሬዚደንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ ቢያንስ ለሚቀጥሉት አራት ዓመታት ሥልጣን ላይ እንዲቆዩ የሚፈቅድ አዲስ ረቂቅ ሕግ አፀደቀ።አዲሱ ረቂቅ ሕግ ፕሬዚደንቶች በምርጫ ሳይሆን በምክር ቤት አባላት እንዲመረጡ እና ሰባት ዓመታት ላሉት ሁለት የሥልጣን ዘመን እንዲያገለግሉ ይፈቅዳል።አሁን ላይ ተግባራዊ እየሆነ ባለው ሕግ አንድ የሥልጣን ዘመን አምስት ዓመታትን የያዘ ነው።የፍትሕ ሚኒስትሩ ዚያምቢ ዚያምቢ ረቂቅ ሕጉ ለምክር ቤት ከመቅረቡ በፊት ከሕዝብ ጋር ውይይት እንደሚደረግበት ገልጸዋል። ሆኖም ሁለቱም ምክር ቤቶች በገዥው ዛኑ ፒኤፍ ፓርቲ በበላይነት የተያዙ ናቸው።ቢሆንም ሕጋዊ ተግዳሮቶች ሊገጥሙት ይችላል።የሕገ መንግሥት ባለሙያዎች የሥልጣን ዘመን የሚቀየር ከሆነ ሕዝበ ውሳኔ ያስፈልጋል ያሉ ሲሆን አዲሱ ረቂቅ ሕግ አሁን ያሉትን ፕሬዚደንት የሚጠቅም አይደለም ሲሉም ተከራክረዋል።ምናንጋግዋ ለመጀመሪያ ጊዜ ሥልጣን ላይ የወጡት ለረጅም ጊዜ የአገሪቷ ፕሬዚደንት የነበሩት ሟቹ ሮበርት ሙጋቤ በወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ከተነሱ በኋላ እአአ በ2017 ነበር።ከዚያም በቀጣይ ዓመት በነበረው ምርጫ ያሸነፉ ሲሆን እአአ በ2023 በተካሄደው አወዛጋቢ ምርጫ ደግሞ ለሁለተኛ የሥልጣን ዘመን ተመርጠዋል።ያጋሩ, ዚምባብዌ የፕሬዚዳንቷን የሥልጣን ዘመን ለማራዘም የሚያስችል አዲስ ረቂቅ ሕግ አወጣች
