የኢራን አብዮታዊ ዘብ በአገሪቱ ላይ ሊቃጣ የሚችል ወደታራዊ ጥቃትን ለመከላከል ያለውን ዝግጁነት ለመፈተሽ ቁልፍ በሆነው የሆርሙዝ ሰርጥ ልምምድ ማድረግ መጀመሩን አስታወቀ።

ጭምቅ ሃሳብ

የቀጥታ ሽፋን

  1. 16 የካቲት 2026የአሜሪካ አውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ ከኢራን አቅራቢያ እንደሚገኝ የሳተላይት ምሥል አመለከተአብረሃም ሊንከን የጦር መርከብየምስሉ መግለጫ,አብረሃም ሊንከን የጦር መርከብአሜሪካ፤ ኢራን በምታካሂደው የኒውክሌር መርሃ ግብር ምክንያት ጫና እያበረታችባት ባለበት በአሁኑ ወቅት ግዙፍ የጦር መርከቦችን በኢራን ዙሪያ እያሰማራች ነው።የቢቢሲ የመረጃ አጣሪያ ቡድን ቢቢሲ ቬሪፋይ፤ በመካከለኛው ምሥራቅ በተለይም በኢራን አቅራቢያ እየተጠናከረ ያለውን የአሜሪካን ወደታራዊ ኃይል በቅርበት እየተከታተለ ነው።ከሦስት ሳምንት በፊት የአሜሪካ ግዙፍ የጦር አውሮፕላን ተሸካሚ የጦር መርከብ ወደ ባሕረ ሰላጤው አካባቢ መድረሱ ከተዘገበ በኋላ ቢቢሲ ትናንት እሑድ በተነሳ የሳተላይት ምሥል አማካኝነት መርከቡ የት እንደሚገኝ አረጋግጧል።መርከቡ ወደ አካባቢው ከተሰማራ ከሦስት ሳምንታት በላይ ቢሆንም እስከ ትናንት ድረስ ግን ከሳተላይት የምሥል ዕይታ ውጪ ሆኖ ቆይቶ ነበር።በብዛት የመርከቦችን ቦታ ለመለየት ከሚውለው እና ዩሮፒያን ሴንቲኔል-2 ከተባለው ለሕዝብ ይፋ ከሆነውን ሳተላይት የተገኘ ምሥልን በመጠቀም ባደረጋው ማጣራት፤ አብረሃም ሊንከን የጦር መርከብ ከኢራን አቅራቢያ ከኦማን የባሕር ዳርቻ 240 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ እንዳለ ቢቢሲ አረጋግጧል።የአሜሪካ ባለሥልጣናት ጄራርድ ፎርድ የተባለው ሁለተኛ ግዙፍ የጦር አውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ አብረሃም ሊንከንን በመቀላቀል ከሌሎች ወታደራዊ መሣሪያዎች ጋር ወደ ቀጣናው መሰማራታቸውን አረጋግጠዋል።ያጋሩ, የአሜሪካ አውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ ከኢራን አቅራቢያ እንደሚገኝ የሳተላይት ምሥል አመለከተ
  2. 16 የካቲት 2026የኢራን አብዮታዊ ዘብ የባሕር ላይ ወታደራዊ ልምምድ ማድረግ ጀመረየኢራን አብዮታዊ ዘብ ፈጣን ጀልባየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,የኢራን አብዮታዊ ዘብ ፈጣን ጀልባየኢራን አብዮታዊ ዘብ በአገሪቱ ላይ ሊቃጣ የሚችል ወደታራዊ ጥቃትን ለመከላከል ያለውን ዝግጁነት ለመፈተሽ ቁልፍ በሆነው የሆርሙዝ ሰርጥ ልምምድ ማድረግ መጀመሩን አስታወቀ።ይህ ወታደራዊ ልምምድ መካሄድ የጀመረው በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ሁለተኛ ዙር ድርድር ጄኔቭ፣ ስዊትዘርላንድ ውስጥ ሊካሄድ በተቃረበበት እና አሜሪካ በኢራን አቅራቢያ ግዙፍ ወታደራዊ መርከቦቿን እያጠናከረች ባለበት ጊዜ ነው።ለድርድር ወደ ጄኔቭ ያመሩት የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ፤ ኢራን ለማስፈራሪያ እንደማትንበረከክ በመግለጽ “ትክክለኛ፣ ፍትሐዊ እና ሚዛናዊ ስምምነት” እንደሚጠብቁ ተናግረዋል።የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ ኢራን እስካሁን ያዳበረችውን ለኒውክሌር ጦር መሣሪያ ሊውሉ የሚችሉ የዩራኒየም ውጤቶችን እና የማብላያ ማዕከላቷን በሙሉ ማስወገድ እንዳለባት አስጠንቅቀዋል።ያጋሩ, የኢራን አብዮታዊ ዘብ የባሕር ላይ ወታደራዊ ልምምድ ማድረግ ጀመረ
  3. 16 የካቲት 2026የኢራን እና የአሜሪካ ድርድር የነዳጅ፣ የማዕድን እና የጦር መሣሪያን እንደሚያካትት ተገለጸየኢራን ሕዝባዊ ተቃውሞየፎቶው ባለመብት,Reutersኢራን ከአሜሪካ ጋር የኒውክሌር ስምምነት ላይ በመድረስ ሁለቱንም አገራት በምጣኔ ሃብት ተጠቃሚ የሚያደርግ መንገድን የመከተል ዕቅድ እንዳላት አንድ ኢራናዊ ዲፕሎማት ተናገሩ።ሮይተርስ የዜና ወኪል እንደዘገበው፤ ዲፕሎማቱ የኢራንን አቋም ያስታወቁት ከአሜሪካ ጋር ሁለተኛ ዙር ውይይት ከመደረጉ ከቀናት በፊት ነው።ከዚህ ቀደም የተደረገው ውይይት ሁለቱ ባላንጣ አገራት በቴህራን የኒውክሌር መርሃ ግብር ላይ ያላቸውን ልዩነት ለማጥበብ እና ግጭትን ለማስወገድ የሞከሩበት እንደነበር ተዘግቧል።የአሜሪካ ባለሥልጣናት ለሮይተርስ እንደተናገሩት፤ አሜሪካ ሁለተኛውን ግዙፍ የጦር መርከብ ወደ ቀጣናው ያስጠጋች ሲሆን፤ አገራቱ ስምምነት ላይ የማይደርሱ ከሆነ ወታደራዊ እርምጃ ሊወሰድ ይችላል።የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ባደረጉት ንግግር እንዳሉት፤ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ምርጫቸው በዲፕሎማሲ እና ድርድር እልባት ማግኘት ነው።“ከኢራን ጋር ስምምነት ላይ መድረስ የቻለ ባይኖርም እንሞክራለን” ሲሉ ማርኮ ሩቢዮ ተናግረዋል።አሜሪካ ኢራን ላይ እርምጃ ከወሰደች ኢራን በምላሹ በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኙ የአሜሪካ ወታደራዊ መቀመጫዎች ላይ ጥቃት እንደምትሰነዝር ዝታለች። ትናንት ግን ኢራን የተለሳለሰ አቋም አንጸባርቃለች።በኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ የምጣኔ ሃብት ዲፕሎማሲ ምክትል ዳይሬክተር ሐሚድ ጋንባሪ “ስምምነቱ ዘላቂነት እንዲኖረው አሜሪካም በምጣኔ ሃብት ተጠቃሚ መሆን አለባት” ብለዋል።“በነዳጅ፣ በማዕድን እና በአየር ጦር መሣሪያ ግዢም ያሉን የጋራ ፍላጎቶች የድርድሩ አካል ናቸው” ሲሉም የአገራቸውን አቋም ይፋ አድርገዋል።በአውሮፓውያኑ በ2015 የተፈረመው የኒውክሌር ስምምነት የአሜሪካን ጥቅም ያስጠበቀ እንዳልሆነ አክለዋል።ትራምፕ በ2018 አሜሪካን ከስምምነቱ ማስወጣታቸው ይታወሳል።ያጋሩ, የኢራን እና የአሜሪካ ድርድር የነዳጅ፣ የማዕድን እና የጦር መሣሪያን እንደሚያካትት ተገለጸ
  4. 16 የካቲት 2026የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኃላፊ ጋር ተወያዩየኢራኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራጋቺ እና የዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ዳይሬክተር ራፈኤል ግሮሲየፎቶው ባለመብት,xየምስሉ መግለጫ,የኢራኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራጋቺ እና የዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ዳይሬክተር ራፈኤል ግሮሲበነገው ዕለት ከአሜሪካ ጋር ለሚያደርጉት ድርድር ጄኔቫ የሚገኙት የኢራኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራጋቺ፣ ከዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ዳይሬክተር ጋር ተገናኝተው ተወያዩ።ራፈኤል ግሮሲ በኤክሰ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕከት ከኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር መገናኘታቸውን ገልጸው “ነገ በጄኔቫ ለሚካሄደው ድርድር ዝግጅት በዝርዝር ቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል” ብለዋል።አራጋቺ ጄኔቫ ከደረሱ ከሰዓታት በኋላ በኤክስ ገጻቸው ላይ “ከአገራችን የኒውክሌር ባለሙያዎች ጋር ለዝርዝር ቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ ለመነጋገር ራፋኤል ግሮሲን አገኛቸዋለሁ” ብለው ነበር።የኢራኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በተጨማሪም ወደ ጄኔቫ የሆኑት “ፍትሃዊ እና ሚዛናዊ የሆነ ሰምምነት ላይ ለመድረስ” የሚያስችሉ ተጨባች ሃሳቦችን በመያዝ መሆኑን ተናግረዋል።በኢራን እና ዩናይትድ ስቴትስ መካከል የሚደረገው ሁለተኛው ዙር ድርድር ነገ በጄኔቫ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።በትናንትናው ዕለት የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ማንኛውም ከኢራን ጋር የሚደረግ ስምምነት ያበለጸገቻቸው ዩራኒየምን ሙሉ በሙሉ የሚያስወግድ መሆን አለበት ሲሉ አስጠንቅቀዋል።በተጨማሪም ስምምነቱ የኢራን ባሌስቲክ ሚሳኤል ፕሮግራምንም ማካተት አለበት ሲሉ ተናግረዋል።ያጋሩ, የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኃላፊ ጋር ተወያዩ
  5. 16 የካቲት 2026የመንግሥታቱ ድርጅት በደቡብ ሱዳን ግጭት ጉዳት የሚደርስባቸው ሰዎች እየጨመሩ መምጣታቸውን ገለፀየደቡብ ሱዳን ጦርየፎቶው ባለመብት,AFP via Getty Imagesየተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት (ኦቻ) በደቡብ ሱዳን በተቀናቃኝ ኃይሎች መካከል ያገረሸውን ግጭት ተከትሎ በርካታ ሰዎች ተጎድተው በአኮቦ ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ገለፀ።ድርጅቱ ባለፈው አርብ ባወጣው መግለጫ በአኮቦ ካውንቲ፣ በሰሜን ጆንግሌይ በደቡብ ሱዳን መከላከያ እና የሱዳን ሕዝቦች ነጻነት እንቅስቃሴ/ተቃዋሚ መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት የቆሰሉ ሕሙማንን የሰብአዊ ድርጅቶች እንክብካቤ እያደረጉ መሆኑን ገልጿል።ድርጅቱ በርካታ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ሕይወት አድን የሆነ ሕክምና ለማግኘት እንዲችሉ ወደ ተሻለ የሕክምና ተቋም የሚሄዱበት መንገድ ባለመኖሩ “አስተማማኝ ባልሆነ ሁኔታ” ውስጥ ይቆያሉ ሲል አስጠንቅቋል።ኦቻ እየተባባሰ የመጣው ግጭት እና በጆንጌሊ የተፈጸመው የአየር ጥቃት ወደ 280,000 ሰዎችን ከቀያቸው ማፈናቀሉን ገልጿል።የተፈናቃዮች ቁጥር ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች የሚያስፈልገውን ሰብዓዊ እርዳታ ጨምሮታል ሲል ኦቻ በመግለጫው ላይ ጠቅሷል።12 የጤና ተቋማት መዘረፋቸውን እና በከፊል መውደማቸው ያስታወቀው ኦቻ፣ ይህም አስፈላጊ የጤና አገልግሎቶችን አስተጓጉሏል፤ እንዲሁም ለችግር ለተጋለጡ ሰዎች የሚሰጠውን እንክብካቤ ገድቧል ብሏል።በመንግሥት እና ለማቻር ታማኝ በሆኑ ታጣቂዎች መካከል ግጭት እየተካሄደ ባለበት በአሁኑ ወቅት ደቡብ ሱዳን በሚቀጥለው ዓመት ታሕሳስ ምርጫ ለማካሄድ እየተዘጋጀች ነው።ደቡብ ሱዳን በአውሮፓውያኑ 2011 ነው ከሱዳን ተገንጥላ የዓለማችን በዕድሜ ትንሿ ሀገር የሆነችው።ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር የአገሪቱ የመጀመሪያው ፕሬዝደንት ሲሆኑ ሪክ ማቻር ደግሞ የመጀመሪያው ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ።ነገር ግን ከሁለት ዓመት በኋላ ፕሬዝዳንት ኪር ሙሉ ካቢኒያቸውን አባረው ማቻር መፈንቅለ መንግሥት እያሴሩ ነው ብለው ከወቀሱ በኋላ በአገሪቱ የእርስ በርስ ጦርነት ተቀሰቀሰ።በዚህ አምስት ዓመት በዘለቀ ደም አፋሳሽ የእርስ በርስ ጦርነት ምክንያት ከ400 ሺህ በላይ ሰዎች ሲገደሉ፤ 2.5 ሚሊዮን ሰዎች ተፈናቅለዋል።በሁለቱ ተፋላሚ ወገኖች መካከል በ2018 የሰላም ስምምነት ተፈርሞ፣ ሁለቱም አካላት አዲስ ሕገ-መንግሥት ለማፅደቅ፣ ምርጫ ለማካሄድ፣ የጦር ኃይሎቻቸውን ለማዋሃድ እንደሁም የሕዝብ ቆጠራ ለማካሄድ እና የታጠቁ ኃይሎችን መሳሪያ ለማስፈታት ተስማምተዋል።ነገር ግን እስካሁን ከስምምነቱ ማዕቀፎች አንዱም ተፈፃሚ አልሆነም። በሀገሪቱ የተለያዩ ግጭቶች መከሰታቸውም ቀጥሏል።ያጋሩ, የመንግሥታቱ ድርጅት በደቡብ ሱዳን ግጭት ጉዳት የሚደርስባቸው ሰዎች እየጨመሩ መምጣታቸውን ገለፀ
  6. 16 የካቲት 2026ቤንያሚን ኔታንያሁ ኢራን ያበለፀገችውን ዩራኒየም ማስረከብ አለባት አሉየእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁየፎቶው ባለመብት,Reutersየእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ አሜሪካ ከቴህራን ጋር በምታደርገው ድርድር ያበለፀገችውን ዩራኒየም በሙሉ እንድታስረክብ እና የበለጠ እንዳታበለጽግ ልትታገድ ይገባል አሉ።ጠቅላይ ሚኒስትሩ እሁድ ዕለት በእየሩሳሌም ባደረጉት ንግግር በአሜሪካ እና በኢራን መካከል በሚካሄደው የኒውክሌር ድርድር ወቅት መኖር ስላለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ዘርዝረዋል።“ሁሉም የበለፀጉ ዩራኒየሞች ከኢራን መውጣት አለባቸው” ያሉት ኔታንያሁ “ምንም የማበልጸግ አቅም መኖር የለበትም” ሲሉ ተናግረዋል።ኔታንያሁ ይህንን ያሉት የኢራን እና የአሜሪካ ባለሥልጣናት ማክሰኞ በስዊትዘርላንድ ለሚካሄደው ሁለተኛ ዙር ድርድር እየተዘጋጁ ባሉበት ወቅት ነው።ኢራን የኒውክሌር ስምምነት ላይ ለመድረስ አሜሪካ ማዕቀቦችን የምታነሳ ከሆነ ለማመቻመች ዝግጁ መሆኗን የኢራኑ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማጂድ ታክት-ራቫንቺ በቴህራን ለቢቢሲ ተናግረዋል።ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ኢራን፤ አሜሪካ የጣለችባትን ማዕቀቦች ለማንሳት ፈቃደኛ ከሆነች፤ ከአቋሟ ፈቀቅ ብላ የኒውክሌር ስምምነት ላይ የመድረስ ሐሳብን ለማጤን ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል።ይሁን እንጂ ኢራን ምንም ዩራኒየም ማበልጸግ የለባትም የሚለውን እንደ ቀይ መስመር እና በኒውክሌር አለማስፋፋት ስምምነት መሠረት መብቷን መጣስ አድርጋ ትቆጥራለች።አሜሪካ ኢራን ስምምነት ላይ እንድትደርስ ጫና እያደረገች ሲሆን በመካከለኛው ምሥራቅም ያላትን ወታደራዊ አቅም በማጠናከር፣ ሁለት የአውሮፕላን ተሸካሚ መርከቦችን ወደ ቀጣናው አስጠግታለች።ተጨማሪ የአሜሪካ የባሕር ኃይል በቀጠናው ውስጥ ሊከሰቱ ከሚችሉ ማናቸውም አደጋዎች ይጠብቃሉ ሲሉ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ በስሎቫኪያ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል።የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን ላይ ከሚሰነዘረው ቀጥተኛ ጥቃት ይልቅ “ዲፕሎማሲያዊ እና በድርድር የሚገኝ ስምምነትን” እንደሚመርጡ ተናግረዋል።የትራምፕ ከፍተኛ ልዑክ ስቲቭ ዊትኮፍ እና ጄሬድ ኩሽነር ወደ ጄኔቫ በመጓዠ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺን እና ልዑካቸውን ያነጋግራሉ።ሩቢዮ “ማንም ሰው ከኢራን ጋር የተሳካ ስምምነት ማድረግ አልቻለም፤ እኛ ግን እንሞክራለን” ብለዋል።ያጋሩ, ቤንያሚን ኔታንያሁ ኢራን ያበለፀገችውን ዩራኒየም ማስረከብ አለባት አሉ
  7. 16 የካቲት 2026ቻይና፤ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለ53 የአፍሪካ አገራት ከቀረጥ ነጻ የሆነ የወጪ ንግድን ተግባራዊ ልታደርግ ነውየቻይና ኩባንያዎች በተለያዩ የአፍሪካ አገራት የመሠረተ ልማት ግንባታዎች ላይ ተሰማርተው ይገኛሉየፎቶው ባለመብት,AFPቻይና ከ53 የአፍሪካ አገራት እአአ ከግንቦት 1፣ 2026 ጀምሮ ወደ አገሯ ለሚያስገቡት ምርቶች ምንም ዓይነት ታሪፍ እንደማትጥል ማስታወቋን የአገሪቱ ብሔራዊ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ።ቻይና ከእነዚህ የአፍሪካ አገራት ጋር የጋራ የኢኮኖሚ አጋርነት ስምምነቶችን ለመደራደር እና ለመፈረም ግፊት ማድረጓን ትቀጥላለች ተብሏል።እንዲሁም እንደ “ግሪን ቻናል” ባሉ የተሻሻሉ ዘዴዎች ወደ ቻይና የሚላኩ የአፍሪካ ምርቶች ተደራሽነትን የበለጠ እንደምታሰፋ የመንግሥት የቴሌቪዥን ዘገባ አመልክቷል።የቻይና ‘ግሪን ቻናል’ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው እቃዎች፣ አገልግሎቶች ወይም ኢንቨስትመንቶች በአነስተኛ ቢሮክራሲ፣ በተቀላጠፈ ሁኔታ ወደ አገሪቱ እንዲገቡ የሚያደርግ አሰራር ነው።ቻይና የጋራ ተጠቃሚነት ያለው ትብብርን ለማጎልበት እና “ሁሉን አቀፍ የቻይና-አፍሪካ ማኅበረሰብ የወደፊት የጋራ ተጠቃሚነት” ለማረጋገጥ ዝግጁ መሆኗን ተናግራለች።ይህ የቻይና የታሪፍ ውሳኔ የአፍሪካን የወጪ ንግድ ተወዳዳሪነት እንደሚያሳድግ፣ የገበያ ተደራሽነትን እንደሚያሰፋ፣ ወደ ቻይና ገበያ ለመግባት ያሉትን የንግድ እንቅፋቶችን በመቀነስ የኢንዱስትሪ እና የግብርና እሴት ሰንሰለትን ይደግፋል ተብሎ ይጠበቃል።የቻይናን ከቀረጥ ነጻ እድል ተጠቃሚ ያልሆነችው ብቸኛዋ አገር ኢስዋቲኒ ናት።ኢስዋቲኒ ተጠቃሚ ያልሆነችው አገሪቱ ከታይዋን ጋር ይፋዊ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ስላላት መሆኑን የመገናኛ ብዙኃን ዘገባዎች ያሳያሉ።ያጋሩ, ቻይና፤ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለ53 የአፍሪካ አገራት ከቀረጥ ነጻ የሆነ የወጪ ንግድን ተግባራዊ ልታደርግ ነው
  8. 16 የካቲት 2026ቱርክ ነዳጅ ቆፋሪ መርከቧን ወደ ሶማሊያ ላከችየቱርክ መርከብ በወደብ ላይየፎቶው ባለመብት,AAቱርክ እሁድ ዕለት ጥልቅ ነዳጅ ቆፋሪ የሆነውን መርከቧን ለመጀመሪያ ተልዕኮው ወደ ሶማሊያ መላኳን አስታውቃለች።የቱርክ የኢነርጂ እና ተፈጥሮ ሐብት ሚኒስትር አልፓስላን ባይራካታር እርምጃውን ታሪካዊ ብለውታል።መርከቡ ከ45 ቀናት ጉዞ በኋላ ሞቃዲሾ ደርሶ ቁፋሮውን እንደሚጀምር ተነግሯል።ቱርክ እና ሶማሊያ እ.አ.አ በ2014 በባሕር እና በባሕር ዳርቻ ላይ የነዳጅ እና ጋዝ ፍለጋ ለማከናወን ተስማምተዋል።አሁን የተላከውን መርከብ ጨምሮ ነዳጅ የሚቆፍሩ የቱርክ መርከቦች ቁጥር ስድስት መድረሱን ሚኒስትሩ ተናግረዋል ሲል የቱርክ የዜና ወኪል አናዶሉ ዘግቧል።ቱርክ ግዙፍ የባሕር ዳርቻ ነዳጅ ፍለጋ በማካሄድ ከዓለም አራተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝም አክለው ተናግረዋል።ከአዲሱ የጎርጎሮሳዊያን ዓመት ወዲህ አገሪቱ በጋዝ እና ነዳጅ ፍለጋ ላይ ከተሰማሩ የአሜሪካ እና ዩናይትድ ኪንግደም ኩባንያዎች ጋር ስልታዊ ስምምነት አድርጋለች።ያጋሩ, ቱርክ ነዳጅ ቆፋሪ መርከቧን ወደ ሶማሊያ ላከች
  9. 16 የካቲት 2026የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራጋቺ ከአሜሪካ ጋር ለመደራደር ጄኔቫ ገቡየኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺየኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራጋቺ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ለሚያደርጉት ሁለተኛው ዙር የኒውክሌር ድርድር የስዊትዘርላንድስ ዋና ከተማ ጄኔቫ ገቡ።አሜሪካ እና ኢራን በተዘዋዋሪ የሚያደርጉት ድርድር ማክሰኞ ዕለት በጄኔቫ እንደሚጀመር ተገልጿል።ድርድሩን የምትመራው ኦማን መሆኗ የተገለፀ ሲሆን የአሜሪካ ልዑካን ቡድንን ስቲቭ ዊትኮፍ እና ጄሬድ ኩሽነር እንደሚመሩ ታውቋል።የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ዋሺንግተን ውጤታማ ስምምነት ላይ ለመድረስ ጥረት እያደረገች መሆኑን ተናግረዋል።“ከኢራን ጋር ማንም ውጤታማ ስምምነት ላይ መድረስ አልቻለም፤ እኛ ግን እየሞከረን ነው” ብለዋል።አክለውም “ስቲቭ ዊትኮፍ እና ጄሬድ ኩሽነር ከኢራን ጋር ለሚደረገው ድርድር ወደ ስፍራው እያመሩ ነው፤ የሚሆነውን እናያለን” ብለዋል።የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ቅዳሜ ዕለት ባደረጉት ንግግር፤ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስምምነት ላይ መድረስን እንደሚመርጡ ገልጸዋል።ሁለቱ አገራት የሚያደርጉት ድርድር የሚካሄደው የኢራንን መንግሥትን የሚቃወሙ ሠልፎች በዓለማችን የተለያዩ ክፍሎች ከተደረጉ ከሁለት ቀናት በኋላ ነው።ያጋሩ, የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራጋቺ ከአሜሪካ ጋር ለመደራደር ጄኔቫ ገቡ
  10. 16 የካቲት 2026በመላው ዓለም የኢራን መንግሥትን በመቃወም የተቃውሞ ሠልፎች ተካሄዱበተለያዩ የዓለም ክፍሎች የኢራንን መንግሥት የሚቃወሙ የተቃውሞ ሰልፎች ተካሄደዋልየፎቶው ባለመብት,LightRocket via Getty Imagesየኢራን የቀድሞው ንጉሥ ልጅ “ዓለም አቀፍ የተግባር ቀን” ሲሉ ያስተላለፉትን ጥሪ ተከትሎ” በመላው ዓለም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሠልፈኞች የኢራንን መንግሥት በመቃወም አደባባይ ወጡ።ሬዛ ፓጃላቪ በሙኒክ 250ሺህ ለሚገመቱ ሰዎች ንግግር ሲያደርጉ የኢራን እስላማዊ አገዛዝ ከሥልጣን እንዲወርድ ጥሪ አቅርበዋል።በንግግራቸው በቅርቡ በአገሪቱ የተካሄደውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የደረሰውን እስር፣ አፈና እና ግድያ ተቃውመዋል።በሙኒክ፣ ሎስ አንጀለስ እና ቶሮንቶ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች አደባባይ በመውጣት በኢራን መንግሥት ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ገልጸዋል።በቁጥር ትንሽ ቢሆኑም በቴል አቪቭ፣ ሊዝበን፣ ሲድኒ እና ለንደንም ተመሳሳይ ሰልፎች ተካሄደዋል። የመብት ተሟጋቾች በአገሪቱ የተከሰተውን የኑሮ ውድነት ተከትሎ በአገር አቀፍ ደረጃ በተካሄደው ተቃውሞ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች 6000 ያህል ሰዎችን መግደላቸውን ይናገራሉ።ፓህላቪ ለተሰበሰበው ሕዝብ “የመጀመሪያው መልዕክቴ በአገር ውስጥ ላሉ ጀግኖች እና ታጋይ ወገኖቻችን ነው፤ ብቻችሁን እንዳልሆናችሁ እወቁ፤ እናም ዛሬ በዚህ ትግል ዓለም ከጎናችሁ ነው።”የኢራንን አመራር በመተቸት “ከዚህ ሙሰኛ፣ ጨቋኝ፣ ሕፃናትን ከሚገድል አገዛዝ በተለየ እናንተ ታላቅ ባህል እና ሥልጣኔን ትወክላላችሁ፤ እና በነገዋ ነፃ ኢራን ውስጥ እኛ ምንኛ ታላቅ አገር መሆናችንን ለዓለም ታረጋግጣላችሁ” ብለዋል።ያጋሩ, በመላው ዓለም የኢራን መንግሥትን በመቃወም የተቃውሞ ሠልፎች ተካሄዱ