ኢሕአፓ/eprp  ·Follow

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ – ኢሕአፓ በሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች የሚገኙትን መዋቅሮቹን እያጠናከረ እንዳለ ይታወቃል። ትናንት የካቲት 07 ቀን 2018 ዓ.ም የኢሕአፓ ከፍተኛ የስራ አስፈፃሚ አባላት እንዲሁም የክልሉ የአመራር አባላትና ደጋፊዎች በተገኙበት ወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።

​በውይይቱ ወቅት የሚከተሉት ዋና ዋና ነጥቦች ተነስተዋል።

የመልካም አስተዳደር እጦት፦ በክልሉ እየተንሰራፋ የመጣው የመልካም አስተዳደር ችግር በሕዝቡ ላይ እያደረሰ ያለው አድሏዊ አሰራርና ጫና በዝርዝር ተመክሮበታል።

​ሀገራዊ ቀውስ፦ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የገጠሟት ዘርፈ-ብዙ ችግሮችና ሀገራዊ ቀውሶች በጥልቀት ተገምግመዋል።

​የሰላማዊ ትግል አቅጣጫ፦ እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ የክልሉ አባላትና አመራሮች በቀጣይ ሊያደርጉት የሚገባው ሰላማዊ ትግል ዙሪያ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።

​በተያያዘም ዛሬ፣ የካቲት 08 ቀን 2018 ዓ.ም በራስ ሆቴል ግቢ፣ የቢሮ ቁጥር 053 የሚገኘው ነባሩ የሐረሪ ክልል የኢሕአፓ ጽሕፈት ቤት በድጋሚ ተመርቆ ተከፍቷል።

​በመጨረሻም ሀገሪቱ ከገባችበት ማህበራዊና ፖለቲካዊ ቅርቃር ነፃ ለማውጣት የሚደረገውን ሰላማዊ ትግል በክልሉ ውስጥ በበላይነት የሚመሩ አዳዲስ የክልል አመራሮች ምርጫ ተካሂዶ መርሀግብሩ ተጠናቅቋል።