
የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ “የዓለም ኃያሉ ሠራዊት መልሶ እንዳይነሳ ሆኖ ሊመታ እንደሚችል” በመግለጽ ለፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ምላሽ ሰጡ።
ጭምቅ ሃሳብ
- የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በቀይ ባሕር እና በአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ከኬንያ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ተወያዩ
- ናይጄሪያ በዩክሬን ዜጎቿ ሞተው መገኘታቸውን ተከትሎ ማስጠንቀቂያ አወጣች
- ትራምፕ በኢራን የኑክሌር ድርድር ላይ በተዘዋዋሪ እንደሚሳተፉ ተናገሩ
- የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢራን ያበለጸገችው ዩራኒየም በሙሉ ‘ከአገሪቱ መውጣት አለበት’ አሉ
- ቻይና ኢትዮጵያን ጨምሮ ለ53 የአፍሪካ አገራት ከቀረጥ ነጻ የሆነ የወጪ ንግድን ተግባራዊ ልታደርግ ነው
- ቱርክ ነዳጅ ቆፋሪ መርከቧን ወደ ሶማሊያ ላከች
- በመላው ዓለም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የኢራንን መንግሥት በመቃወም አደባባይ ወጡ
- የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራጋቺ ከአሜሪካ ጋር ለመደራደር ጄኔቫ ገቡ
የቀጥታ ሽፋን
- ከ 1 ሰአት በፊትአያቶላ ኻሜኒ “የዓለም ኃያሉ ሠራዊት መልሶ እንዳይነሳ ሆኖ ሊመታ ይችላል” ሲሉ አስጠነቀቁ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ “የዓለም ኃያሉ ሠራዊት መልሶ እንዳይነሳ ሆኖ ሊመታ እንደሚችል” በመግለጽ ለፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ምላሽ ሰጡ።ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከኢራን ጋር ከተፈጠረው ፍጥጫ ጋር በተያያዘ የአሜሪካን ጦር ሠራዊት ኃያልነት ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ በተደጋጋሚ ሲናገሩ ሰንብተዋል።በአገራቸው ዙሪያ የጦር መርከቦቿን እያስጠጋች ያለቸው አሜሪካ፤ ኢራን የሚቀርቡላትን ቅድመ ሁኔታዎች በመቀበል ከስምምነት ካልደረሰች እርምጃ እንደሚወሰድባት ፕሬዝዳንት ትራምፕ ሲዝቱ ቆይተዋል።ይህንን በተመለከተ ኻሜኒ በሰጡት ምላሽ “የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሠራዊታቸው በዓለም ላይ ጠንካራው እንደሆነ በተደጋጋሚ ይናገራሉ። ጠንካራ የተባለ ሠራዊት አንዳንድ ጊዜ እንዳይነሳ ተደርጎ ክፍኛ ሊመታ ይችላል” በማለት አስጠንቅቀዋል።ጠቅላይ መሪው ጨምረውም አሜሪካ የጦር መርከቦችን ወደ ኢራን መላኳን በተደጋጋሚ እየገለጸች መሆኗን በመጥቀስ “መርከቦች አደገኛ መሣሪያዎች ናቸው፤ ነገር ግን የበለጠ አደገኛው ነገር እነዚህን መርከቦች ከባሕር ሥር እንዲሰምጡ የሚያደርገው የጦር መሣሪያ ነው” በማለት የአሜሪካ መርከቦች የሚገጥማቸውን ምላሽ አመልክተዋል።አሜሪካ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በዓለም ላይ ካሉ ትልቅ አውሮፕላን ተሸካሚ የጦር መርከቦች መካከል አብርሃም ሊንከን የተባለውን በኢራን አቅራቢያ በሚገኘው ባሕር ላይ ያሰማራች ሲሆን፣ በቬንዙዌላ ላይ በተፈጸመው ጥቃት ውስጥ ተሳታፊ የነበረው ጄራርድ ፎርድ መርከብ ደግሞ ወደ ባሕረ ሰላጤው እንዲያመራ አዝዛለች።ከእነዚህ ግዙፍ የጦር አውሮፕላን ተሸካሚ መርኮቦች በተጨማሪ ሌሎች በርካታ የአሜሪካ የጦር መርከቦች ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ተሰማርተዋል።ያጋሩ, አያቶላ ኻሜኒ “የዓለም ኃያሉ ሠራዊት መልሶ እንዳይነሳ ሆኖ ሊመታ ይችላል” ሲሉ አስጠነቀቁ - ከ 2 ሰአት በፊትየቱርክ ፕሬዝዳንት ለይፋዊ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ
የፎቶው ባለመብት,Abiy Ahmed Ali/FBየቱርክ ፕሬዝዳንት ረሲብ ታይፕ ኤርዶዋን በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ግብዣ መሠረት ለይፋዊ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።ፕሬዝዳንት ኤርዶዋን ማክሰኞ የካቲት 10/2018 ዓ. ም. አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።ፕሬዝዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶዋን በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ የሁለትዮሽ፣ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት እንደሚያደርጉ ጽሕፈት ቤታቸው አስታውቋል።ከኢትዮጵያ ጋር ጥብቅ ግንኙነት ያላት የቱርኩ ፕሬዝዳንት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር ከሚያደርጉት ውይይት በተጨማሪ የተለያዩ የስምምነት ሰነዶች እንደሚፈረም ይጠበቃል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ፕሬዝዳንት ኤርዶዋንን ከተቀበሉ በኋላ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ በሰፈረው መልዕክት ላይ ጉብኝቱ “በቱርክ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ጥልቅ የአጋርነት ጥንካሬ የሚያንጸባርቅ ነው” በማለት የአገራቱን ትብብር ይበልጥ የሚያጠናክር ውጤታማ ውይይት እንዲደረግ ምኞታቸውን ገልጸዋል።ያጋሩ, የቱርክ ፕሬዝዳንት ለይፋዊ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ - ከ 3 ሰአት በፊትታዋቂው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ጀሲ ጃክሰን በ84 ዓመታቸው አረፉ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,ጀሲ ጃክሰን፤ ከማርቲን ሉተር ኪንግ ጁንየር ጋር በመሆን ለጥቁር አሜሪካውያን መብት በጽኑ ታግለዋልታዋቂው አሜሪካዊ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ጀሲ ጃክሰን በ84 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።ቤተሰቦቻቸው ባወጡት መግለጫ “አባታችን ታላቅ መሪ ነበር። ለቤተሰባችን ብቻ ሳይሆን በመላው ዓለም ለሚገኙ ጭቁኖች እና ድምጻቸው ለታፈነ ሰዎችን ጭምር ጠባቂ ነበር” ብለዋል።እንደ አውሮፓውያኑ በ1960ዎቹ ጀሲ ጃክሰን ከማርቲን ሉተር ኪንግ ጁንየር ጋር በመሆን ለጥቁር አሜሪካውያን መብት በጽኑ ታግለዋል።በአውሮፓውያኑ በ1984 እና በ1988 የዴሞክራቲክ ፓርቲ ፕሬዝዳንታዊ ዕጩም ነበሩ።ጀሲ ጃክሰን በ2017 ፓርኪንሰንስ የተባለ በሽታ እንደያዛቸው የተገለጸ ሲሆን፤ ያለፈው ኅዳር ላይ ሆስፒታል ገብተውም ነበር።በሰብአዊ መብት ንቅናቄ ውስጥ አብረዋቸው የሠሩት የመብት ተሟጋች ሬቨረንድ አል ሻርፕተን “አገሪቱን እና ዓለምን የለወጠ ሰው ነው። ፖሊሲ እና ሕግ አስቀይሯል። ሕልማችን እንዳይሞት ጠብቆ ለልጆቻችን አውርሷል” ሲሉ ገልጸዋቸዋል።ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁንየር እንደ አውሮፓውያኑ በ1968 ቴነሲ ውስጥ በተገደለበት ወቅት ከጀሲ ጃክሰን ጋር አብረው ነበሩ።በ1941 ሳውዝ ካሮላይና የተወለዱት ጀሲ ጃክሰን፤ ከወጣትነታቸው አንስቶ በፖለቲካው ንቁ ተሳታፊ ነበሩ።በ1971 ‘ኦፕሬሽን ፑሽ’ የተሰኘ የማኅበራዊ ፍትሕ እና የመብት ተሟጋች ተቋም መሥርተዋል።ያጋሩ, ታዋቂው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ጀሲ ጃክሰን በ84 ዓመታቸው አረፉ - ከ 3 ሰአት በፊትሁለተኛ ቀኑን በያዘው የኬንያ ሠራተኞች አድማ ምክንያት በረራዎች ከ20 ሰዓት በላይ ተቋረጡ
የፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,በመቶዎች የሚቆጠሩ መንገደኞች በረራቸው ተሰርዟልበኬንያ መዲና ናይሮቢ የሚገኘው ዋነኛ የአገሪቱ አውሮፕላን ማረፊያ ከ20 ሰዓት በላይ በረራ በማቋረጡ ሳቢያ በመቶዎች የሚቆጠሩ መንገደኞች ጉዟቸው እንደተስጓጎለ ተገለጸ።በአፍሪካ በርካታ ተጓዦችን ከሚያስተናግዱ አየር ማረፊያዎች መካከል አንዱ በሆነው ጆሞ ኬንያታ አውሮፕላን ማረፊያ፤ ሠራተኞች ለሁለተኛ ቀን የቀጠለ አድማ በማድረጋቸው በረራዎች ተሰርዘዋል።ወደ ዩናይትድ ኪንግደም ለትምህርት ሊጓዝ የነበረው እና በረራው የተሰረዘበት ጃክ ኦኮት የተባለ ተጓዥ “ከ20 ሰዓት በላይ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ቆይቻለሁ። በሰው ተጨናንቋል” ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል።የኬንያ አብራሪዎች ማኅበር “የተፈጠረው መስተጓጎል ከአብራሪዎች የሥራ እና እረፍት ጊዜ ጋር የሚጣረስ ነው” ብሏል።የሥራ ማቆም አድማው ከበረራ ደኅንነት ጥበቃ ጋር እንዳይጣረስ እንደሚሰጋም ማኅበሩ አስታውቋል።የኬንያ አቪየሽን ሠራተኞች ማኅበር ከሳምንት በፊት የሥራ ማቆም አድማ እንደሚኖር ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ ነበር።የበረራ ሠራተኞችን ክፍያቸው እንዲሁም የሥራ ሁኔታቸው የማይሻሻል ከሆነ ሥራ የማቆም አድማ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል።የማኅበሩ ዋና ፀሐፊ ሞስ ንዲማ “ይሄ በቀላሉ የሚታይ አድማ ሳይሆን ሙሉ ኢንዱስትሪውን የሚመለከት ነው” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።ያጋሩ, ሁለተኛ ቀኑን በያዘው የኬንያ ሠራተኞች አድማ ምክንያት በረራዎች ከ20 ሰዓት በላይ ተቋረጡ - ከ 5 ሰአት በፊትዩክሬን የወታደሮቿን ዘር በማቀዝቀዣ እንዲቀመጥ ገንዘብ እንደምትደጉም ተገለፀ
በጦርነት ወታደሮቿን እያጣች ያለችው ዩክሬን የወታደሮቿን ዘር በማቀዝቀዣ ለማስቀመጥ ድጎማ እየሰጠች ነው።በ2022 የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ሲጀምር የግል የስነ ተዋልዶ ክሊኒኮች ሴት ወታደሮች እንቁላላቸውን ወንዶች ደግሞ የዘር ፈሳሻቸውን እንዲያስቀምጡ አማራጭ አቅርበዋል።በ2013 ይህንን ለመቆጣጠር የተነሳው የዩክሬን ምክር ቤት ለአገልግሎቱ በገንዘብ ለመደጎም ሕግ አውጥቷል።ሕጉን ካረቀቁት የምክር ቤት አባላት አንዷ የሆኑት ኦክሳና ዲሚትሪቭ “ወታደሮቻችን ወደፊታችንን እየተከላከሉ ነው፤ ነገር ግን የእነርሱን [ወደፊት] ሊያጡ ይችላሉ። ስለዚህ ዕድል መስጠት ነው የፈለግነው” ብለዋልየሁሉም ወታደሮች ናሙና ከሞቱ እስከ ሦስት ዓመት ድረስ በነፃ የሚቀመጥ ሲሆን፤ የትዳር አጋሮቻቸው እንዲጠቀሙት አስቀድሞ በጽሑፍ ፈቃድ ካላቸው ለመፀነስ መጠቀም ይችላሉ ተብሏል።እርምጃው ከጦርነቱ በፊት ዩክሬንን የገጠማትን የስነ ሕዝብ ቀውስ እና ከጦርነቱ በኋላ ወጣቶቿ ተገድለውባት የተባባሰውን ችግር ለመፍታት ያለመ እንደሆነ ተነግሯል።ያጋሩ, ዩክሬን የወታደሮቿን ዘር በማቀዝቀዣ እንዲቀመጥ ገንዘብ እንደምትደጉም ተገለፀ - ከ 6 ሰአት በፊትየግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በቀይ ባሕር እና በአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ከኬንያ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ተወያዩ
የፎቶው ባለመብት,Ministry of Foreign Affairs Kenyaየግብፅ ከፍተኛ ልዑካን ቡድን ከኬንያ ባለሥልጣናት ጋር በቀይ ባሕር እና በአፍሪካ ቀንድ አሁናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያየ።በግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላቲ እና የውኃ ሐብት እና መስኖ ሚኒስትር ሃኒ ስዊላም የተመራ ከፍተኛ ልዑክ የካቲት 9/2018 ዓ.ም. ኬንያን ጎብኝቷል።የግብፅ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ከኬንያ ዋና የምክር ቤት ፀሐፊ ሙሳሊያ ሙሳቫዲ እና ሌሎችም ከፍተኛ ሹሞች ጋር በቀይ ባሕር እና የአፍሪካ ቀንድ አሁናዊ ሁኔታዎች ላይ መወያየተቻውን ካይሮ አስታውቃለች።የግብፅ ውኃ ሐብት እና መስኖ ሚኒስቴር ንግግሩን አስመልክቶ ባወጣው መረጃ የሁለቱ አገራት ባለሥልጣናት በቀጣናው በዋናነት ደግሞ በሶማሊያ እና ሱዳን ሰላም እና መረጋጋትን መመለስ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ሐሳብ መለዋወጣቸው ተጠቁሟል።ሁለቱ ወገኖች ግንኙነታቸውን የበለጠ ለማጠናከር የመከላከያ እና የተቀናጀ የውሃ ሐብት አስተዳደርን ጨምሮ በሌሎች ዘርፎች ላይ ለመተባበር ተስማምተዋል።የናይል ወንዝን ዘላቂነት ለመጠበቅ እና የጋራ ሐብትነቱን ለማስጠበቅ በጥምረት መስራት አስፈላጊ ስለመሆኑ ሁለቱም ወገኞች እውቅና እንደሰጡ ተመላክቷል።አገራቱ “ሁሉም የናይል ተፋሰስ አገራት የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት አድርጎ በውሃ ደኅንነት፣ በማኅበረ ኢኮኖሚ እድገት እና በስነ ምህዳር ጥበቃ በጋራ ለመስራት” ስለማሰባቸው ተጠቅሷል።ያጋሩ, የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በቀይ ባሕር እና በአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ከኬንያ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ተወያዩ - ከ 9 ሰአት በፊትናይጄሪያ በዩክሬን ዜጎቿ ሞተው መገኘታቸውን ተከትሎ ማስጠንቀቂያ አወጣች
የፎቶው ባለመብት,Reutersናይጄሪያውያን በሌላ አገር ጦርነት ውስጥ በውትድርና ተቀጥረው እንዲሳተፉ በሚካሄድ ሕገወጥ ምልመላ እንዳይታለሉ የአገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስቸኳይ ማስጠንቀቂያ አወጣ።ሚኒስቴሩ ማስጠንቀቂያውን ያወጣው የዩክሬን ባለሥልጣናት ባለፈው ዓመት በጦርነት እንደተገደሉ የገለጿቸውን የሁለት ናይጄሪያውያን አስከሬን እንዳገኙ ከተናገሩ በኋላ ነው።ናይጄሪያ የግለሰቦቹን ሞት ባታረጋግጥም እሁድ ዕለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኪሚቢ ኢሞሞቲሚ ኤቢንፋ ባወጡት መግለጫ “በእንደዚህ አይነት አሳዛኝ ሁኔታዎች ሰለባ የሆኑ በርካታ ናይጄሪያውያን ተታልለው ወታደራዊ አገልግሎት ኮንትራቶችን እንዲፈርሙ ከተገደዱ በኋላ ወደ ውጊያ ቀጠናዎች ተሰማርተዋል” ብለዋል።ኬንያ ለዜጎቿ ተመሳሳይ ማስጠንቀቂያ አውጥታለች።እንደ ናይጄሪያ ባለሥልጣናት ገለጻ፣ የምርመራ እና የደህንነት ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት አንዳንድ ዜጎች ጥሩ ክፍያ የሚከፈልበት የሥራ ዕድል፣ የደህንነት ሥራ፣ የትምህርት ዕድሎች ወይም የፍልሰት ማበረታቻዎች እንደሚሰጡ ቃል ተገብቶላቸው ወደ ጦርነት ቀጠናዎች ተወስደዋል።በአንዳንድ አጋጣሚዎች፣ ተጎጂዎች ተገቢው የሕግ ምክር ሳይሰጣቸው በውጭ ቋንቋዎች የተጻፉ ውሎችን እንዲፈርሙ ይገደዱ ነበር፣ እና የጉዞ ሰነዶቻቸው ወደ ሚሄዱበት አገር እንደደረሱ ይወሰድባቸዋል ተብሏል።በመሃል ያሉ ደላሎችም የቱሪስት ወይም ሌሎች ወታደራዊ ያልሆኑ ቪዛዎችን በመጠቀም ጉዞ እንደሚያመቻቹ ይነገራል።ኤቢንፋ ናይጄሪያውያን እንደዚህ አይነት መደለያዎችን እንዳይቀበሉ አስጠንቅቀዋል። ይህም ሕይወትን አደጋ ላይ ከመጣል ባለፈ የናይጄሪያን እና ዓለም አቀፍ የቅጥረኛ እንቅስቃሴዎችን እና የውጭ ዜጎችን ስለመመልመል የሚደነግጉ ሕጎችን ሊጥሱ እንደሚችሉ አፅንዖት ሰጥቷል።የናይጄሪያ መንግሥት እነዚህን ጉዳዮች ለመመርመር እና የሕዝብ ግንዛቤን ለማሳደግ ከቀጠናው እና ከዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።በውጭ አገር የሚገኙት የዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮዎች የቆንስላ ድጋፍን ለማጠናከር እና ለዜጎች ማሰሳሰቢያ እንዲያስተላልፉ ተነግሯቸዋል።የዩክሬን የስለላ ድርጅት ከ36 የአፍሪካ አገራት የተውጣጡ ከ1,400 በላይ ግለሰቦች ለሩሲያ እንዲዋጉ መመልመላቸውን ይገምታል። ዩክሬን ራሷ አፍሪካውያንን ጨምሮ የውጭ ዜጎችን ለመመልመል በመሞከሯ ቀደም ሲል ትችት ገጥሟታል።የአፍሪካ መንግሥታት ዜጎቻቸውን በተደጋጋሚ እያስጠነቀቁ እና ወደ ግጭቱ ተታልለው የገቡ ዜጎቻቸውን ወደ አገራቸው ለመመለስ እየሰሩ ነው።ያጋሩ, ናይጄሪያ በዩክሬን ዜጎቿ ሞተው መገኘታቸውን ተከትሎ ማስጠንቀቂያ አወጣች - 17 የካቲት 2026ከኢራን ጋር በሚደረገው ድርድር ላይ “በተዘዋዋሪ” እሳተፋለሁ – ዶናልድ ትራምፕ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ እና ኢራን ድርድር በጄኔቫ ከመጀመሩ በፊት “በተዘዋዋሪ እሳተፋለሁ” ሲሉ ተናገሩ።በሁለቱ አገራት መካከል የሚደረገው ድርድር “አይሳካም” ብለው ያስቡ እንደሆን የተጠየቁት ፕሬዚዳንቱ፣ “ከስምምነት ላይ መድረስ የሚፈልጉ ይመስለኛል። ባለመስማማት የሚመጣውን መዘዝ መቀበል የሚፈልጉ አይመስለኝም” ብለዋል።“ኢራን እጅግ ጠንካራ ተደራዳሪ ናት። ለበጎም ሆነ ለክፉ” ያሉት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት “መጥፎ ተደራዳሪ ናት፤ ምክንያቱም የኒውክሌር ተቋማቷን ለማውደም ቢ-2 ጦር አውሮፕላንን ከመላካችን በፊት ልንስማማ እንችል ነበር ። አሁን ግን የበለጠ ኃላፊነት የሚሰማቸው ይመስለኛል። ስምምነት ላይ መድረስ ይፈልጋሉ” ብለዋል።ፕሬዚዳንቱ ይህንን ከተናገሩ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ በድርድሩ ላይ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።ቃል አቀባዩ ዩናይትድ ስቴትስ ከዚህ በፊት ከነበረው በተሻለ አሁን “የበለጠ ምክንያታዊ ነች” ሲሉ ተደምጠዋል።በኢራን እና በአሜሪካ መካከል የሚደረገው ሁለተኛ ዙር ድርድር ማክሰኞ በጄኔቫ ይጀመራል።የእስራኤሉ ቤንያሚን ኔታንያሁ ከድርድሩ መጀመር አስቀድመው የኢራን ዩራኒየም ማበልጸጊያን ሙሉ በሙሉ ማስወገድ እና የበለፀገው ዩራኒየም ሙሉ በሙሉ ከአገሪቱ እንዲወጣ በድርድሩ ላይ መካተት አለበት ሲሉ ተናግረው ነበር።አክለውም ድርድሩ የኢራን ባሌስቲክ ሚሳዔልን ማካተት አለበት ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተው ነበር።ያጋሩ, ከኢራን ጋር በሚደረገው ድርድር ላይ “በተዘዋዋሪ” እሳተፋለሁ – ዶናልድ ትራምፕ - 16 የካቲት 2026የአሜሪካ አውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ ከኢራን አቅራቢያ እንደሚገኝ የሳተላይት ምሥል አመለከተ
የምስሉ መግለጫ,አብረሃም ሊንከን የጦር መርከብአሜሪካ፤ ኢራን በምታካሂደው የኒውክሌር መርሃ ግብር ምክንያት ጫና እያበረታችባት ባለበት በአሁኑ ወቅት ግዙፍ የጦር መርከቦችን በኢራን ዙሪያ እያሰማራች ነው።የቢቢሲ የመረጃ አጣሪያ ቡድን ቢቢሲ ቬሪፋይ፤ በመካከለኛው ምሥራቅ በተለይም በኢራን አቅራቢያ እየተጠናከረ ያለውን የአሜሪካን ወደታራዊ ኃይል በቅርበት እየተከታተለ ነው።ከሦስት ሳምንት በፊት የአሜሪካ ግዙፍ የጦር አውሮፕላን ተሸካሚ የጦር መርከብ ወደ ባሕረ ሰላጤው አካባቢ መድረሱ ከተዘገበ በኋላ ቢቢሲ ትናንት እሑድ በተነሳ የሳተላይት ምሥል አማካኝነት መርከቡ የት እንደሚገኝ አረጋግጧል።መርከቡ ወደ አካባቢው ከተሰማራ ከሦስት ሳምንታት በላይ ቢሆንም እስከ ትናንት ድረስ ግን ከሳተላይት የምሥል ዕይታ ውጪ ሆኖ ቆይቶ ነበር።በብዛት የመርከቦችን ቦታ ለመለየት ከሚውለው እና ዩሮፒያን ሴንቲኔል-2 ከተባለው ለሕዝብ ይፋ ከሆነውን ሳተላይት የተገኘ ምሥልን በመጠቀም ባደረጋው ማጣራት፤ አብረሃም ሊንከን የጦር መርከብ ከኢራን አቅራቢያ ከኦማን የባሕር ዳርቻ 240 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ እንዳለ ቢቢሲ አረጋግጧል።የአሜሪካ ባለሥልጣናት ጄራርድ ፎርድ የተባለው ሁለተኛ ግዙፍ የጦር አውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ አብረሃም ሊንከንን በመቀላቀል ከሌሎች ወታደራዊ መሣሪያዎች ጋር ወደ ቀጣናው መሰማራታቸውን አረጋግጠዋል።ያጋሩ, የአሜሪካ አውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ ከኢራን አቅራቢያ እንደሚገኝ የሳተላይት ምሥል አመለከተ - 16 የካቲት 2026የኢራን አብዮታዊ ዘብ የባሕር ላይ ወታደራዊ ልምምድ ማድረግ ጀመረ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,የኢራን አብዮታዊ ዘብ ፈጣን ጀልባየኢራን አብዮታዊ ዘብ በአገሪቱ ላይ ሊቃጣ የሚችል ወደታራዊ ጥቃትን ለመከላከል ያለውን ዝግጁነት ለመፈተሽ ቁልፍ በሆነው የሆርሙዝ ሰርጥ ልምምድ ማድረግ መጀመሩን አስታወቀ።ይህ ወታደራዊ ልምምድ መካሄድ የጀመረው በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ሁለተኛ ዙር ድርድር ጄኔቭ፣ ስዊትዘርላንድ ውስጥ ሊካሄድ በተቃረበበት እና አሜሪካ በኢራን አቅራቢያ ግዙፍ ወታደራዊ መርከቦቿን እያጠናከረች ባለበት ጊዜ ነው።ለድርድር ወደ ጄኔቭ ያመሩት የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ፤ ኢራን ለማስፈራሪያ እንደማትንበረከክ በመግለጽ “ትክክለኛ፣ ፍትሐዊ እና ሚዛናዊ ስምምነት” እንደሚጠብቁ ተናግረዋል።የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ ኢራን እስካሁን ያዳበረችውን ለኒውክሌር ጦር መሣሪያ ሊውሉ የሚችሉ የዩራኒየም ውጤቶችን እና የማብላያ ማዕከላቷን በሙሉ ማስወገድ እንዳለባት አስጠንቅቀዋል።ያጋሩ, የኢራን አብዮታዊ ዘብ የባሕር ላይ ወታደራዊ ልምምድ ማድረግ ጀመረ - 16 የካቲት 2026የኢራን እና የአሜሪካ ድርድር የነዳጅ፣ የማዕድን እና የጦር መሣሪያን እንደሚያካትት ተገለጸ
የፎቶው ባለመብት,Reutersኢራን ከአሜሪካ ጋር የኒውክሌር ስምምነት ላይ በመድረስ ሁለቱንም አገራት በምጣኔ ሃብት ተጠቃሚ የሚያደርግ መንገድን የመከተል ዕቅድ እንዳላት አንድ ኢራናዊ ዲፕሎማት ተናገሩ።ሮይተርስ የዜና ወኪል እንደዘገበው፤ ዲፕሎማቱ የኢራንን አቋም ያስታወቁት ከአሜሪካ ጋር ሁለተኛ ዙር ውይይት ከመደረጉ ከቀናት በፊት ነው።ከዚህ ቀደም የተደረገው ውይይት ሁለቱ ባላንጣ አገራት በቴህራን የኒውክሌር መርሃ ግብር ላይ ያላቸውን ልዩነት ለማጥበብ እና ግጭትን ለማስወገድ የሞከሩበት እንደነበር ተዘግቧል።የአሜሪካ ባለሥልጣናት ለሮይተርስ እንደተናገሩት፤ አሜሪካ ሁለተኛውን ግዙፍ የጦር መርከብ ወደ ቀጣናው ያስጠጋች ሲሆን፤ አገራቱ ስምምነት ላይ የማይደርሱ ከሆነ ወታደራዊ እርምጃ ሊወሰድ ይችላል።የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ባደረጉት ንግግር እንዳሉት፤ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ምርጫቸው በዲፕሎማሲ እና ድርድር እልባት ማግኘት ነው።“ከኢራን ጋር ስምምነት ላይ መድረስ የቻለ ባይኖርም እንሞክራለን” ሲሉ ማርኮ ሩቢዮ ተናግረዋል።አሜሪካ ኢራን ላይ እርምጃ ከወሰደች ኢራን በምላሹ በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኙ የአሜሪካ ወታደራዊ መቀመጫዎች ላይ ጥቃት እንደምትሰነዝር ዝታለች። ትናንት ግን ኢራን የተለሳለሰ አቋም አንጸባርቃለች።በኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ የምጣኔ ሃብት ዲፕሎማሲ ምክትል ዳይሬክተር ሐሚድ ጋንባሪ “ስምምነቱ ዘላቂነት እንዲኖረው አሜሪካም በምጣኔ ሃብት ተጠቃሚ መሆን አለባት” ብለዋል።“በነዳጅ፣ በማዕድን እና በአየር ጦር መሣሪያ ግዢም ያሉን የጋራ ፍላጎቶች የድርድሩ አካል ናቸው” ሲሉም የአገራቸውን አቋም ይፋ አድርገዋል።በአውሮፓውያኑ በ2015 የተፈረመው የኒውክሌር ስምምነት የአሜሪካን ጥቅም ያስጠበቀ እንዳልሆነ አክለዋል።ትራምፕ በ2018 አሜሪካን ከስምምነቱ ማስወጣታቸው ይታወሳል።ያጋሩ, የኢራን እና የአሜሪካ ድርድር የነዳጅ፣ የማዕድን እና የጦር መሣሪያን እንደሚያካትት ተገለጸ - 16 የካቲት 2026የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኃላፊ ጋር ተወያዩ
የፎቶው ባለመብት,xየምስሉ መግለጫ,የኢራኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራጋቺ እና የዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ዳይሬክተር ራፈኤል ግሮሲበነገው ዕለት ከአሜሪካ ጋር ለሚያደርጉት ድርድር ጄኔቫ የሚገኙት የኢራኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራጋቺ፣ ከዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ዳይሬክተር ጋር ተገናኝተው ተወያዩ።ራፈኤል ግሮሲ በኤክሰ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕከት ከኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር መገናኘታቸውን ገልጸው “ነገ በጄኔቫ ለሚካሄደው ድርድር ዝግጅት በዝርዝር ቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል” ብለዋል።አራጋቺ ጄኔቫ ከደረሱ ከሰዓታት በኋላ በኤክስ ገጻቸው ላይ “ከአገራችን የኒውክሌር ባለሙያዎች ጋር ለዝርዝር ቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ ለመነጋገር ራፋኤል ግሮሲን አገኛቸዋለሁ” ብለው ነበር።የኢራኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በተጨማሪም ወደ ጄኔቫ የሆኑት “ፍትሃዊ እና ሚዛናዊ የሆነ ሰምምነት ላይ ለመድረስ” የሚያስችሉ ተጨባች ሃሳቦችን በመያዝ መሆኑን ተናግረዋል።በኢራን እና ዩናይትድ ስቴትስ መካከል የሚደረገው ሁለተኛው ዙር ድርድር ነገ በጄኔቫ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።በትናንትናው ዕለት የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ማንኛውም ከኢራን ጋር የሚደረግ ስምምነት ያበለጸገቻቸው ዩራኒየምን ሙሉ በሙሉ የሚያስወግድ መሆን አለበት ሲሉ አስጠንቅቀዋል።በተጨማሪም ስምምነቱ የኢራን ባሌስቲክ ሚሳኤል ፕሮግራምንም ማካተት አለበት ሲሉ ተናግረዋል።ያጋሩ, የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኃላፊ ጋር ተወያዩ - 16 የካቲት 2026የመንግሥታቱ ድርጅት በደቡብ ሱዳን ግጭት ጉዳት የሚደርስባቸው ሰዎች እየጨመሩ መምጣታቸውን ገለፀ
የፎቶው ባለመብት,AFP via Getty Imagesየተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት (ኦቻ) በደቡብ ሱዳን በተቀናቃኝ ኃይሎች መካከል ያገረሸውን ግጭት ተከትሎ በርካታ ሰዎች ተጎድተው በአኮቦ ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ገለፀ።ድርጅቱ ባለፈው አርብ ባወጣው መግለጫ በአኮቦ ካውንቲ፣ በሰሜን ጆንግሌይ በደቡብ ሱዳን መከላከያ እና የሱዳን ሕዝቦች ነጻነት እንቅስቃሴ/ተቃዋሚ መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት የቆሰሉ ሕሙማንን የሰብአዊ ድርጅቶች እንክብካቤ እያደረጉ መሆኑን ገልጿል።ድርጅቱ በርካታ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ሕይወት አድን የሆነ ሕክምና ለማግኘት እንዲችሉ ወደ ተሻለ የሕክምና ተቋም የሚሄዱበት መንገድ ባለመኖሩ “አስተማማኝ ባልሆነ ሁኔታ” ውስጥ ይቆያሉ ሲል አስጠንቅቋል።ኦቻ እየተባባሰ የመጣው ግጭት እና በጆንጌሊ የተፈጸመው የአየር ጥቃት ወደ 280,000 ሰዎችን ከቀያቸው ማፈናቀሉን ገልጿል።የተፈናቃዮች ቁጥር ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች የሚያስፈልገውን ሰብዓዊ እርዳታ ጨምሮታል ሲል ኦቻ በመግለጫው ላይ ጠቅሷል።12 የጤና ተቋማት መዘረፋቸውን እና በከፊል መውደማቸው ያስታወቀው ኦቻ፣ ይህም አስፈላጊ የጤና አገልግሎቶችን አስተጓጉሏል፤ እንዲሁም ለችግር ለተጋለጡ ሰዎች የሚሰጠውን እንክብካቤ ገድቧል ብሏል።በመንግሥት እና ለማቻር ታማኝ በሆኑ ታጣቂዎች መካከል ግጭት እየተካሄደ ባለበት በአሁኑ ወቅት ደቡብ ሱዳን በሚቀጥለው ዓመት ታሕሳስ ምርጫ ለማካሄድ እየተዘጋጀች ነው።ደቡብ ሱዳን በአውሮፓውያኑ 2011 ነው ከሱዳን ተገንጥላ የዓለማችን በዕድሜ ትንሿ ሀገር የሆነችው።ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር የአገሪቱ የመጀመሪያው ፕሬዝደንት ሲሆኑ ሪክ ማቻር ደግሞ የመጀመሪያው ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ።ነገር ግን ከሁለት ዓመት በኋላ ፕሬዝዳንት ኪር ሙሉ ካቢኒያቸውን አባረው ማቻር መፈንቅለ መንግሥት እያሴሩ ነው ብለው ከወቀሱ በኋላ በአገሪቱ የእርስ በርስ ጦርነት ተቀሰቀሰ።በዚህ አምስት ዓመት በዘለቀ ደም አፋሳሽ የእርስ በርስ ጦርነት ምክንያት ከ400 ሺህ በላይ ሰዎች ሲገደሉ፤ 2.5 ሚሊዮን ሰዎች ተፈናቅለዋል።በሁለቱ ተፋላሚ ወገኖች መካከል በ2018 የሰላም ስምምነት ተፈርሞ፣ ሁለቱም አካላት አዲስ ሕገ-መንግሥት ለማፅደቅ፣ ምርጫ ለማካሄድ፣ የጦር ኃይሎቻቸውን ለማዋሃድ እንደሁም የሕዝብ ቆጠራ ለማካሄድ እና የታጠቁ ኃይሎችን መሳሪያ ለማስፈታት ተስማምተዋል።ነገር ግን እስካሁን ከስምምነቱ ማዕቀፎች አንዱም ተፈፃሚ አልሆነም። በሀገሪቱ የተለያዩ ግጭቶች መከሰታቸውም ቀጥሏል።ያጋሩ, የመንግሥታቱ ድርጅት በደቡብ ሱዳን ግጭት ጉዳት የሚደርስባቸው ሰዎች እየጨመሩ መምጣታቸውን ገለፀ - 16 የካቲት 2026ቤንያሚን ኔታንያሁ ኢራን ያበለፀገችውን ዩራኒየም ማስረከብ አለባት አሉ
የፎቶው ባለመብት,Reutersየእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ አሜሪካ ከቴህራን ጋር በምታደርገው ድርድር ያበለፀገችውን ዩራኒየም በሙሉ እንድታስረክብ እና የበለጠ እንዳታበለጽግ ልትታገድ ይገባል አሉ።ጠቅላይ ሚኒስትሩ እሁድ ዕለት በእየሩሳሌም ባደረጉት ንግግር በአሜሪካ እና በኢራን መካከል በሚካሄደው የኒውክሌር ድርድር ወቅት መኖር ስላለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ዘርዝረዋል።“ሁሉም የበለፀጉ ዩራኒየሞች ከኢራን መውጣት አለባቸው” ያሉት ኔታንያሁ “ምንም የማበልጸግ አቅም መኖር የለበትም” ሲሉ ተናግረዋል።ኔታንያሁ ይህንን ያሉት የኢራን እና የአሜሪካ ባለሥልጣናት ማክሰኞ በስዊትዘርላንድ ለሚካሄደው ሁለተኛ ዙር ድርድር እየተዘጋጁ ባሉበት ወቅት ነው።ኢራን የኒውክሌር ስምምነት ላይ ለመድረስ አሜሪካ ማዕቀቦችን የምታነሳ ከሆነ ለማመቻመች ዝግጁ መሆኗን የኢራኑ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማጂድ ታክት-ራቫንቺ በቴህራን ለቢቢሲ ተናግረዋል።ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ኢራን፤ አሜሪካ የጣለችባትን ማዕቀቦች ለማንሳት ፈቃደኛ ከሆነች፤ ከአቋሟ ፈቀቅ ብላ የኒውክሌር ስምምነት ላይ የመድረስ ሐሳብን ለማጤን ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል።ይሁን እንጂ ኢራን ምንም ዩራኒየም ማበልጸግ የለባትም የሚለውን እንደ ቀይ መስመር እና በኒውክሌር አለማስፋፋት ስምምነት መሠረት መብቷን መጣስ አድርጋ ትቆጥራለች።አሜሪካ ኢራን ስምምነት ላይ እንድትደርስ ጫና እያደረገች ሲሆን በመካከለኛው ምሥራቅም ያላትን ወታደራዊ አቅም በማጠናከር፣ ሁለት የአውሮፕላን ተሸካሚ መርከቦችን ወደ ቀጣናው አስጠግታለች።ተጨማሪ የአሜሪካ የባሕር ኃይል በቀጠናው ውስጥ ሊከሰቱ ከሚችሉ ማናቸውም አደጋዎች ይጠብቃሉ ሲሉ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ በስሎቫኪያ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል።የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን ላይ ከሚሰነዘረው ቀጥተኛ ጥቃት ይልቅ “ዲፕሎማሲያዊ እና በድርድር የሚገኝ ስምምነትን” እንደሚመርጡ ተናግረዋል።የትራምፕ ከፍተኛ ልዑክ ስቲቭ ዊትኮፍ እና ጄሬድ ኩሽነር ወደ ጄኔቫ በመጓዠ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺን እና ልዑካቸውን ያነጋግራሉ።ሩቢዮ “ማንም ሰው ከኢራን ጋር የተሳካ ስምምነት ማድረግ አልቻለም፤ እኛ ግን እንሞክራለን” ብለዋል።ያጋሩ, ቤንያሚን ኔታንያሁ ኢራን ያበለፀገችውን ዩራኒየም ማስረከብ አለባት አሉ - 16 የካቲት 2026ቻይና፤ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለ53 የአፍሪካ አገራት ከቀረጥ ነጻ የሆነ የወጪ ንግድን ተግባራዊ ልታደርግ ነው
የፎቶው ባለመብት,AFPቻይና ከ53 የአፍሪካ አገራት እአአ ከግንቦት 1፣ 2026 ጀምሮ ወደ አገሯ ለሚያስገቡት ምርቶች ምንም ዓይነት ታሪፍ እንደማትጥል ማስታወቋን የአገሪቱ ብሔራዊ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ።ቻይና ከእነዚህ የአፍሪካ አገራት ጋር የጋራ የኢኮኖሚ አጋርነት ስምምነቶችን ለመደራደር እና ለመፈረም ግፊት ማድረጓን ትቀጥላለች ተብሏል።እንዲሁም እንደ “ግሪን ቻናል” ባሉ የተሻሻሉ ዘዴዎች ወደ ቻይና የሚላኩ የአፍሪካ ምርቶች ተደራሽነትን የበለጠ እንደምታሰፋ የመንግሥት የቴሌቪዥን ዘገባ አመልክቷል።የቻይና ‘ግሪን ቻናል’ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው እቃዎች፣ አገልግሎቶች ወይም ኢንቨስትመንቶች በአነስተኛ ቢሮክራሲ፣ በተቀላጠፈ ሁኔታ ወደ አገሪቱ እንዲገቡ የሚያደርግ አሰራር ነው።ቻይና የጋራ ተጠቃሚነት ያለው ትብብርን ለማጎልበት እና “ሁሉን አቀፍ የቻይና-አፍሪካ ማኅበረሰብ የወደፊት የጋራ ተጠቃሚነት” ለማረጋገጥ ዝግጁ መሆኗን ተናግራለች።ይህ የቻይና የታሪፍ ውሳኔ የአፍሪካን የወጪ ንግድ ተወዳዳሪነት እንደሚያሳድግ፣ የገበያ ተደራሽነትን እንደሚያሰፋ፣ ወደ ቻይና ገበያ ለመግባት ያሉትን የንግድ እንቅፋቶችን በመቀነስ የኢንዱስትሪ እና የግብርና እሴት ሰንሰለትን ይደግፋል ተብሎ ይጠበቃል።የቻይናን ከቀረጥ ነጻ እድል ተጠቃሚ ያልሆነችው ብቸኛዋ አገር ኢስዋቲኒ ናት።ኢስዋቲኒ ተጠቃሚ ያልሆነችው አገሪቱ ከታይዋን ጋር ይፋዊ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ስላላት መሆኑን የመገናኛ ብዙኃን ዘገባዎች ያሳያሉ።ያጋሩ, ቻይና፤ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለ53 የአፍሪካ አገራት ከቀረጥ ነጻ የሆነ የወጪ ንግድን ተግባራዊ ልታደርግ ነው - 16 የካቲት 2026ቱርክ ነዳጅ ቆፋሪ መርከቧን ወደ ሶማሊያ ላከች
የፎቶው ባለመብት,AAቱርክ እሁድ ዕለት ጥልቅ ነዳጅ ቆፋሪ የሆነውን መርከቧን ለመጀመሪያ ተልዕኮው ወደ ሶማሊያ መላኳን አስታውቃለች።የቱርክ የኢነርጂ እና ተፈጥሮ ሐብት ሚኒስትር አልፓስላን ባይራካታር እርምጃውን ታሪካዊ ብለውታል።መርከቡ ከ45 ቀናት ጉዞ በኋላ ሞቃዲሾ ደርሶ ቁፋሮውን እንደሚጀምር ተነግሯል።ቱርክ እና ሶማሊያ እ.አ.አ በ2014 በባሕር እና በባሕር ዳርቻ ላይ የነዳጅ እና ጋዝ ፍለጋ ለማከናወን ተስማምተዋል።አሁን የተላከውን መርከብ ጨምሮ ነዳጅ የሚቆፍሩ የቱርክ መርከቦች ቁጥር ስድስት መድረሱን ሚኒስትሩ ተናግረዋል ሲል የቱርክ የዜና ወኪል አናዶሉ ዘግቧል።ቱርክ ግዙፍ የባሕር ዳርቻ ነዳጅ ፍለጋ በማካሄድ ከዓለም አራተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝም አክለው ተናግረዋል።ከአዲሱ የጎርጎሮሳዊያን ዓመት ወዲህ አገሪቱ በጋዝ እና ነዳጅ ፍለጋ ላይ ከተሰማሩ የአሜሪካ እና ዩናይትድ ኪንግደም ኩባንያዎች ጋር ስልታዊ ስምምነት አድርጋለች።ያጋሩ, ቱርክ ነዳጅ ቆፋሪ መርከቧን ወደ ሶማሊያ ላከች - 16 የካቲት 2026የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራጋቺ ከአሜሪካ ጋር ለመደራደር ጄኔቫ ገቡ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺየኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራጋቺ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ለሚያደርጉት ሁለተኛው ዙር የኒውክሌር ድርድር የስዊትዘርላንድስ ዋና ከተማ ጄኔቫ ገቡ።አሜሪካ እና ኢራን በተዘዋዋሪ የሚያደርጉት ድርድር ማክሰኞ ዕለት በጄኔቫ እንደሚጀመር ተገልጿል።ድርድሩን የምትመራው ኦማን መሆኗ የተገለፀ ሲሆን የአሜሪካ ልዑካን ቡድንን ስቲቭ ዊትኮፍ እና ጄሬድ ኩሽነር እንደሚመሩ ታውቋል።የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ዋሺንግተን ውጤታማ ስምምነት ላይ ለመድረስ ጥረት እያደረገች መሆኑን ተናግረዋል።“ከኢራን ጋር ማንም ውጤታማ ስምምነት ላይ መድረስ አልቻለም፤ እኛ ግን እየሞከረን ነው” ብለዋል።አክለውም “ስቲቭ ዊትኮፍ እና ጄሬድ ኩሽነር ከኢራን ጋር ለሚደረገው ድርድር ወደ ስፍራው እያመሩ ነው፤ የሚሆነውን እናያለን” ብለዋል።የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ቅዳሜ ዕለት ባደረጉት ንግግር፤ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስምምነት ላይ መድረስን እንደሚመርጡ ገልጸዋል።ሁለቱ አገራት የሚያደርጉት ድርድር የሚካሄደው የኢራንን መንግሥትን የሚቃወሙ ሠልፎች በዓለማችን የተለያዩ ክፍሎች ከተደረጉ ከሁለት ቀናት በኋላ ነው።ያጋሩ, የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራጋቺ ከአሜሪካ ጋር ለመደራደር ጄኔቫ ገቡ - 16 የካቲት 2026በመላው ዓለም የኢራን መንግሥትን በመቃወም የተቃውሞ ሠልፎች ተካሄዱ
የፎቶው ባለመብት,LightRocket via Getty Imagesየኢራን የቀድሞው ንጉሥ ልጅ “ዓለም አቀፍ የተግባር ቀን” ሲሉ ያስተላለፉትን ጥሪ ተከትሎ” በመላው ዓለም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሠልፈኞች የኢራንን መንግሥት በመቃወም አደባባይ ወጡ።ሬዛ ፓጃላቪ በሙኒክ 250ሺህ ለሚገመቱ ሰዎች ንግግር ሲያደርጉ የኢራን እስላማዊ አገዛዝ ከሥልጣን እንዲወርድ ጥሪ አቅርበዋል።በንግግራቸው በቅርቡ በአገሪቱ የተካሄደውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የደረሰውን እስር፣ አፈና እና ግድያ ተቃውመዋል።በሙኒክ፣ ሎስ አንጀለስ እና ቶሮንቶ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች አደባባይ በመውጣት በኢራን መንግሥት ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ገልጸዋል።በቁጥር ትንሽ ቢሆኑም በቴል አቪቭ፣ ሊዝበን፣ ሲድኒ እና ለንደንም ተመሳሳይ ሰልፎች ተካሄደዋል። የመብት ተሟጋቾች በአገሪቱ የተከሰተውን የኑሮ ውድነት ተከትሎ በአገር አቀፍ ደረጃ በተካሄደው ተቃውሞ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች 6000 ያህል ሰዎችን መግደላቸውን ይናገራሉ።ፓህላቪ ለተሰበሰበው ሕዝብ “የመጀመሪያው መልዕክቴ በአገር ውስጥ ላሉ ጀግኖች እና ታጋይ ወገኖቻችን ነው፤ ብቻችሁን እንዳልሆናችሁ እወቁ፤ እናም ዛሬ በዚህ ትግል ዓለም ከጎናችሁ ነው።”የኢራንን አመራር በመተቸት “ከዚህ ሙሰኛ፣ ጨቋኝ፣ ሕፃናትን ከሚገድል አገዛዝ በተለየ እናንተ ታላቅ ባህል እና ሥልጣኔን ትወክላላችሁ፤ እና በነገዋ ነፃ ኢራን ውስጥ እኛ ምንኛ ታላቅ አገር መሆናችንን ለዓለም ታረጋግጣላችሁ” ብለዋል።ያጋሩ, በመላው ዓለም የኢራን መንግሥትን በመቃወም የተቃውሞ ሠልፎች ተካሄዱ
