የአሜሪካ ከፍተኛ የብሔራዊ ደኅንነት ባለሥልጣናት ለፕሬዝዳንት ትራምፕ የአገሪቱ ጦር እስከ ቅዳሜ ድረስ ኢራን ላይ ሊፈጸሙ ስለሚችሉ ጥቃቶች ዝግጁ መሆኑን ማሳወቃቸውን በአሜሪካ የቢቢሲ አጋር የሆነው ሲቢኤስ ምንጮችን ጠቅሶ ዘገበ።

ጭምቅ ሃሳብ

የቀጥታ ሽፋን

  1. ከ 1 ሰአት በፊትየተባበሩት መንግሥታት በሱዳን የተፈጸሙ ጥቃቶች “የዘር ማጥፋት ማሳያዎች” ናቸው አለየሱዳን ግጭት የተፈናቀለች ሴትየፎቶው ባለመብት,Reutersየመንግሥታቱ ድርጅት እውነት አፈላላጊ ተልዕኮ የሱዳኗ ኤል ፋሸር በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ቁጥጥር ሥር በዋለችበት ወቅት የተፈጸሙ ወንጀሎች የዘር ማጥፋትን እንደሚያመለክቱ ገለጸ።የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ (አርኤስኤፍ) በምዕራብ ዳርፉር የምትገኛውን ኤል ፋሸርን ለ18 ወራት በከበባ ስር ካቆየ በኋላ በቁጥጥሩ ሥር ያዋላት በጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ ነበር።ይህም ለሦስት ዓመት በቀጠለው የሰዳን የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ በጣም አስከፊው ጊዜ ነበር የተባለ ሲሆን ዓለም አቀፍ ውግዘትንም አስከትሏል።የመንግሥታቱ ድርጅት በግጭቱ ወቅት የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ በዳርፉር የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽሟል የሚል ድምዳሜ ላይ ሲደርስ ይህ የመጀመሪያው ነው።አርኤስኤፍ በመንግሥታቱ ድርጅት ሪፖርት ላይ አስተያየቱን ባይሰጥም ከዚህ ቀድም በቀረቡ ተመሳሳይ ውንጀላዎች ላይ ማስተባባያ ሰጥቷል።የእውነት አፈላላጊ ተልዕኮው ባለሙያ የሆኑት ሞና ሪሽማዊ “የሰበሰብናቸው ማስረጃዎች የተራዘመ ከበባ፣ ረሃብ እና የሰብዓዊ እርዳታን መከልከልን ጨምሮ የጅምላ ግድያ፣ ደፈራ፣ ስቅይት እና አስገድዶ መሰወር፣ ስልታዊ ማዋረድ መፈጸማቸውን ያሳያል በተጨማሪም የጥቃት ፈጻሚዎቹ ቃል እነዚህ ድርጊቶች መፈጸማቸውን ያረጋግጣል” ብለዋል።“አርኤስኤፍ በኤልፋሽር የሚገኙ የዛግሃዋ እና የፉር ማኅበረሰቦችን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል ለማጥፋት ሆን ብሎ በማሰብ ተንቀሳቅሷል። እነዚህም የዘር ማጥፋት ማሳያዎች ናቸው።”ሪፖርቱ በማጠቃለያው ሦስት የዘር ማጥፋት ድርጊቶች መፈጸማቸውን ደምድሟል።ከእነዚህም መካከል ከለላ ያላቸው የማኅበረሰብ ቡድኖችን መግድል፣ ከባድ የሆነ የአካል እና የአእምሮ ጉዳት ማድረስ፣ ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል ቡድኑ ላይ አካላዊ ውድመት ለማድረስ ይሁነኝ ተብሎ እርምጃ መውሰድ ይገኙበታል።የዩናይትድ ኪንግደም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ይቬት ኩፐር ሪፖርቱን “አሰቃቂ” ያሉት ሲሆን መደምደሚያውን ደግሞ ሐሙስ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት እንደሚያቀርቡ ተናግረዋል።ሚኒስትሯ በመግለጫቸው ለወንጀል ፈጻሚዎቹን ተጠያቂ ለማድረግ እና ለተጠቂዎች ፍትህ ለመስጠት እንዲሁም ወደ ግጭቱ የሚሄደውን የጦር መሳሪያ ፍሰት ለማስቆም ዓለም አቀፍ ወንጀል ምርመራ መካሄድ አለበት ብለዋል።የሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት በአገሪቱ ጦር አዛዥ እና በምክትላቸው መካከል በተፈጠረው የሥልጣን ሽኩቻ የተነሳ እአአ በ2023 ተጀምሯል።ያጋሩ, የተባበሩት መንግሥታት በሱዳን የተፈጸሙ ጥቃቶች “የዘር ማጥፋት ማሳያዎች” ናቸው አለ
  2. ከ 1 ሰአት በፊትክራይስስ ግሩፕ በሰሜን ኢትዮጵያ እየተባባሰ የመጣው ውጥረት ወደ ከባድ ግጭት የመመለስ ስጋት እንዳለው አስጠነቀቀየኢትዮጵያ መከላከያ ጦርየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesዓለም አቀፉ ክራይስስ ግሩፕ በኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት፣ በትግራይ ክልል እና በጎረቤት ኤርትራ መካከል እየተባባሰ የመጣው ውጥረት የአፍሪካ ቀንድን ከሦስት ዓመታት በኋላ መልሶ ወደ ደም አፋሳሽ ጦርነት ሊከት ይችላል ሲል አስጠነቀቀ።ተቋሙ ባወጣው መግለጫ የተለያዩ ምክንያቶች ጦርነቱን ሊያፈነዱት እንደሚችሉ ያስጠነቀቀ ሲሆን፤ ወደ ጦርነት ዘው ብሎ ለመግባት ቀላል ቢሆንም ጦርነቱን ለማቆም ግን በጣም ከባድ ይሆናል ብሏል።የአፍሪካ የፕሮግራም ዳይሬክተር የሆኑት ሙሪታ ሙቲጋ “ኢትዮጵያን፣ ኤርትራን እና ትግራይ ክልልን የሚያፋልም አዲስ ጦርነት መቋቋም የማይቻል ዋጋ ያለው ነው። አደጋው ሦስቱንም ወገኖች ለአሁኑ እንዲታቀቡ ያደረጋቸው ይመስላል። ሆኖም እንዳያገረሽ ከዚህ በላይ መደረግ አለበት” ብለዋል።የድርጅቱ ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት ማግነስ ታይለር ከትግራይ ጦርነት መቋጨት በኋላ በዋናነት ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የባህር በር የማግኘት ፍላጎት ምክንያት የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ግንኙነት መሻከሩን አንስተዋል።ኤርትራ ይህ ፍላጎት “ወረራን ሊያካትት ይችላል” የሚል ስጋት እንዳላትም ጠቁመዋል።ምክትል ዳይሬከተሩ አዲስ አበባ ህውሓት ከኤርትራ ጋር ስውር ትብብር መስርቷል ስትል እንደምትከስ ተናግረዋል።የክራይስስ ግሩፕ መግለጫ በቅርቡ በፌደራል መንግሥቱ እና በትግራይ ኃይሎች የድሮን ጥቃትን ያካተተው ግጭት ኤርትራንም በመሳብ ወደ ሰፊ ጦርነት ሊቀየር እንደሚችል ያሳያል ብሏል።ተቋሙ አክሎም በሰሜን ኢትዮጵያ አዲስ የሚቀሰቀስ ግጭት በሱዳን ካለው ግጭት ጋር ተደርቦ ኃያላን የውጭ ተዋንያንን እንደሚስብ እና ተለዋዋጭ የሆነውን የቀይ ባህር ቀጣናን እንደሚያውክ አስጠንቅቋል።ክራይስስ ግሩፕ ተፅዕኖ ፈጣሪ የአፍሪካ አገራት እና ዓለም አቀፍ አጋራት የዲፕሎማሲያዊ ሥራቸውን እንዲጨምሩ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት እና ህወሓትን እንዲያሸማግሉ ጠይቋል።አክሎም የኢትዮጵያ የባህር በር የማግኘት ፍላጎትን እና የኤርትራን ሉዓላዊነቷ ላይ ጥቃት የመሰንዘር ስጋትን ጨምሮ በሁለቱም በኩል ያሉ ወገኖች ቁርሾዎችን እንዲፈቱ ጥሪ አቅርቧል።“ሰሜን ኢትዮጵያ የባሩድ በርሜል ነው። እናም በግጭት በተጎዳው የአፍሪካ ቀንድ ቀጣናን ከዚህ በላይ የሚያናውጥ አዲስ አክሳሪ ጦርነት ሊያቀጣጥል ይችላል” ብሏል።ያጋሩ, ክራይስስ ግሩፕ በሰሜን ኢትዮጵያ እየተባባሰ የመጣው ውጥረት ወደ ከባድ ግጭት የመመለስ ስጋት እንዳለው አስጠነቀቀ
  3. ከ 2 ሰአት በፊትየቀድሞው የደቡብ ኮሪያ ፕሬዚዳንት የእድሜ ልክ እስር ተፈረደባቸውየደቡብ ኮሪያ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዮን ሱክ ዮልየፎቶው ባለመብት,EPAየቀድሞው የደቡብ ኮሪያ ፕሬዚዳንት መንግሥት ላይ አመጽ በማነሳሳት ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው የእድሜ ልክ እስር ተፈረደባቸው።የደቡብ ኮሪያ ፍርድ ቤት የቀድሞ ፕሬዚዳንት እአአ በታሕሳስ 2024 በአገሪቱ ላይ ወታደራዊ አመራር ለመጫን ያደረጉት ሙከራ መክሸፉን ተከትሎ ነው ክስ የተሰረተባቸው።የአገሪቱ ፍርድ ቤት ዛሬ በሰጠው ውሳኔ ዮን ሱክ ዮል መንግሥት ላይ አመጽ በማነሳሳት ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው የእድሜ ልክ እስር ተፈርዶባቸዋል።በወቅቱ የመከላከያ ሚኒስትር የነበሩት ኪም ዮንግ ሂዩንም ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው የ30 ዓመት እስር ተፈርዶባቸዋል።ዮል ሱክ ዮልን በወቅቱ ተቃዋሚ የነበሩት እና አሁን የአገሪቱ ፕሬዚዳንት የሆኑት ሊ ጃይ ሚዩንግ በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ትዕዛዝ ሰጥተው ነበር ተበሏል።ከዚህ በፊት ዮል ሥልጣንን ያለ አግባብ በመጠቀም እንዲሁም ሕገመንግሥታዊ ሥርዓትን በመጣስ ወንጀሎች ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተው ነበር።ዮል እና ከእርሳቸው ጋር የተፈረደባቸው የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ይግባኝ መጠየቅ ይችላሉ ተብሏል።ያጋሩ, የቀድሞው የደቡብ ኮሪያ ፕሬዚዳንት የእድሜ ልክ እስር ተፈረደባቸው
  4. ከ 2 ሰአት በፊትትራምፕ እስከ ቅዳሜ ድረስ በኢራን ላይ ጥቃት መፈጸም ስለሚቻልበት ሁኔታ ከአማካሪዎቻቸው ጋር መወያየታቸው ተነገረትረምፕየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየአሜሪካ ከፍተኛ የብሔራዊ ደህንነት ባለሥልጣናት ለፕሬዝዳንት ትራምፕ የአገሪቱ ጦር እስከ ቅዳሜ ድረስ ኢራን ላይ ሊፈጸሙ የሚችሉ ጥቃቶችን ዝግጁ መሆኑን ማሳወቁን በአሜሪካ የቢቢሲ አጋር የሆነው ሲቢኤስ ምንጮችን ጠቅሶ ዘገበ።ትረምፕ በኢራን ላይ ጥቃት መቼ ሊፈጸም እንደሚችል ከአማካሪዎቻቸው ጋር ቢነጋገሩም ከውሳኔ ላይ አለመድረሳቸው ተገልጿል።ሲቢኤስ ይህ እቅድ ወደፊት ሊገፋ እንደሚችል ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል።ምንጮች የትራምፕ አማካሪዎች የተፈጠረውን ውጥረት እንዲሁም “ጥቃቱ ባይፈጸም” የሚኖረውን ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ አደጋ እየፈተሹ መሆኑ ተገልጿል።በሚቀጥሉት ሦስት ቀናት ፔንታጎን የተወሰኑ ወታደራዊ ኃይሎችን ከመካከለኛው ምሥራቅ በማስውጣት ወደ አውሮፓ ወይንም ወደ አሜሪካ ያሰማራል ተብሏል።ሲቢኤስ ምንጮቹን ጠቅሶ አንደዘገበው ፔንታጎን ያሉትን ወታደራዊ ኃይሎች ከቦታ ወደ ቦታ ማንቀሳቀስ የተለመደ አሰራር መሆኑ የገለጸ ሲሆን በኢራን ላይ የሚፈጸመው ጥቃት የማይቀር መሆኑን አያሳይም ተብሏል።ያጋሩ, ትራምፕ እስከ ቅዳሜ ድረስ በኢራን ላይ ጥቃት መፈጸም ስለሚቻልበት ሁኔታ ከአማካሪዎቻቸው ጋር መወያየታቸው ተነገረ
  5. ከ 3 ሰአት በፊትዋይት ሐውስ አሜሪካ ወታደራዊ ኃይሏን እያጠናከረች ባለችበት ወቅት ኢራን ስምምነት ላይ ብትደርስ “ብልህነት” መሆኑን ተናገረኢራናዊት ሴት እየተራመደችየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን ላይ አዲስ ወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ እየተዘጋጁ መሆኑ በሚነገርበት ወቅት፣ ዋይት ሐውስ ኢራን ከአሜሪካ ጋር ስምምነት ላይ ብትደርስ “በጣም ብልህነት” መሆኑን በመግለጽ አስጠነቀቀ።የዋይት ሐውስ የፕሬስ ፀሐፊ ካሮላይንን ሊቪት ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ትራምፕ አሁንም በቴህራን የኒውክሌር ፕሮግራም ላይ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ እንደሚኖር ተስፋ አላቸው።የሊቪት አስተያየት የተሰማው አሜሪካ ሁለተኛ የጦር መርከቧን ወደ ቀጠናው ካንቀሳቀሰች እና በስዊትዘርላንድ በተካሄደው ውይይት ላይ መግባባቶች መኖራቸው ከተገለጸ ከአንድ ቀን በኋላ ነው።የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ረቡዕ ዕለት ትራምፕ ከአማካሪዎቻቸው ጋር ስለ ጥቃት አማራጮች መወያየታቸውን እና አሜሪካ እስከ ቅዳሜ ድረስ ጥቃት ልትፈጽም እንደምትችል ዘግበዋል።ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ላይ የአሜሪካ ጦር በሦስት የኢራን የኒውክሌር ተቋማት ላይ ጥቃት ፈጽሟል።በአሁኑ ወቅት ትራምፕ ጥቃት ለመሰንዘር የሚያስችል የመጨረሻ ውሳኔ ላይ አልደረሱም ተብሏል።በሁለቱ አገራት መካከል ሊኖሩ የሚችሉ ቀጣይ ውይይቶች ላይ እርግጠኛ መሆን እንደማይቻል ምንጮች ለቢቢሲ የአሜሪካ አጋር ሲቢኤስ ኒውስ ተናግረዋል።ሊቪት ረቡዕ ዕለት ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ” በኢራን ላይ ጥቃት ለመፈጸም የሚያስችሉ ብዙ ምክንያቶች እና ክርክሮች ሊኖሩ ይችላሉ።”በሰኔ ወር ስለነበረው የአሜሪካ የአየር ድብደባ የጠቀሱት ሊቪት “ኢራን ከፕሬዚዳንት ትራምፕ እና ከአስተዳደራቸው ጋር ስምምነት ላይ መድረስ ከቻለች በጣም ብልህነት ነው” ብለዋል።ማክሰኞ ዕለት በጄኔቫ በተካሄደው ቀጥተኛ ያልሆነ ውይይት ምንም ዓይነት እመርታ ያልታየ ቢመስልም፣ ሁለቱም ወገኖች አንዳንድ ጉዳዮችን በተመለከተ በጥሩ ሁኔታ መሄዱን ተናግረዋል።ኢራንም የኒውክሌር መርሃ ግብሯን በተመለከተ ከአሜሪካ ጋር “በዋነኛ መርሆች” ላይ እንደተግባቡ አስታውቃለች።ያጋሩ, ዋይት ሐውስ አሜሪካ ወታደራዊ ኃይሏን እያጠናከረች ባለችበት ወቅት ኢራን ስምምነት ላይ ብትደርስ “ብልህነት” መሆኑን ተናገረ
  6. ከ 5 ሰአት በፊትአሜሪካ ከኢራን ጋር ያላት ውጥረት እየጨመረ ባለበት ወቅት ጦሯን ከሶሪያ ልታስወጣ ነውየሶሪያው ፕሬዚዳንት አህመድ አል ሻራ የአሜሪካውን ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዋይት ሐውስ አግኝተው ተወያይተዋልየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesአሜሪካ በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት ውስጥ በሶሪያ የቀሯትን ወታደሮች ለማስወጣት በዝግጅት ላይ መሆኗን አንድ ከፍተኛ የዋይት ሐውስ ባለሥልጣን ለቢቢሲ ተናገሩ።ባለሥልጣኑ እንዳሉት የሶሪያ መንግሥት በግዛቱ ውስጥ ሽብርተኝነትን በመዋጋት ረገድ የመሪነት ሚናውን ለመጫወት እና የአሜሪካ ወታደራዊ ኃይል “በከፍተኛ ቁጥር” መኖሩ አስፈላጊ እንዳልሆነ ከስምምነት ላይ ተደርሷል።የአሜሪካ ወታደሮች እአአ ከ2015 ጀምሮ በሶሪያ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ይህም የኢስላሚክ ስቴት ቡድን (አይኤስ) ተጽዕኖን ለመግታት የሚደረገው የፀረ-ሽብር ዘመቻ አካል ነበር።የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሱት በመካከለኛው ምሥራቅ አገራቸው ከኢራን ጋር የገባችው ውጥረት እየተካረረ በመጣበት ወቅት ነው። ዶናልድ ትራምፕ ከዚህ ውሳኔያቸው በተቃራኒ በኢራን አቅራቢያ የአሜሪካ ጦር ኃይልን እያሰፈሩ ይገኛሉ።ቢቢሲ ቬሪፋይ በኢራን አቅራቢያ የጦር ጄቶችን መሸከም የሚችለው የዩኤስኤስ አብርሃም ሊንከን መርከብ መኖሩን አረጋግጧል።ባለሥልጣኑ እንዳሉት ወደ 1,000 የሚጠጉ የቀሩትን ወታደሮች ከሶሪያ የማስወጣት ውሳኔ የአገሪቱ አስተዳደር ሽግግር አካል ሲሆን አሜሪካም በቀጠናው ውስጥ ለሚከሰቱ ማናቸውም ስጋቶች ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ሆና ትቀጥላለች።የአሜሪካ ወታደሮች በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ በሶሪያ ከሚገኙ ሁለት የጦር ሰፈሮች ለቅቀው ወጥተዋል።ጦሩ ይህንን እርምጃ የወሰደው እአአ በ2024 የአሳድ መንግሥት መውደቁን ተከትሎ በሶሪያ ከፍተኛ የጸጥታ መሻሻል በመታየቱ እና ኢስላሚክ ስቴት መዳከሙን ተከትሎ ነው።ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የትራምፕ አስተዳደር ከደማስቆ ጋር ያላቸውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማጠናከር እና ከሶሪያ ፕሬዝዳንት አህመድ አል ሻራ ጋር ያላቸውን አጋርነት ለማሳደግ ጥረት አድርገዋል።የሶሪያው ፕሬዚዳንት አህመድ አል ሻራ በኅዳር ወር ትራምፕን በዋይት ሐውስ አግኝተው የተወያዩ ሲሆን ይህም በሶሪያ ታሪክ የመጀመርያው ፕሬዚዳንት ያደርጋቸዋል።ያጋሩ, አሜሪካ ከኢራን ጋር ያላት ውጥረት እየጨመረ ባለበት ወቅት ጦሯን ከሶሪያ ልታስወጣ ነው
  7. 18 የካቲት 2026የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሥራ ጊዜ ለተጨማሪ ጊዜ ተራዘመመስፍን አርአያ (ዶ/ር)የፎቶው ባለመብት,HoPRየምስሉ መግለጫ,የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርአያ (ዶ/ር)የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የጀመረውን ሥራ እንዲያጠናቅቅ ተጨማሪ የስምንት ወራት የሥራ ጊዜ እንዲሰጠው ወሰነ።ለሦስት ዓመት የሥራ ዘመን የተቋቋመው የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ባለፈው ዓመትም በተመሳሳይ ሁኔታ በተካሄደ የምክር ቤቱ አስቸኳይ ስብሰባ የሥራ ጊዜው ለአንድ ዓመት እንዲራዘም መደረጉ ይታወሳል።የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ የካቲት 11/2018 ዓ.ም. ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ የኮሚሽኑን የአራት ዓመታት የሥራ ሪፖርት በማድመጥ ውይይት ካደረገ በኋላ ነው የሥራ ጊዜው ለተጨማሪ ስምንት ወራት እንዲራዘም የወሰነው።የካቲት 14/2014 ዓ.ም. ተቋቁሞ ሥራ የጀመረው ኮሚሽኑ ‎የተራዘመለት የአንድ ዓመት የሥራ ጊዜ የካቲት 14/2018 ዓ.ም. የሚያበቃ በመሆኑ የቀሩ ሥራዎችን ለማከናወን ‎ከየካቲት 15/2018 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ቀጣይ ዓመት ጥቅምት አጋማሽ የሥራ ጊዜው ተራዝሟል።በዶ/ር መስፍን አርአያ የሚመራው የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገራት ምከክር እና የአጀንዳ ማሰባሰብ ሥራ ሲያከናውን ቆይቷል።ነገር ግን ኮሚሽኑ በትግራይ ክልል አጀንዳ ማሰባሰብ እና የምክክር ጉባዔውን ለማካሄድ ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጠው በጠየቀው መሠረት የሥራ ጊዜ ተራዝሟል።ያጋሩ, የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሥራ ጊዜ ለተጨማሪ ጊዜ ተራዘመ
  8. 18 የካቲት 2026ኢራን እና ሩሲያ የጋራ የባሕር ኃይል ወታደራዊ ልምምድ ሊያደርጉ ነውየሩሲያ እና የኢራን ባሕር ኃይል ባለሥልጣናትየፎቶው ባለመብት,IRNAየምስሉ መግለጫ,የሩሲያ እና የኢራን ባሕር ኃይል ባለሥልጣናትከአሜሪካ ጋር ፍጥጫ ውስጥ የምትገኘው ኢራን በኦማን ባሕር አቅራቢያ እና በሰሜን ሕንድ ውቅያኖስ ላይ ከሩሲያ ጋር የባሕር ኃይል ወደታራዊ ልምምድ ልታደርግ ነው።ወታደራዊ ልምምዱን በተመለከተ ቃል አቀባይ የሆኑት ሪር አድሚራል ሐሳን ማግሱድሉ በሰጡት መግለጫ ልምምዱ በአራን ባሕር ኃይክ አስተናጋጅነት የሚካሄድ ነው። “ዋነኛ ዓላማውም በኦማን ባሕር እና በሴማነዊ ሕንድ ውቅያኖስ አስተማማኝ የባሕር ላይ ግንኙነት እና ደኅንነትን ማስጠበቅ ነው” ብለዋል።በልምምዱ የሁለቱ አገራት ባሕር ኃይሎች በቅንጅት በቀጣናው የባሕር ላይ እንቅስቃሴ ስጋት የሆኑ ተግባራትን መከላከል በተለይም የንግድ እና ነዳጅ ጫኝ መርከቦችን መጠበቅ እንዲሁም የባሕር ላይ ሽብርተኝነትን መዋጋት መሆኑ ተገልጿል።ይህ ሐሙስ ይጀመራል የተባለው የባሕር ላይ ወታደራዊ ልምምድ የሚካሄደው የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ በሆርሙዝ ሰርጥ ላይ የባሕር ኃይል ልመምድ ካደረገ ከቀናት በኋላ ነው።በተጨማሪም ኢራን ላይ ወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ እየዛተች ያለችው አሜሪካ ግዙፍ አውሮፕላን ጫኝ እና ሌሎች የጦር መርከቦችን ወደ ፋርስ ባሕረ ሰላጤ እያሰማራች ባለችበት ጊዜ የሚካሄድ ወታደራዊ ልምምድ ነው።ኢራን እና አሜሪካ በመካከላቸው የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ ኦማን እና ስዊትዘርላንድ ውስጥ ሁለት ዙር ድርድር ያደረጉ ሲሆን፣ ሦስተኛ ዙር ንግግር በቀጣይ እንደሚያደርጉ እየተነገረ ነው።ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኢራን በኒውክሌር መራሃ ግብሯ እና በረጅም ርቀት ሚሳኤሎች ግንባታዋ ላይ የሚቀርብላትን ሃሳብ የማትቀበል ከሆነ ወታደራዊ እርምጃ እንደሚጠብቃት ሲያስጠነቅቁ ቆይተዋል።ኢራን በበኩሏ የኒውክሌር ግንባታዋ ለሰላማዊ ዓላማ ብቻ እንደሚውሉ በተደጋጋሚ እየገለጸች ሲሆን፣ ለድርድር የማታቀርባቸው ጉዳዮች እንዳሉ ይፋ ከማድረጓ በተጨማሪ ጥቃት የሚፈጸምባት ከሆነ የምትሰጠው አጸፋ ከባድ እንደሚሆን አስጠንቅቃለች።ያጋሩ, ኢራን እና ሩሲያ የጋራ የባሕር ኃይል ወታደራዊ ልምምድ ሊያደርጉ ነው
  9. 18 የካቲት 2026“አስቸጋሪ” የተባለው የዩክሬን-ሩሲያ ድርድር ያለ ውጤት ተጠናቀቀየሩሲያ፣ የአሜሪካ እና የዩክሬን ተወካዮች ማክሰኞ እና ረቡዕ በጄኔቫ ተገናኝተው ተወያይተዋልየፎቶው ባለመብት,Reutersየሩሲያ እና የዩክሬን ጦርነትን ለማስቆም ያለመው አሜሪካ ያሸማገለችው ውይይት ያለ ምንም ውጤት ተጠናቀቀ።በስዊትዘርላንድ ጄኔቫ የተካሄደው የሦስትዮሽ ንግግር ማክሰኞ ዕለት አመሻሽ ላይ ቢጀምርም ረቡዕ ግን መካሄድ የቻለው ለሁለት ሰዓት ብቻ ነው።የአሜሪካው አምባሳደር ስቲቭ ዊትኮፍ በውይይቱ ላይ ያላቸውን ተስፋ ተናግረው የነበረ ቢሆንም፤ የሩሲያም ሆነ የዩክሬን ተደራዳሪዎች “አስቸጋሪ” መሆናቸውን ገልጸዋል።ሞስኮ እና ኪየቭ በአራት ዓመታት ግጭት ውስጥ ቁልፍ በሆኑ የግዛት ጉዳዮች እና የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ አሁንም ድረስ ልዩነት አላቸው።የነበረው ውይይት አስቸጋሪ እንደነበር ያመኑት የሞስኮ ተደራዳሪ ቭላድሚር ሜዲንስኪ፣ ድርድሩ “የተለመደው ዓይነት” እንደነበር እና ሌላ ስብሰባ በቅርቡ እንደሚካሄድ ተናግረዋል።የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪም ድርድሩን በሁለቱ ወገኖች አቋም ልዩነት የተነሳ “ቀላል አልነበረም” ሲሉ ተናግረዋል።የዩክሬን ተደራዳሪ ሩስቴም ኡሜሮቭ በውይይቱ ምንም እንኳ ለውጥ ባይታይም “ከፍተኛ እና ጥልቅ” በማለት “በዚህ ደረጃ” ምንም ዓይነት ዝርዝር ጉዳዮችን ይፋ ማድረግ እንደማይቻል ተናግረዋል።”ይህ በሁሉም ወገኖች መካከል ስምምነት እና በቂ ጊዜ የሚፈልግ ውስብስብ ሥራ ነው” ሲሉ ኡሜሮቭ ተናግረዋል።የውይይቱ ማብቃቱ ከመነገሩ ጥቂት ቀደም ብሎ ዜሌንስኪ ሩሲያ “ወደ መጨረሻው ደረጃ ሊደርስ የሚችል ድርድርን ለማዘግየት እየሞከረች ነው” ሲል ከስሰዋል።የሩሲያ እና የዩክሬን ልዑካን ቡድን ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኙት በጥር ወር አሜሪካ አቡዳቢ ላይ ባዘጋጀችው የድርድር መድረክ ላይ ነበር።ይህም በጥቂት ወራት ውስጥ የመጀመሪያውን የእስረኞች ልውውጥ ማድረግ አስችሏል። ረቡዕ ዕለት ዜሌንስኪ ሌላ የእስረኛ ልውውጥ ሊኖር እንደሚችል ጠቁመዋል።የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል የሚካሄደው ጦርነት እንዲያበቃ ለማድረግ የሚደረገውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ይመራሉ።ያጋሩ, “አስቸጋሪ” የተባለው የዩክሬን-ሩሲያ ድርድር ያለ ውጤት ተጠናቀቀ
  10. 18 የካቲት 2026ጋቦን “ሐሰተኛ መረጃ እያተሰራጩ ነው” በሚል ማኅበራዊ ሚዲያን አገደችየተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎችን የሚያሳይ የስልክ ስክሪንየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesበማዕከላዊ የአፍሪካ ክፍል የምትገኘው ጋቦን መገናኛ ብዙኃን ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን የማኅበራዊ ሚዲያዎችን በአገሪቱ ውስጥ ግጭትን እያባባሱ እና መከፋፈልን እያሰፉ ነው በሚል ላልተወሰነ ጊዜ አገደ።ማክሰኞ ምሽት በአገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ የአገሪቱ ከፍተኛ ኮሚዩኒኬሽን ባለሥልጣን “ሐሰተኛ መረጃ ሥርጭት”፤ “የኦንላይን ዘለፋ” እንዲሁም “ያለፈቃድ የግል መረጃን ማሠራጨት” ለውሳኔዎቹ ምክንያት መሆናቸውን ገልጿል።የባለሥልጣኑ ቃል አቀባይ ዤን ክላውዴ ሜንዶሜ የትኛው የማኅበራዊ ሚዲያ በዚህ ውሳኔ እርምጃ እንደሚወሰድበት ግልጽ ባያደርጉም በአገሪቱ ውስጥ ግን ዋትስአፕ፣ ቲክ ቶክ እና ፌስ ቡክ ዝነኛ ናቸው።አገሪቱን በፕሬዚዳንትነት የሚያስተዳድሩት ጄነራል ብሪስ ኦሊጉኢ ንጉማ እአአ በ2023 ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ካካሄዱ በኋላ ባለፈው ዓመት የተካሄደውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አሸንፈዋል።የ50 ዓመቱ ፕሬዚዳንት ከመምህራኖች እና ሌሎች የመንግሥት ሠራተኞች የደሞዝ ክፍያ ጋር በተያያዘ ተቃውሞ ገጥሟቸዋል።ረቡዕ ዕለት ረፋዱ ላይ ማኅበራዊ ሚዲያዎቹ መቋረጣቸውን ተጠቃሚዎች ተናግረዋል።ኤኤፍፒ የዜና ወኪል እንደዘገበው ከሆነ የተወሰኑ ተጠቃሚዎች ፌስቡክ እና ቲክቶክን መጠቀም አልቻሉም።ከ2.5 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ባላት ጋቦን ማኅበራዊ ሚዲያዎች በወጣቱ ዘንድ ለመዝናኛም ሆነ ለሥራ ከፍተኛ ተቀባይነት አላቸው።በዋና ከተማዋ ሊብራቪሌ የሚኖር ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀ አንድ የምግብ ቤት ባለቤት ንግዱን የሚያስተዋውቅባቸው ማኅበራዊ ሚዲያ ገጾች መታገዳቸው ሥራው ላይ እንቅፋት እንደሚፈጥርበት ተናግሯል።ያጋሩ, ጋቦን “ሐሰተኛ መረጃ እያተሰራጩ ነው” በሚል ማኅበራዊ ሚዲያን አገደች
  11. 18 የካቲት 2026ሶማሊላንድ የኤርዶዋንን የአዲስ አበባ ንግግር “ተቀባይነት የሌለው” ስትል ነቀፈችየሶማሊላንዱ ፕሬዝደንት አብዲራህማን ኢሮየፎቶው ባለመብት,Somaliland Presidential Officeሶማሊላንድ፤ የቱርክ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶዋን ትናንት በአዲስ አበባ ያደረጉት ንግግር “ተቀባይነት የሌለው፤ በሶማሊላንድ እና ቀጣናዊ አጋሮቿ መካከል ያለውን ግንኙት የሚያውክ” ስትል ነቀፈች።ኤርዶዋን ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ኢትዮጵያ ሳሉ እስራኤል ለሶማሊላንድ የሰጠችው የአገርነት ዕውቅና “ለሶማሊላንድም ሆነ ለአፍሪካ ቀንድ ምንም ጥቅም” አይኖረውም ብለዋል።ለዚህም ሶማሊላንድ በሰጠችው ምላሽ “በአፍሪካ ቀንድ ያሉ አገራት የውጭ ጉዳይ የፖሊሲ ውሳኔዎች የቀጣናው መንግሥታት እና የሕዝቡ መሆን አለባቸው” ብላለች።ከሶማሊላንድ የወጣው መግለጫ “የውጭ ተገዳዳሪ ኃይሎች በቀጣናው ገብተው መረጋጋት እና ትብብር መታወክ የለበትም” ይላል።በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ግብዣ አዲስ አበባ የገቡት ኤርዶዋን፤ ኢትዮጵያ በምትገኝበት የአፍሪካ ቀንድ ቀጣና ውስጥ በተለይም “ለአገራት ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ትኩረት እንደምትሰጥ” ተናግረዋል።”በዚህ ረገድ እስራኤል ለሶማሊላንድ ዕውቅና መስጠቷ ለሶማሊላንድም ሆነ ለአፍሪካ ቀንድ ምንም ጥቅም እንደማይኖረው በድጋሚ መግለጽ እወዳለሁ” ሲሉ እስራኤል ታኅሣሥ መጨረሻ የወሰደችውን እርምጃ ተችተዋል።ሶማሊላንድ ባወጣችው መግለጫ፤ ቱርክ “የቀጣናውን ውጥረት የሚያባብስ” አቋም ከማንጸባረቅ እንድትታቀብ አሳስባለች።ቱርክ “የጋራ ትብብርን” እንዲሁም “ሉዓላዊ ውሳኔ ሰጭነትን” እንድታከብርም ሶማሊላንድ ጠይቃለች።መግለጫው፤ “ሶማሊላንድ ከቀጣናው እና ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የአገርነት ዕውቅና ለማግኘት የምታደርገው ጥረት ሰላማዊ፣ ሕጋዊ እና ዴሞክራሲያዊ መሠረት ያለው ነው” ብሏል።ያጋሩ, ሶማሊላንድ የኤርዶዋንን የአዲስ አበባ ንግግር “ተቀባይነት የሌለው” ስትል ነቀፈች
  12. 18 የካቲት 2026“ኢራናውያን ገና ያልተቀበሏቸው፤ ትራምፕ ቀይ መስመር ያሏቸው ነጥቦች አሉ”- የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንትጄዲ ቫንስየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ ከኢራን ጋር የተደረገው ድርድር “አንዳንድ ጉዳዮችን በተመለከተ በጥሩ ሁኔታ መሄዱን” ተናገሩ።“በሌላ በኩል፤ ፕሬዝዳንቱ ቀይ መስመር ብለው ያስቀመጧቸው እና ኢራናውያን ገና ያልተቀበሏቸው ነጥቦችም አሉ” ሲሉ ከፎክስ ኒውስ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል።ጄዲ ቫንስ አክለውም “ሥራችንን እንቀጥላለን። ነገር ግን ዲፕሎማሲ ሊደርስበት የሚችለው ጥግ መሄዱን የሚወስኑት ትራምፕ ናቸው” ብለዋል።ፕሬዝዳንት ዶናልድት ትራምፕ፤ ኢራን የኒውክሌር የጦር መሣሪያ እንዳይኖራት ዲፕሎማሲ እና ሌሎች አማራጮችንም እየተጠቀሙ እንደሆነ ምክትል ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።“ሁሉም አማራጮች ጠረጴዛው ላይ ናቸው። ኢራን ሽብርን መደገፍ እንድታቆም እንፈልጋለን። የአሜሪካን ብሔራዊ ጥቅም የሚጎዳ እንቅስቃሴ ነው። ከዚህ የበለጠው ስጋት ግን የኒውክሌር የጦር መሣሪያ ነው” ሲሉም አክለዋል።ኢራን የኒውክሌር የጦር መሣሪያ እንደማትፈልግ ብትናገርም “ይሄ እውነት እንዳልሆነ እናውቃለን” ብለዋል ጄዲ ቫንስ።“የኒውክሌር የጦር መሣሪያ እንደሚፈልጉ የሚጠቁሙ ብዙ ድርጊዎች ፈጽመዋል። ግባችን ይሄ እንዳይሳካ ማድረግ ነው” ሲሉም የአገራቸውን አቋም አስታውቀዋል።ያጋሩ, “ኢራናውያን ገና ያልተቀበሏቸው፤ ትራምፕ ቀይ መስመር ያሏቸው ነጥቦች አሉ”- የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት
  13. 18 የካቲት 2026ኢራን፤ ኒውክሌርን በተመለከተ “በዋነኛ መርሆች” ላይ ከአሜሪካ ጋር መግባባት ላይ መደረሱን አስታወቀችየኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺኢራን፤ የኒውክሌር መርሃ ግብሯን በተመለከተ ከአሜሪካ ጋር “በዋነኛ መርሆች” ላይ እንደተግባቡ አስታወቀች።ሁለቱ አገራት በጄኔቫ ቀጥተኛ ያልሆነ ውይይት ካደረጉ በኋላ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ እንደተናገሩት፤ የኒውክሌር “ዋነኛ መርሆችን” በተመለከተ መግባባት ላይ ተደርሷል። አሜሪካም “በውይይቱ መሻሻል ታይቷል” ስትል ገልጻለች።የአሸማጋይዋ ኦማን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አልቡሳዲ “የጋራ ግቦችን በመለየት እና የቴክኒክ ጉዳዮችን በተመለከተ ድርድሩ ጥሩ መሻሻል ታይቶበታል” ብለዋል።የኢራን መንግሥት ተቃዋሚዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን ተከትሎ አሜሪካ ወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ ስትዝት ቆይታለች።አሜሪካ እና የአውሮፓ አጋሮቿ፤ ኢራን የኒውክሌር የጦር መሣሪያ ልትገነባ ነው ቢሉም ቴህራን በተደጋጋሚ አስተባብላለች።አሜሪካ እና ኢራን ከሚደራደሩባቸው ነጥቦች ዋነኛው የኒውክሌር ጉዳይ ነው።አንድ የአሜሪካ ባለሥልጣን “መሻሻል ቢኖርም ብዙ የምንወያይባቸው ዝርዝር ነጥቦች አሉ። የምንለያይባቸውን ነጥቦች በተመለከተ ኢራናውያን በቀጣይ ሁለት ሳምንታት ምክረ ሐሳም ይዘው እንደሚመጡ ገልጸዋል” ሲሉ ስለ ድርድሩ ለቢቢሲ ገልጸዋል።የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ በበኩላቸው “አንዳንድ ጉዳዮችን በተመለከተ ድርድሩ በጥሩ ሁኔታ ተካሂዷል። ፕሬዝዳንቱ ቀይ መስመር ብለው ያስቀመጧቸው እና ኢራናውያን ገና ያልተቀበሏቸው ነጥቦችም አሉ” ሲሉ ከፎክስ ኒውስ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል።ያጋሩ, ኢራን፤ ኒውክሌርን በተመለከተ “በዋነኛ መርሆች” ላይ ከአሜሪካ ጋር መግባባት ላይ መደረሱን አስታወቀች
  14. 17 የካቲት 2026አያቶላ ኻሜኒ “የዓለም ኃያሉ ሠራዊት መልሶ እንዳይነሳ ሆኖ ሊመታ ይችላል” ሲሉ አስጠነቀቁኻሜኒየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ “የዓለም ኃያሉ ሠራዊት መልሶ እንዳይነሳ ሆኖ ሊመታ እንደሚችል” በመግለጽ ለፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ምላሽ ሰጡ።ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከኢራን ጋር ከተፈጠረው ፍጥጫ ጋር በተያያዘ የአሜሪካን ጦር ሠራዊት ኃያልነት ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ በተደጋጋሚ ሲናገሩ ሰንብተዋል።በአገራቸው ዙሪያ የጦር መርከቦቿን እያስጠጋች ያለቸው አሜሪካ፤ ኢራን የሚቀርቡላትን ቅድመ ሁኔታዎች በመቀበል ከስምምነት ካልደረሰች እርምጃ እንደሚወሰድባት ፕሬዝዳንት ትራምፕ ሲዝቱ ቆይተዋል።ይህንን በተመለከተ ኻሜኒ በሰጡት ምላሽ “የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሠራዊታቸው በዓለም ላይ ጠንካራው እንደሆነ በተደጋጋሚ ይናገራሉ። ጠንካራ የተባለ ሠራዊት አንዳንድ ጊዜ እንዳይነሳ ተደርጎ ክፍኛ ሊመታ ይችላል” በማለት አስጠንቅቀዋል።ጠቅላይ መሪው ጨምረውም አሜሪካ የጦር መርከቦችን ወደ ኢራን መላኳን በተደጋጋሚ እየገለጸች መሆኗን በመጥቀስ “መርከቦች አደገኛ መሣሪያዎች ናቸው፤ ነገር ግን የበለጠ አደገኛው ነገር እነዚህን መርከቦች ከባሕር ሥር እንዲሰምጡ የሚያደርገው የጦር መሣሪያ ነው” በማለት የአሜሪካ መርከቦች የሚገጥማቸውን ምላሽ አመልክተዋል።አሜሪካ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በዓለም ላይ ካሉ ትልቅ አውሮፕላን ተሸካሚ የጦር መርከቦች መካከል አብርሃም ሊንከን የተባለውን በኢራን አቅራቢያ በሚገኘው ባሕር ላይ ያሰማራች ሲሆን፣ በቬንዙዌላ ላይ በተፈጸመው ጥቃት ውስጥ ተሳታፊ የነበረው ጄራርድ ፎርድ መርከብ ደግሞ ወደ ባሕረ ሰላጤው እንዲያመራ አዝዛለች።ከእነዚህ ግዙፍ የጦር አውሮፕላን ተሸካሚ መርኮቦች በተጨማሪ ሌሎች በርካታ የአሜሪካ የጦር መርከቦች ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ተሰማርተዋል።ያጋሩ, አያቶላ ኻሜኒ “የዓለም ኃያሉ ሠራዊት መልሶ እንዳይነሳ ሆኖ ሊመታ ይችላል” ሲሉ አስጠነቀቁ
  15. 17 የካቲት 2026የቱርክ ፕሬዝዳንት ለይፋዊ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡኤርዶዋን እና ዐቢይየፎቶው ባለመብት,Abiy Ahmed Ali/FBየቱርክ ፕሬዝዳንት ረሲብ ታይፕ ኤርዶዋን በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ግብዣ መሠረት ለይፋዊ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።ፕሬዝዳንት ኤርዶዋን ማክሰኞ የካቲት 10/2018 ዓ. ም. አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።ፕሬዝዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶዋን በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ የሁለትዮሽ፣ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት እንደሚያደርጉ ጽሕፈት ቤታቸው አስታውቋል።ከኢትዮጵያ ጋር ጥብቅ ግንኙነት ያላት የቱርኩ ፕሬዝዳንት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር ከሚያደርጉት ውይይት በተጨማሪ የተለያዩ የስምምነት ሰነዶች እንደሚፈረም ይጠበቃል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ፕሬዝዳንት ኤርዶዋንን ከተቀበሉ በኋላ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ በሰፈረው መልዕክት ላይ ጉብኝቱ “በቱርክ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ጥልቅ የአጋርነት ጥንካሬ የሚያንጸባርቅ ነው” በማለት የአገራቱን ትብብር ይበልጥ የሚያጠናክር ውጤታማ ውይይት እንዲደረግ ምኞታቸውን ገልጸዋል።ያጋሩ, የቱርክ ፕሬዝዳንት ለይፋዊ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ
  16. 17 የካቲት 2026ታዋቂው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ጀሲ ጃክሰን በ84 ዓመታቸው አረፉጀሲ ጃክሰንየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,ጀሲ ጃክሰን፤ ከማርቲን ሉተር ኪንግ ጁንየር ጋር በመሆን ለጥቁር አሜሪካውያን መብት በጽኑ ታግለዋልታዋቂው አሜሪካዊ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ጀሲ ጃክሰን በ84 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።ቤተሰቦቻቸው ባወጡት መግለጫ “አባታችን ታላቅ መሪ ነበር። ለቤተሰባችን ብቻ ሳይሆን በመላው ዓለም ለሚገኙ ጭቁኖች እና ድምጻቸው ለታፈነ ሰዎችን ጭምር ጠባቂ ነበር” ብለዋል።እንደ አውሮፓውያኑ በ1960ዎቹ ጀሲ ጃክሰን ከማርቲን ሉተር ኪንግ ጁንየር ጋር በመሆን ለጥቁር አሜሪካውያን መብት በጽኑ ታግለዋል።በአውሮፓውያኑ በ1984 እና በ1988 የዴሞክራቲክ ፓርቲ ፕሬዝዳንታዊ ዕጩም ነበሩ።ጀሲ ጃክሰን በ2017 ፓርኪንሰንስ የተባለ በሽታ እንደያዛቸው የተገለጸ ሲሆን፤ ያለፈው ኅዳር ላይ ሆስፒታል ገብተውም ነበር።በሰብአዊ መብት ንቅናቄ ውስጥ አብረዋቸው የሠሩት የመብት ተሟጋች ሬቨረንድ አል ሻርፕተን “አገሪቱን እና ዓለምን የለወጠ ሰው ነው። ፖሊሲ እና ሕግ አስቀይሯል። ሕልማችን እንዳይሞት ጠብቆ ለልጆቻችን አውርሷል” ሲሉ ገልጸዋቸዋል።ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁንየር እንደ አውሮፓውያኑ በ1968 ቴነሲ ውስጥ በተገደለበት ወቅት ከጀሲ ጃክሰን ጋር አብረው ነበሩ።በ1941 ሳውዝ ካሮላይና የተወለዱት ጀሲ ጃክሰን፤ ከወጣትነታቸው አንስቶ በፖለቲካው ንቁ ተሳታፊ ነበሩ።በ1971 ‘ኦፕሬሽን ፑሽ’ የተሰኘ የማኅበራዊ ፍትሕ እና የመብት ተሟጋች ተቋም መሥርተዋል።ያጋሩ, ታዋቂው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ጀሲ ጃክሰን በ84 ዓመታቸው አረፉ
  17. 17 የካቲት 2026ሁለተኛ ቀኑን በያዘው የኬንያ ሠራተኞች አድማ ምክንያት በረራዎች ከ20 ሰዓት በላይ ተቋረጡበመቶዎች የሚቆጠሩ መንገደኞች በረራቸው ተሰርዟልየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,በመቶዎች የሚቆጠሩ መንገደኞች በረራቸው ተሰርዟልበኬንያ መዲና ናይሮቢ የሚገኘው ዋነኛ የአገሪቱ አውሮፕላን ማረፊያ ከ20 ሰዓት በላይ በረራ በማቋረጡ ሳቢያ በመቶዎች የሚቆጠሩ መንገደኞች ጉዟቸው እንደተስጓጎለ ተገለጸ።በአፍሪካ በርካታ ተጓዦችን ከሚያስተናግዱ አየር ማረፊያዎች መካከል አንዱ በሆነው ጆሞ ኬንያታ አውሮፕላን ማረፊያ፤ ሠራተኞች ለሁለተኛ ቀን የቀጠለ አድማ በማድረጋቸው በረራዎች ተሰርዘዋል።ወደ ዩናይትድ ኪንግደም ለትምህርት ሊጓዝ የነበረው እና በረራው የተሰረዘበት ጃክ ኦኮት የተባለ ተጓዥ “ከ20 ሰዓት በላይ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ቆይቻለሁ። በሰው ተጨናንቋል” ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል።የኬንያ አብራሪዎች ማኅበር “የተፈጠረው መስተጓጎል ከአብራሪዎች የሥራ እና እረፍት ጊዜ ጋር የሚጣረስ ነው” ብሏል።የሥራ ማቆም አድማው ከበረራ ደኅንነት ጥበቃ ጋር እንዳይጣረስ እንደሚሰጋም ማኅበሩ አስታውቋል።የኬንያ አቪየሽን ሠራተኞች ማኅበር ከሳምንት በፊት የሥራ ማቆም አድማ እንደሚኖር ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ ነበር።የበረራ ሠራተኞችን ክፍያቸው እንዲሁም የሥራ ሁኔታቸው የማይሻሻል ከሆነ ሥራ የማቆም አድማ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል።የማኅበሩ ዋና ፀሐፊ ሞስ ንዲማ “ይሄ በቀላሉ የሚታይ አድማ ሳይሆን ሙሉ ኢንዱስትሪውን የሚመለከት ነው” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።ያጋሩ, ሁለተኛ ቀኑን በያዘው የኬንያ ሠራተኞች አድማ ምክንያት በረራዎች ከ20 ሰዓት በላይ ተቋረጡ
  18. 17 የካቲት 2026ዩክሬን የወታደሮቿን ዘር በማቀዝቀዣ እንዲቀመጥ ገንዘብ እንደምትደጉም ተገለፀጨቅላ ሕፃን ልጅ ሆስፒታል ውስጥበጦርነት ወታደሮቿን እያጣች ያለችው ዩክሬን የወታደሮቿን ዘር በማቀዝቀዣ ለማስቀመጥ ድጎማ እየሰጠች ነው።በ2022 የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ሲጀምር የግል የስነ ተዋልዶ ክሊኒኮች ሴት ወታደሮች እንቁላላቸውን ወንዶች ደግሞ የዘር ፈሳሻቸውን እንዲያስቀምጡ አማራጭ አቅርበዋል።በ2013 ይህንን ለመቆጣጠር የተነሳው የዩክሬን ምክር ቤት ለአገልግሎቱ በገንዘብ ለመደጎም ሕግ አውጥቷል።ሕጉን ካረቀቁት የምክር ቤት አባላት አንዷ የሆኑት ኦክሳና ዲሚትሪቭ “ወታደሮቻችን ወደፊታችንን እየተከላከሉ ነው፤ ነገር ግን የእነርሱን [ወደፊት] ሊያጡ ይችላሉ። ስለዚህ ዕድል መስጠት ነው የፈለግነው” ብለዋልየሁሉም ወታደሮች ናሙና ከሞቱ እስከ ሦስት ዓመት ድረስ በነፃ የሚቀመጥ ሲሆን፤ የትዳር አጋሮቻቸው እንዲጠቀሙት አስቀድሞ በጽሑፍ ፈቃድ ካላቸው ለመፀነስ መጠቀም ይችላሉ ተብሏል።እርምጃው ከጦርነቱ በፊት ዩክሬንን የገጠማትን የስነ ሕዝብ ቀውስ እና ከጦርነቱ በኋላ ወጣቶቿ ተገድለውባት የተባባሰውን ችግር ለመፍታት ያለመ እንደሆነ ተነግሯል።ያጋሩ, ዩክሬን የወታደሮቿን ዘር በማቀዝቀዣ እንዲቀመጥ ገንዘብ እንደምትደጉም ተገለፀ
  19. 17 የካቲት 2026የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በቀይ ባሕር እና በአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ከኬንያ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ተወያዩየግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላቲ (በስተግራ) እና የኬንያ ዋና የምክር ቤት ፀሐፊ ሙሳሊያ ሙሳቫዲየፎቶው ባለመብት,Ministry of Foreign Affairs Kenyaየግብፅ ከፍተኛ ልዑካን ቡድን ከኬንያ ባለሥልጣናት ጋር በቀይ ባሕር እና በአፍሪካ ቀንድ አሁናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያየ።በግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላቲ እና የውኃ ሐብት እና መስኖ ሚኒስትር ሃኒ ስዊላም የተመራ ከፍተኛ ልዑክ የካቲት 9/2018 ዓ.ም. ኬንያን ጎብኝቷል።የግብፅ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ከኬንያ ዋና የምክር ቤት ፀሐፊ ሙሳሊያ ሙሳቫዲ እና ሌሎችም ከፍተኛ ሹሞች ጋር በቀይ ባሕር እና የአፍሪካ ቀንድ አሁናዊ ሁኔታዎች ላይ መወያየተቻውን ካይሮ አስታውቃለች።የግብፅ ውኃ ሐብት እና መስኖ ሚኒስቴር ንግግሩን አስመልክቶ ባወጣው መረጃ የሁለቱ አገራት ባለሥልጣናት በቀጣናው በዋናነት ደግሞ በሶማሊያ እና ሱዳን ሰላም እና መረጋጋትን መመለስ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ሐሳብ መለዋወጣቸው ተጠቁሟል።ሁለቱ ወገኖች ግንኙነታቸውን የበለጠ ለማጠናከር የመከላከያ እና የተቀናጀ የውሃ ሐብት አስተዳደርን ጨምሮ በሌሎች ዘርፎች ላይ ለመተባበር ተስማምተዋል።የናይል ወንዝን ዘላቂነት ለመጠበቅ እና የጋራ ሐብትነቱን ለማስጠበቅ በጥምረት መስራት አስፈላጊ ስለመሆኑ ሁለቱም ወገኞች እውቅና እንደሰጡ ተመላክቷል።አገራቱ “ሁሉም የናይል ተፋሰስ አገራት የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት አድርጎ በውሃ ደኅንነት፣ በማኅበረ ኢኮኖሚ እድገት እና በስነ ምህዳር ጥበቃ በጋራ ለመስራት” ስለማሰባቸው ተጠቅሷል።ያጋሩ, የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በቀይ ባሕር እና በአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ከኬንያ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ተወያዩ
  20. 17 የካቲት 2026ናይጄሪያ በዩክሬን ዜጎቿ ሞተው መገኘታቸውን ተከትሎ ማስጠንቀቂያ አወጣችመሳሪያ ወደ ሰማይ ያነጣጠረ ግለሰብየፎቶው ባለመብት,Reutersናይጄሪያውያን በሌላ አገር ጦርነት ውስጥ በውትድርና ተቀጥረው እንዲሳተፉ በሚካሄድ ሕገወጥ ምልመላ እንዳይታለሉ የአገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስቸኳይ ማስጠንቀቂያ አወጣ።ሚኒስቴሩ ማስጠንቀቂያውን ያወጣው የዩክሬን ባለሥልጣናት ባለፈው ዓመት በጦርነት እንደተገደሉ የገለጿቸውን የሁለት ናይጄሪያውያን አስከሬን እንዳገኙ ከተናገሩ በኋላ ነው።ናይጄሪያ የግለሰቦቹን ሞት ባታረጋግጥም እሁድ ዕለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኪሚቢ ኢሞሞቲሚ ኤቢንፋ ባወጡት መግለጫ “በእንደዚህ አይነት አሳዛኝ ሁኔታዎች ሰለባ የሆኑ በርካታ ናይጄሪያውያን ተታልለው ወታደራዊ አገልግሎት ኮንትራቶችን እንዲፈርሙ ከተገደዱ በኋላ ወደ ውጊያ ቀጠናዎች ተሰማርተዋል” ብለዋል።ኬንያ ለዜጎቿ ተመሳሳይ ማስጠንቀቂያ አውጥታለች።እንደ ናይጄሪያ ባለሥልጣናት ገለጻ፣ የምርመራ እና የደህንነት ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት አንዳንድ ዜጎች ጥሩ ክፍያ የሚከፈልበት የሥራ ዕድል፣ የደህንነት ሥራ፣ የትምህርት ዕድሎች ወይም የፍልሰት ማበረታቻዎች እንደሚሰጡ ቃል ተገብቶላቸው ወደ ጦርነት ቀጠናዎች ተወስደዋል።በአንዳንድ አጋጣሚዎች፣ ተጎጂዎች ተገቢው የሕግ ምክር ሳይሰጣቸው በውጭ ቋንቋዎች የተጻፉ ውሎችን እንዲፈርሙ ይገደዱ ነበር፣ እና የጉዞ ሰነዶቻቸው ወደ ሚሄዱበት አገር እንደደረሱ ይወሰድባቸዋል ተብሏል።በመሃል ያሉ ደላሎችም የቱሪስት ወይም ሌሎች ወታደራዊ ያልሆኑ ቪዛዎችን በመጠቀም ጉዞ እንደሚያመቻቹ ይነገራል።ኤቢንፋ ናይጄሪያውያን እንደዚህ አይነት መደለያዎችን እንዳይቀበሉ አስጠንቅቀዋል። ይህም ሕይወትን አደጋ ላይ ከመጣል ባለፈ የናይጄሪያን እና ዓለም አቀፍ የቅጥረኛ እንቅስቃሴዎችን እና የውጭ ዜጎችን ስለመመልመል የሚደነግጉ ሕጎችን ሊጥሱ እንደሚችሉ አፅንዖት ሰጥቷል።የናይጄሪያ መንግሥት እነዚህን ጉዳዮች ለመመርመር እና የሕዝብ ግንዛቤን ለማሳደግ ከቀጠናው እና ከዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።በውጭ አገር የሚገኙት የዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮዎች የቆንስላ ድጋፍን ለማጠናከር እና ለዜጎች ማሰሳሰቢያ እንዲያስተላልፉ ተነግሯቸዋል።የዩክሬን የስለላ ድርጅት ከ36 የአፍሪካ አገራት የተውጣጡ ከ1,400 በላይ ግለሰቦች ለሩሲያ እንዲዋጉ መመልመላቸውን ይገምታል። ዩክሬን ራሷ አፍሪካውያንን ጨምሮ የውጭ ዜጎችን ለመመልመል በመሞከሯ ቀደም ሲል ትችት ገጥሟታል።የአፍሪካ መንግሥታት ዜጎቻቸውን በተደጋጋሚ እያስጠነቀቁ እና ወደ ግጭቱ ተታልለው የገቡ ዜጎቻቸውን ወደ አገራቸው ለመመለስ እየሰሩ ነው።ያጋሩ, ናይጄሪያ በዩክሬን ዜጎቿ ሞተው መገኘታቸውን ተከትሎ ማስጠንቀቂያ አወጣች