እናት ፓርቲ ወደ ቅንጅቱ (ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት- ለኢትዮጵያ) መመለሱን ስናበስር በታላቅ ደስታ ነው።
የቅንጅታችን ልባዊ ግንኙነት ኢትዮጵያውያንን ለሰላማዊ ትግል ለማስተባበርና ለመምራት አቅም ይሆናል የሚል ጽኑ ዕምነት አለን።
ሂደቱ ከእነአድካሚነቱ ከተጣለበት ተነስቶ ነፍስ እንዲዘራና ሕልው እንዲሆን ለጣሩ የፓርቲው የምክር ቤት አባላት እንዲሁም የቅንጅቱ አመራሮችና አንዳንድ ቅን ኢትዮጵያውያን ላሳዩን አጋርነት እናመሰግናለን።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አመራሮች የሂደቱ መደናቀፍ ያለውን ጉዳት ተረድተው ለሰጡት በሳል አመራርና ያላሰለሰ ጥረት እውቅና እንሰጣለን፤ ምሥጋናም ለማቅረብ እንወዳለን።




