
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትናንት የአገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ለኮንግረስ ንግግር በሚያደርጉበት ወቅት ተቃውሞ ያሰሙትን የምክር ቤት አባላት ኤልሃን ኦማር እና ራሺዳ ትላቢ “ወደ መጡበት መልሰን መላክ አለብን” አሉ።
ጭምቅ ሃሳብ
- የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በምርጫ ቦርድ ውሳኔ ላይ “ጊዜያዊ ዕገዳ” አሳለፈ
- ሰሜን ኮሪያ ከአሜሪካ ጋር ወዳጅ ልትሆን እንደምትችል መሪዋ ተናገሩ
- ሶማሊላንድ ከፍተኛ ዲፕሎማቷን በእስራኤል የመጀመሪያ አምባሳደሯ አድርጋ ሾመች
- የኩባ ባሕር ጠባቂዎች በአሜሪካ ፈጣን ጀልባ ላይ ተኩሰው አራት ኩባውያንን ገደሉ
የቀጥታ ሽፋን
- ከ 10 ደቂቃዎች በፊትሂላሪ ክሊንተን እና ባለቤታቸው የወሲብ ወንጀለኛው ኤፕስቲንን በተመለከተ ምስክርነት ሊሰጡ ነው
የፎቶው ባለመብት,Reutersየቀድሞዋ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን፤ የሟቹን የወሲብ ወንጀለኛ ጄፍሪ ኤፕስቲንን ወንጀሎች በሚመረምረው የተወካዮች ምክር ቤት ኮሚቴ ፊት ሊቀርቡ ነው።ከዚህ ቀደም ዴሞክራቲክ ፓርቲን ወክለው ለፕሬዝዳንትነት የተወዳደሩት ሂላሪ፤ ከባለቤታቸው የቀድሞው ፕሬዝዳንት ቢል ክሊንተን ጋር በመሆን በምክር ቤቱ የቁጥጥር ኮሚቴ ፊት ለመመስከር የተስማሙት በቅርቡ ነበር።ሁለቱ ጥንዶች ከዚህ ቀደም ምስክርነታቸውን እንዲሰጡ የቀረበላቸውን ጥሪ ፖለቲካዊ ዓላማ እንዳለው በመግለጽ ውድቅ አድገው ነበር።አሁን ለመመስከርመስማማታቸው በምክር ቤቱ ሊከፈትባቸው ይችል የነበረውን ኮንግረስን መዳፈርን የተመለከተ ሂደት ያስቀርላቸዋል።ሂላሪ ክሊንተን ከኤፕስቲን ጋር ስለ መገናኘታቸውም ሆነ ስለ ማውራታቸው እንደማያስታውሱ ተናግረዋል።ከኤፕስቲን ጋር የሚተዋወቁት ባለቤታቸው ቢል ክሊንተን ደግሞ ምንም ጥፋት እንዳልፈጸሙ እና ስለ ግለሰቡ ሌሎች ወንጀሎች እንደማያውቁ ገልጸዋል።ከሁለት አስርት ዓመታት በፊት ከኤፕስቲን ጋር የነበራቸውን ግንኙነት ማቋረጣቸውን የሚናገሩት ቢል ክሊንተን፤ ስማቸው ከግለሰቡ ጋር እንዲነሳ የሚያደርግ ነገር በመኖሩ እንደሚጸጸቱ ተናግረዋል።ሂላሪ ዛሬ ሐሙስ ምስክርነታቸውን የሚሰጡ ሲሆን፣ ቢል ክሊንተን ደሞ አርብ ዕለት ኮሚቴው ፊት እንደሚቀርቡ ይጠበቃል።የጥንዶቹ ምስክርነት የሚደመጠው በኒው ዮርክ ግዛት ቻፓኳ ውስጥ ከመኖሪያ ቤታቸው አቅራቢያ ነው። ብዙውን ጊዜ እንዲህ ዓይነቱ ምስክርነት የሚሰጠው በዝግ ነው።ይሁን እንጂ ክሊንተኖች ከሚቀርበው ማስረጃ ውስጥ የተወሰነው ክፍል ለመገናኛ ብዙኃን ሾልኮ ይወጣል የሚል ስጋት ስላደረባቸው፤ ምስክርነታቸው ለሕዝብ ይፋ እንዳይሆን መሟገታቸው ተዘግቧል።የሂላሪ ክሊንተን ምስክርነት ከተጠናቀቀ በኋላ የኮሚቴው አባል ሆኑ ዴሞክራቶች እና ሪፐብሊካኖች መግለጫ እንደሚሰጡ ይጠበቃል።ምስክርነታቸው በከፍኛ ሁኔታ እየተጠበቀ ያለው ቢል ክሊንተን ከአውሮፓውያኑ 1983 በኋላ በምክር ቤት ኮሚቴ ፊት ቀርበው የመሰከሩ የመጀመሪያው የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ይሆናሉ።ያጋሩ, ሂላሪ ክሊንተን እና ባለቤታቸው የወሲብ ወንጀለኛው ኤፕስቲንን በተመለከተ ምስክርነት ሊሰጡ ነው - ከ 3 ሰአት በፊትፕሬዝዳንት ትራምፕ ሙስሊሞቹን የኮንግረስ አባላት “ወደ መጡበት መልሰን መላክ አለብን” አሉ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ ለኮንግረስ ንግግር በሚያደርጉበት ወቅት ተቃውሞ ያሰሙትን የምክር ቤት አባላት ኢልሃን ኦማር እና ራሺዳ ትላቢን “ወደ መጡበት መልሰን መላክ አለብን” አሉ።ፕሬዝዳንቱ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ንግግር ያደረጉበት ‘ስቴት ኦፍ ዘ ዩኒየን’ የተባለው የምክር ቤት ንግግራቸው ሲካሄድ ዴሞክራቶች በተለያየ መልኩ ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ነበር።ትራምፕ ስለ ስደተኞች እና ሚኒሶታ ውስጥ በሚገኙ የሶማሊ አሜሪካ ማኅበረሰብ አባላት ይፈጸማል ስላሉት የማጭበርበር ተግባር በሚናገሩበት ወቅት የግዛቱ ተወካይ የሆኑት ኢልሃን ኦማር በተደጋጋሚ ፕሬዝዳንቱ ላይ ሲጮኹ ታይተዋል።የኮንግረስ አባሏ “ይሄ ውሸት ነው፣ ውሸታም ነዎት” ሲሉ እርሳቸውን በተመለከተ ሲናገሩ ለነበሩት ትራምፕ ምላሽ ሰጥተዋል።ከኢልሃን አጠገብ ተቀምጠው የነበሩት የሚቺጋን ግዛት ተወካይዋ ራሺዳም ኢልሃንን ተቀላቅለው ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።ፕሬዝዳንት ትራምፕ ትሩዝ በተሰኘው የማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ፤ ሁለቱን የምክር ቤት አባላትን “ዝቅተኛ የማገናዘብ ብቃት ያላቸው” ሲሉ ዘልፈዋል። በስብሰባው ላይ “ከቁጥጥር ውጪ ሆነው ሲጮሁ” ነበርም ብለዋል።ሁለቱ ፖለቲከኞች “ልክ እንደ እብዶች፣ አእምሮአቸው እንደተቃወሰ እና የታመሙ ሰዎች የፈጠጠ እና የደፈረሰ ዐይን ነበራቸው፤ በእውነቱ ከሆነ የሕክምና ተቋም ውስጥ መገባት ያለባቸው ነው የሚመስሉት” ብለዋል።አክለውም “በተቻለ ፍጥነት ወደ መጡበት መልሰን መላክ አለብን” በማለት ጽፈዋል። “አሜሪካን ለመጉዳት እንጂ ለመርዳት ማድረግ የሚችሉት ነገር የለም” ብለዋል።ትራምፕ ይህንን ቢሉም ሁለቱም የምክር ቤት አባላት ዜግነታቸው አሜሪካዊ ነው።
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesያጋሩ, ፕሬዝዳንት ትራምፕ ሙስሊሞቹን የኮንግረስ አባላት “ወደ መጡበት መልሰን መላክ አለብን” አሉ - ከ 5 ሰአት በፊትየፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በምርጫ ቦርድ ውሳኔ ላይ “ጊዜያዊ ዕገዳ“ አሳለፈ
የፎቶው ባለመብት,Reutersየፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአማራ እና ትግራይ ክልሎች መካከል አከራካሪ በሆኑ አምስት የምርጫ ክልሎች ላይ ምርጫ እንዲያካሄድ ያሳለፈው ውሳኔ ላይ ጊዜያዊ ዕግድ ጣለ።ምርጫ ቦርድ በሁለቱ ክልሎች መካከል አወዛጋቢ በሆኑ አምስት የምርጫ ክልሎች ከትግራይ እና ከአማራ ክልል ውጭ ሆነው በቀጥታ የተወካዮች ምክር ቤት ዕጩዎች ምርጫ እንዲካሄድባቸው ውሳኔ ያስተላለፈው ሰኞ የካቲት 16/2018 ዓ.ም. ነበር።ይህንንም ተከትሎ በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት) ፓርቲ ባቀረበው አቤቱታ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሐሙስ የካቲት 19/2018 ዓ.ም. በውሳኔው ላይ ዕግድ ጥሏል።በትግራይ የሚንቀሳቀሰው ስምረት ፓርቲ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔን ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ ሲያደርግ በይፋ ተቃውሞውን በመግለጫ ያሳወቀ ሲሆን፣ ጉዳዩንም በፕሬዝዳንቱ አቶ ጌታቸው ረዳ በኩል ለፍርድ ቤት አቅርቧል።የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ የሆኑት የቀድሞው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በማኅበራዊ ገጻቸው ላይ ባጋሩት በዚህ ውሳኔ ምርጫ ቦርድ መልሱን የካቲት 25/2018 ዓ.ም. እንዲያቀርብ ፍርድ ቤት አዝዟል።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአማራ እና ትግራይ ክልሎች መካካል አከራካሪ ሆነው የቆዩ የተባሉትን አምስት የምርጫ ክልሎች በተመለከተ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ደርሶኛል ያለውን ውሳኔ ይፋ ካደረገ በኋላ የሁለቱ ክልሎች ፖለቲከኞች ድጋፍ እና ተቃውሟቸውን ግልጸዋል።የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር፣ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)፣ ዲሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት) እና ሌሎችም በትግራይ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ውሳኔውን ሲቃወሙ፤ በአማራ ክልል በኩል ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተላለፈውን ውሳኔ ደግፈውታል።ያጋሩ, የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በምርጫ ቦርድ ውሳኔ ላይ “ጊዜያዊ ዕገዳ“ አሳለፈ - ከ 6 ሰአት በፊትሰሜን ኮሪያ ከአሜሪካ ጋር ወዳጅ ልትሆን እንደምትችል መሪዋ ተናገሩ
የፎቶው ባለመብት,AFP PHOTO/KCNA VIA KNSየምስሉ መግለጫ,የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡንየሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን የአገራቸውን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ አቅምን ለማስፋፋት ዕቅድ እንዳላቸው እና ይህንንም አሜሪካ እንድታከበር ጥሪ አቀረቡ።አሜሪካ እና ሰሜን ኮሪያ “ወዳጅ መሆን” እንደሚችሉ የተናገሩት ኪም ነገር ግን ይህ የሚሆነው አሜሪካ ሰሜን ኮሪያ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ባለቤት መሆኗን ስትቀበል ነው ብለዋል።ይህ በፓርቲያቸው ስብሰባ ላይ የተደረገው የመሪው ንግግር ፕሬዝዳንት ትራምፕ በመጪው ሚያዝያ ቻይናን በሚጎበኙበት ወቅት ድርድር ለማድረግ የሚያስችል ዕድል ለመክፈት የታሰበ ነው ተብሏል።ነገር ግን ኪም ደቡብ ኮሪያን “ዋነኛዋ ጠላት” በማለት ከጎረቤታቸው ጋር ሊኖር የሚችልን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ተስፋን አጨልመውታል።አሜሪካ “ያለንን የኒውክሌር ይዞታ የምታከበር ከሆነ እና የጠላትነት ፖሊሲዋን የምታነሳ ከሆነ…የማንስማማበት ምንም ዓይነት ምክንያት የለም” ሲሉ ኪም በኮሪያ ሠራተኞች ፓርቲ ጉባኤ ላይ መናገራቸውን የአገራቸው መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል።መሪው ጨምረውም የአሜሪካ እና የሰሜን ኮሪያ የወደፊት ግንኙነት “ሙሉ ለሙሉ በአሜሪካ አመለካከት ላይ የተመሠረተ ነው” በማለት “ሰላማዊም ሆነ ዘላቂ ፍጥጫ ለሁለቱም ዝግጁ ነን፤ ምርጫውም የእኛ ሳይሆን የእነሱ ነው” ብለዋል።ጎረቤት ደቡብ ኮሪያን በተመለከተም የአገራቸው ወዳጅ ካልሆኑት መካከል መሆኗን እና “ከእኛ ጋር ድንበር አስከተጋራች ድረስ፣ በሰላም ለመኖር ያላት ብቸኛ አማራጭ እኛን በሚመለከቱ ጉዳዮች ውስጥ መግባት የለባትም” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።ያጋሩ, ሰሜን ኮሪያ ከአሜሪካ ጋር ወዳጅ ልትሆን እንደምትችል መሪዋ ተናገሩ - ከ 9 ሰአት በፊትሶማሊላንድ ከፍተኛ ዲፕሎማቷን በእስራኤል የመጀመሪያ አምባሳደሯ አድርጋ ሾመች
የፎቶው ባለመብት,@AmbMohamedHagiየምስሉ መግለጫ,አምባሳደር ሞሐመድ ኦማር ሃጊ ሞሐሙድሶማሊላንድ ባለፈው ታኅሣሥ የመጀመሪያውን የአገርነት ዕውቅና በሰጠቻት እስራኤል ውስጥ አምባሳደር ሆነው የሚወክሏትን ከፍተኛ ዲፕሎማት ሾመች።የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ሞሐመድ ኦማር ሃጊ ሞሐሙድ በእስራኤል ውስጥ የአገሪቱ አምባሳደር እና ቋሚ መልዕክተኛ እንዲሆኑ መሾማቸውን ባወጣው የሹመት ደብዳቤ አሳውቋል።በአምባሳደርነት የተሾሙት ከፍተኛ ዲፕሎማቱ በፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት የዶክትሬት ዲግሪ ያላቸው ሲሆን፣ ቀደም ሲል በውጭ ጉዳይ ላይ የፕሬዝዳንቱ ዋነኛ አማካሪ እንዲሁም በታይዋን ውስጥ የሶማሊላንድ ተወካይ ነበሩ።የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሹመቱ በሶማሊላንድ እና በእስራኤል መካከል በተደረሰው ስምምነት እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ሳአር የሶማሊላንድ ጉብኝት መሠረት የተከናወነ መሆኑን በመግለጽ እንደተቀበለው አሳውቋል።ጨምሮም እስራኤል በቅርቡ በሶማሊላንድ አምባሳደሯን እንደምትሾም እና በሁለቱ ወገኖች መካከል በተለያዩ መስኮች የሚደረጉ ግንኙነቶችን እንደምታጠናክር አሳውቋል።ነጻ አገርነቷን አውጃ ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ ከሶማሊያ ተነጥላ ለቆየችው ሶማሊላንድ እስራኤል የአገርነት ዕውቅናን የሰጠችው ታኅሣሥ 17/2018 ዓ.ም. ነው።ይህን የእስራኤል ውሳኔ ሶማሊያ “በሉዓላዊነቷ ላይ የተፈጸመ ጥቃት ነው” በማለት ያወገዘች ሲሆን፤ አገራት፣ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተቋማትም ዕውቅናውን ተቃውመው ለሶማሊያ የግዛት አንድነት ድጋፋቸውን ገልጸዋል።ያጋሩ, ሶማሊላንድ ከፍተኛ ዲፕሎማቷን በእስራኤል የመጀመሪያ አምባሳደሯ አድርጋ ሾመች - 26 የካቲት 2026የኩባ ባሕር ጠባቂዎች በአሜሪካ ፈጣን ጀልባ ላይ ተኩሰው አራት ኩባውያንን ገደሉ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየኩባ የባሕር ጠረፍ ጠባቂዎች በከፈቱት ተኩስ በአሜሪካ በተመዘገበች ፈጣን ጀልባ ላይ ሲጓዙ የነበሩ አራት ኩባውያን ሲገደሉ ስድስቱ ደግሞ ቆሰሉ።የኩባ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በፈጣን ጀልባዋ ላይ ሲጓዙ የነበሩት ኩባውያን በተጠጓቸው የኩባ የባሕር ጠረፍ ጠባቂዎች ላይ ረቡዕ ዕለት ተኩስ ከከፈቱ በኋላ ነው ጉዳቱ የደረሰባቸው።የኩባ መንግሥት ባወጣው መግለጫ በጀልባዋ ላይ የነበሩት 10 ሰዎች ሲሆኑ ከመካከላቸውም የቀደመ የወንጀል ክስ ያለባቸው እና የታጠቁ እንደነበር እና “የሽብር ዓላማ ይዘው ሰርገው ለመግባት” ዓላማ ነበራቸው ብሏል።የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ አገራቸው “ፈጽሞ ያልተለመደ” ያሉትን ክስተት እየመረመረች መሆኑን ገልጸዋል።በፈጣን ጀልባዋ ላይ ሽጉጦች፣ ጠመንጃዎች፣ ፈንጂዎች እና ሌሎች ወታደራዊ ቁሶች መገኘታቸውን እና በተከፈተው ተኩስ አንድ የጠረፍ ጥበቃ አዛዥ ጉዳት እንደደረሰበት የኩባ መንግሥት አስታውቋል።የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ኩባ ባወጣችው መረጃ ላይ እንደማይተማመኑ በመግለጽ ክስተቱን በተመለከተ የራሳቸውን ምርመራ በማድረግ እንደሚያረጋግጡ አሳውቀዋል።ይህ ሁኔታ የተከሰተው ኩባ ወዳጇ ከሆነችው ቬንዙዌላ የሚቀርብላትን ነዳጅ አሜሪካ ማገዷን ተከትሎ በአገሪቱ ያለው የነዳጅ እጥረት በመባባሱ በሁለቱ አገራት መካከል ያለው ውጥረት ከፍ ባለበት ጊዜ ነው።አሜሪካ በቬንዙዌላ ላይ ጥቃት ፈጽማ የኩባ ወዳጅ የሆኑትን ፕሬዝዳንት ማዱሮን በቁጥጥር ሥር ካዋለች በኋላ ከቬንዙዌላ ወደ ኩባ የሚላከው ነዳጅ በከፍተኛ ደረጃ ቀንሷል።ያጋሩ, የኩባ ባሕር ጠባቂዎች በአሜሪካ ፈጣን ጀልባ ላይ ተኩሰው አራት ኩባውያንን ገደሉ - 25 የካቲት 2026ዚምባብዌ የአፍሪካ አገራት ከአሜሪካ ጋር የደረሱትን የጤና ስምምነት ውድቅ አደረገች
የፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,ስምምነቱ ግላዊ የጤና መረጃዎችን አሳልፎ ይሰጣል የሚል ስጋት ፈጥሯልአሜሪካ እንዲሰጣት በምትጠይቀው ጥበቃ የሚፈልጉ መረጃዎች ምክንያት ዚምባብዌ ከአሜሪካ 376 ሚሊዮን ዶላር የሚያስገኝላትን የጤና ስምምነት ውድቅ አደረገች።ይህ የዚምባብዌ ውሳኔ ይፋ የሆነው ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ ስምምነቱ ለአሜሪካ ያደላ ነው ያሉበት የመንግሥት ማስታወሻ ሾልኮ ከወጣ በኋላ ነው።የመንግሥት ቃል አቀባይ ኒክ ምናንግዋ በስምምነቱ አሜሪካ የጤና ናሙናዎችን ለምርምር እና ለንግድ አገለግሎት መጠየቋን እና ነገር ግን ወደ ፊት ለሚሰሩ ክትባቶች እና መድኃኒቶች ለማጋራት ፈቃደኛ አይደለችም ብለዋል።በዚህም ሳቢያ አሜሪካ ለዚምባብዌ የምትሰጠውን የጤና ድጋፍ ለማቋረጥ እንደምትገደድ በአገሪቱ የአሜሪካ አምባሳደር ፓሜላ ትሬሞንት ባወጡት መግለጫ አሳውቀዋል።ባለፉት ሁለት ዓመታት አሜሪካ ለዚምባብዌ ከ1.9 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚሆን የጤና ድጋፍ ስታደርግ መቆየቷን ኤምባሲዋ ገልጿል።ፕሬዝዳንት ትራምፕ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ በአሜሪካ የእርዳታ አቅርቦት ላይ ባደረጉት ለውጥ የተዋወቀው አዲሱ አሠራር አገራት ጠቃሚ የጤና መረጃዎችን ለአሜሪካ በማጋራት የተለያየ መጠን ያለው ድጋፍን እንዲያገኙ የሚያደርግ ነው።እስካሁን ኢትዮጵያን ጨምሮ 16 የአፍሪካ አገራት ከ18 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ የሚያስገኝላቸውን ስምምነት የፈረሙ ሲሆን፣ ነገር ግን በሚተላለፈው መረጃ እና አገራት በሚያገኙት ጥቅም ላይ ጥያቄ እየተነሳ ነው።ስምምነቱን ቀድማ የፈረመችው ኬንያ ውስጥ ያሉ የመብት ተሟጋች ቡድኖች የዜጎች ግላዊ የጤና መረጃ ለአሜሪካ ተላልፎ መሰጠቱን እንደ ስጋት በመጥቀስ ባቀረቡት ክስ ስምምነቱ በአገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ መታገዱ ይታወሳል።ያጋሩ, ዚምባብዌ የአፍሪካ አገራት ከአሜሪካ ጋር የደረሱትን የጤና ስምምነት ውድቅ አደረገች - 25 የካቲት 2026የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ለጉብኝት እስራኤል ገቡ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,ሕንድ እና የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትሮች ሞዲ እና ኔታኒያሁየሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የጋዛ ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሁለት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት እስራኤል ገቡ።ሞዲ በእስራኤል ፓርላማ፣ ክኔሴት ተገኝተው ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። እንዲሁም ከጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እና ከፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ ጋር ይወያያሉ ተብሏል።ነገር ግን ከፍልስጤም መሪዎች ጋር ለመናኘት ምንም ዓይነት ፕሮግራም እንዳልተያዘላቸው ተገልጿል።ጉብኝቱ የመጣው ሁለቱም አገራት በመከላከያ፣ በቴክኖሎጂ እና በንግድ ረገድ ያላቸውን ግንኙነት ለማጠናከር ጥረት እያደረጉ ባለበት ወቅት ነው።የሁለቱ አገራት ግንኙነት ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ ከአስር ዓመት በፊት ወደ ሥልጣን ከመጡ ወዲህ በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ ነው።ይሁን እንጂ ተንታኞች እንደሚሉት ጉብኝቱ ሕንድ ከእስራኤል እና ከሌሎች የመካከለኛው ምሥራቅ አገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ሚዛን በመጠበቅ ረገድ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲዋን አጣብቂኝ ውስጥ የሚከት ነው ተብሏል።በአውሮፓውያኑ 2017 ሞዲ እስራኤልን የጎበኙ የመጀመሪያው የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነዋል። ጉዞው በሁለቱ አገራት ወዳጅነት መካከል ትልቅ ለውጥ ማምጣቱ ይገለጻል።ሁለቱ አገራት በፀረ-ሽብር እና በመከላከያ ዘርፍ በቅርበት ይሠራሉ። ሕንድ ከእስራኤል የጦር መሳሪያ ገዢዎች መካከልም ዋነኛዋ ናት።የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የናሬንድራ ሞዲን ጉብኝት “ታሪካዊ” ሲሉ ጠርተውታል።“በእስራኤል እና በሕንድ መካከል ያለው ትስስር በሁለት ዓለም አቀፍ መሪዎች መካከል ያለ ጠንካራ ጥምረት ነው። በፈጠራ፣ በደኅንነት እና በጋራ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች አጋሮች ነን። አብረን ለመረጋጋት እና ለዕድገት ቁርጠኛ የሆኑ አገሮቻችንን በጥምረት እየገነባን ነው” ሲሉ በኤክስ ገጻቸው ላይ ጽፈዋል።ያጋሩ, የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ለጉብኝት እስራኤል ገቡ - 25 የካቲት 2026የመንግሥታቱ ድርጅት ጄነራል ዳጋሎን ጨምሮ በሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል መሪዎች ላይ ማዕቀብ ጣለ
የፎቶው ባለመብት,Anadolu via Getty Imagesየመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታ ምክር ቤት ሞሐመድ ሐምዳን ዳጋሎን ጨምሮ አራት የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ መሪዎች ላይ አዲስ ማዕቀብ ጣለ።የመንግሥታቱ ድርጅት ማዕቀቡን የጣለው ወታደራዊ መሪዎቹ በኤል ፋሽር በፈጸሙት ወንጀል ነው ተብሏል። የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ኤል ፋሸርን የተቆጣጠረው በጥቅምት ወር ሲሆን፣ በከተማዋ የተፈጸመው ለሦስት ዓመት ያህል በተካሄደው የሱዳን እርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ ከታየው ሁሉ አስከፊው ነበር ተብሏል።ባለፈው ሳምንት የተባበሩት መንግሥታት እውነት አፈላላጊ ቡድን በከተማዋ የተፈጸመው የዘር ማጥፋት እርምጃ ለመካሄዱ አስረጅ ነው ብሏል።በኤል ፋሽር የጅምላ ግድያን ጨምሮ ማንነት ተኮር ግድያ መካሄዳቸውን በመጥቀስ ሐምዳን ዳጋሎን ጨምሮ አራት የፈጥኖ ደራሽ አባላት ማዕቀብ ተጥሎባቸዋል።ከዳጋሎ በተጨማሪ ‘የኤል ፋሽር ነፍሰ በላ’ በሚል ቅጽል ስም የሚታወቀው አቡ ሉሉ ማዕቀብ ከተጣለባቸው መካከል ይገኛል።ጄነራል ዳጋሎ ማዕቀብ ሲጣልባቸው ይህ ለአራተኛ ጊዜ ነው። ከዚህ ቀድም አሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም እንዲሁም የአውሮፓ ኅብረት ማዕቀብ ጥለውባቸዋል።ከዚህ በተጨማሪ አሜሪካ እና ብሪታኒያ በሦስቱ አዛዦች ላይ ማዕቀብ ጥለዋል።ያጋሩ, የመንግሥታቱ ድርጅት ጄነራል ዳጋሎን ጨምሮ በሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል መሪዎች ላይ ማዕቀብ ጣለ - 25 የካቲት 2026ሴኔጋል በተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን ላይ የሚጣለውን የእስር ቅጣት በእጥፍ ልታሳድግ ነው
የፎቶው ባለመብት,Ousmane SONKOየሴኔጋል ጠቅላይ ሚኒስትር ኦስማኔ ሳንኮ በተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ውስጥ ባሉ ሰዎች ላይ የሚፈረደውን ከፍተኛውን የእስር ቅጣት በእጥፍ ሊጨምር የሚችል ረቂቅ ሕግ አቀረቡ። በአዲሱ ረቂቅ ሕግ መሠረት የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን እስከ 10 ዓመት በሚደርስ እስር ሊቀጡ ይችላሉ።የሴኔጋል ካቢኔ ባለፈው ሳምንት ያጸደቀው ይህ ረቂቅ ሕግ ማክሰኞ ዕለት ለአገሪቱ ፓርላማ ቀርቧል። ቀድሞውኑ በሕግ ክልከላ በጣለችው ሴኔጋል ይህ ረቂቅ የተዘጋጀው፤ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ውስጥ ተገኝተዋል የተባሉ ሰዎች ላይ ተከታታይ እስሮች ከተፈጸሙ በኋላ ነው።ጠቅላይ ሚኒስትር ሳንኮ በፓርላማ ለሕግ አውጪዎች ባደረጉት ንግግር፤ አዲሱ ሕግ “ከተፈጥሮ የተቃረነ ድርጊት” ሲሉ የጠሩትን ተግባር ከአምስት እስከ 10 ዓመት በሚደርስ እስር የሚቀጣ እንደሆነ ገልጸዋል። በነባሩ ሕግ ግን የሚያስቀጣው ከአንድ እስከ አምስት ዓመት በሚደርስ እስር ነበር።“ድርጊቱ በዕድሜ ካልደረሱ ልጆች ጋር የተፈጸመ ከሆነ ከፍተኛውን ቅጣት ያስወስናል” ሲሉ ተናግረዋል። የመብቶች ተሟጋቾች በበኩላቸው ረቂቅ ሕጉን ተችተዋል።የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ተሟጋች መሆን እንደ የውጭ ጣልቃ ገብነት በሚቆጠርባት ወግ አጥባቂዋ ሴኔጋል ውስጥ፤ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት መብትን በተመለከተ የሚደረግ ክርክር ውጥረት የሚፈጥር ጉዳይ ነው።በቅርብ ዓመታት የሃይማኖት ተቋማት ከፍተኛ ቅጣት እንዲጣል የሚጠይቁ ሰልፎችን አካሂደዋል።በዚህ ወር መጀመሪያ ደግሞ የአገሪቱ ፖሊስ በፀረ ተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ሕግ አማካኝነት ሁለት ታዋቂ ግለሰቦች እና አንድ ስመ ጥር ጋዜጠኛን በቁጥጥር ሥር አውሏል። በአጠቃላይ በዚህ ወር 30 ገደማ ሰዎች ከዚሁ ጋር በተያያዘ እንደታሰሩ የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።ያጋሩ, ሴኔጋል በተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን ላይ የሚጣለውን የእስር ቅጣት በእጥፍ ልታሳድግ ነው - 25 የካቲት 2026ትራምፕ ስለ ኢራን ኒውክሌር የተናገሩት “ትልቅ ውሸት ነው” ሲሉ የአገሪቱ ባለሥልጣን ተቹ
የፎቶው ባለመብት,Reutersየኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ፤ የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ስለ ኢራን ኒውክሌር እና ባለስቲክ ሚሳዔል የሰጠው አስተያየት “በተደጋጋሚ የተባለ ትልቅ ውሸት ነው” ሲሉ አጣጣሉ።ትራምፕ ለኮንግረስ አባላት ባደረጉት ንግግር ኢራን የኒውክሌር መሣሪያ እንዲኖራት “በፍጹም አልፈቅድም” ብለዋል።የትራምፕን ንግግር ተከትሎ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኢስማዔል ባቄይ “ውሸት ሲደጋገም እውነት ይሆናል” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።ኢራን ቢያንስ 20,000 ተቃዋሚዎችን ገድላለች ሲሉ ትራምፕ ተናግረዋል። በተጨማሪም “አውሮፓን የሚያሰጋ ሚሳዔል ገንብታለች። አሜሪካ የሚደርስ ሚሳዔልም እየገነባች ነው” ብለዋል።ኢራን “መሰሪ የሆነ የኒውክሌር ዕቅዷን” ለመተግበር እየሠራች ነው ሲሉም የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ከስሰዋል።የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ በሰጡት ምላሽ “ማንም ሰው በዚህ ነጭ ውሸት መታለል የለበትም” ብለዋል።ያጋሩ, ትራምፕ ስለ ኢራን ኒውክሌር የተናገሩት “ትልቅ ውሸት ነው” ሲሉ የአገሪቱ ባለሥልጣን ተቹ - 25 የካቲት 2026የእስራኤል ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር ለመነጋገር አዲስ አበባ ገቡ
የፎቶው ባለመብት,Ministry of Foreign Affairs of Ethiopiaየእስራኤል ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ መግባታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።ፕሬዝዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ እና በምክትላቸው አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ አቀባበል እንደተደረገላቸው ተገልጿል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ እንደሚያመለክተው፤ የእስራኤሉ ፕሬዝዳንት በኢትዮጵያ ቆይታቸው የሁለቱን አገራት ግንኙነት በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ዙሪያ ከመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።የእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሬዝዳንቱ ጉብኝት አስመልክቶ ባሰራጨው መረጃ፤ ሄርዞግ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር እንደሚገናኙ አስታውቋል። ከፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ጋርም እንደሚነጋገሩ ጠቅሷል።እንደ የእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ‘ቤተ እስራኤላውያን’ ተብለው የሚጠሩት የኢትዮጵያ የአይሑድ ማኅበረሰብ አባላት መሪም ከፕሬዝዳንት ሄርዞግ ጋር ይገናኛሉ።“ኢትዮጵያ አፍሪካ ውስጥ ወሳኝ አገር” እንደሆነች የገለጸው የእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ ጉብኝቱ “በእስራኤል እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ትብብር፤ በአጠቃላይም ከአፍሪካ አገራት ጋር ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ትልቅ ምዕራፍ የሚከፍት ነው” ብሏል።የእስራኤሉ ፕሬዝዳንት ወደ ኢትዮጵያ የመጡት የቱርክ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶዋን ወደ ኢትዮጵያ በመጡ በሳምንቱ ነው። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው የቱርኩ ፕሬዝዳንት በአዲስ አበባ በሰጡት መግለጫ እስራኤል ለሶማሊላንድ የሰጠችውን የአገርነት ዕውቅና መተቸታቸው ይታወሳል።ኤርዶዋን፤ እስራኤል ለሶማሊላንድ የሰጠችው የአገርነት ዕውቅና “ለሶማሊላንድም ሆነ ለአፍሪካ ቀንድ ምንም ጥቅም” አይኖረውም ሲሉ ተደምጠዋል። ይህ ንግግራቸው ሶማሊላንድን አስቆጥቷል።”የመላው ዓለም ዐይን ወደ የአፍሪካ ቀንድ” የዞረበት ጊዜ እንደሆነ የገለጹት ኤርዶዋን፤ ቱርክ በቀጣናው አዲስ ግጭት እንዲነሳ እንደማትፈልግ ተናግረው ነበር። “የዚህ ቀጣና ችግሮች በራሳቸው በቀጣናው አገራት ሊፈቱ እንደሚገባ እንዲሁም የአፍሪካ ቀንድ የውጭ ኃይሎች የጦር ሜዳ መሆን እንደሌለበት እናምናለን” ብለውም ነበር።ከትናንት በስቲያ ሰኞ ደግሞ የሳዑዲ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋሊድ አልኬሬጂ አዲስ አበባ መጥተው ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጋር ተነጋግረዋል።ስለ ቀጠናዊ ሰላም እና ሁለቱን አገራት በሚመለከቱ የፀጥታ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል የተባሉት ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ወደ ኢትዮጵያ ከመምጣታቸው አንድ ሳምንት አስቀድሞ ወደ ኤርትራ ተጉዘው ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ተነጋግረው ነበር።ከሁለት ሳምንት በፊት ደግሞ የሳዑዲ አረቢያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልዑል ፋይሰል ቢን ፋርሐን በአዲስ አበባ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በሁለትዮሽ እንዲሁም ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።ያጋሩ, የእስራኤል ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር ለመነጋገር አዲስ አበባ ገቡ - 25 የካቲት 2026ትራምፕ፤ ኢራን የኒውክሌር መሣሪያ እንዲኖራት “አልፈቅድም” አሉ
የፎቶው ባለመብት,EPAየአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ ኢራን የኒውክሌር መሣሪያ እንዲኖራት እንደማይፈቅዱ በመግለጽ አገሪቱ የኒውክሌር መርሃ ግብሯን ለመግታት እንድትስማማ አስጠነቀቁ።ትራምፕ ለኮንግረስ አባላት ባደረጉት ንግግር “የእኔ ምርጫ ችግሩን በዲፕሎማሲ መፍታት ነው። አንድ ጉዳይ ግን እርግጥ ነው። እሱም፤ የዓለም ቁጥር አንድ የሽብር ደጋፊ የኒውክሌር መሣሪያ እንዲኖራት አልፈቅድም” ብለዋል።ሁለት ሰዓት ገደማ በቆየው የ ‘ስቴት ኦፍ ዘ ዩኒየን’ ንግግራቸው ላይ እንደገለጹት፤ ኢራን በአሜሪካ ተጨማሪ ጥቃት እንዳይሰነዘርባት በሚል ስምምነት ላይ መድረስ ትፈልጋለች።ሆኖም ግን ኢራን የኒውክሌር መሣሪያ ግንባታን በተመለከተ ምንም ስምምነት እንዳላደረገች አክለዋል።አሜሪካ በመካከለኛው ምሥራቅ ግዙፍ የጦር መርከቦቿን ማሰማራቷን ተከትሎ ከኢራን ጋር ግጭት ይፈጠራል የሚል ስጋት አንዣቧል።ትራምፕ በዛሬው ንግግራቸው ኢራን ታጣቂዎችን እንደምትደግፍ እንዲሁም ተቃዋሚዎችን እንደገደለች ገልጸዋል።በተጨማሪም “የኢራን መንግሥት እና ገዳይ የሆኑት አጋሮቹ ሽብር፣ ሞት እና ጥላቻን ነዝተዋል” ማለታቸውን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው ኢራን ላይ ሊወሰድ ስለሚችል እርምጃ ቢገልጹም ዝርዝር መረጃዎችን አልሰጡም።ያጋሩ, ትራምፕ፤ ኢራን የኒውክሌር መሣሪያ እንዲኖራት “አልፈቅድም” አሉ - 25 የካቲት 2026ሄዝቦላህ በአሜሪካ እና ኢራን ጦርነት ውስጥ ከተሳተፈ እስራኤል ሊባኖስ ላይ ጥቃት እንደምትፈጸም ማስጠንቀቋ ተነገረ
የፎቶው ባለመብት,EPAሄዝቦላህ በማንኛውም መንገድ በአሜሪካ እና ኢራን ጦርነት ውስጥ የሚሳተፍ ከሆነ፤ እስራኤል አየር ማረፊያን ጨምሮ የሲቪል መሠረተ ልማቶችን ዒላማ ያደረገ ጥቃት በሊባኖስ ላይ እንደምትፈጽም ማስጠንቀቋን የዜና ወኪሉ ሮይተርስ ዘገበ።ሮይተርስ ያነጋገራቸው ሁለት የሊባኖስ ከፍተኛ ባለሥልጣናት፤ እስራኤል የማስጠንቀቂያ መልዕክቷን ያደረሰችው ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ እንደሆነ ገልጸዋል ተብሏል።የሊባኖስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዩሱፍ ራጂ በበኩላቸው በጄኔቫ ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ ሄዝቦላህ በአሜሪካ እና ኢራን ጦርነት ውስጥ የሚሳተፍ ከሆነ አገሪቱ ከእስራኤል ጋር አዲስ ግጭት ውስጥ ልትገባ ትችላለች የሚል ስጋታቸውን ገልጸዋል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኢራን የሚደገፈው ሄዝቦላህ በምንም ዓይነት የዋሽንግተን እና ቴህራን ውጊያ ውስጥ ተሳትፎ እንዳያደርግ ማሳሰባቸውን አሶሺየትድ ፕሬስ ዘግቧል።የሊባኖስ መንግሥት ይህን ጥሪ ያቀረበው አሜሪካ በኢራን ላይ ጥቃት ልትፈጽም ትችላለች የሚል ስጋት ባየለበት በዚህ ጊዜ ነው። ሁለተኛው የአሜሪካ የጦር አውሮፕላን ጫኝ መርከብ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ እየተቃረበ ሲሆን ኢራንም ከሩሲያ ጋር የምታደርገውን ዓመታዊ የጦርነት ልምምድ ጀምራለች።የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አገራቸው ከኢራን ጋር በምታደርገው የኒውክሌር ድርድር ስምምነት ላይ የማይደረስ ከሆነ፤ ለጦርነት ዝግጁ መሆናቸውን ጠቁመዋል።የሊባኖሱ ሄዝቦላህ በአውሮፓውያኑ 2024 የተካሄደውን ጨምሮ ከእስራኤል ጋር ለበርካታ ጊዜያት ተዋግቷል። አሁንም ቡድኑ በአሜሪካ እና ኢራን ጉዳይ ሊሳተፍ ይችላል የሚል ስጋት ያደረባቸው የሊባኖስ ባለሥልጣናት ሄዝቦላህ በአገሪቱ ዜጎች ላይ “መጥፎ ሁኔታን” ሊያመጣ በሚችል መልኩ ምላሽ እንዳይሰጥ ጥያቄ እንዳቀረቡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ራጂ ተናግረዋል ተብሏል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጄኔቫ ውስጥ በተካሄደው የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ “እስራኤላውያን የሲቪል መሠረተ ልማቶችን፤ ምናልባትም ቤሩት የሚገኘውን አየር ማረፊያ ልትመታ እንደምትችል የሚያሳዩ ምልክቶች ለሊባኖስ ደርሰዋል” ብለዋል።የሊባኖስ ጠቅላይ ሚኒስትር ናዋፍ ሳላም ማክሰኞ ዕለት በታተመ ጋዜጣ ላይ በወጣ ቃለ መጠይቃቸው ፤ ሄዝቦላህ ሊባኖስን ወደ “ሌላ ጀብዱ” እንዳያስገባት አሳስበዋል።አዲሱ የሄዝቦላህ መሪ ናኢም ቃሲም በአንጻሩ ባለፈው ወር በቴሌቪዥን በተላለፈ ንግግራቸው፤ ቡድኖ በዋሽንግተን እና ቴህራን ጉዳይ “ገለልተኛ እንዳልሆነ” ተናግረዋል። በዚህ ጦርነት “ሊፈጸም የሚችል ጥቃት ዒላማ እንደሆነም” መግለጻቸውን የሮይተርስ ዘገባ ያመለክታል።ያጋሩ, ሄዝቦላህ በአሜሪካ እና ኢራን ጦርነት ውስጥ ከተሳተፈ እስራኤል ሊባኖስ ላይ ጥቃት እንደምትፈጸም ማስጠንቀቋ ተነገረ - 24 የካቲት 2026የአዲስ ስታንዳርድ የሥራ ፈቃድ ተሰረዘ
የፎቶው ባለመብት,asየኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የአዲስ ስታንዳርድ የበይነ መረብ መገናኛ ብዙኃንን የምዝገባ ምስክር ወረቀት መሰረዙን አስታወቀ።አዲስ ስታንዳርድ በእንግሊዝኛ፣ በአማርኛ እና በኦሮምኛ በበይነ መረብ እንዲሁም በማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ ዜና፣ ትንታኔ እና አስተያየት የሚያቀርብ የመገናኛ ብዙኃን ነው።ባለሥልጣኑ አዲስ ስታንዳርድ “የሚዲያ ሥነ ምግባርን፣ የኢትዮጵያ ሕጎች እና የሀገርን እና የሕዝብን ብሔራዊ ጥቅም አደጋ ላይ የሚጥሉ ዘገባዎችን በማሠራጨት… ተደጋጋሚ ማሳሰቢያ እና ማስጠንቀቂያ ቢሰጠውም ለመታረም ፈቃደኛ አልሆነም” በማለት ለውሳኔው ምክንያት አቅርቧል።በዚህም ውሳኔ መሠረት የአዲስ ስታንዳርድ የበይነ መረብ መገናኛ ብዙኃን የምዝገባ ምስክር ወረቀት ከሰኞ የካቲት 17/ 2018 ዓ. ም. ጀምሮ መሰረዙን ገልጿል።የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በዚህ ዓመት በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን እና ጋዜጠኞች ላይ ተመሳሳይ እርምጃ መውሰዱ ይታወሳል።ባለሥልጣኑ የጀርመን ድምጽ ራድዮ የኢትዮጵያ ዘጋቢዎችን የሥራ ፈቃድ ለወራት ካገደ በኋላ በታኅሣሥ ወር ሁለቱን ዘጋቢዎች በዘላቂነት በማገድ ለሌሎቹ ፈቃድ ሰጥቷል።በጥር ወር አጋማሽ ላይ ደግሞ ዋዜማ ራድዮ የበይነ መረብ መገናኛ ብዙኃን “የኢትዮጵያን ሕገ መንግሥት እና የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ እንዲሁም መመሪያዎች እና የሙያ ሥነ ምግባር” ባለማክበር የተሰጠው ፈቃድ “ተመላሽ” መደረጉን ባለሥልጣኑ ገልጿል።በተጨማሪም ከሳምንት በፊት ዓለም አቀፉ የዜና ወኪል የሮይተርስ ዘጋቢዎች የሥራ ፍቃድ እንደማይታደስላቸው እንደተናገራቸው ድርጅቱ አሳውቋል።ያጋሩ, የአዲስ ስታንዳርድ የሥራ ፈቃድ ተሰረዘ - 24 የካቲት 2026አሜሪካ እግረኛ ጦር ሳታሰማራ በኢራን ላይ ለመጠነ ሰፊ ጥቃት እየተዘጋጀች ነው ተባለ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,ፕሬዝዳንት ትራምፕ እና ኤታማዦር ሹማቸው ጆን ኪንአሜሪካ እግረኛ ሠራዊት ሳታዘምት ለቀናት የሚዘልቅ ወታደራዊ ጥቃት በኢራን ላይ ለመፈጸም የሚያስፈልጓትን የባሕር ኃይል እና የአየር ኃይል መሣሪያዎቿን በኢራን አቅራቢያ ማስጠጋቷን የሳተላይት ምሥሎች እና የአውሮፕላን መከታተያ መረጃዎች አመለከቱ።ባለፈው ሳምንት ስዊዘርላንድ ውስጥ የተደረገው ድርድር ያለ ውጤት ማብቃቱን ተከትሎ አሜሪካ ከ150 በላይ ወታደራዊ አውሮፕላኖችን አውሮፓ እና መካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ ወደሚገኙ ጦር ሰፈሮቿ ማንቀሳቀሷን ዋሽንግተን ፖስት ዘግቧል።ባለፉት ሳምንታት አሜሪካ ያሏትን ሁለት ግዙፍ የጦር አውሮፕላን ተሸካሚ መርከቦች እና ሌሎች የጦር መርከቦችን ወደ ፋርስ ባሕረ ሰላጤው አንቀሳቅሳለች።አሜሪካ ከሃያ ዓመት በፊት በኢራቅ ላይ ወረራ ካካሄደች በኋላ በባሕረ ሰላጤው አካባቢ ከፍተኛ መጠን ያለው ኃይል ስታሰማራ ይህ የመጀመሪያው መሆኑ ተዘግቧል።ወታደራዊ ታዛቢዎች እንደሚሉት የአሜሪካ ጦር ሠራዊት በአካባቢው አሁን ያለበት መጠን ባለፈው ዓመት ሰኔ በኢራቅ ላይ ጥቃት በተፈጸመበት ጊዜ ከነበረው የበለጠ ነው።ይህም አሜሪካ እግረኛ ሠራዊት ሳታዘምት በኢራን ላይ ለበርካታ ቀናት የሚዘልቅ ወታደራዊ ዘመቻ ለማካሄድ እየተዘጋጀች መሆኑን ያመለክታል ሲሉ ተናግረዋል።ነገር ግን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ አሁንም ድረስ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሔ ማግኘት ምርጫዋ መሆኑን እና ነገር ግን ድርድሩ ከከሸፈ ሌላ እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀቷን ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።ጨምረውም ኢራን የኒውክሌር ጦር መሣሪያ እንዲኖራት አሜሪካ እንደማትፈቅድ በመጥቀስ፣ ሁሉም አማራጮች ጠረጴዛ ላይ መሆናቸውን አጽንኦት ሰጥተዋል።የእስራኤል የመገናኛ ብዙኃን አሜሪካ በመጪዎቹ ቀናት በኢራን ላይ ወታደራዊ እርምጃ መውሰዷ አይቀሬ መሆኑን እየዘገቡ ናቸው።አሜሪካ በኢራን ላይ ጥቃት የምትፈጽም ከሆነ እስራኤል በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ተሳታፊ መሆኗ የማይቀር ሲሆን፣ ከኢራን በኩል ጥቃት የሚከፈትባት ከሆነ ከባድ አጸፋ እንደምትመልስ እያስጠነቀቀች ነው።ያጋሩ, አሜሪካ እግረኛ ጦር ሳታሰማራ በኢራን ላይ ለመጠነ ሰፊ ጥቃት እየተዘጋጀች ነው ተባለ - 24 የካቲት 2026በኢራን ዩኒቨርስቲዎች ተቃውሞው በቀጠለበት ጊዜ መንግሥት እርምጃ እንደሚወስድ አስጠነቀቀ
የፎቶው ባለመብት,Moreየምስሉ መግለጫ,የኢራን ዐቃቤ ሕግ ኃላፊበኢራን ዩኒቨርስቲዎች የሚካሄደው ተቃውሞ አራተኛ ቀኑን በያዘበት በአሁኑ ወቅት መንግሥት በተቃዋሚ ተማሪዎች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሯል።የሻሪፍ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት የአገሪቱ “ዐቃቤ ሕግ በዩኒቨርስቲዎች የሚካሄደውን ተቃውሞ ለመቆጣጠር በጉዳዩ ውስጥ ገብቷል” ያሉ ሲሆን፣ የአሚርካቢር ዩኒቨርስቲ ባወጣው መግለጫ “ሕግ የሚጥሱ ተማሪዎች ጉዳይ በፍጥነት እየታየ ያለማወላወል እርምጃ ይወሰዳል” ሲል አስታውቋል።ከዚህ ጋር በተያያዘም በርካታ ተማሪዎችም ወደ ዩኒቨርስቲዎች እንዳይገቡ ዕግድ ተጥሎባቸዋል።የኢራን መንግሥት ቃል አቀባይ በዩኒቨርስቲዎች እየተካሄዱ ያሉትን ተቃውሞዎች በሚመለከት “ተማሪዎች ተቃውሞ የማሰማት መብት አላቸው፤ ነገር ግን “የተቀደሱ ቦታዎች እና ሰንደቅ ዓላማችን የማይታለፉ ሁለት ቀይ መመስሮች ናቸው” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።በዩኒቨርስቲዎች እየተካሄዱ ባሉት ተቃውሞዎች ውስጥ ተማሪዎች የቀድሞው የኢራን ንጉሣዊ መንግሥት ዓርማ ያለበትን ሰንደቅ ዓላማ በመያዝ በምሥሎች እና በቪዲዮዎች ላይ ታይተዋል።የኢራን ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በዩኒቨርስቲዎች የሚካሄደውን ተቃውሞ በተመለከተ “የሚመለከታቸው አካላት የማያዳግም ሕጋዊ እርምጃ እንዲወስዱ” አዝዟል።ዐቃቤ ሕጉ ሞሐመድ ሞቫሄዲ አዛድ “መንግሥት ድርድር በሚያደርግበት ጊዜ በጠላት የሚመሩ እንቅስቃሴዎች በአገር ውስጥ ያለ ችግርን ለማባባስ ጥረት ያደርጋሉ። እነዚህን ግለሰቦች መቆጣጠር ደግሞ የፀጥታ እና የሕግ ተቋማት ግልጽ ኃላፊነት ነው” ብለዋል።ጨምረውም “የሳይንስ ማዕከሎቻችን ሰላም እንዲናጋ አንፈቅድም” ብለው የሚመለከታቸው አካላት አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስዱ አሳስበዋል።ያጋሩ, በኢራን ዩኒቨርስቲዎች ተቃውሞው በቀጠለበት ጊዜ መንግሥት እርምጃ እንደሚወስድ አስጠነቀቀ - 24 የካቲት 2026በኢራን እና አሜሪካ ውጥረት ሳቢያ የነዳጅ ዋጋ በሰባት ወራት ባልታየ መጠን ጨመረ
የፎቶው ባለመብት,Reutersውጥረት ውስጥ ያሉት ኢራን እና አሜሪካ የሚያደርጉት ሦስተኛው ዙር ድርድር በተቃረበበት ወቅት የነዳጅ ዋጋ ባለፉት ሰባት ወራት ከነበረው በከፍተኛ መጠን መናሩ ተገለጸ።ሮይተርስ የዜና ወኪል እንደዘገበው፤ ድፍድፍ ነዳጅ በበርሜል የሚሸጥበት ዋጋ ባለበት (71.49 ዶላር) ቢሆንም የአሜሪካ ድፍድፍ ነዳጅ በበርሜል የሚሸጥበት ዋጋ የ0.2% ጭማሪ አሳይቶ 66.42 ዶላር ገብቷል።ድፍድፍ ነዳጅ ባለፈው ነሐሴ ከሚሸጥበት ዋጋው ዛሬ ጭማሪ ማሳየቱን ዘገባው ይጠቁማል።ኢራን የኒውክሌር መርሃ ግብሯን መዝጋት እንዳለባት አሜሪካ ብትገልጽም፤ ኢራን የኒውክሌር የጦር መሣሪያ የመሥራት ዕቅድ እንደሌላት እና ኒውክሌር ማብላላትም እንደማታቆም ገልጻለች።የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ከፍተኛ ኃላፊ እንደገለጹት፤ ጉልህ ኃላፊነት የሌላቸው ሠራተኞች እና ቤተሰቦቻቸው ሊባኖስ በቤይሩት ካለው የአሜሪካ ኤምባሲ ለቅቀው እንዲወጡ ታዘዋል።ኢራን ስምምነት ላይ ካልደረሰች “በጣም በጣም መጥፎ ይሆናል” ሲሉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስጠንቅቀዋል።ሮይተርስ የጠቀሳቸው የነዳጅ ንግድ ተንታኝ “ጦርነት ይነሳል ከሚለው ስጋት ይልቅ ውጥረቱ መባባሱ ለነዳጅ ዋጋ አለመረጋጋት ምክንያት ሆኗል” ብለዋል።ያጋሩ, በኢራን እና አሜሪካ ውጥረት ሳቢያ የነዳጅ ዋጋ በሰባት ወራት ባልታየ መጠን ጨመረ - 24 የካቲት 2026ኢራን ፀረ መርከብ ሱፐርሶኒክ ሚሳዔሎችን ከቻይና ለመግዛት ከጫፍ መድረሷ ተዘገበ
የፎቶው ባለመብት,NurPhotoኢራን ከቻይና ፀረ መርከብ ክሩዝ ሚሳዔሎችን መግዛት የሚያስችላትን ስምምነት ለመፈጸም ከጫፍ መድረሷን ሮይተርስ የዜና ወኪል ለድርድሩ ቅርብ የሆኑ ስድስት ምንጮችን ጠቅሶ ዘገበ።ኢራን ፀረ መርከብ ሚሳዔሎችን ልትገዛ እንደሆነ የተሰማው፤ ቴህራን ላይ ጥቃት ለመፈጸም እየተዘጋጀች ያለችው አሜሪካ የባሕር ኃይሏን በኢራን ባሕር ዳርቻ ባሰማራችበት በዚህ ጊዜ ነው።ቻይና ሠራሹን ‘ሲኤም-302’ ሚሳዔል ለመግዛት የሚደረገው ድርድር ፍጻሜው ላይ ቢሆንም ኢራን መሳሪያውን የምትረከብበትን ቀን በተመለከተ ስምምነት ላይ አለመደረሱን ምንጮች መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።ሲፐርሶኒክ ሚሳዔሎቹ 290 ኪሎ ሜትር ድረስ የመወንጨፍ አቅም ያላቸው ሲሆን በከፍታ እና በዝቅታ በመምዘግዘግ የመርከብ ላይ መከላከያዎችን ማለፍ እንዲችሉ ሆነው የተሠሩ ናቸው።እንደ ሮይተርስ ዘገባ፤ ኢራን ይህንን መሳሪያ መታጠቋ የማጥቃት አቋሟን በከፈተኛ መጠን እንደሚያሳድግ እንዲሁም የአሜሪካ ባሕር ላይ የምትጋርጠው ስጋት እንዲጨምር እንደሚያደርግ ሁለት የጦር መሳሪያ ባለሙያዎች ተናግረዋል።ቢያንስ ከሁለት ዓመት ገደማ በፊት የተጀመረው የኢራን እና ቻይና የሚሳዔል መሳሪያ ሥርዓት ግዢ፤ ባለፈው ሰኔ ላይ ከተካሄደው የእስራኤል እና ኢራን 12 ቀናት ጦርነት በኋላ በከፍተኛ ፍጥነት ተፋጥኗል ተብሏል።ንግግሩ ከዚህ በኋላ በነበሩ የክረምት ወራት የመጨረሻው ደረጃ ላይ ሲደርስ ከፍተኛ የኢራን የጦር መኮንኖች እና የመንግሥት ኃላፊዎች ወደ ቻይና እንደተጓዙ ሁለት የደኅንነት ምንጮች እንደነገሩት ሮይተርስ ገልጿል።አንድ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለሥልጣን “ኢራን ከአጋሮቿ ጋር ወታደራዊ እና የደኅንነት ስምምነቶች አሏት፤ አሁን ደግሞ እነዚህን ስምምነቶች ለመጠቀም ተገቢው ጊዜ ነው” ሲሉ ለዜና ወኪሉ ምላሽ ሰጥተዋል።የቻይና መንግሥት በጉዳዩ ላይ ምላሽ አልሰጠም ተብሏል። የአሜሪካ መንግሥትም ስለ ኢራን እና ቻይና የሚሳዔል ግዢ ድርድር ለቀረበለት ጥያቄ ቀጥተኛ ምላሽ ከመስጠት እንደተቆጠበ ተገልጿል።አንድ የዋይት ሐውስ ባለሥልጣን በአሜሪካ እና ኢራን መካከል የተካረረውን ፍጥጫ ጠቅሰው፤ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ “ወይ ስምምነት ላይ እንደርሳለን ወይም እንደ ባለፈው ጊዜ በጣም ጠንካራ የሆነ ነገር ማድረግ ይኖርብናል” የሚል አቋም እንዳላቸው አስታውሰዋል።ይህ የሚሳዔል ግዢ የሚፈጸም ከሆነ ከቻይና ወደ ኢራን የተላለፈ እጅግ ዘመናዊው ወታደራዊ መሳሪያ ይሆናል። ይሁን እንጂ በተባበሩት መንግሥታት ኢራን ላይ ተጣለነውን ማዕቀብ የሚጥስ እንደሆነም ሮይተርስ በዘገባው ጠቅሷል።ያጋሩ, ኢራን ፀረ መርከብ ሱፐርሶኒክ ሚሳዔሎችን ከቻይና ለመግዛት ከጫፍ መድረሷ ተዘገበ - 24 የካቲት 2026የግብፅ ፕሬዝዳንት አል ሲሲ እና የሳዑዲው ልዑል ሳልማን በዝግ ተወያዩ
የፎቶው ባለመብት,presidency.egየምስሉ መግለጫ,ፕሬዝዳንት አል ሲሲ እና ልዑል ቢን ሳልማንየግብፁ ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ ሰኞ ዕለት ወደ ሳዑዲ አረቢያ ተጉዘው ከሳዑዲው አልጋወራሽ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ልዑል ሞሐመድ ቢን ሳልማን ጋር መወያየታቸውን ጽህፈት ቤታቸው አስታወቀ።ሁለቱ ባለሥልጣናት በጋዛ፣ በቀጣናው ባለው ውጥረት እና በሌሎችም የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መነጋገራቸው የተገለጸ ሲሆን፣ በአልጋ ወራሹ የግል መኖሪያ ቤት በዝግ ውይይት ማድረጋቸው ተጠቅሷል።በአል ሲሲ ጉብኝት ሁለቱ አገራት የጋራ በሆኑ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሚያደርጉትን ምክክር እና ትብብር በማጠናከር የረጅም ጊዜ ግንኙነታቸውን ማስቀጠልን በተመለከተ መነጋገራቸው ተገልጿል።ሁለቱ መሪዎች በቀጣናው ውጥረት እና ግጭት እንዳይኖር ለማድረግ፣ ሰላማዊ መፍትሄዎችን ለማምጣት፣ የአረብ አገራትን ትብብር ለማጠናከር እና በውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ሳይገባ የአገራትን ሉዓላዊነት እንዲሁም የግዛት አንድነት ለማስከበር ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የፕሬዝዳንቱ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።ያጋሩ, የግብፅ ፕሬዝዳንት አል ሲሲ እና የሳዑዲው ልዑል ሳልማን በዝግ ተወያዩ
