ኢራን ካላት የኒውክሌር መረሃ ግብር በተጨማሪ ያሏት ተወንጫፊ ሚሳዔሎች እና የባሕር ኃይል ሠራዊቷ ከባድ የደኅንነት ስጋት ናቸው ስትል አሜሪካ ገለጸች። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የትራምፕ ከፍተኛ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ የሆኑት ማርኮ ሩቢዮ “ለረጅም ጊዜ የአሜሪካ ስጋት ሆና የቆየችው ኢራን አሁንም አሳሳቢ ሆና ቀጥላለች” ብለዋል።

ጭምቅ ሃሳብ

የቀጥታ ሽፋን

  1. ከ 8 ሰአት በፊትከአፍጋኒስታን ጋር “ግልጽ ጦርነት ውስጥ ገብተናል” – ፓኪስታንየፓኪስታን ታንክየፎቶው ባለመብት,AFP via Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,የፓኪስታን ታንክፓኪስታን በአፍጋኒስታን ዋና ከተማ ላይ ተከታታይ የአየር ድብደባዎችን ከፈጸመች በኋላ “ግልጽ ጦነርት” ውስጥ መግባቷን የመከላከያ ሚኒስትሯ አስታወቁ።ሚኒስትሩ ኻዋጃ ሙሐማድ አሲፍ በአፍጋኒስታን ላይ ጥቃቶች ከተፈጸሙ በኋላ “ትዕግስታችን ተሟጧል” ብለዋል።የአፍጋኒስታን ታሊባኖች ሐሙስ ምሽት በድንበር አቅራቢያ ባሉ በፓኪስታን ሠራዊት ይዞታዎች ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ተከትሎ ነው ምላሽ የሰጠችው።ፓኪስታን ዋና ከተማዋን ካቡልን ጨምሮ በአፍጋኒስታን የተለያዩ ከተሞች ውስጥ የሚገኙ ዒላማዎችን በጄቶች ደብድባላች።በተመሳሳይ የአፍጋን ታሊባኖች አርብ ጠዋት ፓኪስታን ውስጥ የሚገኙ በርካታ ዒላማዎችን መምታታቸውን ተናግረዋል። የመንግሥት ምንጮች ለቢቢሲ ጥቃቱ የተፈጸመው በድሮን መሆኑን ገልጸዋል።የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሼባዝ ሻሪፍ ሠራዊታቸው “የትኛውንም ጠብ ጫሪነት የመደምሰስ አቅም” እንዳለው እና አገራቸውን ለመከላከል የማይወስዱት እርምጃ እንደሌለ ተናግረዋል።የሁለቱ አገራት ኃይሎች በተለያዩ ጊዜያት ሲጋጩ የቆዩ ሲሆን፣ ባለፈው ጥቅምት ያልጸና የተኩስ አቁም ስምምነት ደርሰው ግጭታቻውን በዘላቂነት ለማስቆም የድንበር ስምምነት ላይ ለመድረስ ያደረጓቸው ድርድሮች ውጤት ሳያስገኙ ቀርተዋል።ፓኪስታን በቅርቡ በዋና ከተማዋ መስጂድ ውስጥ የተፈጸመውን የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃትን ጨምሮ አፍጋኒስታን “ፀረ ፓኪስታን ሽብርተኞችን” ትደግፋለች ስትል ትከሳለች።ያጋሩ, ከአፍጋኒስታን ጋር “ግልጽ ጦርነት ውስጥ ገብተናል” – ፓኪስታን
  2. ከ 9 ሰአት በፊትከኒውክሌር በተጨማሪ የኢራን የሚሳዔል ፕሮግራም ስጋት እንደሆነባት አሜሪካ ገለጸችየውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮኢራን ካላት የኒውክሌር መረሃ ግብር በተጨማሪ ያሏት ተወንጫፊ ሚሳዔሎች እና የባሕር ኃይል ሠራዊቷ ከባድ የደኅንነት ስጋት ናቸው ስትል አሜሪካ ገለጸች።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የትራምፕ ከፍተኛ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ የሆኑት ማርኮ ሩቢዮ “ለረዥም ጊዜ የአሜሪካ ስጋት ሆና የቆየችው ኢራን አሁንም አሳሳቢ ሆና ቀጥላለች” ብለዋል።ከአሜሪካ ጋር በምታካሂደው የኒውክሌር ግንባታ ዙሪያ ሦስት ድርድሮችን ያደረገችው ኢራን የኒውክሌር ፕሮግራሟ ለሰላማዊ አገለግሎት ብቻ የሚውል ነው ስትል በተደጋጋሚ ስታስተባብል ቆይታለች።ባለፈው ሰኔ በአሜሪካ እና በእስራኤል ጥቃት የተፈጸመባት ኢራን “የኒውክሌር ማዕከላቷ ከወደሙ በኋላ መልሳ እንዳትገነባ ተነግሯት ነበር። ነገር ግን አሁንም መልሰው ለመገንባት እየሞከሩ ማሆናቸው ይታያል” ያሉት ሩቢዮ፤ “አሁን ዩራኒየም እያዳበሩ ባይሆንም፣ እዚያ ደረጃ ላይ ለመድረስ እየሠሩ ነው” ሲሉ ገልጸዋል።ከኒውክሌር ፕሮግራሟ በተጨማሪ ኢራን ረዥም ርቀት መጓዝ የሚችሉ በርካታ ሚሳዔሎች እንዳሏት እና ይህም በአሜሪካ እና በአጋሮቿ ላይ ከባድ አደጋን የሚደቅን እንደሆነ አክለዋል።ይህ የኢራን የተወንጫፊ ሚሳዔሎች ፕሮግራም በተለይም አጭር ርቀት የሚጓዙት “በቀጣናው ያሉትን የአሜሪካ አጋሮች እና የጦር ሰፈሮችን ዒላማ የሚያደርጉ ናቸው” ብለዋል።አሜሪካ በኢራን ዙሪያ ያሉት የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ ኳታር እና ባህሬን ዋነኛ ወዳጆቿ ሲሆኑ ወታደራዊ ሰፈርም አላት። ሩቢዮ ጨምረውም የኢራን የባሕር ኃይል አቅም አሳሳቢ መሆኑን እና “የንግድ መርከቦችን እና የአሜሪካንን የባሕር ኃይል አባላትን ዒላማ ሊያደርጉ ይችላሉ” ብለዋል።ኢራን ከኒውክልር ፕሮግራሟ ውጪ በሚሳዔሎቿ ላይ ከአሜሪካም ጋር ሆነ ከሌላ ወገን ጋር የመነጋገር ፍላጎት እንደሌላት እና ይህንንም “ትልቅ ችግር” ሲሉ ገልጸውታል።”ሁሉም እንዲያውቀው የምፈልገው ኢራን ከኒውክልር ፕሮግራሟ ባሻገር በዋናነት አሜሪካንን ለማጥቃት የሚውሉ መደበኛ የጦር መሣሪያዎች አላት። ጥቃት ለመፈጸም የሚወስኑ ከሆነ ግን ጉዳዩ ምላሽ ሊሰጠው ይገባል” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።”በአገራቸውን እና በኢራን መካከል የሚደረገውን ድርድር በተመለከተም፤ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ እንዲገኝ እንደሚፈልጉ ነገር ግን ንግግሩ የማይሳካ ከሆነ ሌሎች አማራጮች ክፍት መሆናቸውን አመልክተዋል።ያጋሩ, ከኒውክሌር በተጨማሪ የኢራን የሚሳዔል ፕሮግራም ስጋት እንደሆነባት አሜሪካ ገለጸች
  3. 27 የካቲት 2026ኤፕስቲን ከመታሰሩ አንድ ቀን ቀደሞ ሞሮኮ ውስጥ ውድ ቤተመንግሥት ሊገዛ እንደነበር ተገለጸኤፕስቲን ሊገዛው የነበረው ቤተመንግሥት ውስጣዊ ገጽታየፎቶው ባለመብት,US Department of Justiceየምስሉ መግለጫ,ቅንጡው ፓልሜሬይ ማራኬሽ አካባቢ የሚገኘው ታላቁ ቤተ መንግሥት በ1,300 የእጅ ባለሞያዎች የተገነባ ነውባለፈው ወር የአሜሪካ የፍትሕ መሥሪያ ቤት ይፋ ባደረጋቸው ሰነዶች መሠረት ጄፍሪ ኤፕስቲን እአአ በ2019 ከመታሰሩ አንድ ቀን በፊት በሞሮኮ በብዙ ሚሊዮን ዶላር የሚቆጠር ቤተ መንግሥት ለመግዛት ጫፍ ላይ ደርሶ ነበር ተባለ።ኤፕስቲን እአአ ከ2011 ጀምሮ ቢን ኤናኪልን የተባለውን በሞሮኮ የሚገኝ ቤተ መንግሥት ለመግዛት ሲጥር የነበረ ቢሆንም፣ በዋጋው እና በግዢ ውል ዙሪያ ከሻጩ ጋር ባለመግባባቱ ለዓመታት ተጓትቷል።ቅንጡው ፓልሜሬይ ማራኬሽ አካባቢ የሚገኘው ታላቁ ቤተ መንግሥት በ1,300 የእጅ ባለሞያዎች የተገነባ እና በተጌጡ ቅርጻ ቅርጾችን እና ሞዛይኮችን የተዋበ ድንቅ የሕንጻ ሥራ እንደሆነ ተገልጿል።ኤፕስቲን ከመያዙ አንድ ቀን በፊት እአአ ሐምሌ 5/2019 14.95 ሚሊዮን ዶላር ክፍያ እንዲፈጸም ፈርሟል።ይህም ንብረቱን ከሚያስተዳድረው ኩባንያ ጋር በ18 ሚሊዮን ዩሮ ለመግዛት ስምምነት ላይ ከደረሰ በኋላ ነው።ይፋ በሆኑት ሰነዶች መሠረት ኢፕስቲን በአሜሪካ ባለሥልጣናት ከወሲብ ወንጀሎች ጋር በተገናኘ በቁጥጥር ሥር ከመዋሉ በፊት የፈጸመው የመጨረሻው የግዢ ውል ነው።በቁጥጥር ሥር ከመዋሉ ሦስት ቀናት አስቀድሞ የኢፕስቲን የሒሳብ ባለሙያ ሪቻርድ ኻሃን ገንዘቡ እንዳይከፈል በማድረጉ ግዢው ሳይፈጸም ቀርቷል።የአሜሪካ ፍትሕ መሥሪያ ቤት የወሲብ ንግድ ወንጀለኛው ጄፍሪ ኤፕስቲን የተለያዩ ሰነዶች ይፋ አድርጓል።ኤፕስቲን በ2019 ነሐሴ ላይ በወሲብ ንግድ ዝውውር ተከስሶ፣ የዋስትና ጥያቄው ውድቅ ተደርጎ፣ በኒው ዮርክ በሚገኝ እስር ቤት ብይን እየተጠባበቀ ሳለ ነበር የሞተው።ታዳጊዎችን ለወሲብ ንግድ በማቅረብ ‘የወሲብ ወንጀል’ በሚል ከተፈረጀ በኋላ ታዳጊዎችን ለወሲብ ንግድ የሚያቀርበው “መጠነ ሰፊ በሆነ የወንጀል መረብ ነው” በሚል ተከስሷል። ኤፕስቲን “ጥፋተኛ አይደለሁም” ሲል ተከራክሯል።ቤተ መንግሥቱ በተጌጡ ቅርጻ ቅርጾችን እና ሞዛይኮችን የተዋበ ድንቅ የሕንጻ ስራ እንደሆነ ተገልጿልየፎቶው ባለመብት,US Department of Justiceያጋሩ, ኤፕስቲን ከመታሰሩ አንድ ቀን ቀደሞ ሞሮኮ ውስጥ ውድ ቤተመንግሥት ሊገዛ እንደነበር ተገለጸ
  4. 27 የካቲት 2026ሕንድ እና እስራኤል በመከላከያ እና ቴክኖሎጂ ያላቸውን ትስስር ለማጠናከር ተስማሙጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ እና የእስራኤል አቻቸው ቤንያሚን ኔታንያሁየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በእስራኤል ለሁለት ቀናት ያደረጉትን ጉብኝት ሲያጠናቅቁ ሕንድ እና እስራኤል በመከላከያ እና በሰው ሠራሽ አስተውሎት ዘርፍ ያላቸውን ትብብር እንደሚያጠናክሩ ተናገሩ።ሞዲ እና የእስራኤል አቻቸው ቤንያሚን ኔታንያሁ ሐሙስ ዕለት በጋራ ባወጡት መግለጫ አገራቱ ነፃ የንግድ ስምምነትን ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚሠሩ ገልጸዋል።ሞዲ በኤክስ ገጻቸው ላይ “በጊዜው የተፈተነ አጋርነታችንን ወደ ልዩ ስትራቴጂካዊ ወዳጅነት ለማሳደግ ታሪካዊ ውሳኔ ወስነናል” ብለዋል።ሞዲ ከአውሮፓውያኑ 2017 ወዲህ በእስራኤል ለሁለተኛ ጊዜ ያደረጉት ጉዞ ከሌሎች የመካከለኛው ምሥራቅ አገራት ጋር ካላት ግንኙነት አንጻር የሕንድ የውጭ ፖሊሲ ፈተና ተድርጎ ተቆጥሯል።በጉብኝቱ ወቅት ሞዲ የእስራኤልን የአይሁዳውያን ፍጅት መታሰቢያ የሆነውን ያድ ቫሼምን የጎበኙ ሲሆን፣ በአገሪቱ ምክር ቤት ተገኝተውም ንግግር አድርገዋል።በዚህ ንግግራቸው ላይ መስከረም 26/2016 ዓ.ም. በሐማስ የተፈፀመውን ጥቃት አውግዘዋል።”ሕመማችሁ ይሰማናል። ሐዘናችሁን እንጋራለን። ሕንድ በዚህ ወቅት እና ከዚያም በኋላ . . . ከእስራኤል ጋር በፅኑ ትቆማለች” ብለዋል።ቀደም ሲል ሕንድ የሐማስን ጥቃት አውግዛ ለእስራኤል ያላትን አጋርነቷን በመግለጽ በጋዛ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት በተመለከተም ስጋቷን አስታውቃ ነበር።ሁለቱ አገራት በመረጃ መረብ ደኅንነት፣ በንግድ፣ በኅዋ ምርምር፣ በትምህርት፣ በኢንቨስትመንት፣ በግብርና እና በኢኮኖሚ ትብብር የሁለትዮሽ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል።በተጨማሪም እስራኤል በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ውስጥ ተጨማሪ 50,000 ሠራተኞችን ከሕንድ ወደ አገሯ ለማስገባት ቃል ገብታለች።ያጋሩ, ሕንድ እና እስራኤል በመከላከያ እና ቴክኖሎጂ ያላቸውን ትስስር ለማጠናከር ተስማሙ
  5. 27 የካቲት 2026በአከራካሪ ቦታዎች ምርጫ ለማካሄድ መወሰኑን የሚቃወም ሠልፍ በትግራይ ከተሞች ተካሄደበመቀለ የተካሄደው የተቃውሞ ሠልፍምርጫ ቦርድ በትግራይ እና በአማራ ክልሎች መካከል አወዛጋቢ በሆኑ አምስት የምርጫ ክልሎች ከሁለቱም ክልል ውጭ ሆነው በቀጥታ የተወካዮች ምክር ቤት ዕጩዎች ምርጫ እንዲካሄድባቸው ውሳኔ ማስተላለፉን የሚቃወም ሰልፍ ትበትግራይ የተለያዩ ከተሞች ተካሄደ።የሁመራ፣ የአዲ ረመጽ፣ የጠለምት፣ የኮረም ኦፍላ እና የራያ አላማጣ የምርጫ ክልሎች ምርጫ እንዲካሄድባቸው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ያስተላለፈውን ውሳኔ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኞ የካቲት 16/2018 ዓ.ም ነው።በትግራይ የክልል ከተሞች ዛሬ ከማለዳ ጀምሮ የተካሄደው የተቃውሞ ሠልፍን የተጠራው የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ፣ የህወሓት ሊቀመንበር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል እንዲሁም የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካዮች ንግግር አድርገዋል።በክልሉ ይህንን የተቃውሞ ሠልፍ ለማካሄድ በሚል የመንግሥት እና የግል ተቋማት እንዲሁም ትምሀርት ቤቶች ተዘግተዋል።የምርጫ ቦርድ አምስቱ አከራካሪ ቦታዎች ከሁለቱ ክልሎች ውጭ ሆነው ምርጫ እንዲካሄድባቸው ውሳኔ ያሳወቀው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔን ተከትሎ ነው።በአምስቱ የምርጫ ክልሎች የሚደረገው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ በቀጥታ እንዲሆን እና ለክልል ምክር ቤት ምርጫ አመቺ ጊዜ ተመርጦ ወደፊት እንዲካሄድ በመጀመሪያ የወሰነው የፌዴሬሽን ምክር ቤት መሆኑን ቦርዱ በወቅቱ አስታውቆ ነበር።የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔውን ያስተላለፈው በአማራ እና በትግራይ ክልል ያለው የይገባኛል ጥያቄ በሕገ መንግሥት ውሳኔ እስከሚፈታ ድረስ መሆኑም ተገልጿል።የፌዴሬሽን ምክር ቤት እና ምርጫ ቦርድ ባስተላለፏቸው ውሳኔዎች ላይ የማስተካከያ እርምጃ ካልተወሰደ በምርጫ እንደማይሳተፍ ያስጠነቀቀው ስምረት ፓርቲ፤ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት በመውሰድ “በጊዜያዊነት” እንዲታገድ አድርጓል።የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር፣ ህወሓት፣ ዲሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት) እና ሌሎችም በትግራይ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ውሳኔውን ሲቃወሙ፤ በአማራ ክልል በኩል ያሉ ፖለቲከኞች የምርጫ ቦርድ ውሳኔ ደግፈውታል።ያጋሩ, በአከራካሪ ቦታዎች ምርጫ ለማካሄድ መወሰኑን የሚቃወም ሠልፍ በትግራይ ከተሞች ተካሄደ
  6. 27 የካቲት 2026በፓኪስታን እና በአፍጋኒስታን መካከል ግጭት ሲጀመር፣ ካቡል ላይ የአየር ጥቃት ተፈጸመየፓኪስታን ወታደሮችየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesፓኪስታን የአፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች ላይ ጥቃት መፈጸሟን አስታወቀች።ፓኪስታን አርብ ዕለት ጥቃት መፈጸም የጀመረችው ታሊባን ሁለቱን አገራት በሚያዋስነው ድንበር አካባቢ በሚገኙ ወታደራዊ ካምፖች ላይ ጥቃት መፈጸሙን ካስታወቀ በኋላ ነው።በሁለቱ አገራት መካከል ያለው ውጥረት እየተጋጋለ የመጣ ሲሆን፣ የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሼባዝ ሻሪፍ አገራቸው “ማንኛውም ጠብ አጫሪነትን የመስበር ሙሉ አቅም አላት” ሲሉ ተናግረዋል።የመከላከያ ሚኒስትሩ በበኩላቸው በታሊባን ላይ “ግልጽ ጦርነት” አውጀዋል።የታሊባን ወታደራዊ ቃል አቀባይ “ጥቃት ከተፈጸመብን ምላሽ እንሰጣለን፤ ነገረ ግን ግጭት በአሁኑ ሰዓት አልጀመርንም” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።የታሊባን ቃል አቀባይ ዛቢኡላህ ሙጃሂድ በኤክስ ገጻቸው ላይ በፓኪስታን ወታደሮች ላይ እንደ አዲስ ጥቃት መከፈቱን ጽፈው የነበረ ቢሆንም በኋላ ላይ አጥፍተውታል።የመንግሥታቱ ድርጅት ባለሥልጣናት በሁለቱ አገራት መካከል የተቀሰቀሰው ግጭት እንዲረግብ ያሳሰቡ ሲሆን፣ ኢራን ለማደራደር ጠይቃለች።የሳዑዲ አረቢያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የፓኪስታን አቻቸውን የሁለቱ አገራት ውጥረት እንዲረግብ ማነጋገራቸው ተገልጿል።የታሊባን ባለሥልጣናት ፓኪስታን ለፈጸመችው ጥቃት ምላሽ መስጠታቸውን ገልጸው ከ50 በላይ ወታደሮችን መግደላቸውን እንዲሁም 19 የፓኪስታን የድንበር ኬላዎችን ማውደማቸውን እና በርካታ ወታደሮችን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ተናግረዋል።ፓኪስታን በበኩሏ ታሊባን የሚቆጣጠራቸው 27 የድንበር ኬላዎችን ማውደሟን ገልጻ፣ በታሊባን ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ደርሷል ብላለች።ያጋሩ, በፓኪስታን እና በአፍጋኒስታን መካከል ግጭት ሲጀመር፣ ካቡል ላይ የአየር ጥቃት ተፈጸመ
  7. 27 የካቲት 2026አሜሪካዊ ዲፕሎማት በቡርኪና ፋሶ ሁለት ታዳጊ ሴቶች ላይ ወሲባዊ ጥቃት በመፈፀም የዕድሜ ልክ እስራት ተፈረደበትየአሜሪካ ፍትህ ቢሮየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesቡርኪናፋሶ በሚገኝ የአሜሪካ ኤምባሲ ይሠራ የነበረ አሜሪካዊ ሁለት ታዳጊ ሴቶች ላይ ወሲባዊ ጥቃት በመፈጸም ወንጀል ተከስሶ የዕድሜ ልክ እስራት ተፈረደበት።ጉዳዩን ሲከታተሉ የነበሩ ዳኞች ግለሰቡን ታዳጊዎች ላይ ፆታዊ ጥቃት በመፈጸም፣ በማታለል እና በማስገደድ እንዲሁም የፍትሕ ሥርዓቱን ለማደናቀፍ ሙከራ በማድረግ ወንጀሎች ጥፋተኛ ብለውታል።የአሜሪካ ፍትሕ ቢሮ ግለሰቡ የ41 ዓመቱ ፎዴ ሲታፋ መሆኑን እና ከጥቅምት ጀምሮ ለሁለት ሳምንታት ጉዳዩ በፍርድ ቤት ሲታይ ቆይቶ የጥፋተኝነት ውሳኔ መሰጠቱን አስታውቋል።ዐቃቤ ሕጎች ወንጀሉ የተፈጸመው ከአውሮፓውያኑ 2022 እስከ 2023 በቡርኪናፋሶ ዋና ከተማ ዋጋዱጉ ግለሰቡ በአሜሪካ ኤምባሲ ተቀጣሪ በነበረበት ወቅት ነው ብለዋል።ለፍርድ ቤት የቀረበው ማስረጃ ወንጀሉ የተፈጸመው በአሜሪካ ዲፕሎማት መኖሪያ ቤት መሆኑን ያሳያል።ሁለቱ ጥቃት የደረሰባቸው ታዳጊዎች በወቅቱ የ13 እና የ15 ዓመት ልጆች ነበሩ።ግለሰቡ ለአንዲቷ ታዳጊ ግልጽ ወሲባዊ ይዘት ያላቸው መልዕክቶች በመላክ እንዲሁም የቤቱን ሠራተኛ ለመርማሪዎችን ሐሰተኛ ቃል እንድትሰጥ በማግባባት ጥፋተኛ ተብሏል።ያጋሩ, አሜሪካዊ ዲፕሎማት በቡርኪና ፋሶ ሁለት ታዳጊ ሴቶች ላይ ወሲባዊ ጥቃት በመፈፀም የዕድሜ ልክ እስራት ተፈረደበት
  8. 27 የካቲት 2026የአሜሪካ ወታደራዊ አውሮፕላኖች በእስራኤል አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ታዩየአሜሪካ ኤር ኃይል አውሮፕላኖችየፎቶው ባለመብት,EPAየውጊያ ጄቶችን አየር ላይ ነዳጅ መሙላት የሚችሉ በርካታ የአሜሪካ አየር ኃይል ቦይንግ ኬሲ-135 አውሮፕላኖች ቴል አቪቭ አቅራቢያ በሚገኘው ቤን ጎሪያን አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ታዩ።አውሮፕላኖቹ ከሁለት ቀናት በፊት በስፍራው መድረሳቸው ተገለጿል።እነዚህ ኬሲ-135 አውሮፕላኖች ረጅም ርቀት ተጉዘው ጥቃት የሚፈጽሙ ተዋጊ ጄቶችን በረራ ላይ ሳሉ ነዳጅ መሙላት የሚችሉ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፣ ይህም የአሜሪካ ጦር በቀጠናው ያለውን ዝግጅት የሚያጠናክር ነው ተብሏል።አውሮፕላኖቹ እስራኤል የደረሱት በቴህራን እና ዋሺንግተን መካከል የሚደረገው የኒውክሌር ፕሮግራም ድርድር እየተካሄደ ባለበት ወቅት ነው።ይህ በእንዲህ እንዳለ የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ በኢራን ላይ የሚፈጸም ጥቃት ቀጠናውን ወደ ተራዘመ ጦርነት አይመራውም ሲሉ ተናግረዋል።የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንቱ በኢራን ላይ የሚፈጸም ጥቃት ቀጠናውን ወደ ተራዘመ ጦርነት እንደማይመራ ገልጸው “በመካከለኛው ምሥራቅ ማብቂያው የማይታወቅ ጦርነት እንደምንጀምር የሚነገረው መሠረተ ቢስ ነው” ሲሉ አጣጥለዋል።ቫንስ “ዲፐሎማሲያዊ መንገድን ነው የምንመርጠው” ካሉ በኋላ “ያ ግን የሚመሠረተው ኢራን በምትወስደው እርምጃ ላይ ነው “ ብለዋል።በኢራን እና በአሜሪካ መካከል በስዊትዘርላንድ የተደረገው ሦስተኛው ዙር ድርድር ሐሙስ ዕለት ተጠናቅቋል።የአሜሪካ እና የኢራን ባለሥልጣናት በጄኔቫ ባካሄዱት ድርድር “ከፍተኛ ለውጦች” መታየታቸውን የኦማን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናገረዋል።ያጋሩ, የአሜሪካ ወታደራዊ አውሮፕላኖች በእስራኤል አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ታዩ
  9. 26 የካቲት 2026ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለይፋዊ ጉብኝት አዘርባጃን ገቡጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና የአዘርባጃን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርየፎቶው ባለመብት,@AZERTACየምስሉ መግለጫ,ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና የአዘርባጃን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለይፋዊ ጉብኝት አዘርባጃን ዋና ከተማ ባኩ መግባታቸውን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ።የአዘርባጀን መንግሥት የዜና ወኪል የሆነው ‘አዛርታክ’፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ዛሬ ሐሙስ የካቲት 19/2018 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ በአህጉረ እስያ እና አውሮፓ ወደ ምትገኘው አገር መድረሳቸውን ዘግቧል።የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጽህፈት ቤት ምሽት ላይ ጉብኝቱን በማስመልከት በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ባሰፈረው መልዕክት እና ምሥል አስታውቋል።በዚህም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና ከከፍተኛ የልዑካን ቡድናቸው ጋር ሐሙስ ረፋድ ላይ አዘርባጃን መግባታቸውን አመለክቷል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ባኩ ውስጥ በሚገኘው ሃይደር አሊየቭ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የአገሪቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሳሚር ሻሪፎቭ እና ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያልቺን ራፊየቭ እንዲሁም ሌሎች ባለሥልጣናት ተገኝተው አቀባበል እንዳደረጉላቸው ዘካስፒያን ፖስት እና ሪፖርት የተባሉት የአገሪቱ የዜና ድረገጾች ዘግበዋል።የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ይፋዊ ጉብኝት ለምን ያህል ቀናት እንደሚደረግ፣ ከየትኞቹ የአገሪቱ ባለሥልጣናት ጋር እንደሚገናኙ እና በምን ጉዳይ እንደሚነጋገሩ በይፋ አልተገለጸም።የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት በኢትዮጵያ እና በአዘርባጃን መካከል ያለው ግንኙነት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እየጠነከረ መምጣቱን እና ለዚህም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸው መሳያ መሆነት ጠቅሷል።በአሁኑ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና የልዑካቸው ጉብኝት የአገራቱን የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን ወደ ላቀ እና ትርጉም ወዳለው ደረጃ እንደሚያደርስ ይጠበቃል ብሏል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በካስፒያን ባሕር እና በካውካሰስ ተራሮች መካከል በአውሮፓን እና በእስያ አዋሳኝ ቦታ ላይ ወደምትገኘው የቀድሞዋ ሶቪየት ኅብረት አካል አዘርባጃን፤ ያደረጉት ጉዞን በተመለከተ በራሳቸውም ሆነ በጽህፈት ቤታቸው በኩል እስካሁን የተገለጸ ነገር የለም።ያጋሩ, ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለይፋዊ ጉብኝት አዘርባጃን ገቡ
  10. 26 የካቲት 2026ሂላሪ ክሊንተን እና ባለቤታቸው የወሲብ ወንጀለኛው ኤፕስቲንን በተመለከተ ምስክርነት ሊሰጡ ነውየቀድሞዋ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተንየፎቶው ባለመብት,Reutersየቀድሞዋ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን፤ የሟቹን የወሲብ ወንጀለኛ ጄፍሪ ኤፕስቲንን ወንጀሎች በሚመረምረው የተወካዮች ምክር ቤት ኮሚቴ ፊት ሊቀርቡ ነው።ከዚህ ቀደም ዴሞክራቲክ ፓርቲን ወክለው ለፕሬዝዳንትነት የተወዳደሩት ሂላሪ፤ ከባለቤታቸው የቀድሞው ፕሬዝዳንት ቢል ክሊንተን ጋር በመሆን በምክር ቤቱ የቁጥጥር ኮሚቴ ፊት ለመመስከር የተስማሙት በቅርቡ ነበር።ሁለቱ ጥንዶች ከዚህ ቀደም ምስክርነታቸውን እንዲሰጡ የቀረበላቸውን ጥሪ ፖለቲካዊ ዓላማ እንዳለው በመግለጽ ውድቅ አድገው ነበር።አሁን ለመመስከርመስማማታቸው በምክር ቤቱ ሊከፈትባቸው ይችል የነበረውን ኮንግረስን መዳፈርን የተመለከተ ሂደት ያስቀርላቸዋል።ሂላሪ ክሊንተን ከኤፕስቲን ጋር ስለ መገናኘታቸውም ሆነ ስለ ማውራታቸው እንደማያስታውሱ ተናግረዋል።ከኤፕስቲን ጋር የሚተዋወቁት ባለቤታቸው ቢል ክሊንተን ደግሞ ምንም ጥፋት እንዳልፈጸሙ እና ስለ ግለሰቡ ሌሎች ወንጀሎች እንደማያውቁ ገልጸዋል።ከሁለት አስርት ዓመታት በፊት ከኤፕስቲን ጋር የነበራቸውን ግንኙነት ማቋረጣቸውን የሚናገሩት ቢል ክሊንተን፤ ስማቸው ከግለሰቡ ጋር እንዲነሳ የሚያደርግ ነገር በመኖሩ እንደሚጸጸቱ ተናግረዋል።ሂላሪ ዛሬ ሐሙስ ምስክርነታቸውን የሚሰጡ ሲሆን፣ ቢል ክሊንተን ደሞ አርብ ዕለት ኮሚቴው ፊት እንደሚቀርቡ ይጠበቃል።
  1. የጥንዶቹ ምስክርነት የሚደመጠው በኒው ዮርክ ግዛት ቻፓኳ ውስጥ ከመኖሪያ ቤታቸው አቅራቢያ ነው። ብዙውን ጊዜ እንዲህ ዓይነቱ ምስክርነት የሚሰጠው በዝግ ነው።ይሁን እንጂ ክሊንተኖች ከሚቀርበው ማስረጃ ውስጥ የተወሰነው ክፍል ለመገናኛ ብዙኃን ሾልኮ ይወጣል የሚል ስጋት ስላደረባቸው፤ ምስክርነታቸው ለሕዝብ ይፋ እንዳይሆን መሟገታቸው ተዘግቧል።የሂላሪ ክሊንተን ምስክርነት ከተጠናቀቀ በኋላ የኮሚቴው አባል ሆኑ ዴሞክራቶች እና ሪፐብሊካኖች መግለጫ እንደሚሰጡ ይጠበቃል።ምስክርነታቸው በከፍኛ ሁኔታ እየተጠበቀ ያለው ቢል ክሊንተን ከአውሮፓውያኑ 1983 በኋላ በምክር ቤት ኮሚቴ ፊት ቀርበው የመሰከሩ የመጀመሪያው የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ይሆናሉ።ያጋሩ, ሂላሪ ክሊንተን እና ባለቤታቸው የወሲብ ወንጀለኛው ኤፕስቲንን በተመለከተ ምስክርነት ሊሰጡ ነው
  2. 26 የካቲት 2026ፕሬዝዳንት ትራምፕ ሙስሊሞቹን የኮንግረስ አባላት “ወደ መጡበት መልሰን መላክ አለብን” አሉኤልሃን ኦማር እና ራሺዳ ትላቢየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ ለኮንግረስ ንግግር በሚያደርጉበት ወቅት ተቃውሞ ያሰሙትን የምክር ቤት አባላት ኢልሃን ኦማር እና ራሺዳ ትላቢን “ወደ መጡበት መልሰን መላክ አለብን” አሉ።ፕሬዝዳንቱ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ንግግር ያደረጉበት ‘ስቴት ኦፍ ዘ ዩኒየን’ የተባለው የምክር ቤት ንግግራቸው ሲካሄድ ዴሞክራቶች በተለያየ መልኩ ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ነበር።ትራምፕ ስለ ስደተኞች እና ሚኒሶታ ውስጥ በሚገኙ የሶማሊ አሜሪካ ማኅበረሰብ አባላት ይፈጸማል ስላሉት የማጭበርበር ተግባር በሚናገሩበት ወቅት የግዛቱ ተወካይ የሆኑት ኢልሃን ኦማር በተደጋጋሚ ፕሬዝዳንቱ ላይ ሲጮኹ ታይተዋል።የኮንግረስ አባሏ “ይሄ ውሸት ነው፣ ውሸታም ነዎት” ሲሉ እርሳቸውን በተመለከተ ሲናገሩ ለነበሩት ትራምፕ ምላሽ ሰጥተዋል።ከኢልሃን አጠገብ ተቀምጠው የነበሩት የሚቺጋን ግዛት ተወካይዋ ራሺዳም ኢልሃንን ተቀላቅለው ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።ፕሬዝዳንት ትራምፕ ትሩዝ በተሰኘው የማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ፤ ሁለቱን የምክር ቤት አባላትን “ዝቅተኛ የማገናዘብ ብቃት ያላቸው” ሲሉ ዘልፈዋል። በስብሰባው ላይ “ከቁጥጥር ውጪ ሆነው ሲጮሁ” ነበርም ብለዋል።ሁለቱ ፖለቲከኞች “ልክ እንደ እብዶች፣ አእምሮአቸው እንደተቃወሰ እና የታመሙ ሰዎች የፈጠጠ እና የደፈረሰ ዐይን ነበራቸው፤ በእውነቱ ከሆነ የሕክምና ተቋም ውስጥ መገባት ያለባቸው ነው የሚመስሉት” ብለዋል።አክለውም “በተቻለ ፍጥነት ወደ መጡበት መልሰን መላክ አለብን” በማለት ጽፈዋል። “አሜሪካን ለመጉዳት እንጂ ለመርዳት ማድረግ የሚችሉት ነገር የለም” ብለዋል።ትራምፕ ይህንን ቢሉም ሁለቱም የምክር ቤት አባላት ዜግነታቸው አሜሪካዊ ነው።ኤልሃን ኦማርየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesያጋሩ, ፕሬዝዳንት ትራምፕ ሙስሊሞቹን የኮንግረስ አባላት “ወደ መጡበት መልሰን መላክ አለብን” አሉ
  3. 26 የካቲት 2026የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በምርጫ ቦርድ ውሳኔ ላይ “ጊዜያዊ ዕገዳ“ አሳለፈየፍርድ ቤት መዶሻየፎቶው ባለመብት,Reutersየፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአማራ እና ትግራይ ክልሎች መካከል አከራካሪ በሆኑ አምስት የምርጫ ክልሎች ላይ ምርጫ እንዲያካሄድ ያሳለፈው ውሳኔ ላይ ጊዜያዊ ዕግድ ጣለ።ምርጫ ቦርድ በሁለቱ ክልሎች መካከል አወዛጋቢ በሆኑ አምስት የምርጫ ክልሎች ከትግራይ እና ከአማራ ክልል ውጭ ሆነው በቀጥታ የተወካዮች ምክር ቤት ዕጩዎች ምርጫ እንዲካሄድባቸው ውሳኔ ያስተላለፈው ሰኞ የካቲት 16/2018 ዓ.ም. ነበር።ይህንንም ተከትሎ በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት) ፓርቲ ባቀረበው አቤቱታ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሐሙስ የካቲት 19/2018 ዓ.ም. በውሳኔው ላይ ዕግድ ጥሏል።በትግራይ የሚንቀሳቀሰው ስምረት ፓርቲ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔን ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ ሲያደርግ በይፋ ተቃውሞውን በመግለጫ ያሳወቀ ሲሆን፣ ጉዳዩንም በፕሬዝዳንቱ አቶ ጌታቸው ረዳ በኩል ለፍርድ ቤት አቅርቧል።የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ የሆኑት የቀድሞው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በማኅበራዊ ገጻቸው ላይ ባጋሩት በዚህ ውሳኔ ምርጫ ቦርድ መልሱን የካቲት 25/2018 ዓ.ም. እንዲያቀርብ ፍርድ ቤት አዝዟል።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአማራ እና ትግራይ ክልሎች መካካል አከራካሪ ሆነው የቆዩ የተባሉትን አምስት የምርጫ ክልሎች በተመለከተ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ደርሶኛል ያለውን ውሳኔ ይፋ ካደረገ በኋላ የሁለቱ ክልሎች ፖለቲከኞች ድጋፍ እና ተቃውሟቸውን ግልጸዋል።የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር፣ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)፣ ዲሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት) እና ሌሎችም በትግራይ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ውሳኔውን ሲቃወሙ፤ በአማራ ክልል በኩል ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተላለፈውን ውሳኔ ደግፈውታል።ያጋሩ, የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በምርጫ ቦርድ ውሳኔ ላይ “ጊዜያዊ ዕገዳ“ አሳለፈ
  4. 26 የካቲት 2026ሰሜን ኮሪያ ከአሜሪካ ጋር ወዳጅ ልትሆን እንደምትችል መሪዋ ተናገሩየሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡንየፎቶው ባለመብት,AFP PHOTO/KCNA VIA KNSየምስሉ መግለጫ,የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡንየሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን የአገራቸውን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ አቅምን ለማስፋፋት ዕቅድ እንዳላቸው እና ይህንንም አሜሪካ እንድታከበር ጥሪ አቀረቡ።አሜሪካ እና ሰሜን ኮሪያ “ወዳጅ መሆን” እንደሚችሉ የተናገሩት ኪም ነገር ግን ይህ የሚሆነው አሜሪካ ሰሜን ኮሪያ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ባለቤት መሆኗን ስትቀበል ነው ብለዋል።ይህ በፓርቲያቸው ስብሰባ ላይ የተደረገው የመሪው ንግግር ፕሬዝዳንት ትራምፕ በመጪው ሚያዝያ ቻይናን በሚጎበኙበት ወቅት ድርድር ለማድረግ የሚያስችል ዕድል ለመክፈት የታሰበ ነው ተብሏል።ነገር ግን ኪም ደቡብ ኮሪያን “ዋነኛዋ ጠላት” በማለት ከጎረቤታቸው ጋር ሊኖር የሚችልን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ተስፋን አጨልመውታል።አሜሪካ “ያለንን የኒውክሌር ይዞታ የምታከበር ከሆነ እና የጠላትነት ፖሊሲዋን የምታነሳ ከሆነ…የማንስማማበት ምንም ዓይነት ምክንያት የለም” ሲሉ ኪም በኮሪያ ሠራተኞች ፓርቲ ጉባኤ ላይ መናገራቸውን የአገራቸው መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል።መሪው ጨምረውም የአሜሪካ እና የሰሜን ኮሪያ የወደፊት ግንኙነት “ሙሉ ለሙሉ በአሜሪካ አመለካከት ላይ የተመሠረተ ነው” በማለት “ሰላማዊም ሆነ ዘላቂ ፍጥጫ ለሁለቱም ዝግጁ ነን፤ ምርጫውም የእኛ ሳይሆን የእነሱ ነው” ብለዋል።ጎረቤት ደቡብ ኮሪያን በተመለከተም የአገራቸው ወዳጅ ካልሆኑት መካከል መሆኗን እና “ከእኛ ጋር ድንበር አስከተጋራች ድረስ፣ በሰላም ለመኖር ያላት ብቸኛ አማራጭ እኛን በሚመለከቱ ጉዳዮች ውስጥ መግባት የለባትም” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።ያጋሩ, ሰሜን ኮሪያ ከአሜሪካ ጋር ወዳጅ ልትሆን እንደምትችል መሪዋ ተናገሩ
  5. 26 የካቲት 2026ሶማሊላንድ ከፍተኛ ዲፕሎማቷን በእስራኤል የመጀመሪያ አምባሳደሯ አድርጋ ሾመችሞሐመድ ኦማር ሃጊ ሞሐሙድየፎቶው ባለመብት,@AmbMohamedHagiየምስሉ መግለጫ,አምባሳደር ሞሐመድ ኦማር ሃጊ ሞሐሙድሶማሊላንድ ባለፈው ታኅሣሥ የመጀመሪያውን የአገርነት ዕውቅና በሰጠቻት እስራኤል ውስጥ አምባሳደር ሆነው የሚወክሏትን ከፍተኛ ዲፕሎማት ሾመች።የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ሞሐመድ ኦማር ሃጊ ሞሐሙድ በእስራኤል ውስጥ የአገሪቱ አምባሳደር እና ቋሚ መልዕክተኛ እንዲሆኑ መሾማቸውን ባወጣው የሹመት ደብዳቤ አሳውቋል።በአምባሳደርነት የተሾሙት ከፍተኛ ዲፕሎማቱ በፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት የዶክትሬት ዲግሪ ያላቸው ሲሆን፣ ቀደም ሲል በውጭ ጉዳይ ላይ የፕሬዝዳንቱ ዋነኛ አማካሪ እንዲሁም በታይዋን ውስጥ የሶማሊላንድ ተወካይ ነበሩ።የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሹመቱ በሶማሊላንድ እና በእስራኤል መካከል በተደረሰው ስምምነት እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ሳአር የሶማሊላንድ ጉብኝት መሠረት የተከናወነ መሆኑን በመግለጽ እንደተቀበለው አሳውቋል።ጨምሮም እስራኤል በቅርቡ በሶማሊላንድ አምባሳደሯን እንደምትሾም እና በሁለቱ ወገኖች መካከል በተለያዩ መስኮች የሚደረጉ ግንኙነቶችን እንደምታጠናክር አሳውቋል።ነጻ አገርነቷን አውጃ ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ ከሶማሊያ ተነጥላ ለቆየችው ሶማሊላንድ እስራኤል የአገርነት ዕውቅናን የሰጠችው ታኅሣሥ 17/2018 ዓ.ም. ነው።ይህን የእስራኤል ውሳኔ ሶማሊያ “በሉዓላዊነቷ ላይ የተፈጸመ ጥቃት ነው” በማለት ያወገዘች ሲሆን፤ አገራት፣ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተቋማትም ዕውቅናውን ተቃውመው ለሶማሊያ የግዛት አንድነት ድጋፋቸውን ገልጸዋል።ያጋሩ, ሶማሊላንድ ከፍተኛ ዲፕሎማቷን በእስራኤል የመጀመሪያ አምባሳደሯ አድርጋ ሾመች
  6. 26 የካቲት 2026የኩባ ባሕር ጠባቂዎች በአሜሪካ ፈጣን ጀልባ ላይ ተኩሰው አራት ኩባውያንን ገደሉየኩባ ሰንደቅ ዓላማየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየኩባ የባሕር ጠረፍ ጠባቂዎች በከፈቱት ተኩስ በአሜሪካ በተመዘገበች ፈጣን ጀልባ ላይ ሲጓዙ የነበሩ አራት ኩባውያን ሲገደሉ ስድስቱ ደግሞ ቆሰሉ።የኩባ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በፈጣን ጀልባዋ ላይ ሲጓዙ የነበሩት ኩባውያን በተጠጓቸው የኩባ የባሕር ጠረፍ ጠባቂዎች ላይ ረቡዕ ዕለት ተኩስ ከከፈቱ በኋላ ነው ጉዳቱ የደረሰባቸው።የኩባ መንግሥት ባወጣው መግለጫ በጀልባዋ ላይ የነበሩት 10 ሰዎች ሲሆኑ ከመካከላቸውም የቀደመ የወንጀል ክስ ያለባቸው እና የታጠቁ እንደነበር እና “የሽብር ዓላማ ይዘው ሰርገው ለመግባት” ዓላማ ነበራቸው ብሏል።የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ አገራቸው “ፈጽሞ ያልተለመደ” ያሉትን ክስተት እየመረመረች መሆኑን ገልጸዋል።በፈጣን ጀልባዋ ላይ ሽጉጦች፣ ጠመንጃዎች፣ ፈንጂዎች እና ሌሎች ወታደራዊ ቁሶች መገኘታቸውን እና በተከፈተው ተኩስ አንድ የጠረፍ ጥበቃ አዛዥ ጉዳት እንደደረሰበት የኩባ መንግሥት አስታውቋል።የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ኩባ ባወጣችው መረጃ ላይ እንደማይተማመኑ በመግለጽ ክስተቱን በተመለከተ የራሳቸውን ምርመራ በማድረግ እንደሚያረጋግጡ አሳውቀዋል።ይህ ሁኔታ የተከሰተው ኩባ ወዳጇ ከሆነችው ቬንዙዌላ የሚቀርብላትን ነዳጅ አሜሪካ ማገዷን ተከትሎ በአገሪቱ ያለው የነዳጅ እጥረት በመባባሱ በሁለቱ አገራት መካከል ያለው ውጥረት ከፍ ባለበት ጊዜ ነው።አሜሪካ በቬንዙዌላ ላይ ጥቃት ፈጽማ የኩባ ወዳጅ የሆኑትን ፕሬዝዳንት ማዱሮን በቁጥጥር ሥር ካዋለች በኋላ ከቬንዙዌላ ወደ ኩባ የሚላከው ነዳጅ በከፍተኛ ደረጃ ቀንሷል።ያጋሩ, የኩባ ባሕር ጠባቂዎች በአሜሪካ ፈጣን ጀልባ ላይ ተኩሰው አራት ኩባውያንን ገደሉ
  7. 25 የካቲት 2026ዚምባብዌ የአፍሪካ አገራት ከአሜሪካ ጋር የደረሱትን የጤና ስምምነት ውድቅ አደረገችየደም ናሙናየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,ስምምነቱ ግላዊ የጤና መረጃዎችን አሳልፎ ይሰጣል የሚል ስጋት ፈጥሯልአሜሪካ እንዲሰጣት በምትጠይቀው ጥበቃ የሚፈልጉ መረጃዎች ምክንያት ዚምባብዌ ከአሜሪካ 376 ሚሊዮን ዶላር የሚያስገኝላትን የጤና ስምምነት ውድቅ አደረገች።ይህ የዚምባብዌ ውሳኔ ይፋ የሆነው ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ ስምምነቱ ለአሜሪካ ያደላ ነው ያሉበት የመንግሥት ማስታወሻ ሾልኮ ከወጣ በኋላ ነው።የመንግሥት ቃል አቀባይ ኒክ ምናንግዋ በስምምነቱ አሜሪካ የጤና ናሙናዎችን ለምርምር እና ለንግድ አገለግሎት መጠየቋን እና ነገር ግን ወደ ፊት ለሚሰሩ ክትባቶች እና መድኃኒቶች ለማጋራት ፈቃደኛ አይደለችም ብለዋል።በዚህም ሳቢያ አሜሪካ ለዚምባብዌ የምትሰጠውን የጤና ድጋፍ ለማቋረጥ እንደምትገደድ በአገሪቱ የአሜሪካ አምባሳደር ፓሜላ ትሬሞንት ባወጡት መግለጫ አሳውቀዋል።ባለፉት ሁለት ዓመታት አሜሪካ ለዚምባብዌ ከ1.9 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚሆን የጤና ድጋፍ ስታደርግ መቆየቷን ኤምባሲዋ ገልጿል።ፕሬዝዳንት ትራምፕ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ በአሜሪካ የእርዳታ አቅርቦት ላይ ባደረጉት ለውጥ የተዋወቀው አዲሱ አሠራር አገራት ጠቃሚ የጤና መረጃዎችን ለአሜሪካ በማጋራት የተለያየ መጠን ያለው ድጋፍን እንዲያገኙ የሚያደርግ ነው።እስካሁን ኢትዮጵያን ጨምሮ 16 የአፍሪካ አገራት ከ18 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ የሚያስገኝላቸውን ስምምነት የፈረሙ ሲሆን፣ ነገር ግን በሚተላለፈው መረጃ እና አገራት በሚያገኙት ጥቅም ላይ ጥያቄ እየተነሳ ነው።ስምምነቱን ቀድማ የፈረመችው ኬንያ ውስጥ ያሉ የመብት ተሟጋች ቡድኖች የዜጎች ግላዊ የጤና መረጃ ለአሜሪካ ተላልፎ መሰጠቱን እንደ ስጋት በመጥቀስ ባቀረቡት ክስ ስምምነቱ በአገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ መታገዱ ይታወሳል።ያጋሩ, ዚምባብዌ የአፍሪካ አገራት ከአሜሪካ ጋር የደረሱትን የጤና ስምምነት ውድቅ አደረገች
  8. 25 የካቲት 2026የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ለጉብኝት እስራኤል ገቡሞዲ እና ኔታኒያሁየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,ሕንድ እና የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትሮች ሞዲ እና ኔታኒያሁየሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የጋዛ ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሁለት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት እስራኤል ገቡ።ሞዲ በእስራኤል ፓርላማ፣ ክኔሴት ተገኝተው ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። እንዲሁም ከጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እና ከፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ ጋር ይወያያሉ ተብሏል።ነገር ግን ከፍልስጤም መሪዎች ጋር ለመናኘት ምንም ዓይነት ፕሮግራም እንዳልተያዘላቸው ተገልጿል።ጉብኝቱ የመጣው ሁለቱም አገራት በመከላከያ፣ በቴክኖሎጂ እና በንግድ ረገድ ያላቸውን ግንኙነት ለማጠናከር ጥረት እያደረጉ ባለበት ወቅት ነው።የሁለቱ አገራት ግንኙነት ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ ከአስር ዓመት በፊት ወደ ሥልጣን ከመጡ ወዲህ በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ ነው።ይሁን እንጂ ተንታኞች እንደሚሉት ጉብኝቱ ሕንድ ከእስራኤል እና ከሌሎች የመካከለኛው ምሥራቅ አገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ሚዛን በመጠበቅ ረገድ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲዋን አጣብቂኝ ውስጥ የሚከት ነው ተብሏል።በአውሮፓውያኑ 2017 ሞዲ እስራኤልን የጎበኙ የመጀመሪያው የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነዋል። ጉዞው በሁለቱ አገራት ወዳጅነት መካከል ትልቅ ለውጥ ማምጣቱ ይገለጻል።ሁለቱ አገራት በፀረ-ሽብር እና በመከላከያ ዘርፍ በቅርበት ይሠራሉ። ሕንድ ከእስራኤል የጦር መሳሪያ ገዢዎች መካከልም ዋነኛዋ ናት።የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የናሬንድራ ሞዲን ጉብኝት “ታሪካዊ” ሲሉ ጠርተውታል።“በእስራኤል እና በሕንድ መካከል ያለው ትስስር በሁለት ዓለም አቀፍ መሪዎች መካከል ያለ ጠንካራ ጥምረት ነው። በፈጠራ፣ በደኅንነት እና በጋራ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች አጋሮች ነን። አብረን ለመረጋጋት እና ለዕድገት ቁርጠኛ የሆኑ አገሮቻችንን በጥምረት እየገነባን ነው” ሲሉ በኤክስ ገጻቸው ላይ ጽፈዋል።ያጋሩ, የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ለጉብኝት እስራኤል ገቡ
  9. 25 የካቲት 2026የመንግሥታቱ ድርጅት ጄነራል ዳጋሎን ጨምሮ በሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል መሪዎች ላይ ማዕቀብ ጣለየሱዳን ፈጣኖ ደራሽ ኃይል መሪ መሀመድ ሃምዳን ዳጋሎ በሱዳን ላለፉት ሦስት ዓመታት በዘለቀው አስከፊ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ የተለያዩ ጥቃቶችን በመፈጸም ይወነጀላሉየፎቶው ባለመብት,Anadolu via Getty Imagesየመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታ ምክር ቤት ሞሐመድ ሐምዳን ዳጋሎን ጨምሮ አራት የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ መሪዎች ላይ አዲስ ማዕቀብ ጣለ።የመንግሥታቱ ድርጅት ማዕቀቡን የጣለው ወታደራዊ መሪዎቹ በኤል ፋሽር በፈጸሙት ወንጀል ነው ተብሏል። የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ኤል ፋሸርን የተቆጣጠረው በጥቅምት ወር ሲሆን፣ በከተማዋ የተፈጸመው ለሦስት ዓመት ያህል በተካሄደው የሱዳን እርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ ከታየው ሁሉ አስከፊው ነበር ተብሏል።ባለፈው ሳምንት የተባበሩት መንግሥታት እውነት አፈላላጊ ቡድን በከተማዋ የተፈጸመው የዘር ማጥፋት እርምጃ ለመካሄዱ አስረጅ ነው ብሏል።በኤል ፋሽር የጅምላ ግድያን ጨምሮ ማንነት ተኮር ግድያ መካሄዳቸውን በመጥቀስ ሐምዳን ዳጋሎን ጨምሮ አራት የፈጥኖ ደራሽ አባላት ማዕቀብ ተጥሎባቸዋል።ከዳጋሎ በተጨማሪ ‘የኤል ፋሽር ነፍሰ በላ’ በሚል ቅጽል ስም የሚታወቀው አቡ ሉሉ ማዕቀብ ከተጣለባቸው መካከል ይገኛል።ጄነራል ዳጋሎ ማዕቀብ ሲጣልባቸው ይህ ለአራተኛ ጊዜ ነው። ከዚህ ቀድም አሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም እንዲሁም የአውሮፓ ኅብረት ማዕቀብ ጥለውባቸዋል።ከዚህ በተጨማሪ አሜሪካ እና ብሪታኒያ በሦስቱ አዛዦች ላይ ማዕቀብ ጥለዋል።ያጋሩ, የመንግሥታቱ ድርጅት ጄነራል ዳጋሎን ጨምሮ በሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል መሪዎች ላይ ማዕቀብ ጣለ
  10. 25 የካቲት 2026ሴኔጋል በተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን ላይ የሚጣለውን የእስር ቅጣት በእጥፍ ልታሳድግ ነውየሴኔጋል ጠቅላይ ሚኒስትር ኦስማኔ ሳንኮየፎቶው ባለመብት,Ousmane SONKOየሴኔጋል ጠቅላይ ሚኒስትር ኦስማኔ ሳንኮ በተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ውስጥ ባሉ ሰዎች ላይ የሚፈረደውን ከፍተኛውን የእስር ቅጣት በእጥፍ ሊጨምር የሚችል ረቂቅ ሕግ አቀረቡ። በአዲሱ ረቂቅ ሕግ መሠረት የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን እስከ 10 ዓመት በሚደርስ እስር ሊቀጡ ይችላሉ።የሴኔጋል ካቢኔ ባለፈው ሳምንት ያጸደቀው ይህ ረቂቅ ሕግ ማክሰኞ ዕለት ለአገሪቱ ፓርላማ ቀርቧል። ቀድሞውኑ በሕግ ክልከላ በጣለችው ሴኔጋል ይህ ረቂቅ የተዘጋጀው፤ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ውስጥ ተገኝተዋል የተባሉ ሰዎች ላይ ተከታታይ እስሮች ከተፈጸሙ በኋላ ነው።ጠቅላይ ሚኒስትር ሳንኮ በፓርላማ ለሕግ አውጪዎች ባደረጉት ንግግር፤ አዲሱ ሕግ “ከተፈጥሮ የተቃረነ ድርጊት” ሲሉ የጠሩትን ተግባር ከአምስት እስከ 10 ዓመት በሚደርስ እስር የሚቀጣ እንደሆነ ገልጸዋል። በነባሩ ሕግ ግን የሚያስቀጣው ከአንድ እስከ አምስት ዓመት በሚደርስ እስር ነበር።“ድርጊቱ በዕድሜ ካልደረሱ ልጆች ጋር የተፈጸመ ከሆነ ከፍተኛውን ቅጣት ያስወስናል” ሲሉ ተናግረዋል። የመብቶች ተሟጋቾች በበኩላቸው ረቂቅ ሕጉን ተችተዋል።የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ተሟጋች መሆን እንደ የውጭ ጣልቃ ገብነት በሚቆጠርባት ወግ አጥባቂዋ ሴኔጋል ውስጥ፤ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት መብትን በተመለከተ የሚደረግ ክርክር ውጥረት የሚፈጥር ጉዳይ ነው።በቅርብ ዓመታት የሃይማኖት ተቋማት ከፍተኛ ቅጣት እንዲጣል የሚጠይቁ ሰልፎችን አካሂደዋል።በዚህ ወር መጀመሪያ ደግሞ የአገሪቱ ፖሊስ በፀረ ተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ሕግ አማካኝነት ሁለት ታዋቂ ግለሰቦች እና አንድ ስመ ጥር ጋዜጠኛን በቁጥጥር ሥር አውሏል። በአጠቃላይ በዚህ ወር 30 ገደማ ሰዎች ከዚሁ ጋር በተያያዘ እንደታሰሩ የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።ያጋሩ, ሴኔጋል በተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን ላይ የሚጣለውን የእስር ቅጣት በእጥፍ ልታሳድግ ነው
  11. 25 የካቲት 2026ትራምፕ ስለ ኢራን ኒውክሌር የተናገሩት “ትልቅ ውሸት ነው” ሲሉ የአገሪቱ ባለሥልጣን ተቹየኢራን ሰንደቅ አላማየፎቶው ባለመብት,Reutersየኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ፤ የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ስለ ኢራን ኒውክሌር እና ባለስቲክ ሚሳዔል የሰጠው አስተያየት “በተደጋጋሚ የተባለ ትልቅ ውሸት ነው” ሲሉ አጣጣሉ።ትራምፕ ለኮንግረስ አባላት ባደረጉት ንግግር ኢራን የኒውክሌር መሣሪያ እንዲኖራት “በፍጹም አልፈቅድም” ብለዋል።የትራምፕን ንግግር ተከትሎ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኢስማዔል ባቄይ “ውሸት ሲደጋገም እውነት ይሆናል” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።ኢራን ቢያንስ 20,000 ተቃዋሚዎችን ገድላለች ሲሉ ትራምፕ ተናግረዋል። በተጨማሪም “አውሮፓን የሚያሰጋ ሚሳዔል ገንብታለች። አሜሪካ የሚደርስ ሚሳዔልም እየገነባች ነው” ብለዋል።ኢራን “መሰሪ የሆነ የኒውክሌር ዕቅዷን” ለመተግበር እየሠራች ነው ሲሉም የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ከስሰዋል።የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ በሰጡት ምላሽ “ማንም ሰው በዚህ ነጭ ውሸት መታለል የለበትም” ብለዋል።ያጋሩ, ትራምፕ ስለ ኢራን ኒውክሌር የተናገሩት “ትልቅ ውሸት ነው” ሲሉ የአገሪቱ ባለሥልጣን ተቹ