**********

የእኛ የኢትዮጵያውያን፣ በተለይ ኦርቶዶክሳውያን #የአሁኑ#እልቂታችን#ስደታችን#ውርደታችን እና ከውስጥ ሳይቀር ጠላት ማንገሣችን የረዥም መንገድ የመጣ የተቀናጀ ሁለገብ ዘመቻ ውጤት ነው ።

የጥፋት ፊት አውራሪ ስህተት ውጨ ገብ የባእዳን የተውሶ ፖለቲካዊ ርእዮት እና መርዛማ የሐሰት ትርክት ነው።

ከትርክት አንጻር እስቲ ክርስቲያኖች በተለይ የቤተ ክርስቲያንን ሊቃውንትን መሪዎች ተጠየቁ:-

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እና ክርስቲያን ምሁራን

፩- የሊቃውንት ጉባኤ

፪- የነገረ መለኮት ምሩቃን እና መምህራን

፫- ኦርቶዶክሳውያን የሆናችሁ በየዩኒቨርሲቲው ያላችሁ የታሪክ ምሁራን

፬- በስብከትና በመጽሐፍት ዝግጅት የምትታወቁ ጸሐፊያን፣

👉ጥላቻን፣ መከፋፈልን፣ የሀገር መልክ መቀየርን፣ እምነት በማጥፋትና በመተካት ላይ አነጣጥሮ የሚካሄደው ከ፶ ዓመታት የዘለለ የዉሀብያ ጽንፈኞች፣ የሕወሃት፣ የኦነግ፣ የብልጽግና መንግሥት የሐሰት ትርክቶች በመጽሐፍት እየታተሙ ሲሰራጩና የትውልድ አእምሮ አጥበው #በኦርቶዶክሳውያን ላይ #ሥርዓታዊና#መዋቅራዊ#እልቂት ለመማስፈጸም አቅም እስኪያገኙ ምላሽ ለመስጠት አለመፈለጋችሁ ለምንድነው?

👉ዛሬም የዝምታን ውጤት ካያችሁትም በኋላ በዚሁ የደም ጎርፍ ውስጥ ቆማችሁ “አሁንም መቻቻል፣ ሁሉም ያልፋል፣ ትንቢቱ ይፈጸም ዘንድ ግድ ነው፣ ቤተ ክርስቲያን አትጠፋም፣ ፖለቲካና ሃይማኖት ይለያያል — ወዘተ” በሚሉ ብሂሎችና ንግርቶች በድንዛዜና በማፍዘዣ ትምህርቶችና ስብከቶች በመቀጠል እንደ ሊቢያ፣ ሶሪያ፣ ካርቴጅ፣ ግብፅ፣ ቁስጥንጥንያ፣ አርመን ወዘተ ክርስቲያኖች ሙሉ በሙሉ እንድንፋ ቆማችሁ መመልከታችሁ ዛሬም ይቀጥላልን?

ካልቀጠለ ተግባራዊ ምላሽ አሳዩ!!

መምህር ፈንታሁን ዋቄ