MistreSilasie Tamerat ·Follow
ለአመታት በግፍ እስር ላይ የነበረው ረ/ፕ ሲሳይ አውግቸው በዋስ እንዲለቀቅ ሰኞ የካቲት 16 ቀን 2018 ዓ.ም ከተወሰነና በዛሬው ዕለት ከቀኑ 11 ሰኣት ገደማ ሂደቱን ጨርሶ ከወጣ በኋላ ወድያውኑ በታጠቁና ጭምብል በለበሱ የመንግስት ኃይሎች መስታወቱ ጥቁር በሆነ መኪና ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በር ላይ ታፍኖ ወዳልታወቀ ቦታ መወሰዱን ለማረጋገጥ ችለናል።
የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ – ኢሕአፓ፤ ብልጽግና ሰላማዊ ዜጎች፣ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ላይ የሚፈጽመው የግፍ እስር አልበቃ ብሎት በተደጋጋሚ አፈናዎችን ማድረጉን ተመልክቷል።
ፓርቲያችን መንግስት ያፈነውን ረ/ፕ ሲሳይ አውግቸው በአስቸኳይ በሙሉ ደህንነት እንዲለቅ እና አሁንም በግፍ እስር ላይ የሚገኙ ዜጎችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲፈታ በጽኑ ያሳስባል።
የሰብዓዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ጉዳይ ግድ ይለናል የሚሉ ተቋማት እና ዜጎችም ይህንንና መሰል የብልጽግና መንግስት ወንጀሎችን በብርቱ እንዲያወግዙና ስለ ሰውነት ክብር በምናደርገው ትግል አጋርነታቸውን እንዲያሳዩ ጥሪ እናቀርባለን።
የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ – ኢሕአፓ/eprp
የካቲት 18 ቀን 2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ
