
የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ በአሜሪካ እና እስራኤል ጥቃት እንደተገደሉ ከተረጋገጠ በኋላ የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ በአሜሪካ የጦር ሰፈሮች እና በእስራኤል ላይ “አስከፊ ጥቃት” እንደሚፈጽም አስጠንቅቋል። ይህንንም ተከትሎ ባህሬን፣ ኩዌት፣ ኳታር፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ኢራቅ እና ኦማን ውስጥ ጥቃት ተፈጽሟል። የእስራኤል ጦርም የኢራን ዋና ከተማ ቴህራንን ዒላማ ያደረጉ ጥቃቶችን መፈጸሙን አስታውቋል።
ጭምቅ ሃሳብ
- አያቶላህ አሊ ኻሜኒ መገደላቸውን የኢራን መንግሥት አረጋግጦ 40 የሐዘን ቀናት አወጀ
- የአራኑ ኃያል ሰው አያቶላህ ኻሜኒ ማን ናቸው?
- የኢራን መንግሥት እጣ ፈንታ ምን ይሆናል? አሜሪካ እና እስራኤልስ ለምን አሁን ጥቃት ሰነዘሩ?
- ኢራን የአጸፋ ጥቃት መፈጸም መጀመሯን ተከትሎ ዶሃ ውስጥ ፍንዳታዎች ተሰሙ
- ትራምፕ፤ ኢራን አሜሪካን ወይም እስራኤልን የምታጠቃ ከሆነ “ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ኃይል” ትመታለች አሉ
- ደስታ እና ሐዘን የተቀላቀለበት የአያቶላህ አሊ ኻሜኒ ግድያ
- የኢራን ሁለት ከፍተኛ አዛዦች መገደላቸውን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን አረጋገጡ
- የአፍሪካ መሪዎች፤ የኢራን ጦርነት ዓለም አቀፋዊ እና ቀጣናዊ መረጋጋትን ሊያናጋ እንደሚችል አስጠነቀቁ
- አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ትምህርት ቤት ባደረሱት ጥቃት 108 ሰዎች ተገደሉ
- እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት ፈጽማ የአስቸኳይ ጊዜ አወጀች
- በኳታር ዋና ከተማ ዶሃ ውስጥ ፍንዳታዎች ተሰሙ
- በኢራን የሚሳዔል ጥቃት አቡ ዳቢ ውስጥ ቢያንስ የአንድ ሰው ሕይወት ጠፋ
- የኢራን መንግሥት “ኒውክሌር መታጠቅ የለበትም” – ኔታንያሁ
- ኢራን ሚሳዔል ማስወንጨፏን የእስራኤል መከላከያ አስታወቀ
የቀጥታ ሽፋን
- ከ 37 ደቂቃዎች በፊትየኢራን ፕሬዝዳንት፤ የኻሜኒ ግድያ ሁሉም ሙስሊም ላይ “የተከፈተ ጦርነት ነው” አሉ
የፎቶው ባለመብት,Reutersየኢራን ፕሬዝዳንት ማዑድ ፔዜሽኪያን፤ የአያቶላህ አሊ ኻሜኒ ግድያ “በሁሉም የዓለም ጥግ በሚገኙ ሙስሊሞች፤ በተለይም በሺዓዎች ላይ የተከፈተ ግልጽ ጦርነት” ነው አሉ።ፔዜሽኪያን፤ በኢራን መንግሥት ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል ላይ በወጣ መግለጫቸው፤ ኢራን “በዚህ ታሪካዊ ወንጀል ፈጻሚዎች እና ጠንሳሾች ላይ የሚፈጸምን ደም መፍሰስ እና በቀልን እንደ ቅቡል ግዴታ እና መብት እንደምትቆጥረው” ተናግረዋል።ኢራን፤ ከዚህ ጋር በተያያዘ ያለባትን “ታላቅ ኃላፊነት እና ግዴታ ለመወጣት የተቻላትን ሁሉ እንደምታደርግም” ገልጸዋል።በአሜሪካ እና እስራኤል ጥቃት የኢራኑን ጠቅላይ መሪ ጨምሮ ሌሎችም አመራሮች በመገደላቸው ፕሬዝዳንቱ የት እና ምን ዓይነት ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ጥያቄ ሲነሳ ቆይቷል። የፕሬዝዳንቱ ጽሕፈት ቤት ቃል አቀባይ፤ ፔዜሽኪያን “ፍጹም ጤንነት እና ደኅንነት” ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።ያጋሩ, የኢራን ፕሬዝዳንት፤ የኻሜኒ ግድያ ሁሉም ሙስሊም ላይ “የተከፈተ ጦርነት ነው” አሉ - ከ 38 ደቂቃዎች በፊትየሔዝቦላህ መሪ፤ የኻሜኒ ግድያ “ትልቅ ወንጀል ነው” ሲሉ አወገዙ
የፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,የሔዝቦላህ መሪ ናይም ቃሲምየሔዝቦላህ መሪ ናይም ቃሲም፤ የኢራኑ ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ “በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተከታዮችን ጥለው ያለፉ ሰማዕት ናቸው” በማለት በግድያው የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ።አያቶላህ አሊ ኻሜኒ ላይ “በወንጀለኞቹ አሜሪካውያን እና በአጥቂዎቹ ፅዮናውያን” የተፈጸመው ግድያ “ትልቅ ወንጀል ነው” ሲሉም አውግዘዋል።በሊባኖስ የሚንቀሳቀሰው የሺአ ሙስሊም ቡድን ሔዝቦላህ በኢራን ይደገፋል።በመካከለኛው ምሥራቅ ኢራን ድጋፍ ከምትሰጣቸው ቡድኖች በግንባር ቀደምነት የሚጠቀሰው ሔዝቦላህ፤ ለኻሜኒ ያለውን “ታማኝነት” ለማሳየት ሕዝባዊ ሰልፍ ጠርቷል።ያጋሩ, የሔዝቦላህ መሪ፤ የኻሜኒ ግድያ “ትልቅ ወንጀል ነው” ሲሉ አወገዙ - ከ 45 ደቂቃዎች በፊትየመካከለኛው ምሥራቅ አየር ክልል በመዘጋቱ በረራዎች ተሰረዙ
የፎቶው ባለመብት,Reutersእስራኤል እና አሜሪካ ላደረሱት ጥቃት ኢራን የአጸፋ እርምጃ እየወሰደች በምትገኝበት በአሁኑ ወቅት ወደ ቀጣናው የሚደረጉ በረራዎች ተሰርዘዋል። አንዳንድ በረራዎች ደግሞ ሌላ አማራጭ መንገድ እንዲከተሉ ተደርጓል።የዱባይ ዋነኛው ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እና እንዲሁም ማክቱም አውሮፕላን ማረፊያ አጠቃላይ በረራዎችን ሰርዘዋል።በተጨማሪም የዱባይ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አራት ሠራተኞች መጎዳታቸው ተገልጿል።ኤምሬትስ እስከ ነገ ሰኞ ድረስ ከዱባይ የሚነሱ በረራዎችን መሰረዙን አስታውቃለች። ኢቲሀድ ደግሞ መነሻቸውን ከአቡ ዳቢ ያደረጉ በረራዎችን ሰርዟል።ሌላኛው አየር መንገድ ብሪትሽ ኤርዌይስ ወደ ቴል አቪቭ እና ባሕሬን የሚደረጉ በረራዎችን እስከ ረቡዕ ድረስ ሰርዟል። ወደ አቡ ዳቢ፣ አማን፣ ዶሃ እና ዱባይ የሚደረጉ ጉዞዎች እንደሚሰረዙም ይፋ አድርጓል።ቨርጂን አትላንቲክ፣ ሲንጋፖር ኤርላይንስ፣ ኤር ኢንዲያ እና ሌሎችም አየር መንገዶችም ወደ መካከለኛው ምሥራቅ የሚደረጉ በረራዎችን ሰርዘዋል።ያጋሩ, የመካከለኛው ምሥራቅ አየር ክልል በመዘጋቱ በረራዎች ተሰረዙ - ከ 51 ደቂቃዎች በፊትበኢራን በ24 ሰዓታት ውስጥ 57 ሰዎች መገደላቸው ተዘገበ
የፎቶው ባለመብት,Reutersባለፉት በ24 ሰዓታት ኢራን 60 ጥቃቶች እንደተፈጸሙባት እና በእነዚህ ጥቃቶች 57 ሰዎች መገደላቸውን የቴህራን ግዛት የቀይ ጨረቃ ማኅበርን መግለጹን የኢራን መንግሥት የዜና ወኪል ‘ኢርና’ ዘገበ።የእስራኤል ጦር ዋና ከተማዋ ቴህራንን ዒላማ ያደረጉ ጥቃቶችን መፈጸሙን ገልጿል። ጦሩ ዒላማ ያደረገው ከኢራን አገዛዝ ጋር ግንኙነት ባላቸውን ሥፍራዎች ላይ እንደሆነ ተናግሯል።በከተማዋ ሰማይ ላይ ጭስ ሲወጣ ሚያሳዩ ምሥሎችም ወጥተዋል።ቢቢሲ እኩለ ቀን ላይ ያነጋገራቸው የምሥራቃዊ እና ሰሜን ምዕራባዊ ቴህራን ነዋሪዎች በከተማዋ ከፍተኛ ፍንዳታ መሰማቱን ገልጸዋል።በምሥራቃዊ ቴህራን የሚገኝ አንድ ምንጭ የዛሬዎቹ “ፍንዳታዎች ከትናንቱ የባሱ” እንደነበሩ ተናግሯል። “ክፍሌ በሙሉ ሲንቀጠቀጥ ነበር” ሲልም ሁኔታውን ገልጿል።የኢራን መገናኛ ብዙኃንም በተለያዩ የቴህራን አካባቢዎች ፍንዳታዎች ስለመሰማታቸው ዘግበዋል።
የፎቶው ባለመብት,AFP/Getty Images
የፎቶው ባለመብት,AFP/Getty Imagesያጋሩ, በኢራን በ24 ሰዓታት ውስጥ 57 ሰዎች መገደላቸው ተዘገበ - ከ 1 ሰአት በፊትፑቲን፤ የኻሜኒን ግድያ “እኩይ ድርጊት” ሲሉ አወገዙ
የፎቶው ባለመብት,Alexander Nemenov/Pool via REUTERSየሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን፤ የኢራኑ ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒን ግድያ “እኩይ ድርጊት” እና “ሰብአዊ ሞራልን እንዲሁም ዓለም አቀፍ ሕግን የጣሰ ነው” በማለት ኮነኑ።በአያቶላህ አሊ ኻሜኒ ግድያ የተሰማቸውን ሐዘን መግለጻቸውን የሩሲያ መንግሥት የሚያስተዳድረው ታስ ዘግቧል።እስራኤል እና አሜሪካ በፈጸሙት የተቀናጀ ጥቃት የኢራኑ ጠቅላይ መሪ መገደላቸውን ተከትሎ በአገሪቱ የ40 ቀን ሐዘን ታውጇል።ኢራን የሩሲያ የቅርብ ወዳጅ ሰትሆን፤ ከዓመታት በፊት በምዕራባውያን አገራት በተፈረመው የኒውክሌር ስምምነት ውስጥ ከሚገኙ አገራት አንዷ ሩሲያ ነበረች።ያጋሩ, ፑቲን፤ የኻሜኒን ግድያ “እኩይ ድርጊት” ሲሉ አወገዙ - ከ 1 ሰአት በፊትየባሕረ ሰላጤው አገራት የኢራንን ጥቃት “እየመከቱ” እንደሆነ ገለጹ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,ኢራን ጥቃት ከፈጸመች በኋላ ከዱባይ የባሕር ዳርቻ ላይ ጥቅጥቅ ያለ ጭስ ሲወጣ ታይቷልኢራን የአጸፋ ምላሽ ዒላማ ያደረገቻቸው የባሕረ ሰላጤው አገራት የተሰነዘረባቸውን ጥቃት “እየመከቱ” እንደሚገኙ አስታውቀዋል።ባሕሬን የተተኮሱባትን ባለስቲክ ሚሳዔሎች በአየር መቃወሚያዋ አማካኝነት ማክሸፏን ገልጻለች። ሆኖም የተወሰኑ “ስብርባሪዎች” በአንዳንድ የአገሪቱ ክፍል መውደቃቸውን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።ኩዌት “የተቃጡብኝን አደገኛ የአየር ጥቃቶች መከላከል ችያለሁ” ስትል በመከላከያ ሚኒስቴሯ በኩል አስታውቃለች። በሰሜናዊ የአገሪቱ ክፈል የተሰነዘሩ ጥቃቶችን በማምከኗ ሰዎች እንዳልተጎዱ የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘገባ ያሳያል።ኳታር በበኩሏ የተሰነዘረባት የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ቢከሽፍም አንዲት ሴት እና ልጇ መጎዳታቸውን ይፋ አድርጋለች። በአቡ ዳቢ የሚገኘው ‘ዩኒየን ታወር’ ጉዳት እንደደረሰበት ተገልጿል።የኳታር መከላከያ እንዳለው ከኢራን የተወነጨፉ ሚሳዔሎች እና ተዋጊ ጀቶችን “በተሳካ ሁኔታ” ማምከን ተችሏል።ያጋሩ, የባሕረ ሰላጤው አገራት የኢራንን ጥቃት “እየመከቱ” እንደሆነ ገለጹ - ከ 1 ሰአት በፊትበኢራን የሚሳዔል ጥቃት ሁለት እስራኤላውያን መገደላቸው ተገለጸ
የፎቶው ባለመብት,IDFየምስሉ መግለጫ,የእስራኤል መከላከለያ ቃል አቀባይ ኤፊ ደርፊንኢራን በፈጸመችው የአጸፋ የሚሳዔል ጥቃት ሁለት እስራኤላውያን መገደላቸው ተገለጸ። የእስራኤል መከላከለያ ቃል አቀባይ ኤፊ ደርፊን “የአየር መቃወሚያ መሣሪያችን ጠንካራ ቢሆንም ፍጹም አይደለም” ብለዋል።እስራኤላውያን የሚተላለፍላቸውን ትዕዛዝ ተከትለው ከምድር በታች በሚገኙ መጠለያዎች እንዲቆዩ አሳስበዋል።የኢራንን መከላከያ “ክፉኛ እንደጎዱ” የተናገሩት ቃል አቀባዩ፤ ከአሜሪካ ጋር የከፈቱት የተቀናጀ ጥቃት እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።ሁለቱ አገራት ኢራን ላይ ጥቃት ከከፈቱ በኋላ 456 ሰዎች ተጎድተው ሆስፒታል እንደገቡ እና 86 የሚሆኑት በጽኑ ሕሙማን ክፍል እንደሚገኙ ቃል አቀባዩ ገልጸዋል።ያጋሩ, በኢራን የሚሳዔል ጥቃት ሁለት እስራኤላውያን መገደላቸው ተገለጸ - ከ 1 ሰአት በፊትበእስራኤል ጥቃት 30 ከፍተኛ የኢራን ባለሥልጣናት መገደላቸው እየተነገረ ነው
የፎቶው ባለመብት,ISNA/WANA/Reutersየምስሉ መግለጫ,ቴህራን ውስጥ ጥቃት የደረሰበት ተሽከርካሪየእስራኤል አየር ኃይል ቅዳሜ ዕለት ኢራን ላይ በፈጸመው ጥቃት ጠቅላይ መሪው አያቶላህ አሊ ኻሜኒን ጨምሮ በአጠቃላይ 30 የአገሪቱን ከፍተኛ ባለሥልጣናት መግደሉ ተነገረ።ቻናል 12 የተባለው የእስራኤል ቴሌቪዥን እንደዘገበው ዒላማ የተደረጉት መሪዎች የተገደሉት “ጥቃቱ በተጀመረ በመጀመሪያው ግማሽ ደቂቃ” ላይ መሆኑን አመልክቷል።ጨምሮም የእስራኤል የፖለቲካ እና የደኅንነት ባለሥልጣናት ኢራን ላይ የተከፈተው ጥቃት “ጅማሬ እንደሆነ እና ዘመቻው ለቀጣይ በርካታ ቀናት እንደሚቀጥል” መናገራቸውን ዘግቧል።ሌሎች የእስራኤል መገናኛ ብዙኃን ደግሞ የአሜሪካ እና እስራኤል ጦር ሠራዊቶች በኢራን ላይ የፈጸሙት በመጠነ ሰፊ ዕቅድ እና ጠንካራ ትበብር እንደነበረ እና ትክክለኛ መረጃ እንደነበራቸው ጠቅሷል።በኢራን ላይ የተፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ የተባበሩት መንግሥታት እና አገራት ተቃውሟቸውን እያሰሙ ነው። የእስራኤል ባለሥልጣናት እንደሚፈልጉት አሜሪካ ዘመቻውን ለረዥም ጊዜ የማካሄድ ፍላጉት ላይኖራት እንደሚችል የመከላከያ ተንታኙ ዮአቭ ሊሞር ተናግረዋል።በጥቃቱ ከምክር ቤት አባላት እና ከአሜሪካውያን ተቃውሞ እየቀረበባቸው ያሉት ትራምፕ ኢራን ውስጥ የሚፈልጉት የሥርዓት ለውጥ እስኪመጣ ላይቀጥሉ ይችለሉ።ከዚህ ቀደም እስራኤል በኢራን ላይ በፈጸመችው ጥቃት የተገደሉ የጦር አዛዦች እና የኒውክሌር ሳይንቲስቶች እነማን ናቸው?ያጋሩ, በእስራኤል ጥቃት 30 ከፍተኛ የኢራን ባለሥልጣናት መገደላቸው እየተነገረ ነው - ከ 2 ሰአት በፊትየኢራን አብዮታዊ ዘብ አዲስ አዛዥ ተሾመለት
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesአህመድ ቫሂዲ የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ አዲስ ዋና አዛዥ ሆነው ተሾሙ።ወታደራዊ ኃይሉን ሲመሩ የነበሩት ጄነራል መሐመድ ፓክፑር እስራኤል እና አሜሪካ ቅዳሜ ዕለት ኢራን ላይ በፈጸሙት ጥቃት ተገድለዋል።አብዮታዊ ዘቡ ኢራን ውስጥ ወታደራዊ፣ ፖለሪካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ኃይሎችን የሚያንቀሳቅስ ዋና ኃይል ሲሆን የተዋቀረውን ከአገሪቱ መደበኛ ጦር ተነጥሎ ነው።አሜሪካ እና እስራኤል በፈጸሙት ጥቃት በርካታ የኢራን ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች መገደላቸውን ተከትሎ፤ በአሁኑ ሰዓት የኢራንን ወታደራዊ ኃይል በማን እየተመራ ነው የሚለው እያነጋገረ ነው።በኢራን መገናኛ ብዙኃን ዘገባዎች መሠረት ሜጀር ጄኔራል አሊ አብዶላሂ ወታደራዊ ኃይሉን እየመሩ ይመስላል።ሜጀር ጄነራሉ፤ በኢራን ጦር እና በአብዮታዊ ዘቡ መካከል ሆኖ የአገሪቱን መከላከያ ሠራዊት የሚያስተባብረው የኻተም አል አንቢያ ማዕከላዊ ዋና መሥሪያ ቤት አዛዥ ናቸው።ሜጀር ጄነራሉ፤ ኢራን “ለጠላቶች ዛቻ ምላሽ የምትሰጠው በጦር ግንባር” ነው ብለዋል። “ጦር ኃይሎቹ ዝግጁነት ከመቼውም በላይ ከፍተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝም” ተናግረዋል።አብዶላሂ፤ ኢራን ኢራቅ ውስጥ የሚኝ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮች ላይ የሚሳዔል ጥቃት መፈጸሟን ተከትሎ በዋሽንግተን ማዕቀብ ከተጣለባቸው ወታደራዊ አዛዦች አንዱ ናቸው።ኢራን የምትተማመንበት እስላማዊው አብዮታዊ ዘብ ማን ነው? ምንስ አቅም አለው?ያጋሩ, የኢራን አብዮታዊ ዘብ አዲስ አዛዥ ተሾመለት - ከ 2 ሰአት በፊትፓኪስታን ውስጥ ኢራንን በመደገፍ የአሜሪካ ቆንስላ አቅራቢያ ሰልፍ ከወጡ ሰዎች ቢያንስ ዘጠኙ ሞቱ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesበፓኪስታን ካራቺ ከተማ ውስጥ የሚገኘው የአሜሪካ ዋና ቆንስላ አቅራቢያ ተቃውሟቸውን ያሰሙ ሰልፈኞች ከፖሊስ ጋር ተጋጭተው ቢያንስ ዘጠኝ ሰዎች እንደሞቱ እና 32 እንደቆሰሉ ተነገረ።ቢቢሲ ያነጋገራቸው በካራቺ የሚገኝ የሲቪል ሆስፒታል ከፍተኛ ሐኪም የዘጠኝ ሰዎች አስከሬን ወደ ሕክምና ተቋሙ እንደተወሰደ ገልጸዋል።አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የፈጸሙትን ጥቃት ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ የቴህራን ደጋፊዎች በካራቺ፣ ላሆር እና ኢስላማባድ ከተሞች ወደ ጎዳና በመውጣት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።ኤድሂ ፋውንዴሽን’ የተባለው የግል የነፍስ አድን ተቋም አንድ ኃላፊ፤ ዘጠኝ አስክሬን እና በርካታ የቆሰሉ ሰዎችን ወደ ሆስፒታል መውሰዳቸውን አረጋግጠዋል።ግጭቱ የተጀመረው ፖሊስ ተቃዋሚዎች ወደ አሜሪካ ቆንስላ ግቢ እንዳይገቡ በተከላከሉበት ወቅት ነው። ክስተቱን በተመለከተ እስካሁን ፖሊስ ይፋዊ መግለጫ አልሰጠም።ጊልጊት ከተማ ውስጥ ደግሞ አንድ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቢሮ መቃጠሉን አንድ የድርጅቱ ባለሥልጣን ለቢቢሲ ኒውስ ተናግረዋል።በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ ጎዳና የወጡበትን ተቃውሞ ተከትሎ በአካባቢው የሰዓት እላፊ እንደታወጀ ፖሊስ አረጋግጧል።የአገሪቱ የሺዓ ድርጅቶች፤ ዋና ከተማዋ ኢስላማባድን ጨምሮ በበርካታ አካባቢዎች የተቃውሞ ሰልፎች ጠርተዋል።ያጋሩ, ፓኪስታን ውስጥ ኢራንን በመደገፍ የአሜሪካ ቆንስላ አቅራቢያ ሰልፍ ከወጡ ሰዎች ቢያንስ ዘጠኙ ሞቱ - ከ 2 ሰአት በፊትኢራናውያን በመሪያቸው ሞት ሐዘናቸውን ለመግለጽ አደባባይ ወጡ
የፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,በመሪያቸው ሞት ሐዘናቸውን ለመግለጽ አደባባይ የወጡ ኢራናውያንአራት አስርት ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ ኢራንን በጠቅላይ መሪነት ያስተዳደሩት አያቶላህ አሊ ኻሜኒ መገደልን ተከትሎ ዜጎች አደባባይ ወጥተው ሐዘናቸውን እየገለጹ ነው።እስራኤል እና አሜሪካ በፈጸሙት ጥቃት ከቅርብ የቤተሰብ አባሎቻቸው እና ከፍተኛ የአገሪቱ ባለሥልጣናት ጋር የተገደሉት ጠቅላይ መሪው ሞት ኢራናውያንን ለሁለት ከፍሏል።በአገር ውስጥ እና በውጪ ያሉ የአገሪቱ ዜጎች በመሪው ኅልፈት ሐዘናቸውን እና ደስታቸውን ሲገልጹ መታየታቸው ተዘግቧል።ለእስላማዊው የኢራን ሪፐብሊክ መንግሥት ከባድ ጉዳት ለሆነው የኻሜኒ ሞት ከአንድ ወር በላይ የሚቆይ የሐዘን ጊዜ ታውጇል።የአገሪቱ ቴሌቪዥን አቅራቢ በከባድ ሐዘን እንባ እየተናነቀው የመሪው ሞት ካወጀ በኋላ በዋና ከተማዋ ቴህራን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኢራናውያን ሐዘናቸውን ለመግለጽ አደባባይ ወጥተዋል።ያጋሩ, ኢራናውያን በመሪያቸው ሞት ሐዘናቸውን ለመግለጽ አደባባይ ወጡ - ከ 2 ሰአት በፊትየኢራን ጄቶች በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮችን መደብደባቸው ተዘገበ
የፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,ከኢራን የሚሳዔል ጥቃት በኋላ ዶሃ ውስጥ ጭስ ታይቷልየኢራን የአየር ኃይል አብራሪዎች በባሕረ ሰላጤው አገራት እና በኢራቅ ኩርዲስታን ግዛት የሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች ላይ በተሳካ ሁኔታ ድብደባ መፈጸማቸውን የአገሪቱ መንግሥት የዜና ወኪል የሆነው ‘ኢርና’ ዘገበ።የኢራን ጦር፤ ጄት አብራሪዎቹ በጦር ሰፈሮቹ ላይ የተሳካ ጥቃት የፈጸሙት በተለያዩ ምዕራፎች እንደሆነ ገልጿል። ሁሉም በቀጣናው የሚገኙ “የጠላት ወታደራዊ ማዕከላት” በአየር ኃይሉ ተዋጊ ጄቶች የመድረስ አቅም ሥር እንደሚገኙም አክሏል።በተያያዘ ዜና ኢራን በባሕረ ሰላጤው በሚገኙ የአሜሪካ አጋር አገራት ላይ የፈጸመችውን ጥቃት ተከትሎ በከተሞቹ ጭስ እና እሳት ታይቷል። ይህንን ሁኔታ የሚያሳዩ ምሥሎችም መውጣት ጀምረዋል።ትናንት ሌሊት እና ዛሬ ጠዋት የተነሱት እነዚህ ምሥሎች፤ በባህሬን ዋና ከተማ ማናማ እና በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ጀበል አሊ ወደብ የተከሰተውን እሳት ያሳያሉ።
የፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,በባህሬን ዋና ከተማ ማናማ ውስጥ በኢራን ድሮን ተመትቶ ከሚቃጠል ህንጻ ላይ ጭስ ሲወጣ ታይቷል
የፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,የኢራን ጥቃት ከደረሰበት የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ጀበል አሊ ወደብ ጥቁር ጭስ ወደላይ ሲጎን ተስተውሏልያጋሩ, የኢራን ጄቶች በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮችን መደብደባቸው ተዘገበ - ከ 3 ሰአት በፊትኢራን የአጸፋ ጥቃት መፈጸም መጀመሯን ተከትሎ ዶሃ ውስጥ ፍንዳታዎች ተሰሙ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,በኢራን ጥቃት የተመታው የዱባይ ጄበል አሊ ወደብ ላይ እሑድ ጠዋት ጭስ ታይቷልበመካከለኛው መሥራቅ የሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮችን ዒላማ እያደረገች ያለችው ኢራን፤ በባሕረ ሰላጤው አገራት ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት በድጋሚ ጀምራለች።ዛሬ ጠዋት በኳታር ዋና ከተማ ዶሃ ውስጥ ከፍተኛ ፍንዳታ ተሰምቷል፤ በከተማዋ ሰማይ ላይም ወደላይ የሚጎን ጭስ ታይቷል።የኳታር የአገር ውስጥ ደኅንነት ሚኒስቴር፤ እንዲከሽፍ በተደረገ ሚሳዔል ስብርባሪ ምክንያት በከተማዋ በሚገኝ የኢንዱስትሪ ዞን ውስጥ የተከሰተውን መጠነኛ የእሳት አደጋ ለመቆጣጠር እየሠራ መሆኑን አስታውቋል።የኳታር ባለሥልጣናት ሌሊት ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ኢራን ትናንት ብቻ 65 ሚሳዔሎችን እና 12 ድሮኖችን ማስወንጨፏን ተናግረዋል።አብዛኛዎቹ ተወንጫፊዎች እንዲከሽፉ ቢደረጉም ጉዳት ያደረሱ መኖራቸውን ገልጸዋል። በወደቁ ስብርባሪዎች ምክንያት ስምንት ሰዎች እንደተጎዱም አክለዋል።በተጨማሪም ዛሬ ጠዋት በዱባይ እና በባሕሬን ዋና ከተማ ማናማ ፍንዳታዎች ተሰምተዋል። በኦማን የንግድ ወደብ ላይ የድሮን ጥቃት እንደተፈጸመ የአገሪቱ መንግሥት የዜና ወኪል ዘግቧል።አሜሪካ እና ኢራንን ለማስታረቅ በሚደረገው ድርድር ለዓመታት ቁልፍ አሸማጋይ የነበረችው ኦማን እስካሁን ድረስ ከኢራን ጥቃቶች ተርፋ ነበር።ኳታር እና ሌሎች የተወሰኑ የአረብ አገራት፤ የኢራንን ጥቃት በጽኑ አውግዘዋል። ለተፈጸመባቸው ጥቃት ምላሽ የመስጠት መብት እንዳላቸውም አስታውቀዋል።የባሕረ ሰላጤው አገራት ባለፉት ዓመታት ከኢራን ጋር ያላቸውን ውጥረት ለማርገብ ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል።ከአሜሪካ ጋር ለገባችበት ቀውስ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሔ ለማበጀትም በአሸማጋይነት ሲሠሩ የሰነበቱት እነዚህ አገራት፤ ኢራን በግዛታቸው ውስጥ በሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች ላይ ጥቃት እንዳትፈጽም ሲከለክሉ ነበር።ይህ ማሳሰቢያቸው ግን ግዛታቸው ውስጥ ቀጥታ ጥቃት እንዳይፈጸም ሊያደርግ አልቻለም። አሁን ደግሞ የኢራን ጠቅላይ መሪ በተፈጸመው ጥቃት መገደላቸውን ተከትሎ ከቴህራን በተጨማሪ የመላው ቀጣናው መጻኢ ሁኔታ ምን ሊመስል እንደሚችል በእርግጠኝነት መናገር አዳጋች ሆኗል።ያጋሩ, ኢራን የአጸፋ ጥቃት መፈጸም መጀመሯን ተከትሎ ዶሃ ውስጥ ፍንዳታዎች ተሰሙ - ከ 3 ሰአት በፊትየኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ ማን ነበሩ?
የፎቶው ባለመብት,leader.irእስራኤል “ከምድረ ገጽ እንድጠፋ ይፈልጋሉ” ስትል የምትከሳቸውን ኻሜኒን ለማጥመድ ለአስርታት ስታደባ ቆይታለች።ጠቅላይ መሪውን ግን በቀላሉ ዒላማ ሳይሆኑ ቆይተው ቅዳሜ የካቲት 21/2018 ጽህፈት ቤታቸው ላይ በተፈጸመ ከባድ ጥቃት መገደላቸው ተረጋግጧል።የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ መሪ የነበሩት የ86 ዓመቱ አዛውንቱ መሪ ማን ነበሩ? በኢራን አብዮት እና በጠቅላይ መሪነቱ ውስጥ ምን ሚና ነበራቸው? ከየትስ ተነስተው የኢራን ጠቅላይ መሪነት ላይ ደረሱ?የኻሜኒን ሙሉ ታሪክ እዚህ ያንብቡ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ፡ ከልጅነት እስከ ዕውቀት፣ ከእስር እስከ ስደት፣ ከአብዮተኝነት እስከ መሪነትያጋሩ, የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ ማን ነበሩ? - ከ 3 ሰአት በፊትየአፍሪካ መሪዎች፤ የኢራን ጦርነት ዓለም አቀፋዊ እና ቀጣናዊ መረጋጋትን ሊያናጋ እንደሚችል አስጠነቀቁ
የፎቶው ባለመብት,EPA/State House Kenyaየምስሉ መግለጫ,የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ እና የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶየአፍሪካ አገራት መሪዎች በአሜሪካ፣ እስራኤል እና ኢራን ግጭት ምክንያት በመካከለኛው ምሥራቅ እየተባባሰ የመጣው ውጥረት የዓለምን ደኅንነት ሊያናጋ እና ለአፍሪካ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጉዳት ሊያመጣ እንደሚችል አስጠነቀቁ።የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ሁሉም ወገኖች በከፍተኛ መጠን እንዲታቀቡ እና ወደ ዲፕሎማሲ እንዲመለሱ አሳስበዋል። እየጨመረ የመጣው ውጥረት በዓለም አቀፍ ሰላም እና ደኅንነት ላይ ከፍተኛ ስጋት መደቀኑንም በማንሳት አስጠንቅቀዋል።የደቡብ አፍሪካን ታሪክ ለአብነት የጠቀሱት ራማፎሳ፤ ዘላቂ ሰላም ሊሳካ የሚችለው በንግግር፣ በፍትሕ እና አብሮ በመኖር ብቻ እንደሆነ ተናግረዋል።አገርነቷን ያወጀችው ሶማሊላንድ እና በግዛቷ የሚገኙ የተቃዋሚ ፓርቲዎች በበኩላቸው ኢራን በባሕረ ሰላጤው የፈጸመችውን ጥቃት በማንሳት ወቅሰዋል። የኢራን ጥቃት ቀጣናዊ መረጋጋትን አደጋ ላይ እንደሚጥለውም አስጠንቅቀዋል።ሱዳንም በተመሳሳይ ኳታር፣ ኩዌት፣ ዮርዳኖስ እና ባሕሬን ላይ የተፈጸመውን የኢራን የሚሳዔል ጥቃት የሚያወግዝ ጠንካራ መግለጫ ማውጣቷን በአገሪቱ የሚገኘው የዜና ምንጭ ‘ሱዳን ትሪቡን’ ዘግቧል። በኻርቱም መግለጫ ላይ ጥቃት የተፈጸመባት ሌላኛዋ የባሕረ ሰላጤው አገር የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ሳትጠቀስ ቀርታለች።በተባበሩት መንግሥታት የሚገኘው የአፍሪካ ኅብረት ተልዕኮ በበኩሉ፤ አሜሪካ እና እስራኤል ኢራን ላይ የፈጸሙትንም፤ የቴህራንንም የአጸፋ ምላሽ ተችቷል። ግጭቱ ይበልጥ እንዳይባባስ ለመከላከል ሲባል በተባበሩት መንግሥታት በኩል እንደ አዲስ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እንዲደረግም አሳስቧል።በርካታ የአፍሪካ አገራት በቀውሱ የተጠለፉ ዜጎቻቸውን ደኅንነት ለማስጠበቅ የተለያዩ እርምጃዎችን ወስደዋል። ኡጋንዳ፤ ኢራን ውስጥ የሚገኙ ዜጎቿ የሚቻል ከሆነ ለቅቀው እንዲወጡ አሳስባለች። በቴህራን በሚገኘው ኤምባሲ ውስጥ የሚገኙ ወሳኝ ያልሆኑ ሠራተኞችንም አስወጥታለች።ኬንያ ደግሞ በመካከለኛው ምሥራቅ የተፈጠረው አለመረጋጋት፤ በቀጣናው በሚገኙ መስመሮች አማካኝነት ወደተለያዩ አገራት የሚደርሱትን እንደ ሻይ፣ ቡና፣ አበባ፣ ሥጋ እና አትክልት ያሉ ዋና ዋና የወጪ ንግድ ምርቶችን ለመላክ እንቅፋት እንደሚሆን ተናግራለች።ከባሕረ ሰላጤው አገራት ጋር ጠንካራ የንግድ ትስስር ያላቸው ኬንያ እና ታንዛኒያ፤ የመርከብ መስመሮች ለተራዘመ ጊዜ የሚዘጉ ከሆነ በወጪ ንግድ ገቢያቸው ላይ ሊደርስ ስለሚችለው ጉዳት ስጋታቸውን ገልጸዋል።ተጨማሪ፡ የዓለም መንግሥታት በኢራን ላይ ስለደረሰው ጥቃት ምን አሉ?ያጋሩ, የአፍሪካ መሪዎች፤ የኢራን ጦርነት ዓለም አቀፋዊ እና ቀጣናዊ መረጋጋትን ሊያናጋ እንደሚችል አስጠነቀቁ - ከ 4 ሰአት በፊትዱባይ እና እስራኤል ውስጥ የተፈጸመውን የኢራን ጥቃት የሚያሳዩ ምሥሎችኢራን፤ ትናንት ሌሊት እና ዛሬ ዱባይ እና እስራኤል ላይ በፈጸመቻቸው ጥቃቶች የደረሰውን ጉዳት የሚያሳዩ ምሥሎች እየወጡ ነው።ኢራን ምሽት ላይ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያን ጨምሮ በዱባይ የሚገኙ ዒላማዎችን አጥቅታለች። በተጨማሪም ቅዳሜ ሌሊት የተወነጨፉ የኢራን ሚሳዔሎች በማዕከላዊ ቴል አቪቭ ውስጥ የሚገኙ የመኖሪያ ሕንጻዎችን መትተዋል።
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,በኢራን ጥቃት ከተመታው የዱባይ ጄበል አሊ ወደብ ላይ እሁድ ጠዋት ጭስ ታይቷል
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,ኢራን ጥቃት ከፈጸመች በኋላ ከዱባይ የባሕር ዳርቻ ላይ ሲወጣ የነበረ ጥቅጥቅ ያለ ጭስ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,ቅዳሜ ምሽት የተወነጨፈ የኢራን ሚሳዔል ቴል አቪቭ ውስጥ የሚገኝ የመኖሪያ ሕንጻን አውድሟል
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች በኢራን ሚሳዔል በተመታው የቴል አቪቭ የመኖሪያ ሕንጻ እገዛ ሲያደርጉ ነበርያጋሩ, ዱባይ እና እስራኤል ውስጥ የተፈጸመውን የኢራን ጥቃት የሚያሳዩ ምሥሎች - ከ 5 ሰአት በፊትከኢራን ጦርነት ጋር በተያያዘ ሌሊት ላይ የተፈጠሩ ዋና ዋና ክስተቶች
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየአሜሪካ እና እስራኤል ጥቃት የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒን መግደሉን ተከትሎ የአገሪቶ ጦር፤ “እጅግ አስከፊ” የሆነ የአጸፋ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል። ባለፉት ሰዓታት ከኢራን ጦርነት ጋር የተያያዙ በርካታ ክስተቶች ተፈጥተዋል፤ ዋና ዋናዎቹ እነዚህ ናቸው፦- አያቶላህ አሊ ኻሜኒ ቢሮቸው ውስጥ መገደላቸውን የኢራን የመንግሥት ቴሌቪዥን ዘግቧል። አገሪቱን ለ37 ዓመታት የመሩት ጠንካራውን የሃይማኖት መሪ የተገደሉባት ኢራን የ40 ቀናት ብሔራዊ ሐዘን አውጃለች።
- የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ለመሪው መገደል አጻፋ የሚሆን “አስከፊ ጥቃት” በአሜሪካ የጦር ሰፈሮች እና በእስራኤል ላይ እንደሚፈጽም አስጠንቅቋል።
- በኢራን ሕገ መንግሥት መሠረት የአያቶላህ አሊ ኻሜኒ ተተኪ የሚመረጠው እርሳቸውንም እዚህ ሥልጣን ላይ በሾማቸው የአመራር ሊቃውንት ጉባኤ ነው።
- ጥቃቱ ከተፈጸመ እና የኻሜኒን ሞት ከተረጋገጠ በኋላ አንዳንድ ኢራናውያን ደስታቸውን ሲገልጹ የታዩ ሲሆን ሌሎች ደግሞ ሐዘን ላይ ናቸው።
- የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው አያቶላህ ኻሜኒ፤ ”በታሪክ ከታዩ እጅግ ክፉ ሰዎች አንዱ” ነበሩ ብለዋል። የኻሜኒ ሞት፤ “የኢራን ሕዝብ አገሩን መልሶ ለመያዝ የሚያስችለው ብቸኛው ታላቅ ዕድል” እንደሆነም ገልጸዋል።
- የቀይ ጨረቃ መረጃ እንደሚያመለክተው ኢራን ውስጥ በተፈጸመው ጥቃት ከ200 በላይ ሰዎች ተገድለዋል። በአሜሪካ የቢቢሲ አጋር የሆነው ‘ሲቢኤስ ኒውስ’ በበኩሉ 40 ገደማ የኢራን ባለሥልጣናት መሞታቸውን ዘግቧል።
- ኢራን፤ በመካከለኛው ምሥራቅ ባሉ የአሜሪካ አጋሮች ላይ እና የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች በሚገኙባቸው ቦታዎች ላይ ጥቃቶችን ፈጽማለች። ጥቃቱ ከተሰነዘረባቸው መካከል፤ ዱባይ፣ ዶሃ፣ ባህሬን እና ኩዌት ይገኙበታል።
- በዓለም ላይ እጅግ በርካታ በረራዎችን ከሚያስተናግዱ የአቪዬሽን ማዕከላት አንዱ በሆነው በዱባይ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እንዲከሽፍ የተደረገ ኢራን የሚሳዔል ስብርባሪዎች ወድቆ አራት ሰዎች እንደቆሰሉ የአገሪቱ መንግሥት አስታውቋል።
- የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታርመር በበኩላቸው፤ ብሪታንያ ዜጎቿን እና ቀጣናዊ አጋሮቿን ለመጠበቅ ስትል “የተቀናጀ የቀጣናዊ የመከላከል ዘመቻ” ውስጥ እየተሳተፈች መሆኑን አስታውቀዋል።
- ከ 5 ሰአት በፊትአሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ትምህርት ቤት ባደረሱት ጥቃት 148 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ
የፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,ቢቢሲ በአካባቢው ፍንዳታ ከደረሰ በኋላ ነዋሪዎች ተደናግጠው መሰባሰባቸውን አረጋግጧል።በደቡባዊ ኢራን በሚገኝ ትምህርት ቤት ላይ አሜሪካ እና እስራኤል ባደረሱት ጥቃት ቢያንስ 148 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ።የኢራን ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዚሽኪያን “ኋላ ቀር ድርጊት ነው። አጥቂዎቹ ከፈጸሟቸው አሰቃቂ ድርጊቶች አንዱ ሆኖ ተመዝግቧል” ብለዋል።አሜሪካ እና እስራኤል በትምህርት ቤት ላይ ጥቃት ስለመድረሱ ያሉት ነገር የለም።የኢራን ቀይ ጨረቃ እንዳለው በመላው አገሪቱ ቢያንስ 201 ሰዎች የሞቱ ሲሆን 747 ሰዎች ተጎድተዋል።በጄኔቫ የሚገኙ የቀይ ጨረቃ እና ቀይ መስቀል አመራሮች እንዳሉት፤ የባለሙያዎች ቡድን ወደ ትምህርት ቤቱ ተልኳል።በኢራን ሆርሞግዣን ግዛት፣ ሚንዳብ ከተማ በሚገኘው ትምህርት ቤት ላይ “ሦስት የሚሳዔል ጥቃት” መፈጸሙን አንድ ባለሥልጣን ተናግረዋል።ቢቢሲ በአካባቢው ፍንዳታ ከደረሰ በኋላ ነዋሪዎች ተደናግጠው መሰባሰባቸውን አረጋግጧል። ምን ያህል ሰዎች እንደተገደሉ ግን ማረጋገጥ አልተቻለም።ኢራናውያን ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ቁጣቸውን እየገለጹ ነው። አንድ ከኢራን ውጭ የሚኖሩ የአገሪቱ ዜጋ ወታደራዊ እርምጃውን አውግዘው “የጦርነታቸው የመጀመሪያዎቹ ሰለባዎች በሚሳዔል የተመቱ 40 ታዳጊ ሴቶች ናቸው። ይሄንን ድርጊት ነው የምታወድሱት?” ብለዋል።ያጋሩ, አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ትምህርት ቤት ባደረሱት ጥቃት 148 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ - ከ 6 ሰአት በፊትየመጨረሻው የኢራን ንጉሥ ልጅ የአያቶላህ ኻሜኒ መገደል “የአገሪቱን አቅጣጫ ሊቀይር ይችላል” አሉ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesአሜሪካ ውስጥ ስደት ላይ ያሉት የመጨረሻው የኢራን ንጉሥ (ሻህ) ልጅ ረዛ ፓህላቪ፤ የጠቅላይ መሪው አያቶላህ አሊ ኻሜኒን ሞት በደስታ መቀበላቸውን የሚገልጽ ጽሁፍ አውጥተዋል።ፓህላቪ ምሽት ላይ በአሜሪካው ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ ላይ ባወጡት ጽሁፍ፤ “የነፃነታችሁ ሰዓት ተቃርቧል” በማለት ለኢራን ሕዝብ መልዕክት ላስተላለፉት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ምስጋና አቅርበዋል።ለግማሽ ክፍለ ዘመን ያህል እስላማዊ ሪፐብሊኳ “የጎረቤት አገራትን ሉዓላዊነት ስትጥስ፣ በዓለም ዙሪያ ግጭቶችን ስታቀጣጥል እንዲሁም የኒውክሌር መሣሪያዎችን እና ኒውክሌር የሚያስወነጭፉ ረዥም ርቀት ተጓዥ ሚሳዔሎችን ለመታጠቅ ስትሠራ ቆይታለች” ብለዋል።የእስላማዊ ሪፐብሊኳ እጅግ “አስከፊ ወንጀሎች” የተፈጸሙት ግን አገር ውስጥ ነው ሲሉ ጽፈዋል። ባለፈው ጥር ላይ ተቃውሞ በወጡ ሰልፈኞች ላይ በተወሰደው እርምጃ በሺህዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች መገደላቸውንም በማሳያነት ጠቅሰዋል።የአገሪቱ ቀጣይ ጉዞ አዲስ ሕገ መንግሥት ማርቀቅ እና በሕዝበ ውሳኔ መጽደቅን፤ በመቀጠልም “ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች” በተኙበት ነጻ ምርጫዎች ማካሄድን ማካተት እንደሚገባው ገልጸዋል።“ብዙውን ጊዜ ታሪክ የሚታጠፍባቸውን ነጥቦች አስቀድሞ አያሳውቅም። ነገር ግን የአገርን አቅጣጫ መቀየር የሚችሉ አጋጣሚዎች ከድፍረት፣ አመራር እና አብሮነት ጋር ይመጣሉ” ብለዋል።ያጋሩ, የመጨረሻው የኢራን ንጉሥ ልጅ የአያቶላህ ኻሜኒ መገደል “የአገሪቱን አቅጣጫ ሊቀይር ይችላል” አሉ - ከ 6 ሰአት በፊትትራምፕ፤ ኢራን አሜሪካን ወይም እስራኤልን የምታጠቃ ከሆነ “ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ኃይል” ትመታለች አሉ
የፎቶው ባለመብት,Los Angeles Times via Getty Imagesየአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትሩዝ ሶሻል በተሰኘው የማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ኢራን አሜሪካ ወይም እስራኤል ላይ የአጸፋ ጥቃት እንዳትፈጽም አስጠንቅቀዋል።ትራምፕ በጽሑፋቸው፤ “ኢራን ዛሬ እጅግ በኃይለኛው እንደምታጠቃ ገልጻለች፤ ከዚህ ቀደም ከፈጸሙት [ጥቃት] ሁሉ ኃይለኛ የሆነ” ብለዋል።“ይህንን ባያደርጉ ይሻላቸዋል፤ ምክንያቱም የሚያደርጉት ከሆነ ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ኃይል እንመታቸዋለን!” ሲሉ በአጽንኦት አስጠንቅቀዋል።ትራምፕ ይህንን ያሉት፤ የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ለአያቶላህ አሊ ኻሜኒ ግድያ የአጸፋ ምላሽ ለመስጠት የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች እና እስራኤል ላይ ጥቃት እንደሚፈጸም ካስጠነቀቀ በኋላ ነው።አብዮታዊ ዘቡ ከሰዓታት በፊት፤ “በኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ የጦር ኃይሎች ታሪክ ውስጥ እጅግ አስከፊ የሆነው የማጥቃት ዘመቻ፤ በተወረሩ ግዛቶች እና በአሜሪካ ሽብርተኛ የጦር ሰፈሮች ላይ በደቂቃዎች ውስጥ መፈጸም ይጀምራል” ብሎ ነበር።ያጋሩ, ትራምፕ፤ ኢራን አሜሪካን ወይም እስራኤልን የምታጠቃ ከሆነ “ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ኃይል” ትመታለች አሉ
