በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ሽርካ ወረዳ በጃዊ ቀበሌ 21 ኦርቶዶክሳውያን በታጣቂዎች ጥቃት ሕይወታቸው ማለፉ ተገለጸ።

(#EOTCTV የካቲት 20 ቀን 2018 ዓ.ም)

በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ሽርካ ወረዳ በጃዊ ቀበሌ 21 ኦርቶዶክሳውያን በታጣቂዎች ጥቃት ሕይወታቸው ማለፉን በመግለፅ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ከሚመለከተው የፌደራል የመንግሥት አካላት ጋር ተወያይቶ ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ እንዲፈልግ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሶማሌ እና የምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ጳጳስ አሳሰቡ።

ሊቀ ጳጳሱ እያሰለሰ በቀጠለው የምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ችግር ዛሬም የካቲት 19 ለ 20 አጥቢያ 21 ኦርቶዶክሳውያን የተገደሉ ሲሆን አንድ ካህን ሁለት ሴቶች እና 18 ወንድ ኦርቶዶክሳውያን በግፍ መገደላቸውን ገልጸዋል።

2 የታገቱ 8 የደረሱበት የማይታወቅ ሲሆን 8 ወገኖቻችን በጎቤላ ሆስፒታል በህክምና ላይ እንደሚገኙ በደብዳቤው ተገልጿል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የብዙኃን መገናኛ ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት በወገኖቻችን ላይ በደረሰው

ጥቃት የተሰማውን ሐዘን እየገለጸ እግዚአብሔር ነፍሶቻቸውን በቅዱሳን እቅፍ እንዲያሳርፍልን ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እንዲያድልልን ይመኛል።